ለብልሹ አስተዳደር መፍትሄው ዲሞክራሲያዊ ተቋማትን መርጨት ነው
ጆሮዬ ላይ ኢርፎን ሰክቻለሁ ከሞባይሌ በኤፍ ኤም ሬዲዮ የሚሰራጨውን ዜና ለማዳመጥ፡፡ በከፊል ጆሮዬ ግን የተሳፋሪዎችን ወሬ፣ ሃሜት፣ ምሬት፣ ማዳመጤ አልቀረም፡፡ ይቅርታ ያለሁበትን አልነገርኳችሁም፡፡ ሚኒባስ ውስጥ ነኝ፡፡ አንዳንዴ ግን ምን አስባለሁ መሰላችሁ? ወሬ በሚዲያ ከማዳመጥ ይልቅ ሲያጋጥም እንዲህ Live (በቀጥታ) ሥርጭት መከታተል ይሻላል - ከመንገደኛ፣ ከተሳፋሪ፣ ከዘይትና ስኳር ወረፋ ጠባቂ፣ ወደ አረብ አገር ለመሄድ ሰልፍ ከያዙ እንስቶች፣ ኢህአዴግን ለመደገፍ ከወጡ ሰልፈኞች ወዘተ . . .
ፈረሱ ምን ሆኖ ነው እየሳቀ የሚያለቅሰው?
የድሮ (ሴት) እመቤት:- . . . አዎ . . . ፈረስን ሳይሆን ሴቶችን የሚያስቅ ዘመን መጥቷል፡፡ የሴቶች ትንሳኤን በልጆቹ ላይ ማየቱ ደስ አሰኝቶ አስቆታል፡፡ . . . እንግዲህ እስቲ ቆይ . . . ለምን አለቀሰ ነው ያልከኝ?. . .አየህ ነፃነትን ላልተረዳ ሰው ነፃነቱን ብትሰጠውም ምን እንደሚያደርግበት አያውቀውም . . . ልጆቻችን፤ ቤት እንጂ ቤተሰብ የማይፈልጉ፣ ልጅ መውለድ እንጂ እናት መሆን የማይችሉ፣ ዶሮ ወጥ መብላት እንጂ መስራት የሚቀፋቸው፣ . . .ለገላቸው የሚገባውን ክብር የሚነፍጉ . . . ምስኪን የነፃነታቸው እስረኞች መሆናቸው ፈረሱን አስለቅሶታል፤ ብል አልተሳሳትኩም አይደል? ኧረ ኤዲያ እቴ!
ፕሬዚዳንት ግርማ በኑሮ ውድነት ምክንያት መንግስትን አልገሰፁም የዋጋ ንረቱ መንስኤ፤ የነዳጅ ዋጋ ነው?
ነጋዴዎች ናቸው? ወይስ የመንግስት የብር ህትመት?
ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ሰኞ እለት በፓርላማ ያደረጉት አመታዊ ንግግር፤ ያን ያህልም የዜጎችን ትኩረት የሚስብ አልነበረም። የንግግራቸው ቀዳሚ ርእሰ ጉዳይ፤ በአገራችን ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት መመዝገቡን የሚያበስር ነው። አምና የአገራችን ኢኮኖሚ በ11.4 በመቶ እንዳደገ የገለፁት ፕ/ት ግርማ፤ እድገቱም የመንግስት ፖሊሲዎች ትክክለኛ እንደሆኑ አስመስክሯል ብለዋል። ለዚህም ሶስት ምክንያቶችን አቅርበዋል።
መብላት ያስለመድከው ሲያይህ ያዛጋል
ዳኛውም፤
“ለዛሬ ሰዓት ስለደረሰ ነገ ተመለሰ” ሲሉ ቀጠሮውን
ያሸጋግሩታል፡፡
ባለጉዳዩም፤ በመከፋት ስሜት፤
“ጌታዬ ብዙ ሰዓት ጠብቄ ነው እዚህ የደረስኩት”
ዳኛው፤
“ነገም ብዙ ሰዓት ልትጠብቅ ትችላለህ፡፡ ፍትሕ
እንዲህ በአጭር ጊዜ የምትገኝ እንዳትመስልህ”
ይሉታል፡፡
ባለጉዳዩ በጣም ተናዶ፤
“ምን ያለ ገሀነም ውስጥ ነው ያለነው ባካችሁ”
አለ፡፡ ይሄንን የሰሙት ዳኛ፤
የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከፍፃሜው ደርሷል
በ2012 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ የመጨረሻው ዙር ጨዋታዎች ዛሬና ነገ በመላው አህጉሪቱ ሲከናወኑ ታላላቅ ቡድኖች ላለመውደቅ የገቡበት አጣብቂኝ ትኩረት ሳበ፡፡ ምድብ 2በናይጄርያና ጊኒ ትንቅንቅ ብቻ ትኩረት ቢያገኝም እዚህ አዲስ አበባ ላይ ኢትዮጵያ ከማዳጋስካር ከማጣሪያው በክብር ለመሰናበት ይጫወታሉ፡፡ በአዲስ አበባ ስታድዬም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከማዳጋስካር ጋር ስታድዬም ሲጫወት በሰፊ የግብ ልዩነት እንዲያሸንፍ ተጠብቋል፡፡ ቡድኑ በሳምንቱ አጋማሽ ላይ የወዳጅነት ጨዋታውን ከማሊ አድርጎ 1 እኩል አቻ ተለያይቷል፡፡ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ቤልጅማዊው ቶም ሴንትፌይት በሃላፊነታቸው 6 ወር ያለፋቸው ሲሆን ከማዳጋስካር ጋር ከሚደረገው ጨዋታ በኋላ ኮንትራቱ ያበቃል፡፡
የአካል ብቃት ማዘውተሪያ ፊልም ተሰርቷል፣ ለምን?
