Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

ጾታዊ ጥቃት ማለት ማንኛውም በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን የስርዓተ ጾታ ያልተማከለ (የኃይል/የስልጣን) ግንኙነት በመመርኮዝ በሌላው ላይ የሚደርስ ጉዳት/ጥቃት ወይም ማስፈራራት ነው፡፡ በርካታ አዋቂ ሴቶችና ሴት ሕጻናት የጸታ መድልዎ በሚደረግባቸው ማህበረሰቦች ውስጥ የሚገኙ ከመሆናቸው የተነሳ በአብዛኛው በእነሱ ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ወይም የሃይል ተግባራትን ጾታን መሰረት ያደረጉ ናቸው፡፡ ጾታዊ ጥቃት በተለይ በአዋቂ ሴቶችና ሴት ሕጻናት ላይ በጣም የከፋ ጉዳት፣ የመብት መጣስ የሚያደርሱና የተለያዩ እድሎችን ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ያደርግላቸዋል፡፡ ጾታዊ ጥቃት ሲባል በአብዛኛው በሴቶች ላይ የሚደርሱ ቢሆኑም ወንዶችም ተጠቂ ሊሆኑባቸው የሚችሉባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡

የመታሻ አገልግሎት የሚሰጡ ወንበሮች ተገጥመውለታል

ሴባስቶፖል ሲኒማ ቤትን በተመለከተ በየጊዜው ከተመልካች የሚሰነዘሩ አስተያየቶች ያስጨንቁት እንደነበር የገለፀው አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ፤ ምንም እንኳን በኤግዚቢሽን ማዕከል የሚገኘው ሲኒማ ቤት በኪራይ የተገኘ ቢሆንም ለፊልም ተመልካቹ ምቾት ለመስጠት ሲል በ4 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደገና ማደሱን ለአዲስ አድማስ ተናገረ፡፡ ቀደም ሲል የነበረው ሲኒማ ቤት ለሲኒማ ቤት ምቹ ያልሆኑ ወንበሮች የታጨቁበት፣ የሰው ትንፋሽ እና የአዳራሹ ሙቀት የሚፈጥረው ወበቅ ተመልካቹን ሰላም የሚነሳ ነበር፡፡

የኢንዱስትሪውን ዕድገት ወደኋላ ይመልሳል ተብሏል

በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቀበሌ 32 ልዩ ስሙ “ጎንደር በረንዳ” ወይም “ቄጠማ ተራ” እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከግለሰብ ላይ መጋዘን ተከራይተው የዘፈን እና የፊልም ሕትመቶችን ሲቸረችሩ እና ሲያከፋፍሉ የነበሩ 50 አሳታሚ እና አከፋፋዮች በሦስት ቀን ውስጥ ሱቆቻቸውን እንዲያፈርሱ የተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ ተገቢ አለመሆኑን ገለፁ፡፡ ከሁለት ቀናት በፊት በተጠቀሰው ቦታ ተገኝተን ሱቆቹን እንደተመለከትናቸው መጋዘኑ በጥቁር ድንጋይ የተሠራ ሲሆን ውስጡ በኮምፖርሳቶ እና በብረት የተከፋፈሉ ሱቆች ተሠርተውበታል፡፡

ዕውቀት መሰላል ነው፡፡ በዕውቀት መሰላልነት የማያመልጡት አዘቅጥ የለም፡፡ በዕውቀት መሰላልነት የማይወጡት ከፍታ የለም፡፡ ዕውቀት መሰላል ነው፡፡ ከድህነት አረንቋ ወደተሻለ የኑሮ ረባዳ ያወጣል፡፡ ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ ወደተደላደለ ኑሮ ከፍ ያደርጋል፡፡ ከለየለት የከፋ ድህነት ወደተጨበጨበለት የተደነቀ ሀብት ያደርሳል፡፡ ዕውቀት መሰላል ነው፡፡ ተግቶ የረገጠውንና የጨበጠውን ወደ ላይ ያስመነጥቃል፡፡ ሳይታክት ለሚፈልገውና ለሚጠቀምበት የስኬት ፍኖት ሆናል፡፡ “ሰው ሲፈጠር ከፍ ያለ አእምሮ ተሰጠው፤ ከፍ ባለው አእምሮውም ላይ በጊዜ ብዛት ዕውቀት ጨምሮበት የምድር ጌታ ሆነ፡፡ “ ይላሉ ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ፡፡

በብርሃኑ ገበየሁ “ልቦለድ እንደ ርዕዮተዓለም መገለጫ” በሚለው ጥናታዊ ስራ የሀዲስን ተረቶች ለምን ይሆን ያልተካተቱት?

