Administrator

Administrator

የግዮን ሆቴሉ ሰፊ መናፈሻ በበርካታ ካፌዎች ሬስቶራንቶችና የምግብ አዘጋጆች ተሞልቷል። እዚህም እዚያም በረድፍ ተሰድረው ከተተከሉት ውብ ድንኳኖች የሚወጣው የምግብ አምሮትን የሚቀሰቅሰውና አፍንጫን የሚፈታተነው የተለያዩ ምግቦች ሽታ ስፍራውን አውዶታል። ከወዲያ በተንጣለለው የሙዚቃ መድረክ ላይ እየነጠረ ስፍራውን ያደመቀው የዲጄ ሙዚቃ የመዝናናትና የመነቃቃት  ስሜትን ይፈጥራል። ስፍራው ደስ ይላል። ዋሊያ ቢራ ከብሉ ሚዲያ ጋር በመተባበር ላለፋት 6 ዓመታት “ቴስት ኦፍ አዲስ”ን ሲያዘጋጅ ቆይቷል። በአመት ሁለትና ሶስት ጊዜ የሚዘጋጀውን ይህንን ፕሮግራም በርካቶች በጉጉት ይጠብቁታል። ዓለም በሯንም ደጇንም ዘግታ እንድትከርም ባስገደዳት የኮሮና ወረርሽኝ ጦስ ሣቢያ ተቋርጦ የነበረው ይህ 22ኛው ዙር “የቴስት ኦፍ አዲስ” (የሞግብና የመዝናኛ ፕሮግራም) በብዙ ወጣቶች ዘንድ ተናፍቆ ሠንብቷል።
የ”ቴስት ኦፍ አዲስ” ዝግጅት ታዳሚዎች የሆኑት ኤርምያስ ዘውዱና ጓደኞቹ የነገሩኝም ይህንኑ ነበር። “ራሣችንን ፈታ የምናደርግበት በመድረክ ሙዚቃዎች የምንዝናናበት ፕሮግራም ነው። በተለይ እንዲህ የመዝናኛ ዝግጅቶች በሌሉበትና በተለያዩ ጉዳዮች ተጨናንቀን በሰነበትንበት ጊዜ ራስን ለማዝናናት የሚያስችሉ ፕሮግራሞች መጀመራቸው ደስ የሚል ነገር ነው። ከሁሉም በላይ ደግሞ በቀላሉ እድል ለማግኘት የማይችሉ ግን አስገራሚ አቅም ያላቸው ጀማሪዎች ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡ እድል መስጠቱ ጥሩ ነገር ነው” ሲሉ አውግተውኛል።
የዋሊያ ቢራ ሲኒየር ብራንድ ማናጀር ፋይዳ ዘውዱ እንደነገሩኝ፤ የፕሮግራሙ አላማ ጀማሪ የሙዚቃ ባለሙያዎች ራሳቸውን የሚያስተዋውቁበት አዳዲስ ሬስቶራንቶችና የምግብ አዘጋጆች ራሣቸውንና የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ለተገልጋዩ በስፋት ለማስተዋወቅ እድል የሚያገኙበት፣ ዋሊያ ቢራ ከደንበኞቹ ጋር በስፋት የሚገናኝበት እድልን የሚያመቻችና በተለይ ለወጣቶች መልካም የመዝናኛ አጋጣሚን የፈጠረ ፕሮግራም ነው። ዋልያ ቢራም ዘንድሮም ይዞ የቀረበው በአዲስ መልክና ጣዕም አዲስ ዝግጅት እንደሆነም ገልጸዋል።
ራሣቸውን ለማውጣት እድል ያላገኙ አዳዲስና አቅም ያላቸው የሙዚቃ ባለሙያዎችን እድል በመስጠት ሰፋ ያለ ተመልካች አግኝተው እንዲበረታቱ በማድረጉ ረገድም ዝግጅቱ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተነግሯል።
ግንቦት 14 እና 15  ቀን 2013  ዓ.ም በተዋበው የግዮኑ መናፈሻ ውስጥ የተካሄደው የ”ቴስት ኦፍ አዲስ” የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል ላይ የሆድን ብቻ ሣይሆን የአዕምሮን ረሃብ የሚያስታግሱ የተለያዩ ዝግጅቶችም ተካሂደዋል።
ፕሮግራሙ የኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ መመሪያዎችን በጠበቀ መልኩ የተከናወነ ሲሆን በዚህም መሠረት ከመደበኛው ጊዜ 1/4ኛውን የፕሮግራም ታዳሚ ብቻ ማስተናገዱንም አዘጋጆቹ ተናግረዋል።

   የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ በመላው አለም በቫይረሱ ሳቢያ ለሞት የተዳረጉ  የጤና ባለሙያዎች ቁጥር ከ115 ሺህ ማለፉ የተነገረ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ወረርሽኙ ለ9 አዳዲስ ቢሊየነሮች መፈጠር ምክንያት መሆኑ ተዘግቧል፡፡
ፒፕልስ ቫክሲን አሊያንስ የተባለው ጥምረት በበኩሉ ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው መረጃ፤ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በክትባት ምርት ዘርፍ ለተሰማሩ ኩባንያዎችና ባለሃብቶች መልካም አጋጣሚ መሆኑንና፣ ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ በዘርፉ የተሰማሩ 9 ሰዎች ወደ ቢሊየነርነት መቀየራቸውን አስታውቋል፡፡
ግለሰቦቹ ከፍተኛ ገቢ ለማግኘት የቻሉት የኮሮና ክትባቶችን በብቸኝነት የማምረት መብት ባለቤት የሆኑ ኩባንያዎቻቸው በስፋት ምርታቸውን መሸጥ በመቻላቸው ነው ያለው ጥምረቱ፣ ዘጠኙ ቢሊየነሮች በድምሩ 19.3 ቢሊዮን ዶላር ያህል ሃብት ማፍራታቸውንና ይህ ገንዘብ አነስተኛ ገቢ ያላቸው አገራትን ዜጎች ሙሉ ለሙሉ ለመከተብ የሚያስችል መሆኑንም አክሎ ገልጧል፡፡
ከዘጠኙ ቢሊየነሮች አመካከል ከፍተኛ ገቢ በማግኘት በአንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ሞዴርና የተባለው ክትባት አምራች ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑትና የተጣራ ሃብታቸው 4.3 ቢሊዮን ዶላር የደረሰው ስቴፋኒ ባንሴል ሲሆኑ፣ የባዮንቴክ ኩባንያ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ኡጉር ሳሂን በ4 ቢሊዮን ዶላር፣ ተመራማሪውና ከሞዴርና መስራቾች አንዱ የሆኑት ቲሞቲ ሰፕሪንገር በ2.2 ቢሊዮን ዶላር ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡
የሞዴርና ሊቀ መንበር ኑባር አፊያን በ1.9 ቢሊዮን ዶላር፣ የሮቪ ኩባንያ ሊቀ መንበር ጁኣን ሎፔዝ ቤልሞንቴ በ1.8 ቢሊዮን ዶላር፣ ሳይንቲስትና የሞዴርና መስራች የሆኑት ሮበርት ላንገር በ1.6 ቢሊዮን ዶላር፣ የካንሲኖ ባዮሎጂክስ ኩባንያ መስራች የሆኑት ዙ ታኦ በ1.3 ቢሊዮን ዶላር፣ የካንሲኖ መስራችና የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ዢኡ ዶንግዡ በ1.2 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም የኩባንያው የቀድሞ ከፍተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ማኦ ሁኢሁኣ በ1 ቢሊዮን ዶላር እንደ ቅደም ተከተላቸው ከአራተኛ እስከ ዘጠነኛ ያለውን ደረጃ መያዛቸውም ተነግሯል፡፡
በሌላ ተያያዥ ዜና ደግሞ፣ ቫይረሱ ወረርሽኙን ለመከላከልና የወገኖችን ህይወት ለመታደግ ደፋ ቀና ሲሉ የነበሩ ከ115 ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎችን ለሞት መዳረጉን ከሰሞኑ ያስታወቀው የአለም የጤና ድርጅት፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ባለሙያዎችም በቫይረሱ ተይዘው እንደሚገኙ መግለጹን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

   ብራንድ አፍሪካ የተባለው ተቋም የ2021 የአፍሪካ እጅግ ተወዳጅና ተመራጭ የንግድ ምልክቶችን ዝርዝር ከሰሞኑ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ የአሜሪካው ናይኪ በአፍሪካ የአመቱ እጅግ ተወዳጅ ብራንድ ለመሆን ችሏል፡፡
የጀርመኑ የአልባሳትና ጫማዎች አምራች አዲዳስ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፣ የደቡብ ኮርያው ሳምሰንግ ሶስተኛ ደረጃን የያዘ ተወዳጅ ብራንድ መሆኑን ብራንድ አፍሪካ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡
በአመቱ በአፍሪካ እጅግ ተወዳጅ ብራንዶች ዝርዝር ውስጥ ከአራተኛ እስከ አስረኛ ደረጃን የያዙትም፣ የአሜሪካው ኮካ ኮላ፣ የአሜሪካው አፕል፣ የቻይናው ቴክኖ፣ የጀርመኑ ፑማ፣ የጣሊያኑ ጊቺ፣ የጃፓኑ ቶዮታ እና የስፔኑ ዛራ ናቸው፡፡
በአፍሪካ ተወዳጅ ከሆኑ አፍሪካዊ ብራንዶች መካከል ቀዳሚነቱን የያዘው ኤምቲኤን ሲሆን የናይጀሪያው ዳንጎቴ ይከተላል፡፡


