Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ባለው የባህል ትብብር ስምምነት መሠረት የቻይና የባህላዊ ቅርስ አውደርዕይ እና የባህላዊ ሙዚቃና አክሮባት ትርዒት ሊቀርብ ነው፡፡ የቻይና ባህላዊ ቅርስ አውደርዕዩ ረቡዕ ከቀኑ 9 ሰዓት እንዲሁም የባህላዊ ሙዚቃ የአክሮባት ትርዒቱ ከቀኑ 11 ሰዓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ይቀርባሉ፡፡

በዩቲውብ 2 ቢሊዮን ተመልካች በማግኘት አዲስ ሪከርድ ያስመዘገበው ዝነኛው ዘፋኝ ጀስቲን ቢበር፤ ‹ቤቢ› በተሰኘ የሙዚቃ ቪድዮው ከፍተኛ ተመልካች እንዳገኘ ተገለፀ፡፡ “ማይ ዋርልድ 2.0” የተባለ አልበሙን የለቀቀው የ17 ዓመቱ ካናዳዊ አርቲስት፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት በመላው አለም 12 ሚሊዮን የአልበሞቹን ቅጂ ሸጧል፡፡ በሳምንቱ አጋማሽ “አንደር ሚስሌትዎ” የተሰኘ አዲስ አልበሙን የለቀቀው ቢበር፤ በፈረንጆች አዲስ ዓመት (2012) ‹ቢሊቭ› በሚል ስያሜ ሌላ አዲስ አልበም ለመልቀቅ በዝግጅት ላይ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

“21” በተባለ የዘፈን አልበሟ የዓመቱን ከፍተኛ ሽያጭ የተቀዳጀችው ድምፃዊቷ አዴሌ፤ በጉሮሮዋ ላይ ቀዶ ጥገና ልታደርግ ነው፡ አርቲስቷ ለህክምናዋ ትኩረት በመስጠት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ልታቀርብ ያቀደቻቸውን ዝግጅቶች ሰርዛለች ተብሏል፡፡ አንዳንድ ዘገባዎች ቀዶ ጥገናው ከጉሮሮ ካንሰር በሽታ ጋር የተያያዘ መሆኑን ቢጠቁሙም ዘገባው ሙሉ በሙሉ ውሸት እንደሆነ አሳታሚ ኩባንያዋ ገልጿል፡፡ የ23 ዓመቷ አርቲስት ከመድረክ ስራዋ ውጭ ብዙ ማውራቷ ለጉሮሮዋ መቁሰል ምክንያት እንደሆነ የገለፀው የኩባንያው ቃል አቀባይ፤ ቀዶ ጥገናው ቀላል ህክምና የምታገኝበትና በወደፊት የሙዚቃ ስራዋ ላይ ምንም የሚፈጥረው ችግር እንደሌለ አስታውቋል፡፡ በመላው ዓለም 12 ሚሊዮን ቅጂ ተሰራጭቶ የዓመቱን ከፍተኛ ሽያጭ ያስመዘገበው የአዴሌ “21” የተሰኘ አልበም፤ በቢልቦርድ ምርጥ 200 አልበሞች ደረጃ ለ13 ሳምንታት አንደኛ በመሆን ሪኮርድ ይዟል፡፡

የሟቿ ኤሚ ዋይን ሃውስ 3ኛ አልበም ‹ላዮነስ፡ ሂድን ትሬዠርስ› በሚል ስያሜ ከወር በኋላ ለገበያ ሊበቃ ነው፡፡ በአይስላንድ ሪከርድስ የተዘጋጀው አልበሙ 12 የኤሚ አዳዲስ ዘፈኖችን ያካትታል፡፡ ኤሚ ዋይን ሃውስ ከልክ ባለፈ አልኮል መጠጥ ተመርዛ በ27 ዓመቷ ድንገት ህይወቷ እንዳለፈ በምርመራ መረጋገጡ ይታወሳል፡፡ ከሞተች ከ3 ወር በኋላ ለገበያ በሚበቃ ስራዋ ከሟች የዓለማችን ምርጥ ሙዚቀኞች ተርታ የሚያሰልፍ ገቢ እንደምታገኝ ተጠብቋል፡፡ ለገበያ ከቀረበ 2ኛ ዓመቱን የያዘው የኤሚ ዋይን ሃውስ “ባክ ቱ ብላክ” የተባለ አልበም ከሞተች በኋላ በወር ውስጥ 175ሺ ቅጂ ተሸጧል፡፡ ከሞታቸው በኋላ ከፍተኛ ገቢ ያገኙ ሙዚቀኞችን ዓመታዊ የገቢ ደረጃ ከሳምንት በፊት ያወጣው ፎርብስ መፅሄት፤ አንደኛው 170 ሚሊዮን ዶላር ያገኘው ማይክል ጃክሰን መሆኑን ሲያመለክት ኤልቪስ ፕሪስሊ በ55 ሚሊዮን ዶላር ሁለተኛ፤ የቢትልሱ ጆን ሌነን በ12 ሚሊዮን ዶላር ሶስተኛ እንዲሁም ጂም ሄንድሪክስ በ7 ሚሊዮን ዶላር ገቢ 5ኛ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