ተረት “እንደ ርዕዮተ ዓለም መገለጫ”

ፈርመያዣ- ከሳምንት በፊት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል ግንባታ ሲቋቋም መጠሪያውንና መታሰቢያነቱን ለታላቁ ደራሲያችን ለሀዲስ አለማየሁ ማድረጉ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ይፋ ሆኗል፡፡ የሀገራች ስመጥር የባህልና የስነጽሁፍ ባለሟሎች በባህል ማእከሉ ምረቃ ወቅት የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎችን ማቅረባቸውም፣ የሚመሰገን ተግባር ነው፡፡ ዝግጅቱ ዳር እንዲደርስ አዲስ አበባ ድረስ በመምጣት ለተሳታፊዎች የጥሪ ወረቀት ሲያደርስ የነበረው፣ የዩኒቨርሲቲው መምህር አቶ መስፍን የአንዳንዶቹን አድራሻ ለማግኘት ብዙ መልፋቱን ተመልክቻለሁና ዝግጅቱን ለማሳካት ባደረገው ትጋት መመስገን ይገባዋል፤ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ሀላፊዎች ለባህል ጥናት መስፋፋት ያደረጉት ትርጉም ያለው ውሳኔና ተግባር ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡

Friday, 06 January 2012 11:32

ማራኪዕርገት

የቀበሌ አርባ ሁለት ፅህፈትቤት ፀጥ ብሏል …

ሰፊ ግቢ ነው፡፡ የግቢውን የጀርባ አጥር የኋላ ግድግዳዉ አድርጎ የተነሣ ትልቅ፣ ባለ አንድ ፎቅ ሕንፃ የግቢውን አጋማሽ ይዞታል፡፡ ከሲሚንቶ ይልቅ ብረትና መስታወት የሚበዛበት ብርሀናማ፣ ግሩም ሕንፃ ነው፡፡

ከኮብላይ የተወረሰ፡፡

የግቢውን ግራና ቀኝ የግንብ አጥር ተደግፈው በሸካራ ብሎኬት የተሰሩ በርከት ያሉ ደጃፍ ቤቶች ተደርድረዋል፡፡ አያምሩም፡፡ በጥበብና በጥንቃቄ ከታነጸው ትልቅ ፎቅ ቤት እግሮች ላይ የበቀሉ ዕጢዎች ይመስላሉ፡፡ ከፎቁ አጠገብ በስተቀኝ - መጀመሪያ ካለው ጠባብ የእስር ቤት ክፍል የምስራች ብቻዋን በጀርባዋ ተኝታ ጣራ ጣራውን እያየች በሃሳብ ተመስጣለች፡፡ ራሷን ያስደገፈችበት ቀኝ እጇ ስለ ዛለባት በቀስታ አሾልካው የግራ እጅዋን በቦታው ተካችና በረጅሙ ተነፈሰች፡፡

ሠራዊት ፍቅሬ ያሰናዳውን “ሠካራሙ ፖስታ” የተሰኘውን ፊልም ካየሁ በኋላ ገና ከአዳራሽ ሳንወጣ አጠገቤ ለነበረው ጌጡ ተመስገን “በመዳብ የተለበጠ ወርቅ” አልኩት፤  ምክንያቱስ ብትል ሃሳቡ ትልቅ ነው ርዕሱ ግን ፍሬ ነገሩን የመሸከም ጉልበት የለውም፡፡ መዳብ በወርቅ ይለበጣል እንጂ ወርቅ በመዳብ አይለበጥም፤ የወርቅ ዋጋና ክብር ከመዳብ ዋጋና ክብር ይልቅ እጅግ ከፍ ያለ ነው፡፡ ሁለገብ ተሰጥኦ ያለውን ስመ ጥሩውን፣ ልበ ብሩህ አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬን በጣም በትሁት ሆኖም ቆራጥ በሆነ አቀራረብ “አድዋ”ን ካልሠራህ በቀር ፊልም ሠራሁ እንዳትል ብዬዋለሁ፡፡

