Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

“የሚገባበት አይታወቅምና በደንብ ይገንቡ”

ጊዜው ቆየት ብሏል፡፡ ደራሲ ሲሳይ ንጉሱ በአንድ መድረክ ተጋብዞ ልምዱን ሲያካፍል “በሕይወቴ ትልቁን ትምህርት የተማርኩት በማረሚያ ቤት አንድ ዓመት በቆየሁበት ጊዜ ነው፡፡ ከመታሰሬ በፊት የዩኒቨርስቲ ምሩቅ የነበርኩ ቢሆንም ከትምህርት ያላገኘሁትን ዕውቀት በእስርቤትአግኝቻለሁ”
ማለቱን አስታውሳለሁ፡፡ ዐፈሩ ይቅለለውና ጋዜጠኛ አብርሃም ረታ ዓለሙም “እስር ቤት ገብቶ የወጣ ሰው ስለ ዓለምና ሕይወት ያለው አመለካከት ከሌሎች ይለያል፡፡ መታሰርን ማንም የማይመርጠውና የማይደገፍ ነገር ቢሆንም ከአስተማሪነቱ አንፃር ሁሉም ታስሮ ቢያየው አይጠላም” ብሎ ነበር፡፡ ስለ እስር፣ አሳሪዎችና እስር ቤት ከጥንት ጀምሮ እየተነገሩና እየተፃፉ የመጡ ብዙ ታሪኮች አሉ፡፡ በአገራችንም ነገሥታት ተወላጅ ቤተሰቦቻቸው በስልጣን እንዳይጋፏቸው በተመረጠ ቦታ ሰብስበው ያስቀምጧቸው (ያሰሯቸው) እንደነበር፤ ይህም ሂደት ለብዙ ዘመናት ባህል ሆኖ መቆየቱን በተለያዩ የታሪክ መፃሕፍት ተመዝግቧል፡፡ ነገሥታት ቤተሰቦቻቸውን ብቻ ሳይሆን በስልጣናቸው የሚመጣባቸውን ወይም ከሕግ ውጪ ነው ያሉትን ተራ ዜጋም ቢሆን በማረሚያ ቤት እንዲቆይ ማድረግ አንዱ ተግባራቸው ነው፡፡

“ወርቅ በወርቅ” ሲመረቀ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ የሆነውም ይህ ነበር፡፡ ፊልሙን ለመታደም የክብር መጥሪያ ደርሶአቸው ወደ አዳራሹ ለመግባት በር ላይ የተኮለኮሉት በርካታ ቁጥር ያላቸው ተመልካቾች ሙሉ ሱፍ በለበሱና ቁጥራቸው የትየለሌ በሆኑት የዝግጅት አስተባባሪዎች አቧራ ተነስቶባቸዋል፡፡ካሳንቺስ ቶታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አዘውትሮ ለተመላለሰ ሰው ወይ በቶታሉ ቅጥር ክልል በሚገኝ አንድ ጥግ ወይንም ደግሞ ከፊት - ለፊቱ ባለ አንድ ካፌ በረንዳ ላይ አንድ ታላቅ ኢትዮጵያዊን ይመለከታል፡፡ እኚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ በበርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የስኬት ታሪክ ውስጥ ቁጥር አንድ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ አንጋፋው አሰልጣኝ ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ!

ኤግዚዝቴንሻሊዝም የውድቀት ወይንም ዝቅጠት ፍልስፍና ተብሎ ነው በቅፅል ስሙ የሚጠራው፡፡ የሀሳብ ባህል ሞት ውስጥ የተወለደ “የመሆን (being)” ምንምነትን የሚያስረዳ የፍልስፍና አይነት ነው፡፡ … ምንምነትን የሚገልፀው ግን መግለፅ የሚችለውን ብቸኛውን ፍጡር፣ ሰውን ሆኖ ነው፡፡ በህልውና መገኘት ለህልውና ትርጉም ከመስጠት ይቀድማል፡፡ “የምንምነትን አንዳች ነገርነት (ምንምነት ባዶነት አለመሆኑን) መጀመሪያ የተነተነው ሀይደርጋር (Heidgger) ቢሆንም፤ “ምንምነትን ወደ አለም ያመጣው የሰው ልጅ ነው” ያለው ግን ዣን ፖል ሳርተር ነው፡፡ …ለዚህ ግኝቱ የኖቤል ሽልማት ተበርክቶለት … ለመጀመሪያ ጊዜ አልቀበልም ያለውም ይኸው ፈረንሳዊ ፈላስፋ ነበር፡፡ ምናልባት ምንምነት ስለሆነበት ሊሆን ይችላል፡፡