 ባለፈው ነሃሴ ወር በማሊ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት በመራው ኮሎኔል አስሚ ጎይታ ባለፈው ሰኞ በቁጥጥር ስር የዋሉትና በእስር ላይ የሚገኙት የአገሪቱ የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት ባህ ንዳው እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሙክታር ኳኔ ባለፈው ረቡዕ በፈቃዳቸው ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡
ባለፈው አመት በአገሪቱ የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት የመሩትና በሽግግር መንግስቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ሲሰሩ የቆዩት ኮሎኔል አስሚ ጎይታ፣ ባለፈው ሰኞ የአገሪቱን ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር የተጣለባቸውን መንግስታዊ ሃላፊነት በአግባቡ አልተወጡም፣ ያልተገባ ሹም ሽር አድርገዋል በሚል ማሰሩን የዘገበው ቢቢሲ፤ ኮሎኔሉ ስልጣኑን በመረከብ በቀጣዪ አመት ሊካሄድ ቀን የተቆረጠለት ምርጫ ወቅቱን ጠብቆ እንደሚካሄድ መግለጹንና ይህን ተከትሎም በእስር ላይ የሚገኙት ባለስልጣናቱ ባለፈው ረቡዕ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን በይፋ ማስታወቃቸውን አመልክቷል፡፡
ከማሊ ዋና ከተማ ባማኮ አቅራቢያ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙት ፕሬዝዳንቱና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ማስታወቃቸውን ተከትሎ፣ ከእስር እንዲለቀቁ ከወታደራዊው ሃይል ጋር ድርድር እየተደረገ እንደሚገኝም አልጀዚራ ዘግቧል።
ኮሎኔሉ ባለፈው አመት በመሩት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት የአገሪቱን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ኬታን ከሥልጣን መውረዳቸውን ተከትሎ በአገሪቱ የ18 ወራት የሽግግር ምክር ቤት መቋቋሙን ያስታወሰው ዘገባው፣ ኮሎኔሉ ግን ዳግም መፈንቅለ መንግስት በሚባል መልኩ ፕሬዝዳንቱንና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማሰሩ አገሪቱን ወደከፋ ሁኔታ ሊያመራት ይችላል መባሉን አመልክቷል፡፡
የአፍሪካ ህብረት፣ ኢኮዋስ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና አውሮፓ ህብረትን ጨምሮ አለማቀፍ ተቋማት ኮሌኔሉ ከሰሞኑ ያሰራቸውን ፕሬዝዳንቱንና ጠቅላይ ሚኒስትሩን በአፋጣኝ እንዲፈታ ጥሪ ቢያቀርቡም ምንም ተስፋ ሰጪ ምላሽ ሳይገኝ መቆየቱንም አመልክቷል፡፡   የስነ ፅሁፍና ቋንቋዎች ፕሮፌሰር የሆኑትና በታሪክ ምርምሮችና ጥናቶች ላይም የሚሳተፉት ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ፤ ከዚህ ቀደም "የኦሮሞና አማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ" እንዲሁም "ስውሩና ያልተነገረው የአይሁዳውያንና የኢትዮጵያውያን ታሪክ" የተሰኙ ታሪክ ላይ ያተኮረ መፃህፍትን በአማርኛ ቋንቋ ለአንባቢያን ያቀረቡ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ “ኢትዮጵያ ግብፅን እንደፈጠረቻት እና እንዳሰለጠነቻት” የተሰኘ የታሪክ መጽሐፍ ለአንባቢያን ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ናቸው። ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ይህን የታሪክ መፅሐፍ ለማዘጋጀት የታሪክ አባት ተብሎ -ከሚታወቀው ግሪካዊው ሄሮዱተስ እስከ አውሮፓ ታሪክ አጥኚዎች ከትበው ያቆዩዋቸውን የታሪክ ሰነዶች መመርመራቸውንና ማመሳከራቸውን  ይናገራሉ።
በአሁኑ ወቅት አብዛኛውን ጊዜያቸውን በኢትዮጵያ በማሳለፍ በታሪክ ላይ ምርምርና ጥናት እያደረጉ የሚገኙት ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ፤ ከቀናት በኋላ ለአንባቢያን በሚቀርበው መፅሐፋቸው ጭብጥ ዙሪያ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ እንደሚከተለው አነጋግሯቸዋል፡፡ እነሆ፡-