Saturday, 17 December 2011 11:01

ከቡና ቤት

ሥዕሎች እስከ ፒያሳ ወግ ሲባል

ፈር መያዣ ከሣምንት በፊት፣ “የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለሙያ ማህበራት፣ ለሚዲያና ሥነ - ጥበብ ባለሙያዎች ባዘጋጀው ብሔራዊ ኮንፍረንስ” ላይ ከ6 በላይ የመወያያ “ጥናታዊ ጽሑፎች” ቀርበው ነበር፡፡
በርካታ ታዳሚያን በተሳተፉበት በዚህ መድረክ፣ የመወያያ ጽሑፎች በአንድ ተጠርዘው ለንባብ በቅተዋል፡፡ መድረኩም ሆነ የመወያያ ጽሑፎቹ በመንግስት በኩል ታላቅ አትኩሮት ያገኙ ይመስላሉ፤ ኢቲቪም በተደጋጋሚ እየቀነጫጨበ፣ አጽንኦት ያገኙ ጥናታዊ ጽሑፎች በሚል የአየር ጊዜ ሲመድብላቸው ታይቷልና፡፡
ከቀረቡት የመወያያ ጽሑፎች መካከል በ29 ገጽ ብዛት ቀዳሚ ደረጃ የያዘው፣ “የኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ወቅታዊ ሁኔታ ከኢ ፌ.ዲ.ሪ ህገመንግስት አኳያ” የሚለው ጽሑፍ ነው፡፡ በቋንቋና ስነ ጽሑፍ የመጀመሪያ ዲግሪ ባላቸው በደራሲ ዳንኤል ወርቁ የቀረበው መለስተኛ “ጥናታዊ ጽሑፍ”፤ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን አንስቷል፡፡ ብዙዎቹ ሃሳቦች ጠንከር ባለ ድምፀት የቀረቡ በመሆኑ፣ ለሌሎች ጥያቄዎችና ውይይቶች ይጋብዛሉ፡፡
ጥናት አቅራቢው ደራሲ ዳንኤል ወርቁም፣ የረጅምና የአጫጭር ልቦለዶች ፀሐፊ፣ የበርካታ ሥራዎች ተርጓሚና ተሸላሚ የፊልም ባለሙያ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ጊዜ “የጥበብ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር” በመሆን በሃገሪቱ የጥበብ እድገት ትልቅ ድርሻ እየተወጡ እንዳሉ የሚነገርላቸው ደራሲና የፊልም ባለሙያ፣ የንባብ ባህል እንዲዳብር በተለይ ህፃናት የንባብ ክሂላቸውን እንዲያጐለብቱ በሚያደርጉት ጥረት ለሃገር ባለውለታ መሆናቸውን መመስከር ይገባል፡፡ ደራሲው የአመኑበትን ጉዳይ በድፍረትና በስሜት በፊትለፊት በመናገር፣ ለብዙዎች አርአያ እንደሆኑም ይነገራል፡፡
ብዙ የህይወት ልምድ እውነቶችና የአካዳሚክ እውቀቶች እንዳሉት የሚታሰብ ደራሲ የሰራው ጥናታዊ ጽሑፍ ደግሞ፣ ብዙዎች እንዲያነቡት የሚያነቃ ይመስለኛል፡፡ ለመወያያ የቀረበው ጽሑፍ እኔንም ለውይይት ጋብዟል፡፡ እናም፣ በጥናታዊ ጽሑፉ ጥንካሬና ድክመት ዙሪያ የተለያዩ መረጃና ማስረጃዎች እየነቀሱ መወያየት፣ የዚች አጭር ሂሳዊ መጣጥፍ የትኩረት አቅጣጫ ነው፡፡
የጥናቱ ወፍ በረራዊ ቅኝት
የመወያያ ጽሑፉ፣ “መግቢያ” ብዙ ርዕሰ ጉዳዮችን ነካክቷል፡፡ ከአጠቃላይ የጥናቱ ገጽ በብዛት አንጻር ሲታይ ሰፊ የሚባል ሲሆን በ4 ገጽ ተስፋፍቶ ቀርቧል፡፡ የጥናቱ የትኩረት አቅጣጫ በአማርኛ ሥነ ጽሑፎች ላይ መሆኑን ከመግለጹ በላይ የአማርኛ የሥነ ጽሑፍ ዳራ (Back ground) አስቃኝቷል፡፡ በመቀጠል፣ “ሥነ ጽሑፍ ባለፉት ሥርአቶች ምን ገጽታ ነበረው” በሚል ከመግቢያው ጋር የሚመሳሰሉ ጉዳዮች ተነስተዋል፡፡
“የኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ ወቅታዊ ሁኔታ” በሚል ርዕስ ስር፣ “ሥነጽሑፍ ለምን ያስፈልገናል?”፣ “ከሌሎች ሀገሮች ተሞክሮዎች ምን እንማራለን?”፣ “አዲሱ ህገመንግስት ለስነጽሑፍ ምን ዕድሎችን ከፍቷል?”፣ “እነዚህን እድሎች ለመጠቀም እንቅፋት የሚሆን ስጋቶች”፣ “ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መንገድ ለውጥ ለማምጣት ምን ጥያቄዎች መመለስ አለባቸው?” እና “የሀገራችን የሥነጽሑፍ እድገት አሁን የደረሰበት ደረጃ እንዴት ይታያል? እያደገ ነው?” የሚሉ ጥያቄዎች እየተነሱ ምሳሌ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ጥናቱ፣ አብይ ርዕስ የሚመስል፣ “በድርሰቶቻችን ላይ ምን ለውጦች ታይተዋል?” የሚል ጥያቄ ያስከትላል፡፡ ከዚህ ጥያቄ ስር፣ “ፌዴራሊዝምን በተመለከተ፣ የአዲስ አበባን ጉልህ ሚና በማንፀባረቅ ረገድ” ፣ “በቋንቋ አጠቃቀም ረገድ” እና “በገፀባህሪያት አሳሳል ረገድ” የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች እየተነሱ ተጥለዋል፡፡ በመጨረሻ፣ “ማጠቃለያ” እና “የዋቢ ጽሑፎች መዘርዘር” ቀርበዋል፡፡
የጥናቱ መልካም አስተዋጽኦ (ግኝት)
ጥናቱ፣ በበርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለውን ተነሳሽነትና ቅንነት ሳይሠስት ገልጿል፡፡ ሥነ ጽሑፍ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ያለውን ሰፊ ድርሻ ጠቁሞ፣ መንግስት ለዘርፉ ትኩረት እንዲሰጥ ህገመንግስታዊ ግዴታ እንዳለበት ጭምር ለማሳሰብ ሞክሯል፡፡ ጥናቱ፣ የጀርመንንና የአሜሪካን ልምድ አጣቅሶ፣ ሥነጽሑፍ ታላላቅ ሀገራዊ ጉዳዮችንና የመንግስት ፖሊሲዎችን ወደ ህዝብ ለማውረድ ያለውን ሚና አስታውሶ፣ መንግስት በወጉ እንዲገለገልበት መክሯል፡፡ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ህገመንግስቱን የማወቅ “የውዴታ ግዴታ እንዳለበት” (ገጽ 10) ያስገነዝባል፡፡