ስለ ኢትዮጵያ ማንነትና ታሪክ፤ ስለ አገራችን ባህልና አዝማሚያ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጥያቄዎችን በማንሳት፤ ከቴዲ አፍሮ ጋር ያደረግነውን ቃለ ምልልስ ባለፈው ሳምንት ማቅረባችን ይታወሳል። በዛሬው የመጨረሻ ክፍል፤ በአንድ ርእሰ ጉዳይ ላይ እናተኩራለን - የኪነጥበብ ፈጠራ ላይ። የመረጥነው ርእሰ ጉዳይ፤ በጣም አስፈላጊ የመሆኑን በዚያው ልክ ለውይይትና ለትንታኔ፤ ለጥያቄና ለመልስ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ እንገነዘባለን። ቢሆንም ልንደፍረው ሞክረናል።

Saturday, 16 June 2012 09:31

የዝነኞች ጥግ

ሁሉም ተዋናይ ቢያንስ አንድ ጊዜ ፊልም ዳይሬክት ማድረግ አለበት - በፊልም ሥራ ወቅት ያለውን

ችግር የመረዳት ትዕግስት እንዲላበስ፡፡ በእርግጥ ሁሉም ዳይሬክተርም መተወን አለበት፡፡

ክሊንት ኢስትውድ

(አሜሪካዊ የፊልም ተዋናይና ዳይሬክተር)

ስለተመልካቾች

ሙዚቃ ስጫወት ተመልካቹ ካንጓጠጠኝ ሙዚቃውን እየተሳደበ ነው፤ ስለዚህ መጫወቱን

አቆማለሁ፡፡ ሙዚቃ መስማት ካልፈለጉ እኔ ለምን እጫወታለሁ? ተመልካቹ እኔ ስጫወት ለማየት

መርጦኝ መጣ እንጂ እኔ ተመልካቹን አልመረጥኩትም እኮ!

Saturday, 09 June 2012 10:57

የሐሳብ ታቦታት

መጋረጃው ሲገለጥ የንጉሡ ዙፋን አለ፡፡ መንጠላቴቱ ሲከፈት መንበሩን እናያለን፡፡ በመንበሩ ላይ ታቦቱን …በታቦቱ ውስጥም …ፅላቱን…በፅላቱ ላይ ቃላቱ፡፡ የትዕዛዝ ቃላቶች፡፡ ቃላት የሐሳብ መሠወርያ ታቦታት ናቸው፡፡ ሐሳቡ በራሱ ደግሞ ሊል የሚፈልገው ነገር ጽላት ነው፡፡ የምንደርስበት ነገር ደግሞ ነገሩ በቁሙ ካለው ማንነት ውጪ መንፈስ የሚመገበው መስዋዕት ነው፡፡

ምሳሌ አንድ…

ሊነገረን የተፈለገው ነገር በውስጡ አለ እንጂ ነገሩ (ሃሳቡ) ራሱ በራሱ ፍፁም መልዕክት ሊሆን አይችልም…(የጠይም ሕዝብ ማንነት ነውና)…

Saturday, 02 June 2012 09:59

የጥር ቅዳሜ

ታክሲ ውስጥ ከተዋወቅን በኋላ በአካለ ሥጋና በመጠነ ሐሳብ ለመገናኘት ዛሬ የመጀመሪያ ቀጠሮዋችን ነው…

ፒያሳ

Five town

ቀደም ብዬ እየጠበኩት ነው፡፡ እንደሚመጣ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ሌላ…ብዙው ምክንያት ቢቀር እንኳ ከእኔ ለመገናኘት ዛሬ…የመጀመሪያው ቀጠሮዋችን ስለሆነ…ይመጣል…የተንቀዠቀዡ ዐይኖች ቢኖሩትም የኔን ውበት ለማክበር እንደማይዘገይ ተስፋ አደርጋለሁ…ስለዚህ እጠብቀዋለሁ…እዚህ ፒያሳ “Five house” (በነገራችን ላይ ይሄን ቤት በጣም እወደዋለሁ…ሌላ…ብዙ …ምርጥ…ቤቶች …ሳላይ ቀርቼ አይደለም…ያየኋቸው…ምርጥ መሸታ ቤቶች ዶሮ ማነቂያ ውስጥ ስላለሆኑ ከዚህ ቤት አይልቁብኝም…) እዚያ…ነኝ…

የተለያዩ የውስኪ ዓይነቶች ለምሳሌ…white horse, Red label, Black label, Jock Daniel…የተለያዩ የቮድካ ዓይነቶች Smirnoff, stochilyta, Absolute vodka, witer palace, የወይን …የምናምን…የመጠጥ ዓይነቶች ለዐይን ማራኪ በሆነ መልኩ ከተደረደሩበት ፊት ለፊት ባልኮኒው አጠገብ ተቀምጬ እየጠበኩት ነው…