           በቅርቡ የሚወጣው መፅሐፍዎ በምን ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው?
ርዕሱ “ኢትዮጵያ ግብፅን እንደፈጠረቻትና እንዳሰለጠነቻት” የሚል ነው። እንግዲህ  እንዲህ ብሎ ደፍሮ ለመፃፍ ማስረጃ ያስፈልጋል፤ ለዚህ ደግሞ በቂ ማስረጃ አለኝ። ኢትዮጵያ እንዴት ግብፅን ፈጠረቻት? እንዴት አሰለጠነቻት? ለሚለው ሁሉ ከእነ ማስረጃው የቀረበበት ሰፊ ጥናት የተደረገበት መፅሐፍ ነው።
እስኪ የመጽሐፉን ጭብጥ በጥቂቱ ያብራሩልን?
ግብፅ መጀመሪያ ዝም ብሎ የአባይ ወንዝ የሚፈስበት ረግረግ ቦይ መሬት ነበር። ከ7 ሺህ አመት በፊት ማለት ነው። ያኔ ኢትዮጵያኖች፣ ከኢትዮጵያ ወደ ቦታው ሄደው፣ ቦታውን ሰልለው አይተው ቆረቆሯት። በወቅቱ የኢትዮጵያ ነገስታት ሁለት ሃላፊነትና ማዕረግ ነበራቸው። አንድም ንጉስ ናቸው፤ በሌላ በኩል ካህናት ናቸው። ካህንም ንጉስም ሆነው መለኮታዊና ዓለማዊ ማዕረግ ነበር፣ የኢትዮጵያ ነገስታት የነበራቸው። ህዝቡን በንግስናቸው ያስተዳድራሉ፤ ለህዝቡና ለሃገራቸው በፀሎት ፈጣሪን ይማለዳሉ። ከእግዚአብሔር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ነበራቸው፤ የወቅቱ ነገስታት። እነዚህ ነገስታት ወደ ረግረጋማው ምድር ግብፅ ወረዱ፤ ቦታውን አለሙት፣ ፒራሚድ ገነቡ፤ መድሃኒት አገኙ፤ ፍልስፍናውን ፈለሰፉ፤ ከግሪክና ከጣሊያን እየመጡ የእነሱን ፍልስፍና ይማሩ ነበር። እነ አርስቶትል ፕሌቶ የሚባሉት ፈላስፎች በሙሉ ግብፅ ውስጥ ነው የተማሩት። በመፅሐፉ የመጀመሪያ ምዕራፍ፣ እነዚህ ከማስረጃዎች ጋር ይብራሩበታል።
ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ምዕራባውያን አሁን ድረስ የሚከራከሩበት የፍልስፍና ምንጭ ግሪክ ነች የሚለውን በማስረጃ የሚሞግት ነው። የኛ ፈላስፎች ለግሪኮችና ለጣሊያኖች እንዳስተማሯቸው የሚተነትን ነው። ራሳቸው ፈላስፎቹ #ግብፅ ሄደን ተማርን; ያሉትን ማስረጃ ጭምር ነው የማቀርበው። የአውሮፓውያን መሰረታዊ ስልጣኔ ከግሪክና ከጣሊያን ሳይሆን ግብፅን ከፈጠሯት ኢትዮጵያውያን እንደተቀዳ መጽሐፉ ያብራራል። ማስረጃም በሰፊው ያቀርባል። እስከ ዛሬ ግሪክና ጣሊያን የሚጠቀሱት ውሸት እንደሆነ የሚያስረዳ ነው። የታሪክ አባት የሚባለው ሄሮዱተስ የዛሬ 2450 አመት ግብፅ ሄዶ ማናችሁ? ከየት ናችሁ? ሲል "ኢትዮጵያውያን ነን እኛ፤ ማስረጃ ከፈለግህ ፒራሚዱም የኛ ነው። ተጨማሪ ከፈለክ የ330 ንጉሶች ስም ዝርዝር ይሄውልህ" ብለው ሰጥተውታል። እሱም ያንን መሰረት አድርጎ ስለ ኢትዮጵያውያ ግብፅን መፍጠርና ማስተዳደር ጽፏል። እኔም እሱን ነው ያጣቀስኩት። የፈጠራ ስራ አይደለም። አሁን ላይ እነሱ ዝቅ ብለው ስላሉ የትናንት አባቶቻችንም ዝቅ ያሉ የሚመስላቸው አሉ። ለእነሱ አስተማማኝ ማስረጃ ጭምር አቅርቤያለሁ።
ከሄሮዱተስ በኋላ የመጣው ዲዮዶሮስ የሚባለው የግሪኩ የታሪክ ፀሐፊ፣ "ፒራሚዱንም ሄሮግራፊውንም ኢትዮጵያውያን ናቸው የሰሩት" ብሎ የመሰከረው አለ። እሱንም አጣቅሻለሁ። ከዚያ በኋላም የአውሮፓ የታሪክ ተመራማሪዎችም ጭምር ግብፅን የፈጠርነው ኢትዮጵያውያን መሆናችንን፣ እንደውም ከግብፅ አልፈን እስከ ሳይቤሪያ ድረስ ከተማ እንደገነባን፣ እስከ ማያ ስልጣኔ ድረስ የኢትዮጵያ ስልጣኔ መሆኑን የሚመሰክሩ የታሪክ ማስረጃዎችን በሙሉ አግኝቼ በመፅሐፉ ውስጥ አካትቻለሁ።
በሌላኛው የመፅሐፉ ምዕራፍ ደግሞ ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ተዋግታ ሁሌም እንደተሸነፈች መሆኑን በማስረጃ የሚብራራበት ነው። ኢትዮጵያውያን የማሸነፋቸውን ሚስጥር አውጥቻለሁ። ግብፅንና ሱዳንን የመሩ ኢትዮጵያውያን ሴት ነገስታትን ስም ዝርዝር አስቀምጫለሁ። ከእነዚህ ነገስታት ውስጥ አራቱ አማልክት ተብለው ይመለኩ እንደነበር፣ በሌላ በኩል አምላክ ተብለው የተመለኩ ወንድ ኢትዮጵያውያን ፈርኦኖችንም ጠቅሻለሁ። እነዚህ ነገስታት በግብፅ፣ ፐርሽያ፣ ኢራቅ፣ ሱዳን የተመለኩ ናቸው። በሌላኛው ምዕራፍ ደግሞ ግብፅን የገዙ የኢትዮጵያ ስርወ መንግስታትንም ከነማስረጃው አቅርቤያለሁ። የአፋር ስርወ መንግስት ግብፅን ከመቼ እስከ መቼ እንደገዛ ተዘርዝሯል። ለምሳሌ ነፈርቲቲ የተባለች የአፋር ንግስት ነበረች፡፡ ከዚያ ደግሞ የኦሮሞ ስርወ መንግስት ግብፅን የገዛበት ታሪክ አለ። 18ኛው ስርወ መንግስት የኦሮሞ ነበር። ለዚህ ስዕላዊ ማስረጃዎች ሁሉ አሉ። ከዚያ ደግሞ የአማራ ስርወ መንግስት የገዛበት ዘመን አለ። የአማራ ስርወ መንግስት አማርና የምትባል ከተማን በስሙ ቀይሮ ሰይሟል። ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ጊዜ የአማራ ንጉስ ነበር። ይሄ ንጉስ የጎጃም ሰው ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወለዱ 1800 ዓመት ቀደም ብለው አማርና የሚባል ከተማ በአማሮች ተከትሞ ነበር። ለማሪያም፣ ዮሴፍና ኢየሱስ ጥገኝነት የሰጧቸው ኢትዮጵያውያ ነገስታት ነበሩ። መፅሐፍ ቅዱስ ወደ ግብፅ ሄዱ ይላል እንጂ እነማን ተቀበላቸው የሚለውን አያብራራም፡፡ ነገር ግን ሌሎች የታሪክ ማስረጃዎች ኢትዮጵያዊው ንጉስ እንደተቀበላቸው ነው የሚጠቁሙት። በወቅቱ ጥበቃ ያደርግላቸው  የነበረውም የጎጃሙ ሰው የሆነው አማናቱ ተትናይ የሚባል ንጉስ ነበር። ሌላው በመፅሐፉ የሚገለፀው ልክ እንደ ግብፅ ሁሉ ኑባ የሚባል የኢትዮጵያ አራተኛ የልጅ ልጅ፣ ወደ አሁኗ ሱዳን ወርዶ፣ ኑቢያ እንዳሰኛትና ከተማዋንም መረዌ እንዳሰኛት በማስረጃ ቀርቧል። መረዌ የሚለው መርሃዊ ከሚል የግዕዝ ቃል የመጣ ነው። ሙሽራ ማለት ነው። መርዌ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነበር። በቅርብ ጊዜ እንኳ አፄ ቴዎድሮስም በሱዳን ካሉ ሃያላን ጋር በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ግንኙነት ነበራቸው። ምን ዓይነት ግንኙነት የሚለው በመፅሐፉ ተዘርዝሯል።
ኢየሱስ በህፃንነቱ የተቀበሉትና የሚያውቃቸው በመሆኑ በ22 ዓመት ተኩል እድሜው፣ ወደ መርዌ መጥቶ ለአንድ ሳምንት ክርስትናን አስተምሮ፣ ሱዳንን በሞላ የክርስቲያን ሃገር አድርጎ ነበር። ሱዳን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የክርስቲያን ሃገር ነበረች። ቱርኮች ናቸው ሙስሊም ያደረጓቸው። ነገር ግን በአፄ ፋሲልም በአፄ ቴዎድሮስም ዘመን፣ የሱዳን ገዥዎች በኢትዮጵያ ነገስታት ስር ነበሩ። ካርቱም የተባለችው ከተማም በአፄ ላሊበላ ዘመን፣ ክርስቲያኖች በግብፅ እየተጠቁ መሆኑን ሲያውቅ፣ የዛሬዋ ካርቱም ድረስ ወርዶ ነጭና ጥቁር አባይ የሚገናኙበት ላይ ውሃውን በከፍተኛ የድንጋይ ቴክኖሎጂ ጥበብ ወደ ሰሃራ በረሃ እንዲፈስ አደረገው። በወቅቱ ከግብፅ #እባክህ ማረን; ብለው ለምነው፣ ስጦታ ሰጥተው፣ ውሃው ተከፈተላቸው። በወቅቱ ውሃው “ተከረተመ” ስለተባለ ቦታው ካርቱም ተባለ- በሂደት። አሁን ቦታው ካርቱም ይባላል። በአጠቃላይ ዛሬ  የኢትዮጵያ ግዛት ይገባኛል የምትለው ሱዳን ምንም ያልነበረች ናት። እንግሊዞች መጥተው እስከያዟት ድረስ በኢትዮጵያ ስር የነበረች፣ የሰፊዋ ኢትዮጵያ ግዛት አካል ነች። በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር ማለትም አፄ ቴዎድሮስ ከእነ ኢድሪስ መሃዲ ጋር በመተባበር ነፃ ለማውጣት ብዙ ጥረት ሲያደርጉ ነበር። አሁን ሱዳን ቤንሻንጉል የኔ ነው የሚል ነገር ታነሳለች። በዚህ ሎጂክ ከተሄደ ሙሉ ሱዳንን የቆረቆርነው እኛ ስለሆንን፣ እኛም ሙሉ ሱዳንን የኛ ነች ማለት እንችላለን  ማለት ነው።