በሌላ በኩል፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚዲያና የሥነጥበብ ባለሙያዎች የህገመንግስት ግንዛቤ እንዲያገኙ አስቦ፣ ብሔራዊ ኮንፈረንስ ከአዘጋጀበት አብይ የመድረኩ ዓላማ አንፃር ሲመዘን፣ ጥናቱ፣ ግቡን እንዲመታ ጥናት አቅራቢው ያላቸውን ቅንነትና ቁርጠኝነት አሳይተዋል፡፡ ጥናቱም፣ የአጥኒውን ህገመንግስታዊ ወገንተኝነት ብቻ ሳይሆን፣ “ደራሲያን የህገመንግስት እውቀታቸው ጥልቅ አለመሆኑን” (ገጽ 23) አረጋግጧል፡፡ እናም ጥናቱ፣ የወቅቱ የኢትዮጵያ ደራሲያን ህገመንግስቱን እንዲያነቡ፣ መንግስትም የግንዛቤ መድረኮችን እንዲያመቻች ጠይቋል፡፡ በተለይ፣ ህፃናት በህገመንግስቱ መልካም እሴት ተቀርፀው እንዲወጡ የሁሉም አካል ሃላፊነት መሆኑን መግለፁን የጥናቱ መልካም አስተዋጽኦ አድርጐ መመዝገብ መልካም ነው፡፡
የጥናቱ ፈርጀ ብዙ ድክመቶች
የመወያያ ጥናታዊ ጽሑፉ፣ ሳይሉት ኢትዮጵያን የምታህል አርበ ሰፊ (ቀለመ ብዙ) ሀገር፣ በአርበ ጠባብ አቅሙ አካልዬ አጠናለሁ በማለቱ ፈርጀ ብዙ ፈተና የገጠመው ይመስላል፡፡ በአንድ በኩል የመረጃና የማስረጃ እጦት ሠቅዞ ሲይዘው፣ በሌላ በኩል የተጠቀሱትም መረጃና ማስረጃዎች እርስ በርስ ሲጣረሱ ይታያል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ዋቢዎቹ አላማቸውን ስተው ሲከሽፉ፣ ሌላ ጊዜ ያለ አቅማቸው ተለጥጠው ሲበጠሱ ይስተዋላል፡፡ ጥናቱ፣ ከመረጃና ማስረጃ ድህነቱ በላይ፣ አብዝቶ የጮኸው ድምፀቱ ያሳጣው ይመስላል፤ ያለ በቂ ማስረጃ ደፋር ማጠቃለያና አስተያየት ለመስጠት መፍጠኑ ግን እንኳን ከታዳሚውና ከተጠኝው ጋር ቀርቶ ከራሱም ጋር (“ጥናት” ከመሆኑ ጋር) እንዳይቆራረጥ ያሰጋን ብዙ ነን፡፡ እናም ይሄም ሂሳዊ መጣጥፍ “ደፋር ፍርደ ገምድል ዳኛ” እንዳይመስል፣  ማስረጃ እያጣቀስን ውይይታችን እንቀጥል፡፡
ጥናታዊ ጽሑፍ ያለምንም በቂ መረጃና ማስረጃ ብዙ ጉዳዮችን አውስቷል፡፡ አብዛኛው አካሂያዱም፣ ከአጠቃላይ ወደ ዝርዝር ጉዳዮች የሚሄድ (deductive method) ነው፡፡ ይህም ማለት በአንድ ርዕሰ ጉዳዩ ቅድሚያ አጠቃሎ (ወይም ወስኖ) ቀድሞ ለደረሰበት ማጠቃለያ የሚሆን መረጃ የሚያፈላልግ ስልት እንደማለት ነው፡፡ ዝርዝር ማስረጃዎችን አሰባስቦ ወደ አጠቃላዩ ጉዳይ ወይም ማጠቃለያ (መደምደሚያ) ለመድረስ አይሞክርም፡፡
ለምሣሌ “ህብረተሰቡ ህገመንግስቱን ማወቅ የውዴታ ግዴታው መሆኑ ገና በቅጡ አልተገነዘበም፡፡ ይህ በምሁሩም ላይ ጭምር የሚታይ እውነታ ነው፡፡ ደራሲውም ሆነ አርቲስቱ የዚሁ ችግር አካል በመሆናቸው ድርሰቶቻቸውም ሆነ የጥበብ ስራዎቻቸው ላይ የሚንፀባረቁ ምንም ተያያዥነት ያላቸው ሃሳቦች የሉም” (ገጽ 10) የሚለው ማየት ይቻላል፡፡
ጥናቱን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ሁሉንም ገጽ አንጠፍጥፈንም ሆነ አጠንፍፈን ብናነብ፣ አንድም ሰው በህገመንግስቱን ዙሪያ የቃል፣ የጽሑፍ መጠየቅ ወይም ሌላ ነገር ሲጠየቅ አይታይም፡፡ የተወሰኑ ናሙናዎች ለወጉ እንኳ ተጠቅሞ (ከምሁሩም ሆነ ከደራሲ መካከል መርጦ) መረጃ ለመጠየቅ አልሞከረም፡፡ ህብረተሰቡ ህገመንግስቱን ስላለማወቁ ግን ጥናቱ አውቋል፡፡ እንዴት? የጥበብ ሥራዎቹም ህገመንግስቱን የሚያንፀባርቁ ምንም ተያያዥነት ያላቸው ሃሳቦች እንደሌላቸው ጥናቱ ማጠቃለል ችሏል፡፡ “ምንም ተያያዥነት የሌላቸው” የሚለውን በአጽንኦት ስታነቡት ግን ህገመንግስቱ ስለምን ይሆን የሚናገረው የሚል ጥያቄ ሁሉ ይፈጥራል፡፡ ምክንያቱም ማንኛውም የጥበብ ሥራ ቢያንስ ማህበራዊነት፣ “ሰዋዊነት፣ ሳይዳስስ የጥበብ ሥራ ሆኖ ህልውናውን ሊያቆም አይችልም፡፡ በሌላ አነጋገር፣ በሰው፣ ስለሰው የተፈጠረ የጥበብ ሥራ ሰዋዊ ጉዳዮችን ማንሳቱ ግዴታው ብቻ ሳይሆን ህልውናውም ነው ማለት ይቻላል፡፡ ህገመንግስቱም በሰው፣ ስለሰው የተፈጠረ ነው፡፡ ሰዋዊ ጉዳዮችን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ወዘተ እንደሚያነሳ ይታወቃል፡፡ ጥናቱ እንደቀልድ “ምንም ተያያዥ ሃሳቦች የሉም” ማለቱ፣ “ሰው” የመሆን ወይም “ጥበብ” የመሆን አጠቃላይ ሀቅን (fact) ሁሉ እየጣሰ መሆኑን የተገነዘበ አይመስልም፡፡
ሌላ ዋቢ እናንሳ፤ ጥናቱ፣ “ህገመንግስታችን ከብዙ የአፍሪካም ሆነ የሌላው ዓለም ህገመንግስታት በተሻለ መልኩ በተደጋጋሚ የመናገር እና የመፃፍ ነፃነትን አስቀምጧል” (ገጽ 15) ይላል፡፡ እዚህ ላይ፣ “የሌላው ዓለም” የሚለውን የከሸፈ ጥቆማ ትተን “ከአፍሪካ ሀገራት” የአንዷን ለምሣሌ የደቡብ አፍሪካን ወይም የጋና የመናገርና የመፃፍ ነፃነት የሚደነግጉ አንቀፆችን በአሀዝ (ቢያንስ እቺን ጉዳይ እንኳ በሳይንስ ለመመለስ) ገልፆ፣ ከኢትዮጵያዊው ጋር በንጽጽር ለማሳየት አልቻለም፡፡ ጥናቱ ግን፣  ህገመንግስታችን ከሌላው ዓለም ህገመንግስታት ሁሉ የተሻለ መሆኑን በአጽንኦት ይገልፃል፡፡ እንዴት ነው ነገሩ? እንዲህ አይነቱን “ስሜታዊ ሀሳብ” ያለ ማስረጃ እንኳን ለኢትዮጵያ ህዝብ በሚቀርብ “ጥናታዊ” ጽሑፍ ቀርቶ፣ በሻይ ቡና ላይ ለቅርብ ጓደኛ ለማውራትም የሚከብድ ይመስላል፡፡
