Administrator
Tuesday, 09 September 2025 08:20
ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ/ም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታው ተጠናቆ ለምረቃ በመብቃቱ መላውን ኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አላቹሁ
Published in
ዜና
Tagged under
Tuesday, 09 September 2025 07:04
በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ለሚመሰረቱ ከተሞች ማስተር ፕላን እየተዘጋጀ ነው
• ዘመናዊ የመኖሪያና የቱሪዝም ከተሞች ይመሰረታሉ ተብሏል
በሕዳሴው ግድብ በተፈጠረው "ንጋት" 246 ኪ.ሜ ባህር ዙሪያ ለሚመሰረቱ ዘመናዊ ከተሞች ማስተር ፕላን የማዘጋጀት ሥራ መጀመሩ ተገለጸ፡፡
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ለሚመሰረቱ ዘመናዊ የመኖሪያና የቱሪዝም ከተሞች ማስተር ፕላን የማዘጋጀት እንዲሁም የአሶሳ ከተማ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራ፤ 'ሲቲስ አሊያንስ' በተሰኘ ድርጅት አማካኝነት በይፋ መጀመሩን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ አስታውቋል።
ወደፊት በአካባቢው ብዙ ከተሞች ይመሰረታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የተገለጸ ሲሆን፤ አካባቢው የዓለም አቀፍ ባለሀብቶችን ትኩረት መሳቡ ተነግሯል።
ቀደም ሲልም የኢንቨስትመንት ፈቃድ የወሰዱ አልሚዎች እንዳሉ የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ የሐይቁን መሃል በተመለከተ ከፌደራል መንግሥት ጋር በትኩረት የሚሰራ መሆኑ የተጠበቀ ቢሆንም፣ ብዙ ደሴቶች በመኖራቸው ጥናት እንደሚፈልግ ተናግረዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…


Published in
ዜና
Tagged under
Tuesday, 09 September 2025 07:01
ኢትዮጵያ ህዳሴን ለገደበችበት ካሳ መጠየቅ እንዳለባት ተገለጸ
የህዳሴው ግድብ ግንባታ ጠቃሚነቱ በተለይ ለታችኛዎቹ ተፋሰስ ሀገራት በመሆኑ ኢትዮጵያ በራሷ ፋይናንስ ግድቡን ለገደበችበት ካሳ መጠየቅ አለባት ሲሉ ኢንጂነር ጥላሁን ኤርዲኖ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
በአፍሪካ ቀንድና በመካከለኛው ምስራቅ የሃይድሮ ፖለቲካ ተንታኝ ኢንጂነር ጥላሁን ኤርዲኖ፤ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ከግድቡ ግብጽና ሱዳን ከፍተኛ ተጠቃሚ በመሆናቸው ኢትዮጵያ ግድቡን ለብቻዋ መገደብ አልነበረባትም።
የህዳሴ ግድብ ከሌሎች ጥቅሞቹ ባሻገር ግብጽ ውስጥ በከፍተኛ ትነት የሚባክን ውሃን አስቀርቷል ያሉት ኢንጂነር ጥላሁን፤ በዚህም በቀጠናው ተጨማሪ የውሃ ሀብት እንዲኖር ማስቻሉን ጠቁመዋል፡፡
እንደ ኢንጂነር ጥላሁን ገለጻ፤ ግድቡ መገንባቱ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የሚደርስባቸውን አደጋ ማስቀረት ችሏል፤ ለአብነትም ጎርፍና የመሳሰሉትን ማንሳት ተገቢ ነው፡፡ በዚህም በዓመት ከሦስት እስከ አራት ጊዜ ያለምንም አደጋ ማምረት እንዲችሉ እድል ፈጥሯል፡፡
ግድቡ ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች እንዳሉት የጠቆሙ ሲሆን፤ ሀገራቱ አሁንም የዓባይ ተፋሰስ እንዲለማ ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ውሃ ሲጨምር ሌሎች ሀገራት ላይ መጨመሩ የግድ መሆኑን የገለጹት ኢንጂነር ጥላሁን ኤርዲኖ፤ ህዳሴ በትነት የሚባክነውን ውሃ የሚቀንስ በመሆኑ በድርቅ ጊዜ ለቀጠናው ከፍተኛ እፎይታ የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡

Published in
ዜና
Tagged under
Tuesday, 09 September 2025 06:59
የረዳን ፈጣሪ አምላክ ይመስገን !!
መላዉ ኢትዮዽያዊን በሙሉ እንኳን ደስ አለን!!
የፅናታቻን ፣ የላባችን ፣ የደማችን ፣ የጥረታችን ዉጤት ፣ የዘመናት ቁጭታችን መደምደሚያ ፣ የብልፅግናችን መሰረት ፣ የአይበገሬነታችን ምልክት ለሆነዉ የታላቁ ህዳሴ ግድባችን ምረቃ እንኳን አደረሰን!!
ባንድነት ስንቆምና ስንተባበር የማችለዉም የለም !!
ፈጣሪ ኢትዮዽያና ህዝቦቿን ይባርክ
-ከንቲባ አዳነች አቤቤ-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…