ቀጥሎ ባለው የመፅሐፉ ክፍል ደግሞ ከግብፅ የሚላኩ ጳጳሳት እንዴት ኢትዮጵያን እንዳቆረቆዟትና ለማጥፋት ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር በማስረጃ ይተነትናል። በመፅሐፉ ሌላኛው ምዕራፍም፣ ለግብጻውያን የተፃፈ የደብዳቤ መልዕክት አለ። ደብዳቤው ምንድን ነው የሚለውን አንባቢያን መፅሐፉን ሲያገኙት ይረዱታል።
መፅሐፉን ያዘጋጁት በምን ዓላማና ግብ  ነው?
መፅሐፉን  ለመፃፍ ያነሳሳኝ ለኢትዮጵያ ያለኝ ቅንአት ነው። ለኢትዮጵያ በመቅናትና ግብፃውያን የሚያደርጉት ነገር የፈጠረብኝ ስሜት ነው ታሪኩን የበለጠ እንድመረምር የገፋፋኝ። ምክንያቱም እኛ ግብፅን መስርተን ገንብተን እዚህ አድርሰን ከኋላ የመጡ አረቦች፣ አውሮፓውያን፣ ቱርካውያን፣ ፈረንሳውያን፣ እንግሊዞች ተቀላቅለው የፈጠሩት ማህበረሰብ በዚህ መጠን በግብፅ ቆርቋሪዎች ላይ መነሳታቸው የፈጠረብኝ ስሜት ነው። እነዚህ ሰዎች የመጡት እኮ እኛ ግብፅን መስርተን አሰልጥነን ከጨረስን ከ4 ሺህ 5 መቶ ዓመት በኋላ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ከኋላ የመጣ አይን አውጣ ሆነው፣ አባይን ለብቻቸው መጠቀማቸው አንሶ ፒራሚዱንም፣ ነገስታቱንም አስከሬናቸውንም፣ ቀለሙ የኢትዮጵያውያን መሆኑን እያሳያቸው፣ አረብ ለማድረግ መሞከራቸው አስቆጭቶኝ ነው። ፒራሚዱም ነገስታቱም የኛው መሆናቸው እውቅና መነፈጉ የፈጠረብኝ ቁጭት ነው መፅሐፉን ለማዘጋጀትና ታሪኩን ለመግለጥ የፈለግሁት። ፒራሚዱም ሁሉም የኛ ሆኖ ሳለ፣ ዛሬ በታሪክ እንኳ እውቅና ለመስጠት አለመፈለጋቸው ያሳዝናል። እንደውም እኛ በሰራነው ሃብታም እየሆኑ፣ እኛ የተፈጥሮ ሃብታችንን እንኳ እንዳንጠቀም ሴራ ሲሸርቡብን  ያሳዝናል። ቢችሉ አሁንም ከሚያገኙት ማካፈል አለባቸው፤ ይሄንን መብታችንንም በአለማቀፍ ፍ/ቤት መጠየቅ እንችላለን። በሌላ በኩል፤ ለዚህ መፅሐፍ መዘጋጀት ገፊ ምክንያቱ እኛ ታሪካችንን በአግባቡ አውቀን ለምን ሞጋቾች አንሆንም የሚል ነው። ግብፅ ሱዳን፣ ሊቢያ የጥንት የኛ ግዛቶች ነበሩ። ህዝቡም መልኩም የኛ ህዝብ ነበር። አሁን ያሉት ከየትም የመጡና በዘመናት ሂደት የተሰባሰቡ ናቸው እንጂ የእነዚህ አካባቢዎች ጥንታዊ ህዝቦች ኢትዮጵያውያን ነን። ግብፆቹም ይህን ታሪክ ማሰብ አይፈልጉም። ስለዚህ እንዲያስታውሱ ማስታወስ ያስፈልጋል። አጋዚያንም፣ አፋሮችም፣ ኦሮሞዎችም፣ አማሮችም ግብፅን የገዙት በኢትዮጵያዊነት፣ ኢትዮጵያ ብለው ነው። ስለዚህ እኛም ይህን ገናና ታሪካችንን ማወቅ አለብን። ዛሬ ግብፅን የያዙት ግብፃውያንም፣ ይህን ስረ መሰረታዊ ታሪክ ማወቅ አለባቸው። የሚንቁን አረቦች ታሪካችንን አውቀው፣ እንዲያከብሩን ነው ፍላጎቴ። ይሄን ለማድረግ መፅሐፉ በአረብኛ ተተርጎሞ፣ በአረቡ ዓለም እንዲሰራጭ ይደረጋል። ግብፅም ልኳን እንድታውቅ ነው ፍላጎቴ።
እርስዎ ይሄን ታሪክ ለመግለፅ ምን ያህል ቅቡልነት ያላቸው ሁነኛ ማስረጃዎች ተጠቅመዋል?
የኢትዮጵያን ገናና ታሪክና ክብርን በዛሬው ውድቀት በመለካት እውነት የማይመስላቸው አሉ። በራሱ መጠን የሚገምት ትውልድ አለ። ይሄ  ባለማወቅ የሆነ ነው። ሌላው ደግሞ ኢትዮጵያን ስለሚጠላ የኢትዮጵያ ገናና ታሪክ እንዲወሳ አይፈልግም። ኢትዮጵያ ትንሽ ሃገር መስላ፣ ትንሽ ታሪክ ያላት መስላ እንድትታይ ነው የሚፈለገው። የመቶ ዓመት ታሪክ ብቻ እንደሆነ እንዲታሰብ ነው የሚፈለገው። ግብጾች ወይም ሌላው ጋ ብትሄድ ደግሞ የራሳቸው ያልሆነውንም የኛ ነው ብለው ገናና ታሪክ ለመፍጠር ይጥራሉ። እኛ በዚህ መፅሐፍ የምናወሳው የ7 ሺህ እና 6 ሺህ ዓመታት ታሪክ ነው። ስለዚህ ይሄን የረዥም ዘመን ታሪክ የማያውቅና ሁኔታዎችን በሙሉ በዛሬ ውድቀት የሚለካ ሰው፣ ነገርየው ተረት ነው ሊል ስለሚችል፣ በቀጥታ የታሪክ አባት የሚባሉት እነ ሄሮዱተስ የመሰከሩትን ነው ያጣቀስኩት።
በሰፊው የሄሮዱተስና የወቅቱ ባለታሪኮችን ምስክርነት ነው የጠቀስኩት። ቀጥሎም የጀርመን፣ የአውሮፓ የታሪክ ተመራማሪዎች፣ ጥቁር ምሁራንና ፈላስፎች የተናገሯቸውን፤ ከኢትዮጵያውያንም ቀደም ብለው በጉዳዩ ላይ ምርምር የሰሩ ሰዎችን ምስክርነት አድርጌ ነው በሰፊው ያጣቀስኩት፡፡ ማጣቀሻውን በአማርኛም በእንግሊዝኛም ነው ያቀረብኩት። ዋቢ መፅሐፍትም 50 ያህል  አስቀምጫለሁ። ሰዎች እነሱንም አግኝተው መመልከት ይችላሉ።
መፅሐፉ መቼ ለአንባቢያን ይቀርባል?
በቀጣይ ሳምንት ለአንባቢያን ይቀርባል። ዋጋው በእጅጉ እንዲቀንስ አድርጌያለሁ። ምክንያቱም በብዛት ታትሞ አንባቢያን እጅ እንዲደርስ እፈልጋለሁ። ሁሉም ታሪኩን እንዲያውቅ ስለምፈልግ ከ350 ብር በላይ የተገመተውን መፅሐፍ ወደ 220 ብር ገደማ እንዲሆን ነው የወሰንነው።
ፕሮፌሰር ካገኘህዎት አይቀር ስለ አሜሪካ የሰሞኑ ማዕቀብ ምን አስተያየት አለዎት?
በእውነት በኢትዮጵያ ላይ የተደረገው አግባብ አይደለም። በትግራይም ቢሆን መንግስት በትልቅ ጥንቃቄ ነው እርምጃ የወሰደው። ህውኃት የፈጸመው አረመኔያዊ ድርጊት ነው። ወገኔ መሃል ነኝ ብሎ ተደላድሎ የተቀመጠን ሰራዊት አድፍጠው ያደረሱበት ግፍ ከሚታሰበው በላይ አሳዛኝ ነው። በማይካድራ ያደረጉት የጅምላ ጭፍጨፋ  አሰቃቂ ነው። ሆነ ብለው ህዝብ በሚሰበሰብበት ቤተ ክርስቲያንና አደባባይ እየገቡ የፈጸሙት የፈሪ ድርጊት በጣም ነውር ነው። ነገር ግን  የኢትዮጵያ ሰራዊት እነሱን ብቻ ለይቶ ለመምታት ያደረገው ጥረት የሚያስመሰግን ሆኖ ሳለ፣ ተቃራኒው መደረጉ በጣም አሳዛኝ ነው። ልክ እንደ ባዕድ ሃገር መሰረተ ልማት አፈራርሰው፣ ምግብ ለዜጎች እንዳይደርስ እንቅፋት አዘጋጅተው፣ መንግስት የምግብ እርዳታ ሲያደርስም እርዳታውን እየቀሙ እንዳይተላለፍ እያደረጉ፣ የጭካኔ ተግባር እየፈጸሙ ሳለ፣ ጩኸታቸው መበርታቱ በጣም የሚገርም ነው። የህውኃት ሰራዊት ላለፉት 27 ዓመታት መጠነ ሰፊ ግፍ ሲፈፅም በዝምታ ነበር የተመለከቱት፤ በሺህ የሚቆጠር የሰብአዊ መብት ጥሰት ሪፖርት ሲቀርብላቸው ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው የነበሩ ምዕራባውያን፣ ዛሬ ምን ታይቷቸው ይሆን ይህን ለማድረግ የፈለጉት።
"ለናንተ አሻንጉሊት አንሆንም" መባሉ አስቆጭቷቸው ነው ማዕቀብ ያደረጉት። ለዚህ ዋና ተዋናይ ደግሞ ሱዛን  ራይስ የተባለችው የአቶ መለስ ዋና ወዳጅ የነበረች ሴት ነች። ይቺ ሴት ከአቶ መለስ ብዙ እጅ መንሻ ትቀበል የነበረች፣ የሰውየው አንደኛ ወዳጅ የነበረች ነች። አሁን ይቺ ሴት በባይደን አስተዳደር ተመልሳ መጥታለች።  የኢትዮጵያ መንግስት ለምዕራባውያን አልታዘዝም ማለት ነው የማዕቀቡ መንስኤ። አሁን የብልፅግና መንገድ ስለተጀመረና ግድቡም ፍሬያማ እየሆነ በመምጣቱ ኢትዮጵያ የበላይ ልትሆን ትችላለች፤ በዚህም ጥቁር ሁሉ አልታዘዝ ሊለን ይችላል ከሚል መነሻ ነው እቀባው። በነገራችን ላይ እቀባው ያን ያህል ጉዳት የለውም። ምናልባት የኢትዮጵያን ህዝብ በኢኮኖሚ ሊጎዱ ይችላሉ፡፡ ለማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ ዝግጁ ሆኖ ራሱን ማጠናከር አለበት። መተባበርና በጋራ መቆም ያስፈልጋል።


