ገመድ አልባ ስፒከር ለገበያ ቀረበ
የእንግሊዝ አምባሳደር - ስለ ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ግሪግ ዶሪ ከጠ/ሚኒስትር መለስ ህልፈት በኋላ ስላለው የኢትዮጵያ ሁኔታ፣ ስለበጀት ድጋፍ፣ ስለ ኢንቨስትመንት፣ ስለ ሰብዓዊ መብት አያያዝና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ መልካሙ ተክሌ ጋር ሰፊ ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡ እነሆ:-የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈትን ተከትሎ በአገሪቱ ውስጥ ችግር ይፈጠራል ብለው የገመቱ ሰዎች ነበሩ፡፡ እርስዎ ተመሳሳይ ግምት ነበርዎት?የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ድንገተኛ ሞት አሳዛኝ ነው፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያ ማለት አንድ ሰው ማለት አይደለችም፡፡ ይሄ የታሪክ መጨረሻ አይመስለኝም፡፡ በአገሪቱ ብቃት ያለው መንግስት አለ፡፡ አገሪቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድን ጨምሮ በርካታ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች አሏት፡፡ ይህም ወደሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ያስጉዛችኋል፡፡ የወትሮ እንቅሥቃሴና ሥራ እንደተለመደው ይቀጥላል፡፡ ባለፉት ሳምንታትም ሆነ አሁን የፀጥታና ደህንነት ችግር አላየሁም፤ ደንብና ስርዓት እንደተጠበቀ ነው፡፡
መሪዎች፣ ሞታቸውና ለቅሶአችን
አጼ ቴዎድሮስ በመሞታቸው ምንአልባት የቅርብ ቤተሰባቸው (እሱም ከነበረ ነው) በቀር ያለቀሰ መኖሩ ያጠራጥራል፡፡ ምክንያቱም ሰውየው በውጭ በእንግሊዞች፣ በውስጥ ደግሞ ለዘውድ ሲሻኮቱ በነበሩ የየአካባቢው ባላባቶች ወጥመድ ውስጥ ገብተው ስለነበር ነው፡፡ ራሳቸውም ቢሆኑ በፖለቲካና በስርቆት ምክንያት ለሚገድሏቸው ሰዎች እንዳይለቀስ በአዋጅ ከልክለው ነበር ይባላል፡፡ ሀገራችን በሺህ ለሚቆጠሩ ዘመናት ሉዓላዊት ሆና መኖሯና አሁንም ሉዓላዊት ሀገር መሆኗ አያጠያይቅም፡፡ ይሁን እንጂ በዕድሜ የመገርጀፏን ያህል የረጋ የፖለቲካ ስርዓት አልነበራትም፤ የላትምም፡፡ በዚህ የተነሳ መሪዎች ወደ ከፍተኛው የስልጣን እርካብ የሚቆናጠጡት ወይ ገድለው ነው፤ ርህሩህ ከሆኑም የነበረውን መሪ ከርቸሌ አሽቀንጥረው ነው፡፡ ዙሩ ሲደርስ እነሱም በመጡበት መንገድ ይሰናበታሉ፡፡
ልጅ እንዳልካቸው መኮንን
ለተመድ ዋና ጸሐፊነት የተወዳደሩት የመጀመሪያው አፍሪካዊ
በአስራ ሰባቱ የደርግ ዘመናት የኢትዮጵያ ሥም በረሐብና በእርስ በእርስ ጦርነት ከመጉደፉ በፊት፤ አገሪቱ የምትታወቀው በጥንት ስልጣኔዋ፣ በነጻነቷና እርሱን ባስገኙላት ጀግኖቿ ነበር፡፡ በተለይ በአድዋ የተጎናጸፈችው አንጸባራቂ ድል የኮሎኒያሊስቶችን ቅስም የሰበረ ምት ከመሆኑም ሌላ በአስከፊ ቅኝ አገዛዝ ሥር ወድቀው ሲማቅቁ ለነበሩት ሕዝቦች የነጻነት ተስፋን ጎህ የፈነጠቀ ነበር፡፡
ከታሪክ መማር ብልህነት ነው
በ930 ዓ.ዓ (ቅድመ ልደት ክርስቶስ) የአንዲት የቀጣናዋ ልዕለ - ሃያል የነበረች ሀገር ሕዝቦች፤ ለአርባ አመታት (ከ970 ዓ.ዓ - 930 ዓ.ዓ) የምድሪቱ ንጉስ የነበረውንና በሞት የተለየውን አባቱን ተክቶ የንግስና ዘውዱን ሊደፋ ተገቢ ሆኖ የተገኘው ልጁ የአባቱ አልጋ ወራሽ ሆኖ ወደ ዙፋኑ ለመምጣት በተዘጋጀበት ወቅት፣ ለበዓለ ሲመቱ በመረጧት ሴኬም በተባለች ከተማ በነቂስ ወጥተው ተሰበሰቡ፡፡
ንግሥተ ሳባ እና እራስን የመውቀስ ጥበብ
ነባር የግዕዝ ቅኔ (በስማ በለው) ልጥቀስሽ፡-
..እመ ተናገርኩ ድቅ ሰብአዛቲ ዓለም ይፀልዑኒ
ወከመ ኢይ ንብብ ሐሰተ ኩነኔ ዘአከ ያፈርሃኒ፤..