Published in
ዜና
Tagged under
Tuesday, 09 September 2025 06:58
የህዳሴ ዋዜማ በድሮኖችና በጀልባዎች ትርኢት
የህዳሴ ዋዜማ በእግር ጉዞ፣ በድሮንና በጀልባዎች ትርኢት፣ በባሎንና በሰርከስ ሥራዎች ተጀምሮ እየተካሄደ ነው።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የምረቃ የዋዜማ ዝግጅት በዚያው በጉባ እየተካሄደ ይገኛል።
በምረቃ ዋዜማ ዝግጅቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ፣ ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እንዲሁም ሌሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በግድቡ መመረቂያ ዋዜማ ላይ የድሮኖች ትርኢት፣ የተለያዩ የሰርከስ፣ የመብራትና የጀልባ ትርኢቶች እየተካሄዱ ነው።
ቀደም ሲልም በግድቡ አናት ላይ የ1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የእግር ጉዞ መደረጉም ተዘግቧል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…





Published in
ዜና
Tagged under
Tuesday, 09 September 2025 06:56
የህዳሴው ግድብ ምርቃት ዋዜማ ላይ
የህዳሴው ግድብ ምርቃት ዋዜማ ላይ
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Tuesday, 09 September 2025 06:55
የሕዳሴ ግድብ ምረቃን በነፃ ኢንተርኔት ይከታተሉ
የታላቁ የኢትዮጵያን ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የድል ብስራት፣ በቀጥታ ስርጭት በነፃ ይከታተሉ ሲል ኢትዮ ቴሌኮም ብስራት አሰምቷል።
የዓመታት ሕልማችን በይፋ ዕውን የሚሆንበት ታላቅ ታሪካዊ የድል ብስራት፣ ነገ ዻጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከኢንተርኔት ክፍያ ነፃ በቀጥታ ስርጭት በኢቢሲ ይከታተሉ።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Tuesday, 09 September 2025 06:47
ለህዳሴ ግድቡ 260 ሚ.ብር ያሰባሰቡት - ጊዜሽወርቅ ተሰማ
የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ሲነሳ መዘንጋት የሌለባቸው አንዲት ኢትዮጵያዊ እንስት አሉ - ወ/ሮ ጊዜሽወርቅ ተሰማ፡፡
በኢትዮጵያ በግሉ ዘርፍ በስራ ፈጠራና በንግዱ ዓለም በስኬታማነታቸው የሚታወቁ ባለሃብት ናቸው፡፡
በሀገራዊ የልማት ሥራዎች ላይ ትልቅ ተሳትፎ ያላቸው ወ/ሮ ጊዜሽወርቅ፤ ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ስኬት በቅንጅት የሚሰራውና "ትስስር ለሕዳሴ ግድብ" የተሰኘው ጥምረት መሥራች ናቸው፡፡
ስለግድቡ ግንዛቤን ለማሳደግ፣ በተበታተነ መልኩ የሚሰሩ ሥራዎችን ለማቀናጀትና ስለ ግድቡ ያለውን እውነታ ለዓለም ማህበረሰብ ለማስረዳት የሚንቀሳቀሰው ጥምረቱ፤ በአገር ውስጥና በውጭ ያሉ ምሁራን፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የሚሳተፉበት ነው።
ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ስኬት የሚሰራ ጥምረት እንዲመሰረት ለዓመታት ሲሞግቱ የነበሩት ወ/ሮ ጊዜሽወርቅ፣ ጥምረቱ በ2013 ሲመሰረት፤ "የግድቡ ግንባታ በአሁኑ ወቅት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በመድረሱ፤ በተለይ ወጣቱ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ኢትዮጵያን ማገዝ አለበት፤ ልክ እንደሠራዊቱ በበይነ መረብ የአገሬን ሉዓላዊነት አላስነካም ማለት አለበት" ሲሉ ተናግረዋል።
ወ/ሮ ጊዜሽወርቅ ተሰማ "ትስስር ለሕዳሴ ግድብ" የተሰኘውን ጥምረት መመሥረት ብቻ ሳይሆን በጥምረቱ ውስጥ የሀብት ማሰባሰብ ሥራውን በዋናነት መርተዋል፡፡
ወ/ሮ ጊዜሽወርቅ ከዚህ ቀደም ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ከግሉ ዘርፍ 260 ሚሊዮን ብር አሰባስበው ለሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ም/ቤት ገቢ በማድረግ ለሀገራቸውን ያላቸውን ፍቅር አስመስክረዋል።
በታላቁ የህዳሴ ግድብ የምረቃ በዓል ዋዜማ ላይ ሆነን እኒህን ሃገር ወዳድ እንስት ያነሳነውም ለሃገራቸው ላከናወኑት ትልቅ ተግባር በጥቂቱም ቢሆን መመስገንና መታወስ ስላለባቸው ነው፡፡
እንኳን ለታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ
መጠናቀቅና ምርቃት በሰላም አደረሰን!!
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