ጥናቱ ስሜታዊነት ጐልቶበታል የሚባለው፣ እስከ አሁን በተጣቀሱት ማስረጃዎች ብቻ ቢሆን እዳው ገብስ ነበር፡፡ ግን ቀደም ሲል በጥናቱ ወፍ በረራዊ ቅኝት ላይ የተዘረዘሩት፣ ጥናቱ ያነሳቸው ርዕሰ ጉዳዮች አብዛኞቹ (እደግመዋለሁ “አብዛኞቹ”) በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የጠቆሟቸው መረጃዎችና ማስረጃዎች ከሽፈውባቸዋል ማለት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ “ከአርነት የተላቀቀ ሥነጽሑፍ ሆነ ደራሲ” ለመስከን 4 ደረጃዎች ማለፍ እንዳለባቸው አንድም ባለሙያ ሳይጠቅስ “ብዙ አጥኚዎች ይስማማሉ” (ገጽ 13) መባሉ፣ አንድም ደራሲ ሳይጠየቅ፣ “ደራሲው ህገመንግስቱ መኖሩን እንጂ ምን እንደሚል ስላለመረዳቱ (ገጽ 10)፣ በሀገራችን የሳንሱርን አፋኝነትና ፀርነት የሚያመለክት አንድም ድርሰት ሳይፃፍ ሃያ አመት ስለማለፉ (11)፣ “ህገመንግስቱ ይዞት የመጣውን መብት እና ነፃነት ተጠቅሞ ጐላ ያለ ስራ የሰራ ደራሲም ሆነ ድርሰት ለማግኘት አስቸጋሪ ስለመሆኑ” (ገጽ 12)፣ የነ ራስ እምሩ ኃይለሥላሴ ግለ ታሪክ “ጽሑፎቻቸው የተደበቁ ምስጢሮችን ሊያሳውቁን ይችላሉ በሚል በከፍተኛ ቁጥር ቀደም ብሎ ባልነበረ ነፃነት” ስለመታተማቸው (ገጽ 14) ፣ በኢትዮጵያ “አንድ በመቶ እንኳን አንባቢ እንደሌለ” (ገጽ 23) ወዘተ የሚሉ አንድም በሳይንሳዊ ዘዴ (በአሀዝ) የተጠቀሰ ዋቢ ያልያዙ ብዙ ስሜታዊ ሀሳቦችን (ግኝቶችን) ጥናቱ አስተንትኗል፡፡
“ከሌሎች አገሮች ተሞክሮዎች ምን እንማራለን?” በሚለው ውጭ ተኮር ርዕሰ ጉዳይ ላይም፣ በጥናት የተደገፉ ማስረጃዎች ሳይጠቀሱ የተሰጡ አጠቃላይ አስተያየቶችም ደፈር ያሉ ይመስላሉ፡፡ የአንድ ጀርመናዊ አንድ መጽሐፍ ጠቅሶ፣ “ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት በኋላ በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች የነበሩ ደራሲያን ተግባር በድርሰቶቸቸው ህዝባቸው ከነበረበት አዘቅት የሚወጣበትን መንገድ ማመላከት እና ራሱን እንዲፈልግ ማገዝ ነበር” (ገጽ 9) ሲል፣ የወቅቱ ሁሉም ደራሲዎች የፈፀሙት ተግባር ያስመስላል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ አሜሪካዊያን ደራሲዎች ህገመንግስታቸውን ለህፃናት ለማስተማር ሲሉ ሁሉ ድርሰት ይጽፉ እንደነበረ የአንድ ደራሲ ነጠላ ሥራ በመጠቆም አጠቃላይ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ ተሞክሯል (ገጽ 9 እና 24)፡፡
የአሜሪካን ተመክሮ እንኳን በምሣሌነት ብናይ አንዳንድ መረጃዎች ጥናቱ የገለፃቸውን መረጃዎች ሙሉ በሙሉ ባያከሽፉ እንኳ፣ መጠርጠር እንዳለብን የሚያነቁን ይመስላል፡፡ የአሜሪካ ደራሲዎች ህገመንግስቱን ለማስረጽ ጥረት እንደሚያደርጉ በጅምላ በተነገረበት በዚያን ጊዜ አንዳንድ ወጣት ደራሲያን በህገመንግስቱ ላይም ሆነ በስነጽሑፍ ላይ ያምጹ እንደነበረ አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ለምሣሌ አለን ብሉም የተባሉት ስመ ጥር አሜሪካዊ ፕሮፌሰር፣ The Closing of the American Mind (1987) በሚለው መጽሐፋቸው፤ አሜሪካዊ ወጣቶች በተፈጥሮም ሆነ በስምምነት የማይዳኙ፣ የሙዚቃንም ሆነ የመጽሐፍን ዋጋ አሳንሰው የሚመለከቱ፣ እግዚአብሔር የለም እስከ ማለት የደረሱ የባዶነት ፍልስፍና (Nihilism) የተጠናወታቸው እንደሆኑ በመግለጽ፣ “ሀገሬ ምን ይበጃት ይሆን?” እያሉ ይጨናነቃሉ፡፡
ጥናቱ፣ እርስ በርስ የሚጣረሱ ሀሳቦችም በየፈርጁ የነገሱበት ይመስላሉ፡፡ ለምሣሌ፣ “አሁን ባለንበት ተጨባጭ ሁኔታ ግን በሁሉም ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቋንቋዎች ያሉትን ማህበራዊ እውነታዎችንና ባህላዊ ገጽታዎችን የሚገልጹ ኪነጥበባዊ ሥራዎች ጐልተው እየወጡ አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ የየብሔር ብሔረሰቡን ነባርና ትውፊታዊ ባህል ይዘው የሚወጡ የክዋኔ ስራዎች ግንባር ቀደሙን ቦታ ይዘዋል” (ገጽ 16) በሚለው አንቀጽ ያሉት አረፍተነገሮች መዋቅራዊ ፅምረታቸው ከመንኮላሸቱ ባሻገር፣ ቀደም ሲል እንዳየናቸው ያለበቂ ማስረጃ ደፋር መደምደሚያ ያስቀምጣሉ፡፡ ሰሞኑን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ፣ የብሔር ብሔረሰቦች አንድነታቸውን የሚያጠነክሩ ኪነጥበባዊ ባህሎቻቸው ጐልተው እንደወጡ የገለጹትን ማንፀሪያ ትተን እንኳ የጥናቱን ሃሳቦች እርስ በርስ ስናናብብ የሚጣረሱ ስህተቶች ያጋጥሙናል፡፡ በጥናቱ መግቢያ ላይ የተገለፀው የመግቢያ አረፍተ ነገር ጥናቱ በአማርኛ ሥራዎች ላይ የሚያተኩረው፣ “በሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የተሰሩ ስራዎችን አንብቦ ለመረዳት ያለው የቋንቋ ገደብና የመረጃዎች እጥረት” (ገጽ 11) በመኖሩ እንደሆነ ቢገለጽም፣ እንዴት እንደተሰፈሩ ሳይታወቁ የብሔር ብሔረሰቦች ኪነጥበባዊ ሥራዎች ጐልተው አለመውጣታቸው ያለ ጥርጥር መስተጋባቱ ግን ጥናቱን ትዝብት ላይ የሚጥለው ይመስላል፡፡