        ዙማ የተከሰሱበትን የ5 ቢ. ዶላር ሙስና አልፈጸምኩም አሉ


            የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ወደ 4.8 ሚሊዮን በደረሰባትና የሟቾች ቁጥርም ወደ 129 ሺህ በተጠጋባት አፍሪካ በሚገኙ በርካታ አገራት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ የሙስና ወንጀሎች በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋታቸውንና በአንዳንድ አገራት ሙስናው ከወረርሽኙ በላይ አሳሳቢ ሆኗል መባሉን አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል፡፡
በብዙ የአፍሪካ አገራት ወረርሽኙን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚመደብን በጀትና የእርዳታ ገንዘብ ከመዝረፍ አንስቶ የተለያዩ ከፍተኛ ወንጀሎች መስፋፋታቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ መሰል ሙስናዎች ከተስፋፉባቸው አገራት መካከልም ደቡብ አፍሪካ፣ ማላዊ፣ ኬንያና ኡጋንዳ እንደሚገኙበት ጠቁሟል፡፡
ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ እጅግ ከፍተኛ ሙስና የተስፋፋበት ቀዳሚዋ አገር እንደሆነች በሚነገርላት ደቡብ አፍሪካ፤ ባለፈው የፈረንጆች አመት 2020 ብቻ 418 ሙስናዎች መፈጸማቸው ሪፖርት መደረጉን ኮራፕሽን ዎች የተባለ የጸረ ሙስና ተቋም ይፋ ማድረጉን አመልክቷል፡፡
በማላዊ ባለፈው ወር ለኮቪድ የተመደበን 1.3 ሚሊዮን ዶላር መዝብረዋል የተባሉ 64 የስራ ሃላፊዎችና የመንግስት ባለስልጣናት መታሰራቸውን ያስታወሰው ዘገባው፣ በኬንያ የመንግስት ባለስልጣናትና የመድሃኒት ቁሳቁስ አምራች ኩባንያ ባለሃብቶች በመመሳጠር ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ መዝረፋቸው እንደተደረሰበት አመልክቷል፡፡
በናይጀሪያ የጤና ሚኒስቴር የእቃ ግዢ ክፍል ከነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር ለሃሰተኛ የፊት ጭንብል ግዢ 96 ሺህ ዶላር ያህል ያላግባብ ማባከኑ እንደተደረሰበት የጠቆመው ዘገባው፣ በኡጋንዳ አራት የመንግስት ባለስልጣናት በከፍተኛ ሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸውንም አስታውሷል፡፡
በሌላ የአፍሪካ የሙስና ዜና ደግሞ፣ ከፍተኛ የሙስናና የተለያዩ የማጭበርበር ወንጀሎችን ፈጽመዋል ተብለው 18 ክሶች የተመሰረተባቸው የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ መሪ ጃኮብ ዙማ፣ ባለፈው ረቡዕ በከፍተኛ ሙስና ክስ ፍርድ ቤት ቀርበው ወንጀሉን አልፈጸምኩም ሲሉ መከራከራቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
አገሪቱን እ.ኤ.አ ከ2009 እስከ 2018 በፕሬዚዳንትነት የመሩት ዙማ ከተመሰረቱባቸው ከፍተኛ የወንጀል ክሶች መካከል ከአንድ የጦር መሳሪያዎች አምራች ኩባንያ ጋር ከ20 አመታት በፊት በጥቅም በመተሳሰር የፈጸሙት 5 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የግዢ ስምምነት እንደሚገኝበት ያስታወሰው ዘገባው፣ ዙማ ግን ረቡዕ ዕለት በፒተርማርቲዝበርግ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተገኝተው በሰጡት ምላሽ ወንጀሉን አልፈጸምኩም ሲሉ መከራከራቸውን ገልጧል፡፡
የ79 አመቱ ዙማ የፍርድ ሂደት ለመጪው ሃምሌ 19 መቀጠሩን የጠቆመው ዘገባው፣ ግለሰቡ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ እስከ 25 አመታት በሚደርስ እስር ሊቀጡ እንደሚችሉ መነገሩንም አመልክቷል፡፡


          ከዕለታት አንድ ቀን አንድ አውራዶሮና ሚስቱ በአንድ ቄስ የእህል መጋዘን አጠገብ ሲጓዙ፣ አውራዶሮው አንድ ባቄላ አግኝቶ ሲውጥ፤ አነቀውና፤ ውጪ ነብስ ግቢ ነብስ ሆነ። ሚስቲቱ ዶሮ የምታደርገው ብታጣ ውሃ ፍለጋ ወደ ወንዝ ወረደች፡፡
 “ወንዝ ሆይ! እባክህ ባለቤቴ ባቄላ አንቆት፣ መተንፈስ አቅቶት ሊሞትብኝ ነው፡፡ ትንሽ ውሃ ስጠኝና ነብሱን ልታደገው?” አለችው፡፡
ወንዝም፤ “ወደ ሎሚ ዛፍ ሄደሽ አንድ የሎሚ ቅጠል ካመጣሽልኝ ውሃ እሰጥሻለሁ” አላት፡፡
ዶሮይቱ ወደ ሎሚ ዛፍ ሄደችና፤ “ሎሚ ዛፍ ሆይ! ባለቤቴ ባቄላ አንቆት መተንፈስ አቅቶት፣ ሊሞትብኝ ነው ብዬ ወንዝን ውሃ ስጠኝ ብለው፤ “የሎሚ ቅጠል ካመጣሽ እሰጥሻለሁ” አለኝ፡፡ እባክህ አንዲት ቅጠል ስጠኝ?” አለችው፡፡
የሎሚ ዛፍም፤ “ወደ ቄሱ ቤት ሠራተኛ ሄደሽ የመርፌ ክር ካመጣሽልኝ እሰጥሻለሁ” አላት፡፡
 እመት ዶሮ ወደ ቄሱ ቤት ሠራተኛ ሄዳ ጉዳይዋን አስረዳች፡፡
የቤት ሠራተኛዋም፤ “ወደ ላም ሄደሽ ትንሽ ወተት ካመጣሽልኝ ክሩን እሰጥሻለሁ” አለቻት፡፡
እመት ዶሮ ወደ ላም ሄዳ፤ “ትንሽ ወተት ስጪኝ ባክሽ” ብላ ጉዳይዋን ሁሉ ዘረዘረችላት።
 ላምም፤ “ወደ አጫጆቹ ዘንድ ሄደሽ ትንሽ ጭድ ካመጣሽልኝ እሰጥሻለሁ” አለቻት፡፡
እመት ዶሮ እንደፈረደባት ወደ አጫጆቹ ሄዳ፤ “እባካችሁ ትንሽ ጭድ ስጡኝ” አለቻቸው፡፡
አጫጆቹም፤ “ወደ ቀጥቃጮች ሄደሽ ትንሽ ማጭድ ከሰጡሽ ጭዱን እንሰጥሻለን” አሏት፡፡
 እመት ዶሮ ወደ ቀጥቃጮቹ ሄዳ ለመነቻቸው፡፡
ቀጥቃጮቹ ደግሞ “ወደ ከሰል አክሳዮቹ ጋ ሄደሽ አንድ አራት ራስ ከሰል አምጪልንና የጠየቅሽንን እንሰጥሻለን” አሏት፡፡
 ወደ ከሰል አክሳዮቹ ላዕያውያን (Laians) ምርር ባለ ምስኪን ቃና አስተዛዝና፤ “ከሰል አክሳዮቹ ሆይ፤ ባለቤቴ አውራዶሮ ባቄላ አንቆት፣ መተንፈስ አቅቶት ሞት አፋፍ ቢደርስ፣ አንድ ጉንጭ ውሃ ወንዝን ብጠይቀው፣ የሎሚ ቅጠል ከሎሚ ዛፍ አምጪ፤ የሎሚ ዛፍ ጋ ብሄድ ከቄሱ ሠራተኛ የመርፌ ክር አምጪ፤ የቄሱ ሠራተኛ ከላም ወተት አምጪ፤ ላም ጋ ብሄድ ከአጫጆቹ ጭድ አምጪ፤ አጫጆቹ ጋ ብሄድ ከቀጥቃጮች ማጭድ አምጪ፤ ቀጥቃጮቹ ዘንድ ብደርስ ከላዕያውያን ከሰል ካመጣሽ እንሰጥሻለን አሉኝ፡፡ እባካችሁ እናንተ እንኳ እሺ በሉኝ፡፡”
ከሰል አክሳዮቹ ራሩላትና ከሰሉን ሰጧት፡፡ እመት ዶሮ እየከነፈች ከሰሉን ይዛ ለቀጥቃጮቹ ሰጠች፡፡ ማጭድ ተቀብላ ለአጫጆች፤ ከነሱ ጭድ ተቀብላ ለላም፤ ከላም ወተት ወስዳ ለቄሱ ሰራተኛ፤ ከሷ የመርፌ ክር ተቀብላ ለሎሚ ዛፍ፤ ከሎሚ ዛፍ ቅጠል ተቀብላ ወደ ወንዙ በረረች፡፡ ከወንዙ ውሃ ተቀብላ ወደ አውራ ዶሮ ባሏ ከነፈች፡፡ አውራ ዶሮ ባሏ ግን ለአንዴም ለሁሌም ፀጥ ብሏል፡፡ ሞት ቀድሟታል፡፡
 * * *
ችግር ሠንሠለቱን ሲተረትር ሰው በማህል ያልቃል፡፡ አያድርስ ነው፡፡ ገጣሚ ደበበ ሰይፉ፤ በ “አክሱም ጫፍ አቁማዳ” ግጥሙ ትግራይ ለሸዋ፣ ለአርሲ ለሲዳሞ፣ ለወለጋ፣ ለጐንደር፣ ለኤርትራ እህል ተለማምነው፤ የተላከችው አቁማዳ አንዳችም እህል ሳይገባባት ተመልሳ ለባለቤቱዋ ለትግራይ ባዶዋን ትመጣለች፡፡ “…አክሱም ላይ ሠቀላት ከባዶ አቁማዳ ነው፣ እሚዛቅ ፍቅራችን” ብሎ ይደመድማል፡፡ አንድምታው ብዙ ነው፡፡ የችግሩ መጠን ይለያያል እንጂ በየሠንሠለቱ ቀለበት ላይ ችግር አለ፡፡ ቢሮክራሲያችንም እንደዚያው ነው! ሁሉም ለየግብዓቱ ጥሬ ዕቃውን ይጠይቃል፡፡ ይሄን ሠንሰለት ሙስና ብንለውም፤ ወይም የቅብብሎሽ ሂደት፤ አሊያም ዱላ ቅብብሎሽ፤ ዞሮ ዞሮ የታነቀው ህዝብ ለአንዲት ፍሬ መሞቱ አሳዛኝ ሀቅ ነው! የችግሮቻችን ብዛት የመፍትሔዎቻችንን ውስብስብ ገፅታ ከወዲሁ ጠቋሚ ነው፡፡ የቆዩ ችግሮች መፍትሔ ሳያገኙ፤ አዳዲሶቹን ለመፍታት መጣራችን ራሱ አንድ ተጨማሪ ችግር ይሆንብናል፡፡ የሀገራችን ቁልፍ ጉዳይ ችግርን በሌላ ችግር መፍታት መሆኑ አሳሳቢ ከሆነ ቆይቷል፡፡ አብሮ መታየት ያለበት ግን ችግርን የመገንዘብ አቅማችንም አናሳ መሆን ነው፡፡ አንድ ፈላስፋ እንዳለው፡- “The Problem is us; the Solution us” (ችግሩም እኛ፤ መፍትሔውም እኛ እንደማለት) ስለዚህ “እንዳልተመለሰው ባቡር” ያልተመለሱ ጥያቄዎች ሲደመሩ አዲስ ጥያቄ እያደረግን ማሰብ ይበጃል፡፡  የዱሮ ችግር ብለን በመዝገብ የተያዙ ሂሳቦችን ካላወራረድን ነገ ኦዲተር አይለቀንም! ከዲሞክራሲ ምን ጐሎ ነበር? ከፍትሕ ምን ጐሎ ነበር? ከሙስና መፍትሔ ምን ጐሎ ነበር? ከመልካም አስተዳደር ምን ጐሎ ነበር? ከሹምሽር ሥራ ምን ጐሎ ነበር? ህዳሴውስ ተመርምሯል ወይ? ከምርጫ ዝግጅት አሁን ምን ጐሎዋል? ከዱሮ ምርጫዎችስ ምን ጐሎ ነበር? ከዲፕሎማሲው ምን ጎሎ ነበር? በዚህ ሁሉ ድምር ሂሳብ ዛሬ ምን ላይ ነን? በአየር ጊዜ ክርክር አድማጩ ህዝብ እየረካ ነው? ምርጫው የተበላ ዕቁብ ነውን? የሚለው አስተሳሰብ መክኗል ወይስ በየልቡ ያኮበኩባል?
 በተፅዕኖ ከመምረጥ ጀምሮ አንዳንዱን ጠፍቶ ድንገት የመጣ ተመራጭ “አፋልጉኝ” እስከማለት የደረሰ፤ በስላቅ በሚኖር ህብረተሰብ ውስጥ ምርጫው አድሎ የሌለውና ዕውነተኛ (ነፃ) [Fair and Free] ነው ብሎ ለመኩራት፣ ለመተማመንና “አሹ!” ለማለት ከባድ ነው፡፡ “ዐባይን ጭብጦዬን ከወሰደብኝ በኋላ አላምነውም!” ያለውን ባላገር ደግመን ደጋግመን እንድናስብ የሚያደርገን ፖለቲካዊም ባህላዊም ተፈጥሮ ያለን ነንና፣ እንዴት ይሆን ወደፊት የምንገፋው ማለት አመላችን ነው!