በአዲስ አበባ የአካል ብቃት እንቅስቅሴ የሚደረግባቸው የስፖርት ቤቶች ወይም ጂሞች እየበዙ ናቸው፡፡ በበቂ ሁኔታ ነው ለማለት ባይቻልም በህብረተሰቡም እየተለመዱ መጥተዋል፡፡ በመስኩ የተሰማሩ ባለሙያዎችም ብቅ እያሉ ነው፡፡ በጥሩ ደረጃ እየሰሩ ያሉ የአዲስ አበባ ጂሞች ከ10 አይበልጡም፡፡ ጥሩ ጂሞች የተሟላ የሚባሉት በሚይዟቸው የስፖርት መሳርያዎች ዘመናዊነት፤ በወቅታዊ ቴክኖሎጂና በሳይንስ የተደገፈ የስልጠና መመርያቸው፤ በሚኖራቸው ተገልጋይ ብዛት፤ በባለሙያዎቻቸው ወይም በአሰልጣኞቻቸው የሙያ ብቃትና ደረጃ ይሆናል፡፡
ላባ አልባዋ ዶሮ እንደወፍ በራለች
በአለማችን በየአመቱ ከሚከናወኑት በርካታ አለምአቀፋዊ ጉባኤዎችና ስብሰባዎች አንዱ የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ነው፡፡ በየአመቱ አንድ ወር ለሚጠጋ ጊዜ በድርጅቱ ዋና ጽሕፈት ቤት በሚከናወነው በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ፤ በርካታ የሀገራት መሪዎች እየተገኙ መናገር አለብን ያሉትን ንግግር አድርገው ይመለሳሉ፡፡ በዚህ በአሁኑ የተባበሩት መንግስታት 66ኛ ጠቅላላ ጉባኤም የበርካታ ሀገራት መሪዎች በወጣላቸው ፕሮግራም መሠረት ንግግራቸውን አሠምተዋል፡፡
ኃይሌ ገሪማ ለጥቁር ፊልም ሰሪዎች ፈር ቀዳጅ ተባለ
ኃይሌ ገሪማ በ1970ዎቹ በሎስ አንጀለስ ለጥቁር ፊልም ሰሪዎች ፈር ቀዳጅ የሆኑ ተግባራትን ካከናወኑ ባለሙያዎች ተጠቃሽ እንደሆነ ሎስ አንጀለስ ታይምስ ዘገበ፡፡ በሎስ አንጀለስ ከሚታወቁ ታላላቅ ዳይሬክተሮች ተርታ ሎስአንጀለስ ታይምስ ያሰለፈው ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ፤ በ1993 የሰራውን “ሳንኮፋ” የተባለ ፊልሙን የሚያከፋፍልለት ኩባንያ አጥቶ ራሱ በ35 አገራት ዞሮ ማሳየቱ ተደንቆለታል፡ ኃይሌ ገሪማ “ዘ ኤልኤ ሬበሊዮን” በሚል የሚታወቀውን የፊልም ሰሪዎች እንቅስቃሴ ከመሰረቱ አፍሮ አሜሪካን ተማሪዎች አንዱ ነው፡፡
የ ”ዘ ኢትዮጵያን ባንድ” መስራች አረፈ
በስካና ሮክስቴዲ የሙዚቃ ስልቶች የሚታወቀውና በሬጌ ፈር ቀዳጅነት የሚጠቀሰው የ”ዘ ኢትዮጵያን ባንድ” መስራች ሊዮናርድ ዲሎን በ68 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ በአንጎል ካንሰር የሞተው ጃማይካዊው የግጥም ደራሲና ድምፃዊ ዲሎን፤ የሙዚቃ ስልቶችን በአፍሮሴንትሪክ ጭብጥ በመስራት ከጃማይካ ድምፃውያን ቀዳሚው እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ባንዱ የተመሰረተበት ዓመት የቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉስ ሃይለስላሴ በጃማይካ ካደረጉት ጉብኝት ጋር የተገጣጠመ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡ ሊዮናርድ ዲሎን በ2009 ያሳተመው አልበም “ኦሪጅናል ሂትሜከርስ ፍሮም ጃማይካ ቮሊውም 1”፤ “ሊዮናርድ ኮመን ዘ ኢትዮጵያን” የመጨረሻ ስራው ሲሆን “ ዘ ኢትዮጵያን ባንድ” ባለፉት 46 ዓመታት 13 አልበሞችን ለገበያ አብቅቷል፡፡
ኪፈር ሰዘርላንድ ስለሌላ ዓለም ፍጡራን ይናገራል
ታዋቂው የፊልም ተዋናይ ኪፈር ሰዘርለንድ የሌላ ዓለም ፍጡር መኖራቸውን እንደሚያምን ለዴይሊ ቴሌግራፍ ተናገረ:: ኪፈር ከፍተኛ ስኬት ባገኘው ”24” ተከታታይ ፊልም ውስጥ ጃክ ባወር የተባለውን መሪ ገፀባህርይ በመወከል ለስምንት ተከታታይ ዓመት ሰርቷል፡፡ ኪፈር በየምሽቱ ወደ ሰማይ አንጋጦ ክዋክብቱን ሲመለከት የሚያስበው በሌላ ዓለም ስላሉ ፍጡራን መሆኑን ሲገልፅ፤ መላው ዩኒቨርስ ሰው ብቻ ነው ያለበት ማለት ያዳግታል ብሏል፡፡