እስከ አሁን የተወሱት፣ ጥናቱ ያለምን ተጨባጭ ማስረጃ የደረሰባቸውን ስሜታዊ ማጠቃለያዎች ነው፡፡ በርግጥ፣ በቂ ማስረጃዎች ባይጠቀስባቸውም አጥኒው ካላቸው የገጠመኝና የአካዳሚክ እውቀት ሳቢያ የምንቀበላቸው ተጠየቂያዊ ሀሳቦች እንዳሉ ይታመናል፡፡ በሌላ በኩል፣ በተጨባጭ መረጃነት የተቆጠሩት ማስረጃዎች ያለቦታቸው እየተሰነቀሩ የስህተት ምንጭ የሆኑበትን ሁኔታ ስናጤን፣ የጥናቱ አስተማማኝነት (Reliability) እና ጽኑነት (Validity) ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚገቡ ይመስላል፡፡
ጥናቱ፣ ያጋጠሙት የተሳሳቱ መረጃዎችን በሚመለከት ሁለት ምሣሌዎችን ማንሳት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው፣ ከ20ኛው ክ/ዘመን አብይ ነጥቦች አንዱ፣ ሌላውን የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ገጽታ እንኳን ትተን የሥነ ጽሑፍን መስክ ስናይ   “ብዙ አንጋፋ የኢትዮጵያ ደራሲያን ከዘመናዊ ትምህርት ጋር መተዋወቃቸውና ውጭ አገር እየሄዱ ሰፊ ልምድ ይዘው ወደ አገራቸው መምጣታቸው ነው፡፡ ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ መንግስት እና የህዝብ አስተዳደር የዚሁ ጥረት ውጤት ነው”   (ከገጽ 3) የሚለው ነው፡፡
ከላይ ከቀረበው ማስረጃ ላይ፣ “ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ገጽታ እንኳ ትተን የሥነ ጽሑፍን መስክ ስናይ” የሚለውን በአጽንኦት ስናጤን ፀሐፊውም ሆኑ መጽሐፋቸው ካለ ቦታው የተሰነቀረ መረጃ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ገብረሕይወት በተጠቀሰው መጽሐፋቸው፣ በምጣኔ ሀብት እንዴት እራስን መቻል እንደሚቻል በማስተንተን “የፖለቲካዊ ኢኮኖሚ” አዋቂነታቸውን እንዳስረገጡ ይታወቃል፡፡ ሁለተኛው ተጠቃሽ ምሣሌ ደግሞ፣ ጥናቱ በገጽ 21 ላይ የቅርብ ጊዜ የረጅም ልቦለድ መፃሕፍትን (ለምሳሌ የደርቡ፣ ሽንብሩት እና የአስማማው ከደንቢያ ጐንደር እስከ ዋሽንግተንን ከዘረዘረ በኋላ፣ “የእንዳለ ጌታ ከበደ፣ ኬርሻዶ ከነዚሁ ጐራ የሚጠቀስ ነው” ይላል፡፡ ኬርሻዶ ግን ደራሲው ከአያቶቹ ጋር ስላሳለፈው የልጅነት ትዝታው የምታቀነቅን፣ ፍክሎራዊ ገጽታዋ ደመቅ ያለ ኢ- ልቦለድ መጽሐፍ ናት፡፡
እስከ አሁን የተነሱትን ጉዳዮች ብቻ ብናስተውል ጥናቱ፣ በርከት ያሉት ህፀፆች አጋጥመውታል ማለት የሚቻል ይመስለኛል፡፡ በተለይ የህገመንግስቱን መልካም እሴቶች የሚዘክሩ ሥራዎች የሉም እና ደራሲያኑም ህገመንግስቱን አያውቁትም በማለት በጅምላ ጨራሽ የቃል ጦር ከመረፍረፍ ይልቅ፣ ህገመንግስቱን ስለማያምኑበት እያወቁትም  ወይም እንዲሻሻል ስለሚፈልጉ፣ ወይም ህገመንግስቱን በቀጥታ እያነበነቡ ከመስበክ ይልቅ እሴቶቹን፣ ሰዋዊ ትርጓሜውን በዜጐች የህይወት ዑደት ውስጥ በሌሎች ወካዮች (ተምሣሌቶች) ሰይመው እየፃፉበት እንደሆኑ ወዘተ ብሎ ሌሎች አቅጣጫዎችን (በጥናት  ማረጋገጥ ፈተና ቢሆን እንኳን) ማመላከት ብልህነት ነው፡፡
ጥናቱ ባተኮረባቸው የጊዜ ምዕራፎች ውስጥ ምን ያህል እረጅም ልቦለድ፣ አጭር ልቦለድ እና ግጥም እንደታተሙ ይታወቃሉ? ይህን ጥያቄ የጠየቅኩት “ጥናታዊ ጽሑፍ” በመቅረቡ ነው፡፡ አጥኒው ላይ ታች ብለው ተቀራራቢ አሀዝ ማግኘት ቢከብዳቸው እንኳ፣ የሥነፅሁፍ ባለሙያዎቹን እነ አስፋው ዳምጤን እና ዘሪሁን አስፋውን (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ብቻ እንኳ ለማነጋገር ቢሞከር ቢያንስ ከ85% በላይ ትክክለኛ መረጃ ያገኙ ነበር፡፡   የህገመንግስቱን እሴቶች እንደ ዓላማ ለማስረጽ የተገዳደሩ፣ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን የሚያጠይቁ፣ በፖፕሌሽ ሚዲያ እንኳ በተለያዩ ዘውጐች የታተሙ የሥነጽሑፍ ሥራዎች እያሉ፤ በስደት፣ በኤድስ በሽታ፣ በሙስና፣ በህግ ጥሰት ዙሪያ፣ በብሔር ክፍፍል፣ በጐጂ ልማድ፣ በፍትህ ጥያቄ ወዘተ ዙሪያ በርከት ያሉ ረጅምና አጭር ልቦለዶች እንዲሁም የግጥም ስብስቦች በእነዚህ 20 ዓመታት ውስጥ መታተማቸው ይታወቃል፤ የነ ዘሪሁን አስፋው የቅኝት ጥናትና፣ የነ አስፋው ዳምጤን “ጥበበ ቃላት” ለተመለከተ፣ ወይም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ ክፍል የተሠሩ የቅርብ ጊዜ መዘርዝራዊ ጥናቶችን የጠየቀም፣ ቢያንስ በእነዚህ 20 ዓመታት ውስጥ የህገመንግስቱን እሴቶች ለማስተዋወቅ የሞከረ (ከሲሳይ ንጉሱ ሥራ በቀር) ሥራ የለም የሚል ስሜታዊ ማጠቃለያ ከመስጠት ይቆጠባል፡፡ ጥናቱ፣ ቀደም ሲል እንደተጠቆመው ሌላ የውይይት መድረክ ፈጥረን እንድንማማር እድል ሰጥቶናል፡፡ ለመወያያ የሚሆኑ ፈርጀ ብዙ ጉዳዮችን እንድናነሳ ያነቃናል፡፡ እናም፣ ሣምንት ጥናታዊ የመወያያ ጽሑፉ፣ ምን ያህል የጥናትና ምርምር መርሆዎችን ስለመከተሉ፣ ደራሲያን ህገመንግስቱን የማስተዋወቅ የውዴታ ግዴታ እንዳለባቸው የማሳሰቡ አንድምታና እንዳሸን የፈሉት የግጥም መጻሕፍት የተለመደ የሀዘን እንጉርጉሮ ብቻ ነው የሚያቀርቡት ከተባለበት ማዕዘን አንፃር ለመወያየት ቀጠሮ ይዘን ብንሰነባበትስ …