በ”ቫይብ” መፅሄት የዓመቱ ምርጥ የራፕና ሂፕሆፕ አርቲስት የተባለው ሊል ዋይኔ፤ ጄይዚንና ካናዬ ዌስትን በማጣጣል፣ ሙዚቃዎቻቸውን የመስማት ፍላጎት የለኝም አለ፡፡ ሊል ዋይኔ ከእስር ቤት መልስ “ዘካርተር 5 አልበም” በሚል ለገበያ ባበቃው አልበሙ ላይ ጄይ ዚና ካናዬ ዌስት በተጋባዥነት መስራታቸው ይታወሳል - “ዎች ዘ ትሮን” የተሰኘውን የራሳቸው አልበምም ለገበያ በማቅረባቸው ከሊል ዋይኔ አልበም ጋር ተፎካካሪ ሆነዋል፡፡ ጄይዚና ካናዬ ዌስት የአልበማቸውን ገበያ ለማሟሟቅ በአሜሪካ ለ6 ሳምንት የሚዘልቅ ኮንሰርት ሰሞኑን የጀመሩ ሲሆን፤ አልበሙ በሁለት ወራት 994ሺ ቅጂ እንደተቸበቸበ ታውቋል፡፡
በቢልቦርድ የሂፕሆፕና ራፕ ዘርፍ ላለፉት 3 ሳምንታት በ1ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የሊል ዋይኔ “ዛ ካርተር 5”፤ 1 ሚሊዮን 615ሺ ቅጂ ተሸጧል - በዘርፉ አንደኛ በመሆን፡፡ የጄይዚና ካናዬ ዌስት አልበም ደግሞ 16ኛ - 1 ሚሊዮን 13ሺ ቅጂ ተሸጧል፡፡ ከሂፕሆፕና ራፕ ሙዚቀኞች በገቢው የመሪ ደረጃ የያዘው ጄይ ዚ፤ ዘንድሮ 37 ሚሊዮን ዶላር ሲያገኝ፤ ካናዬ ዌስት በ16 ሚሊዮን ዶላር፣ ሊል ዋይኔ በ15 ሚሊዮን ዶላር 3ኛና 4ኛ ሆነዋል፡፡

ሆሊውድ በፊልም ስራዎች ላይ የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎችን እየተጠቀመ መሆኑ ቢዘገብም እየተሻሻሉ በድጋሚ የሚወጡ ፊልሞች እንደበዙ ተጠቆመ፡፡
ተሻሽለው እየወጡ ያሉት የድሮ ፊልሞች ተከታታይ ክፍል ያላቸው ሲሆኑ በ3ዲና ሌሎች የሲኒማ ቴክኖሎጂዎች በድጋሚ እየተሰሩ እንደሆነ ታውቋል፡፡በእንዲህ ዓይነቱ የፊልም ስራዎች የተጠመዱ የፊልም ኩባንያዎች ከበጀታቸው እጥፉን በማግኘት በገቢ ቢሳካላቸውም ከኦርጅናል ስራ ተራርቀዋል ለሚል ትችት ከመጋለጥ ግን አልዳኑም፡፡ዘንድሮ ብቻ በተመሳሳይ ሁኔታ የተሰሩ ፊልሞች ብዛት ከ27 በላይ እንደሆነ ሲታወቅ፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በየዓመቱ ከሚታዩ ፊልሞች በድጋሚ ተሻሽለው የተሰሩ ፊልሞች 57 በመቶውን ድርሻ ይዘዋል፡፡


