መሮ በረሮ.. የሕፃናት ፊልም መታየት ጀመረ
በቀንዲል ፊልም ፕሮዳክሽን ደራሲና ገጣሚ አያልነህ ሙላቱ ተደርሶ በአሸናፊ ማህሌት የተዘጋጀው ..መሮ በረሮ.. የሕፃናት ፊልም ለሕዝብ መቅረብ ጀመረ፡፡ ለመስራት ዘጠኝ ወራት በፈጀው ፊልም ፋሲካ ረዳይ፣ አብዱልከሪም ዴተሞና ሌሎችም ተውነዋል፡፡ ፊልሙ ጳጉሜ 6 በዓለም ሲኒማ መመረቁንም ማወቅ ተችሏል፡፡
አዲስ የጉራጊኛ አልበም ገበያ ላይ ዋለ
በታዋቂው የጉራጊኛ ዜማ ድምፃዊ ደሳለኝ መርሻ የተዜመና ሒታኒያ የተሰኘ አዲስ አልበም ገበያ ላይ ዋለ፡፡
በጉራጌው ማህበረሰብ ባህል፣ የአኗኗር ዘዴ፤ የመስቀልና የአረፋ በዓል አከባበር ላይ መሠረት አድርጐ የተሰራው ይኸው አዲስ አልበም፤ በያዝነው ሳምንት በማሬ ሙዚቃ ቤት አሳታሚነት ገበያ ላይ ውሏል፡፡ አዲሱ አልበም ለድምፃዊው 5ኛ አልበሙ ሲሆን ሐታኒያ የሚለው የጉራጊኛ ቃል ፍቺው እርሷ ነች የሚል እንደሆነ ድምፃዊው ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡
ሞዴል ምህረት ክፍሌ በነፍስ ግድያ ተወነጀለች
..ኤሊት ሞዴል ሉክ.. ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ ይችላል
ማርቆስ ሳሙኤልሰን ለኢትዮጵያ የገቢ ማሰባሰቢያ ግብዣ አዘጋጀ
በፓሪስና በኒውዮርክ ከፍተኛ ዝናን ያተረፈው ኢትዮጵያዊው የምግብ ዝግጅት ባለሙያ (chef) ማርቆስ ሳሙኤልሰን ከባለቤቱ ሞዴል ሚያ ሃይሌ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው የገቢ ማሰባሰቢያ ግብዣ ማድረጉን ዎልስትሪት ጆርናል ዘገበ፡፡ ..ብራንች ፎር ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ.. በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የቁርስና የምሳ ግብዣ (ብራንች)፣ እሰከ 200 ሰዎች የ50 ዶላር ትኬት በመቁረጥ ታድመዋል፡፡ ከእራት ግብዣው የተሰበሰበውን ገቢ በኢትዮጵያ ለሚገኝ አንድ የበጎ አድራጎት ተቋም እንደሚለግስም ታውቋል፡፡ ማርከስ ሳሙኤልሰን በታላቁ የአሜሪካ አየረንሼፍ 8ኛ ውድድር ከሌሎች ዝነኛ ምግብ አብሳዮች ጋር ሊወዳደር መመዝገቡን ኒውዮርክ ዴይሊኒውስ ዘግቧል፡፡
ሞዴል ማያ ሃይሌ የተሰበሰበውን ገቢ ለተመረጠ ተቋም ለማበርከትና ለጉብኝት ከወር በኋላ ወደ ኢትዮጵያ እንደምትመጣ ዎልስትሪት ጆርናል ጨምሮ አመልክቷል፡፡
በአዲሱ ጊነስ ባለሪከርድ ሙዚቀኞችና ተዋናዮች በዝተዋል
ላዮን ኪንግ በ3ዲ መጣ