ፈር መያዣ ከሣምንት በፊት፣ “የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለሙያ ማህበራት፣ ለሚዲያና ሥነ - ጥበብ ባለሙያዎች ባዘጋጀው ብሔራዊ ኮንፍረንስ” ላይ ከ6 በላይ የመወያያ “ጥናታዊ ጽሑፎች” ቀርበው ነበር፡፡ በርካታ ታዳሚያን በተሳተፉበት በዚህ መድረክ፣ የመወያያ ጽሑፎች በአንድ ተጠርዘው ለንባብ በቅተዋል፡፡ መድረኩም ሆነ የመወያያ ጽሑፎቹ በመንግስት በኩል ታላቅ አትኩሮት ያገኙ ይመስላሉ፤ ኢቲቪም በተደጋጋሚ እየቀነጫጨበ፣ አጽንኦት ያገኙ ጥናታዊ ጽሑፎች በሚል የአየር ጊዜ ሲመድብላቸው ታይቷልና፡፡

ብራዚል በ2014 ለምታስተናግደው 20ኛው ዓለም ዋንጫ ለማለፍ በአፍሪካ ዞን የሚደረገውን የምድብ ማጣርያ ሰሞኑን ለመቀላቀል የበቃው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቀጣይ ትኩረት ያስፈልገዋል፡፡
ብሄራዊ ቡድኑ በ20ኛው የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣርያው የዛሬ ሳምንት ጅቡቲ ላይ ከሶማሊያ ያደረገውን ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ሲመለስ በርካታ ደጋፊዎቹን አበሳጭቶ የነበረ ሲሆን በሳምንቱ አጋማሽ ላይ በመልስ ጨዋታው 5ለ0 አሸንፎ ወደ ምድብ ማጣርያው መግባቱ የተፈጠረውን ተስፋ መቁረጥ አብርዶታል፡፡