Monday, 07 November 2011 12:56

የተዓምር ዓለም

ተአምር የተፈጥሮ ህግ መዛባት ነው፡፡ ድንጋይ ወደ ላይ ተወርውሮ መሬት በመውደቅ ፋንታ በአየር ላይ ተንጠልጥሎ ቢቀር ሁኔታው ከታወቀው ውጭ ስለሆነ ተአምር ነው፡፡ 
አቶ ዘካሪያስ የግል ፋብሪካ ባለቤት ናቸው፡፡ ፋብሪካ የማንቀሳቀሻ ፈቃድ ከመንግስት አግኝተዋል፡፡ . . . ከወር በፊት ለፋብሪካው ሰራተኛ የሚሆኑ ሰዎችን በተለያየ የእጅ ሞያ ዘርፍ አወዳድረው ቀጥረዋል፡፡ . . . ሰራተኞቹ ግን ወሩን ሙሉ ለስራ ሲዘጋጁ ቆዩ እንጂ ምንም ተግባር አላከናወኑም፡፡
ማሽኖቹ በሸራ ተሸፍነው በፋብሪካው ውስጥ ቆመዋል፡፡ ሰራተኞቹም የተሸፈነውን ገልጠው አላዩም፤ ባለቤትየውም ገልጦ አላሳዩዋቸውም፡፡
ለወር ያህል በእየቀኑ ወደ ስራ ቦታቸው ይመጣሉ፡፡ በስራ መግቢያ ሰአታቸው ቱታቸውን ለብሰው ይቆማሉ፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት ድመት አንድ አውራ ዶሮ ታይና አድፍጣ ልትበላው ትፈልጋለች፡በእርግጥ ልትበላው አይገባትም በህጉ፡፡ አውራ ዶሮው በመሠረቱ ድመት አውራ ዶሮ የመብላት ባህል የላትም በሚል በቸልተኝነት ግቢው ውስጥ እየተጐማለለ ይዝናናል፡፡ አመሻሽ ላይ ነው፡፡ 
በመጨረሻ ድመቷ ዘልላ ከመያዙዋ በፊት፤ ምክንያት እንደሚያስፈልጋት አሰበችና እንዲህ አለችው
“እንደምን ውለሃል አያ አውራ ዶሮ?”
አውራዶሮም፤ “ደህና ነኝ፡፡ እንደምን ውለሻል እመት ድመት”
እመት ድመትም፣
“ሌሊት ሌሊት እየጮህክ ሰዎችን ከእንቅልፋቸው እየቀሰቀስክ እስከዛሬ ስትረብሽ ከርመሃል፡፡ ከእንግዲህ ግን ይሄ አጉል የምትጮኸው ነገር ያበቃል፡፡ አሁን እርምጃ ልወስድብህ ነው” አለችው፡፡

የኢትዮጵያው መንግታዊ ፋብሪካ ለ25 አመታት በተከታታይ ከስሯል - ሰሞኑን ኢዜአ እንደዘገበው። በቻይና ሲከስሩ የቆዩ የመንግስት ፋብሪካዎች እየተዘጉ በየአመቱ በሺ የሚቆጠሩ አመፆች ይፈጠራሉ። በምስራቅ ጀርመን፤ በመንግስት ፋብሪካ የተሰሩ መኪኖች አገልግሎት ሳይሰጡ እየተበላሹ ያስቸግሩ ነበር። በህንድ መንግስት ተቋቁሞ የነበረ የማዳበሪያ ፋብሪካ ምንም ሳያመርት የሰራተኞችን ደሞዝ ከፍሏል - ለአመታት። አምና በአሜሪካ መንግስት ድጎማና ብድር የተሰጣቸው ፋብሪካዎች ከስረው እየተዘጉ ነው - ብሉምበርግ እንደዘገበው።

የኢትዮጵያው መንግታዊ ፋብሪካ ለ25 አመታት በተከታታይ ከስሯል - ሰሞኑን ኢዜአ እንደዘገበው። በቻይና ሲከስሩ የቆዩ የመንግስት ፋብሪካዎች እየተዘጉ በየአመቱ በሺ የሚቆጠሩ አመፆች ይፈጠራሉ። በምስራቅ ጀርመን፤ በመንግስት ፋብሪካ የተሰሩ መኪኖች አገልግሎት ሳይሰጡ እየተበላሹ ያስቸግሩ ነበር። በህንድ መንግስት ተቋቁሞ የነበረ የማዳበሪያ ፋብሪካ ምንም ሳያመርት የሰራተኞችን ደሞዝ ከፍሏል - ለአመታት። አምና በአሜሪካ መንግስት ድጎማና ብድር የተሰጣቸው ፋብሪካዎች ከስረው እየተዘጉ ነው - ብሉምበርግ እንደዘገበው።