“የሃገሪቱን አቅም ያላገናዘበ ነው” ገንዘብ ሚ/ር
                       
              በትግራይ ክልል ተፈፀመ የተባለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመመርመር ተጨማሪ በጀት  እንደሚያስፈልገው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል።
ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ጋር በትግራይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ምርመራ ለማድረግ እየተዘጋጀ የሚገኘው ኢሰመኮ፤ በክልሉ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለመክፈትና መርማሪዎችን ለመቅጠር ተጨማሪ በጀት የጠየቀው።
ኮሚሽኑ ለ2014 የበጀት ዓመት የተመድ የበጀት ጣሪያ 103 ሚሊዮን ብር ቢሆንም አሁን የጠየቀው 211.6 ሚሊዮን ብር መሆኑ ተመልክቷል። ይህም ከተፈቀደው የ108.6 ሚሊዮን ብር ጭማሪ የበጀት  ፍላጎት መኖሩን አመላካች ነው ተብሏል።
የገንዘብ ሚኒስቴር በበኩሉ፤ ኮሚሽኑ የጠየቀው የበጀት ጭማሪ  የሃገሪቱን አቅም ያላገናዘበ ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በአክሱም ከተማ ባከናወነው የመጀመሪያ ዙር ምርመራ፣ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን ሪፖርት ማድረጉ አይዘነጋም።

  የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከፍተኛ አመራሮች በጉራጌ ዞን በሚገኙ የምርጫ ወረዳዎች ከግንቦት 13 - ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሲያደርጉ የነበረው የምርጫ ቅስቀሳ በወልቂቴ ከተማ በተደረገ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ።
በወልቂጤ ከተማ በተደረገው ዝግጅት ላይ የኢዜማ መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)፤ መራጮች በተለያየ መንገድ የሚደረግባቸውን ማስፈራራትና ጫና በመቋቋም ምንም ዓይነት ግጭት ውስጥ ሳይገቡ ሰኔ 14 በካርዳቸው የፍላጎታቸውን እንዲመርጡ አሳስበዋል። የገዢው ፓርቲ ሰዎች ኅብረተሰቡን ለማስፈራራት የተለያየ ሙከራ እያደረጉ እንደሆነ የጠቀሱት የኢዜማ መሪ ፤«የምርጫ ዕለት ለማን ድምጻችሁን እንደሰጣችሁ ከራሳችሁ እና ከፈጣሪያችሁ ውጪ ማንም አያውቅም። በሚያደርጉትና በሚያወሩት ሳትረበሹ የልባችሁን ምረጡ!» ብለዋል።  ምርጫው በሰላም ተካሂዶ ማኅበረሰቡ የሰጠው ድምፅ በንፅህና ከተቆጠረ ማንም ያሸንፍ ማን ሁላችንም እናሸንፋለን ያሉት መሪው፤ ለዚህም ከምርጫው ጋር በተያያዘ ኃላፊነት ያለባቸው ተቋማት በሙሉ የየበኩላቸውን ኃላፊነት በከፍተኛ አትኩሮት እንዲወጡ የአደራ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የኢዜማ ከፍተኛ አመራሮች ባለፉት 5 ቀናት በጉራጌ ዞን በሚገኙት ቡዒ፣ ኬላ፣ ቡታ ጅራ፣ አገና፣ ሐዋሪያት፣ አረቅጥ፣ ቋንጤ፣ ጉንችሬ፣ ድንቁላ፣ እምድብር እና ወልቂቴ ከተሞች የተሳካ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረጋቸው ተጠቁሟል።
የኢዜማ መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የምርጫ ቅስቀሳ ዝግጅቶቹ ላይ ፀሐይና ዝናብ ሳይበግራቸው ረጅም ርቀት ጭምር እየተጓዙ ለተሳተፉ ነዋሪዎች እንዲሁም ቅስቀሳዎቹ የተሳኩ እንዲሆኑ ላደረጉት የየአካባቢው የኢዜማ መዋቅሮች አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


Saturday, 22 May 2021 12:38

“ከአመጿ ጀርባ”

     “ከአመጿ ጀርባ” የሚል ነው - መጽሐፉ። እውነተኛ ታሪክ ነው? ልብወለድ ድርሰት ነው? እርግጡን መናገር ያስቸግራል። መጽሐፉ፣ አዲስ ነው - በኤደን የተፃፈ፣ ወይም የተደረሰ።  ሽፋኑም ላይ፣ ገለጥ ሲደረግም፣ “ልብወለድ” ወይም “እውነተኛ ታሪክ” የሚል ታፔላ አልተለጠፈለትም። “አልነግራችሁም። አንብባችሁ ድረሱበት!” ለማለት ይሁን አይሁን አይታወቅም። በእርግጥ፣ ከድርሰቱ ወይም ከታሪኩ በፊት፣.... ስለመጽሐፉ ይዘት የሚናገር፣ መግቢያ ጽሑፍ አለ - አንድ ገፅ። እዚሁ መግቢያ ላይ፣ ስለ “ገፀባሕርያት” ትነግረናለች - ደራሲዋ። ልብወለድ ታሪክ ቢሆን ነው።
ግን ደግሞ፣ በመጽሐፉ ውስጥ፣ በእውነተኛ ስማቸው ለተጠቀሱና ለተተረኩ ሰዎች፣ መልዕክት ታስተላልፋለች። እውነተኛ ታሪክ ቢሆን ነው።
ልብወለድ ድርሰት ወይስ እውነተኛ ታሪክ?  ወይስ የሁለቱ ቅልቅል - አንዱ በሌላው ውስጥ ሰርጎ ገብ? ቁርጡን፣ ከደራሲዋ እስክንጠይቅ ድረስ፣... ከመጽሐፏ የመጀመሪያ ገፆች፣... ጥቂት ጥቂት እናስነብባችሁ - ልብወለድ ታሪክ እንደሆነ በመተማመን ወይም  ከልብ በእጅጉ ተስፋ በማድረግ።