በድሪምዎርክስ የተሰሩት “ፑስ ኢን ዘ ቡትስ” በሰሜን አሜሪካ፤ ስቴቨን ስፒልበርግ ዲያሬክት ያደረገው “ዘ አድቬንቸር ኦፍ ቲን ቲን” በመላው ዓለም በሳምንታዊ ገቢያቸው የቦክስ ኦፊስ ደረጃን እየመሩ ነው፡፡ በ130 ሚሊዮን ዶላር በጀት በዲጅታል 3ዲ የተሰራው “ፑስ ኢን ዘ ቡትስ” በታዋቂው የሽሬክ ፊልም ላይ ያለውን የድመት ገፀባህርይ ፕስ መሪ ተዋናይ አድርጓል፡፡ በኮምፒውተር አኒሜሽን የተፈረጀው ፊልሙን በድምፅ መሪ ተዋናይ ሆኖ አንቶኒዮ ባንደራስ ሰርቶታል፡፡ ሳልማ ሃይክ፤ ዛክ ጋልፊናኪስና ቢሊ ቦብ ቶርተንም ተሳትፈውበታል፡ ፑስ የተባለው ድመት በሽሬክ ፊልም ላይ ከሽሬክና ከዶንኪ ጋር ከመገናኘቱ በፊት በነበረው ጀብደኛ ህይወቱ ላይ የሚያጠነጥን ታሪክ ይዟል፡፡