በኢትዮጵያ ስነ ጽሁፍ አዲስ ዘዴን የሞከረ፣ የፈጠረ እና ተወዳጅ የስነ ጽሁፍ ሰው ነው፡፡  እንደሌሎቹ የስነ ጽሁፍ ሰዎች፣ ስነ ጽሁፍ የነፍስ ጥሪው እና የተፈጥሮ ስጦታው ብቻ አልነበረም፡፡ ስነ ጽሁፍን እስከ ሁለተኛ ዲግሪ (በማስተርስ ዲግሪ) የተማረ፣ ቴክኒኮቹንም በስራዎቹ ተግባራዊ ያደረገ ነው፡፡ በዚህም በወቅቱ ከነበሩት ደራሲዎች፡- ከሃዲስ ዓለማየሁ፣ አቤ ጉበኛ፣ በዐሉ ግርማ  እና ሌሎችም የስነ ጽሁፍ ሰዎች ይለያል፤ዳኛቸው ወርቁ፡፡ዳኛቸው የጻፈው በአማርኛ ብቻ አልነበረም፤ በእንግሊዝኛ ስራዎቹም ጭምር ታዋቂነትን አትርፏል፡፡ በ1973 የታተመው ‘The Thirteenth Sun’ የተባለው መፅሃፉ ምእራቡን ዓለም የማረከ ስራው ሲሆን በፖርቹጋልኛ፣ በጀርመንኛ እና በቻይንኛ ተተረጎሞ በሰፊው ተነቦለታል፡፡ መጽሃፉ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በ312 ዶላር ይሸጥ ነበር፡፡ ይህ ታላቅ የጥበብ ሰው የተወለደው በ1928 ዓ.ም ነው፡፡ ለዳኛቸው ታላቅነትና የተስተካከለ ህይወት መስመር አባቱ ትልቅ ሚና አለው፡፡ አባቱ፣ አቶ ወርቁ በዛብህ ከጊዜው የቀደመ ተራማጅ ሰው ነበር፡፡

42 ዓመት በመጽሐፍ ንግድ

የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ንባብን በማበረታታት አስተዋጽኦ አድርገዋል ያላቸውን ተቋማትና ግለሰቦች ግንቦት 4 ቀን 2004 ዓ.ም በጣይቱ ሆቴል ባሰናዳው መድረክ ሠርተፊኬት በመስጠት አመስግኗል፡፡ መጽሐፍ በመሸጥ ሥራ ከ40 ዓመት በላይ አገልግሎት በመስጠት ተሸላሚ ከሆኑት አንዱ አቶ ይለማ በረካ ስለ ሥራ ዘርፉና ስለ ግል ሕይወታቸው ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ከብርሃኑ ሰሙ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ሥራውን በስንት ዓመትዎ ቢጀምሩ ነው፤ በ42 ዓመት አገልግሎት ሰጪነትዎ ለመሸለም የበቁት?በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ ዳቁና ቀበሌ በ1948 ዓ.ም ነው የወለድኩት፡፡ እስከ 9 ዓመቴ ድረስ በትውልድ መንደሬ ቆይቼ በ1957 ዓ.ም አዲስ አበባ መጣሁ፡፡ አጐቴን ተከትዬ ነበር የመጣሁት፡፡ መርካቶ ወስጥ የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራሁ እራሴን የማስተዳደሩን ኃላፊነት የወሰድኩት ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡

Saturday, 02 June 2012 09:16

ብርሐን እና ጥላ

በጣም ለረጅም ዘመን … ማስታወስ እስከሚችልበት ጊዜ … ሁሌ ለመሞት ሲዘጋጅ … ለመሞት ሲጓጓ ነው የቆየው፡፡ የሚያውቀውን እየጠላ ለማያውቀው ሲጐመጅ ራሱን አጥብቆ ጠይቆ አያውቅም፡፡ “ለምን … ለምንድነው ለመሞት የምትፈልገው?” ልጅ እያለ መሞት የሚፈልገው የሂሳብ አስተማሪ በእየቀኑ ስለሚገርፉት … ከሳቸው ዱላ ለመትረፍ ያለው ብቸኛ አማራጭ መሞት ብቻ ይመስለው ስለነበር ነው፡፡  ሁለተኛ ክፍል በነበረበት ወቅት እሁድ ማታ ሙሉ የልብስ ሳሙና በልቶ ለመሞት ሞክሮ ነበር፡፡ እሱም አልሞተም፤ ሰኞም በጠዋት እንደሌላው የትምህርት ቀን በሰአቱየመጀመሪያው  ፔሬድ ተደወለ፡፡ የሂሳብ አስተማሪውም “ዳንኤል በቀለ ና ውጣ! አንተ ድንጋይ!” ብለው  ሁለተኛው ፔሬድ ላይ ገረፉት፡፡ ሳሙናውን በውሀ እያወረደ ለመብላት የፈጀበትን ጊዜ የቤት ስራውን በመስራት ቢተካ ኖሮ፣ ከመገረፍ ይተርፍ እንደነበረ ያኔም ሆነ አሁን አልተከሰተለትም፡፡