ከ17 ዓመት በፊት ለዕይታ የበቃው የካርቱን ፊልም ..ዘ ላዮን ኪንግ.. ከሳምንት በፊት በ3ዲ ለገበያ ሲቀርብ በከፍተኛ ሳምንታዊ ገቢ ቦክስ ኦፊስን እንደመራ ተገለፀ፡፡ የዋልት ዲዘኒ ፊልም የሆነው ..ዘ ላዮን ኪንግ 3ዲ.. በዓለም ዙሪያ በ2733 ስፍራዎች በሚገኙ ሲኒማ ቤቶች እየታየ ሲሆን፣ ሳምንታዊ ገቢ በሰሜን አሜሪካ ብቻ 40 ሚሊዮን ዶላር አስገብቷል፡፡ ከ17 ዓመት በፊት ላየን ኪንግ በመላው ዓለም ለእይታ በቅቶ ከ60 ሚሊዮን በላይ ተመልካች ያገኘ ሲሆን 4.6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማስገባቱ ታውቋል፡፡ ላየን ኪንግ፤ በዓለም ዙርያ ከ70 በላይ የምርጥ ፊልም ሽልማቶችን የተሸለመ ሲሆን 2 የኦስካር፣ 3 የጎልደን ግሎብ፣ 6 የቶኒ አዋርድ፣ 3 የግራሚ ሽልማቶችን ሰብስቧል፡፡ አቫተርን በ3ዲ የሰራው ጀምስ ካሜሮን፤ ሰሞኑን ..ላየን ኪንግ.. በተመሳሳይ ቴክኖሎጂ ታግዞ ለእይታ መብቃቱ የ3ዲ ተፈላጊነት መጨመሩን ያመለክታል ሲል ተናግሯል፡፡ ..ታይታኒክ..ም በቅርብ ወራት በዲቪዲ ተሰርቶ ለእይታ ይበቃል፡፡
ኢሕአዴግንም ተቃዋሚንም ያስማሙ ጉዳዮች - ግድብና የኑሮ ውድነት
ሥልጣን መልቀቅና ሥልጣን መረከብን ለመለማመድ ያህል የሰንደቅ ዓላማ ቀን...
ዓውዳመቶቻችን የአፍሪካ ህብረትን መቀመጫ እንዳስቀይሩብን...
አንዳንድ ጊዜ ሁላችንንም የሚያግባባ (የሚያስማማ) ነገር ሲገኝ ደስ ይላል አይደል... (ብዙ ጊዜ ከምንግባባበት
ይልቅ የማንግባባበት ስለሚበዛ ነው) እናም በ2003 ከአንድ በላይ የተግባባንባቸው ነገሮች ስለተገኙ እራሳችንን ..ኮንግራ!.. ብንል ግምት ውስጥ የሚከተን አይመስለኝም፡፡ ነገሩ ምን መሰላችሁ? አንደኛው ያለ አግባብ የኢቴቪ የፕሮግራም ማድመቂያ የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ነው፡፡
ሰው፣ ስም፣ ሰላምታ(እና ማህበራዊ ኑሮ)
..እግዚአብሄር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ ከመሬት አደረገ፤ በምን ስም እንደሚ-ሯቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፤ አዳምም ህያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስመ እንደ ጠራው ስሙ ያው ሆነ..
(ኦሪት ዘፍጥረት፣ ምእራፍ ሁለት፣ ቁጥር አስራ ዘጠኝ)
አንድ
የተከበራችሁ አንባብያን
ሰው ገና ሲወለድ ቀዳሚው ጥያቄ ..ወንድ ነው ሴት?.. ነው፡፡ (..አፍንጫው ልክ የሴት አያቱን.. ..ቅንድቡ መገናኘቱ ቁርጥ አጎቱን.. ወዘተ ይባላል በጎን በቅንፍ)
የተረገመችን እግር በቅሎ ነስቶ ጫማ ያሳጣታል
ከዕለታት አንድ ቀን የዱር አራዊት ሁሉ ንጉሥ አያ አንበሶ ታሞ አልጋ ላይ ይውላል፡ የጫካው አውሬዎችና እንስሳት በሙሉ ሊጠይቁት ይመጣሉ፡፡ - ከቀበሮ በስተቀር፡፡
ተኩላ የቀበሮን አለመምጣት ተመልክቶ አጋጣሚውን ሊጠቀም ፈለገ፡፡ የረዥም ጊዜ ቂሙን ለመወጣት አስቦ ነው፡፡ ስለዚህም ወደ አያ አንበሶ ጠጋ ብሎ፤
«የዱር አራዊት ሁሉ የእርሶ ጤንነት አሳስቧቸው ሊጠይቁዎት ሲመጡ ቀበሮ ግን ምን ንቀት አድሮበት እንደሆን አይታወቅም በአካባቢውም የለች፡፡ በጣም የሚገርም ነገር ነው» አለ
አያ አንበሶም፤