በዚያው በስማበለው ሲተረጐም፣
..እውነትን እንዳልናገር የዚህ ዓለም ሰዎች ይጠሉኛል
ሐሰትንም እንዳልናገር ፍርድህ (የእግዚአብሔር) ያስፈራኛል..
የዚህ ቅኔ መድፊያ እኔን አይመለከተኝምና ነው የቆረጥኩት፡፡ እንዲህ ይላል ..ወእምኩሉስ አርምሞ ይኀኄይስ ወይሣኔ.. (ከሁሉ ግን ዝም ማለት ይሻለኛል) ይሄ ነባር ቅኔና አመለካከቱ ተጋግዘው ኢትዮጵያውያን በሌለን የታሪክ ቁመና ለመዘናከት እንድንሞክር አድርገውናል፡፡
ኑሮና ህይወት በ2003እነሆ አዲሱ ዓመት መጣ
አሮጌውም ወደ ኋላ ቀረ፡፡ አዲሱ ዓመት አዲስ ተስፋ ይዞልን ስለመምጣቱ
አስረግጠን መናገር ባንችልም አሮጌው ዓመት ጭኖብን ያለፈውን የኑሮ ቀንበር ወደ ኋላ መለስ ብለን መታዘብ አይቸግረንም፤ አዲሱ ዓመት በአዲስ ተስፋ ሞሻሽሮ ከፊታችን የሳለብን የሚያጓጓ ህይወት ስለመኖሩ አፋችንን ሞልተን ለመናገር ቢገደንም፤ አሮጌው ዓመት በኑሮ ውጥንቅጥ አጨመላልቆ በወጉ ሳናጣጥመው የነጠቀንን፣ ድፍርስ ህይወት፣ እያሰብን አንዳንድ ነገሮችን መዘከር አያቅተንም፡፡ ነገን መተንበይ የሚያስችል የነቢይነት ዓቅም ባይኖረንም ትናንትን ቆም ብሎ ለመገርመም፣ ትዕግስት አያንሰንም፡፡
|ሌባ እና ፖሊስ..
አንድ ኬንያዊ ህፃን ..ስታድግ ምን መሆን ትፈልጋለህ?.. ብላችሁ ብትጠይቁት እንደ እኛ ሀገር ህፃን ..ዶክተር.. ወይም ..ኢንጂነር.. ይላል ብላችሁ እንዳትጠብቁ፤ ካለምንም ማመንታት ፖሊስ ሊላችሁ እንደሚችል እርግጠኛ ሁኑ፡፡ ናይሮቢ ሌላም ገድል አላት፡፡ ፖሊሶቹ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ የማይወጥኑት ነገር የለም፡፡ አንድ ስደተኛ ገንዘብ አልከፍልም ካለ ድብደባ ይደርስበታል ብላችሁ እንዳትሰጉ፡፡ ወይም ደግሞ ሕገ ወጥ ስደተኛ ነው በሚል ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ አይታሰብም፤ ሌላ ዘዴ አለ፡፡
ጉዱ ካሳ ናፈቀኝ!
ጋዜጠኛ፤ ሰዓሊና የጥበብ ታሪክ አጥኚ የነበሩት ስዪም ወልዴ ራምሴ ግለ-ታሪካቸውን በጻፉበት ..ኩረፊያ የሸፈነው ፈገግታ.. መጽሀፋቸው ላይ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ካሰፈሯቸው ትዝብቶች በአንዱ እንዲህ ..የህጉ ሰው በኢኮኖሚስቱ ሙያ ላይ ወይም ኢንጂነሩ በሕክምና ላይ ወይም ሐኪሙ በግብርና ላይ ወዘተ የመሰለወን ሀሳብ ከመስጠት የሚቆጠበውን ያህል በሌሎች መስኮች የተሰማሩ ባለሙያዎች በባህል ጥያቄ ላይ ሃሳብ ለመሰንዘር ቅንጣት ያህል አያቅማሙም፤ አሁን በጋዜጣ፤ በመጽሔት፤ በሬድዮና ቴሌቭዥን ከዝነኛ ሰዎች አንደበት የሚባሉትን ነገሮች ላነበበና ለሰማ ስዩም ወልዴ ከአስርት አመታት በፊት የታዘቡት በባህልና ጥበብ ነክ ጉዳዮች ላይ የሚሰጡ ደፋርና ጥራዝ-ነጠቅ አስተያየቶች፣ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ህክምና ኢኮኖሚክስ ግብርና በሚል መስክ መምረጥ እንዳቆሙ ቢሰሙ ምን ይሉ ነበር