              የአመፅ ዋዜማ።
ሁሉም ነገር ዋዜማ አለው፤ እውነቴን ነው።
...ህይወት፣ አንድ ሁነት ከመዝራቱ በፊት፣ ብዙ ሂደቶችን አልፎ፣ በርካታ የመግቢያ ደውል አስምቶ ነው። ሳይረገዝና ሳይማጥ የሚወለድ፣ ምንም የሕይወት ክስተት የለም። ነገሩ የማስተዋል ጉዳይ ነው።
የዛሬ አስራ ሁለት ዓመት ገደማ መሆኑ ነው፤ ... ግን፣ ልክ እንደትላንት ነው የማስታውሰው። በጊዜው፣ በጣም እወደው ከነበረው፣ ከድሮ ፍቅረኛዬ ጋር የተገናኘንበትን ቀን ልናከብር፣ ቀጠሮ ነበረን።
ከዚህ ቀን በፊት... ለጥቂት ወራት ምን ሳስብ እንደነበር፣ በአጭሩ...
የሕይወቴን ብኩንነትና እርባና ቢስነት፣ ከመቼውም በላይ የተረዳሁበት ጊዜ ነበር። ከሶስቱ ቁልፍ የሕይወቴ ማእዘኖች ውስጥ፣ ሁለቱ (ቤተሰቦቼና ስራዬ)፣ ፍሬ እና ደስታ አልባ ነበሩ። የእነሱ ሸክም ደግሞ፣ ሶስተኛውንና ጤነኛውን ጎኔን፣ ፍቅሬን እየገደለው ነበር።
ቤተሰቦቼን መሸከምና ማስታመም የታከትኩበት፤ የስራ ቦታ አለቃዬን ማከምና ማስተማር በቃኝ ያልኩበት፤ እራሴንም ጭምር ማደንዘዝ እና ማደነዝ የታከትኩበት ጊዜ ነበር። እነዚህ ሁለት ክፉኛ የታተሙ የሕይወቴ ጎኖች፣ ሦስተኛውና የምሳሳለት ፍቅሬ ላይ መጣል “ይብቃ” ያልኩበት፣ ታሪክ ቀያሪ ወቅት ነበር።
ሁለቱ የሕይወቴ ጎኖች ምንም ማብራሪያ አይሹም። ብዙ ሸክም እና ሕመም ይዘዋል። በተለይም ከቤተሰቦቼ ጋር የተያያዘው ጎኔ። እንደው ጎኔ ልበል እንጂ፣ የትኛው ጎኔ፣ የትኛው አናቴ ወይም እንጀቴ እንደሆነ መለየት ከባድ ነው።
አንደኛው የሕይወቴ ማእዘን፤ ፍቅሬ።
ስለ ስሱ ጎኔ ላውራ፣ ስለ የድሮ ፍቅረኛዬ። ሄኖክ ይባላል። እስከዛሬ ድረስ ሳስበው፣ ፈገግታው ልቤን ያበራዋል።
ወጣቶች ነበርን። ከ”ዩንቨርስቲ” ተመርቀን፣ ጥቂት ዓመታት መስራታችን ነበር። ፍቅራችን ወሰን አልነበረውም። ከተማው ውስጥ የነበርነው ከዋክብት፣ እኛ ብቻ ነበርን።
ስንገናኝ፣ ከተማችን ብቻ ሳትሆን ምድርም ትሞቃለች፤ ትደምቃለች። ሌሎችም ፍቅረኞች ሲዋደዱ ይሰማናል።
እኛ ስንስቅ፣ ግማሽ ጨረቃ ትሞላች። ሰዎች ሐዘናቸውን ይረሳሉ። ያለ ምክንያት ይፈነጥዛሉ። ይደሰታሉ። ፍቅራችን ከእኛ በላይ ነበር። የእኛም አልነበረም። ፍቅር ከነበረበት ጥልቀት ውስጥ ገብተን ስለቀመስነውና፣ ጠጥተነው ስለሰከርን፣ የእኛ መስሎን በፍቅር ወይን ልባችን ታወረ። ሰከርን።
ከስካራችን እና ከፍቅራችን ጀርባ ግን፣ ሁሌም አንድ ነገር ይታወቀኝ ነበር... የጨላለሙት ሁለቱ የሕይወት ማእዘኖቼ፣ ፍቅሬን እንዳፈኑት።
ሁለቱን ሸክሞቼን የማራግፈው፣ ውዴ ላይ እንደሆነ አውቃለሁ። ሸክሜ፣ ከእኔ አልፎ እሱንም እንደከበደው፣ ባይናገረውም ገብቶኛል። ምድርን የሚያሞቀው ፍቅራችንን፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሲያቀዘቅዘው ይታወቀኛል። ይሁን እንጂ፣ ሸክሜን ማውረድ፣ ወይም ውዴን ብቻ መምረጥ፣ ቀላል አልነበረም። ያው... እስኪሆን ድረስ ማለት ነው።
ፍቅራችን ወሰን አልነበረውም። በአንድ ሳንባ፣... ማለቴ በአንድ የሰው ሳንባ፤ የምንተነፍስ ነበር የምንመስለው። ግን ከቀን ወደ ቀን፣ የእኔ የህይወት ሸክም እጅግ እንደከበደው ገባኝ።
እንዴት ሁል ጊዜ ንትርክ እና ብሶት እያወራሁ፣ ቀናችንን ላበላሸው?
የለየላቸው ወመኔ ወንድሞቼንና ተስፋ የቆረጠው አባቴን፣ መጦር፣ መንከባከብ፣ መልሶም ማስተዳደር ደከመኝ። በዚያም ላይ፣ የሚያሳዩኝ ንቀትና ማንቋሸሽ፣ ታከተኝ። እንዴት ልበለው?
የአለቃዬን ጆሮ የሚወጋ ድምጽና ጭቅጭቅ መስማትና ትንኮሳዎቹን ማስተናገድ ሰለቸኝ። እያንዳንዷን ጉዳይ፣ ለአለቃዬ መልሼ እንደ ልጅ ማብራራት ታከተኝ። አቅሜን የሚመጥን ስራ እና ደሞዝ ናፈቁኝ። እንዴት ልበለው? ይሔንንስ፤ በየጊዜው እንዴት ደጋግሜ ልንገረው?
ህመሜ፣ ከእኔ አልፎ፣ ለውዴ መትረፉ ግልጽ ነበር። የፊቱ የፈገግታ ብርሃን፣ የልቡን የፍቅር እሳት እንዳደበዘዘው ታወቀኝ። ፈራሁ። ፈርቼ፣ በማላውቀው ጥልቀት ፈራሁ። ከእኛ ህይወት እልፎ ተርፎ ምድርን ያበራ ፍቅራችንን እንደማጣው ገባኝ። ሸክሜ፣ ስስ ጫንቃውን ክፉኛ እንደተጫነው ታወቀኝ።
ውዴ፣ እንደ እኔ የተወሳሰበ እና ሸክሙ የበዛ ህይወት ያለው አይመስለኝም። ጤነኛ ቤተሰብ እና ጤነኛ ስራ አለው። “ጤነኛ” የሚለው ቃል እራሱ፣ አሁን እንዲያግባባን እንጂ፣ ትርጉሙ ብዙ ነው።
...ፍቅራችን፣ በነበርንበት አካሄድ፣ ይሞታል እንጂ ህይወት አይዘራም ብዬ አምኛለሁ። ያንን ማየት፣ ለእኔ የሞት ሞት ነበር። በህይወቴ የነበረኝን ብቸኛ ተስፋ ላለማጣት የነበረኝ ሌላ ብቸኛ አማራጭ፤ እኔው እራሴ ቀድሜ መልቀቅ ነበር፤ ሳልነጠቅ መስጠት።
ውዴ ግን፣ ከአኳኋኔ ገብቶታል። የአፍቃሪ ቀልብ አይስትም። ከሶስት ወር ምጥ በኋላ፤ ሶስተኛ ዓመት ሊሞላን አካባቢ፤ እውነቱን እንደምነግረው አወቅኩ። እኔ ቀኑን አልመረጥኩም፤ ቀኑ ነው የመረጠን።
አንደኛው የሕይወት ማእዘን፤ ስንበት።
ሐሙስ ነበር ቀኑ። ከሰዓት በኋላ፣ ከቢሮ ፍቃድ ጠይቄ፣ እውዴ ቤት ሄድኩ። ምኔ እንደሄደም አላውቅም። ብቻ የተወሰነ ነገሬ ሄዷል። ቤቱን በአበባ፣ በጥቃቅን ጣፋጭ ነገሮችና በፍቅር ሞልቶታል። ሦስተኛ ዓመታችንን ልናከብር መሆኑ ነው።
ውዴ እና እኔ... በብዙ ነገርም እንመሳሰላለን። እጅ ለእጅ ተቆላልፈን፣ በፍቅር ሰረገላ፣ ቸርቸር ጎዳናን ቁልቁል እየከነፍን ስንወርድ... ዙረታችን ይገርመኛል። ፒያሳን እንደ ታቦት እንዞራታለን። ክሪያሶዝ እየተሻማን እንበላል። ቶሞካ ማኪያቶ እንጠጣለን። ምንም ከማንገዛቸው ትልቅ የልብስና የወርቅ መደብሮች፣ በአይናችን እንቀላውጣለን። ከየአዟሪው ማስቲካ እንገዛለን፤ ስናኝክ እንውላለን።
ትንሽ ኪሳችን ሞላ ካለ፤ ድሃብ ምሳ እንበላና፣ ሳንቲም ከተረፈን ሲኒማ አምፒየር እንገባለን። ...ጊዜው ካልመሸ መላቀቅ ስለሚከብደን፤ የጫማችን ተረከዝ እስኪጣመም ድረስ ፒያሳ ለፒያሳ እንዞራለን። አሁን አሁን ሳስበው፣ ፒያሣ ላይ የሚያጣብቅ አንዳች አባዜ ነበረብን።
እናም ውዴ የዚያን ሀሙስ... ጠብ እርግፍ ብሎ፣ እንደ አዲስ እንግዳ አስተናገደኝ። ምን እየሆንኩ እንደነበር በቅጡ አላስታውስም። ብቻ የሆነ ሰዓት ላይ እንደምንም ብዬ....
“ማ... (ለምን ሙሉውን “ማር” ብዬ እንደማልጠራው አላውቅም)፤ አንድ ምነግርህ ነገር አለኝ” አልኩት። አይኖቹን ሙሉ ለማየት እየተሳቀቅኩ።
“እኔም የምነግርሽ ከባድ ጉዳይ አለኝ፤ ማን ይቅደም?” አለኝ፣ ፀጉሬን በለስላሳ እጆቹ እየደባበሰኝ።
ዝም አልኩ። ዝምታዬ፣ በጣም ጮክ ያለ ነበር። ብዙ ድምፁ ነበረው። ሰምቶኛል። ግብቶታል። ማመን ስላልቻለ ጠየቀኝ።
“የኔ ማር አንቺ ቅደሚ፤ ምንድንነው የምትነግሪኝ?”፤... ፍርሀትና ልመና ድምጹ ውስጥ ነበር።
“ልቤ አብዝቶ ስለሚወድህ፣ እዚህ ላይ ይብቃን። እኔ ጣጣዬ ብዙ ነው። አንተ በቻልከው ሁሉ አክመኸኛል። የማያገግም የቤተሰቦቼን ህመም አብረኸኝ ታመሃል። የስራ ቦታ ሸክሜንና ብሶቴን ተቀብለኻል። አንተንም፣ ፍቅራችንም፣ ከዚህ በላይ መግደል አልፈልግም። እዚህ ላይ ይብቃን” አልኩና...
“ኡ፣ኡ... ፍፍፍፍ”... አልኩ። እንደወለድኩ ያህል ተሰማኝ። ለእርሱ ደግሞ፣ ሲሸሸው የከረመው መራራ እውነት ነበር። በተቀመጠበት ፈዞ ቀረ። ሁለታችን፣ የተለያየ መደንዘዝ ውስጥ ገብተን ስለነበር፣ ከዚያ በኋላ የነበረውን ነገር ብዙ አላስታውስም።
* * *
ዓርብ ጠዋት እንደምንም እየተጎተትኩ ቢሮ ገባሁ። ይቅርታ አሁንም፤ እኔ ልግባ፣ ወይንም ቀፎው ሰውነቴ ይግባ፣ እርግጠኛ አይደለሁም። ብቻ ሰውነቴ፣ እንደ ድንጋይ ከብዶኝ አረፈድኩ።
ወደ አራት ሰዓት አካባቢ፣ ስልኬ ጠራ። የውዴ አከራይ ነበረች። የምትለው ነገር፣ በግልጽ አይሰማም። ለቅሶና ጮኸቷ ውስጥ ግን፣ መርዶዬ ገባኝ። በቅፅበት ዙሪያዬ ሲጨልምብኝ ትዝ ይለኛል። ከእዛ በኋላ የሆነውን አላስታውስም።
* * *
ዓርብ ከሰዓት፣ ከዚህኛው ምድር አልነበረኩም። ምናልባትም፣ አራተኛው ወይንም አምስተኛው ሰማይ ላይ ነበርኩ። ይሄ እንግዲህ፣ የእኔ ግምት ነው። እዚህ ምድር ላይ እንዳልተገናኘን አውቃለሁ። ምናልባት፣ እኔ ግማሽ መንገድ ሄጄ፤ ውዴም ግማሽ መንገድ ወርዶ፣ ሊያበረታታኝ እና አይዞሽ ሊለኝ ይሆናል የተገኛኘነው። እኔ ምን አውቃለሁ? ለሁሉም፣... ከውዴ ጋር የመጨረሻ ስንብት አደረግን።
የነበርንበት ቦታ፣ ብዙም የሚያላቅስ አልነበረም። አብረን ለረጅም ሰዓት የተቀመጥን ይመስለኛል። ምንም ምናወራው ነገር አልነበረንም። አፍም አልነበረንም። ድምጽም አልነበረንም። በዝምታችን ውስጥ ግን፣ በቃላት የማይገለጽ፣ ጥልቅ አንድነትና የሚሞቅ ፍቅር ነበር። ፈገግታው ምድርን ያሞቃል። በመለያየት ጥልቀት ውስጥ ያለን አንድነት፣ ያየው ብቻ ያውቀዋል። የመለያየት ጥጉ ጋ ስትደርሺ ብቻ ነው፣ መለያየት የሚባለው ሀሳብ የውሸት እንደሆነ የምትረጂው። ያኔ የህይወትን አንድነት እና ሙሉነት ትረጂያለሽ። የእኔ፣ የእሱ፣ የእሷ፣ የእነርሱ የሚባል ነገር እንደሌለ ይገባሻል። እርግጥ ነው፣ ይሔ የሚገባው ለጥቂት እብዶች ብቻ ነው። ከዛማ ውዴን፤ ለስራ ጉዳይ እንደሚሸኝ ፍቅረኛ ሸኘሁት። በናፍቆት እና በስስት።
* * *
ቅዳሜ ጠዋት፣ ሆስፒታል አልጋ ላይ ነቃሁ። ለመስማትም ለማልቀስም እቅም አልነበረኝም። ከጥቂት ደቂቃ ንቃትና ህመም በኋላ፣ እንደገና ወደ ጥልቅ እንቅልፍ ገባሁ።
ለምንድን ነው መልካም ሰዎች የማይበረክቱት? ለምንስ በየጓዳችንና በየአደባባዩ፣ “ኧረ ይሄን ሰው ንቀልልኝ!” የሚባሉ ጨካኝ ሰዎች፣ እንደ ማቱሳላ ዘልዛላ እድሜ የሚሰጣቸው? ምክንያቱ አልገባኝም።
ማታ ላይ ወደ ለቅሶ ቤት ሄድኩኝ። የገባኝ ቢመስለኝም ብዙ ያልገባኝ ነገር ነበር። ብዙውን አላስታውስም። ማን ምን እንዳለ አላውቅም። ስወጣ ግን፣ አከራዬ ጠጋ ብላ አቀፈችኝና እያለቀሰች፣...
“አፈር ልብላ ልጄ፤ አንድ ፍሬ ልጅ!... ምን ሰይጣን ሹክ አለብኝ?” ብላ፣ አንዲት ብጣሽ ወረቀት ሰጠችኝ፤ ...አንጀት የሚበጣጥስ ነገር የያዘች።
* * *
ውዴ፤ ህይወት፣ ለብዙዎቻችን ቀላል ጓደኛ አይደለችም። አብረን ስንሆን ግን፣ የማልችለው ነገር አልነበረም። ያንቺም የኔም፣ ትልልቅ ፈተና፣ ተራ ነበር። ፍቅራችን ያሸንፈው ነበር። ፍቅራችን ስትወስጂብኝ ግን፣ ሁሉም ነገር ይከብዳል። ካንቺ በፊት፤ ብቻዬን ኖሬዋለሁ፤ አውቀዋለሁ፤ አልችለውም።
የእኔ የህይወት ፈተና፣ ካንቺ በጣም ቢብስ እንጂ፣ አያንስም። በሸክም ላይ ሸክም ለመጨመር፣ ዝርዝር ውስጥ አልገባም። ህይወቴ፣ ጣእምና ትርጉም ያላት፣ ካንቺ ጋር ስሆን ነበር። እኔ ልጠይቅሽ የተዘጋጀሁት አብረን እንድንኖር ነበር። አንቺ ደግሞ...
ከባድ ልዩነት ነው። ግን እረዳሻለሁ። ፍቅር ይረዳል። ህይወት በብዙ መልኩ ፈትናኝ እዚህ ደርሻለሁ። አሁን ግን ይብቃኝ። ደክሞኛል። ለመሄዴ፣ ራስሽን ምክንያት ለማድረግ አትሞክሪ። ከራሴ ውጪ ማንም ተጠያቂ አይደለም። ይልቅ፣ እያንዳንዷን ቀን ኑሪባት። ሳቂባት። ጀግና እንደሆንሽ አሳያት። መኖርን፣ እንደኔ አትፍሪ። ታሸንፊዋለሽ። ማንም ደስታሽን እንዲወስድ አትፍቀጂ።...Page 4 of 530