Administrator
የ3ዲ ሕትመት እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ለቤት ፈላጊዎች ይዘውት የመጡት መፍትሔ
በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ የከተሞች መስፋፋትና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ያመጣውን የቤት አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ መንግሥት በ10 ዓመት የልማት ዕቅዱ 4.4 ሚሊዮን ቤቶችን ለመገንባት አቅዷል። ይህንን ግብ ለማሳካትም የግል ዘርፉን ማሳተፍና ነዋሪዎችን በማኅበር ማደራጀት ላይ ከሚደረጉ ድጋፎች ባሻገር፣ እንደ አሜሪካና አውስትራሊያ ያሉ የበለጸጉ ሀገራት የሚጠቀሙባቸውን ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂዎች በሀገራችን ማስተግበር ተጀምሯል።
ወደ ተግባር ከገቡት ቴክኖሎጂዎች መካከል የ3ዲ ኮንክሪት ሕትመት፣ ቀላል የዓረብ ብረት ግንባታ እና ተገጣጣሚ (የቅድመ-ፋብሪካ) ቤቶች ቀዳሚዎቹ ናቸው። እነዚህ ዘዴዎች የሲሚንቶ እና የብረት ግብዓት ወጪን እስከ 40 በመቶ የሚቀንሱ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋን የሚቋቋሙ እንዲሁም የግንባታ ጊዜን በአጭር በመቅጨት ለፈጣን የቤት አቅርቦት ምላሽ መስጠት የሚችሉ አዋጭ አማራጮች ናቸው።
በተለመደው የግንባታ ሒደት ብቻ ሊፈታ ያልቻለውን የቤት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ መንግሥት እነዚህን ጊዜ፣ ጉልበትና ወጪ ቆጣቢ ዘዴዎች በስፋት እየተጠቀመ ይገኛል። ይህ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የለውጥ ፍጥነት ተጠናክሮ ሲቀጥል፣ ለዓመታት የዘለቀው የዜጎች የመኖሪያ ቤት ጥያቄ በመጪዎቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ዘላቂ መፍትሔ ያገኛል ተብሎ ታላቅ ተስፋ ተጥሎበታል።
"አፍሪካ በአግባቡ አልተመራችም እንጂ ድሃ አይደለችም!"
ከሩሲያ የኒውክሌር ተቋም በላቀ ውጤት የተመረቀው ወጣቱ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት
"1,000 ሚሳይሎች ወደ ኢራን ተደግነዋል!"
ከ11.5 % በላይ ጭማሪ የሚጠይቁ አከራዮች የ3 ወር የኪራይ ቅጣት ይጠብቃቸዋል
ፌደራል ፖሊስ ለመቄዶኒያ የ2 ሚ. ብርና የአምቡላንስ ድጋፍ አበረከተ
ጋምቤላ ከ7 ቶን በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አስገባ
አቶ ተወልደ የፓኪስታን አየር መንገድን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲመሩ ታጩ
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 18ኛው የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ከትላንትና ወዳያ በእለተ ሰኞ ተከፍቷል
እስከ ፊታችን ሰንበት ክፍት ነው ። እኔ እና ደራሲ ባዩልኝ አያሌው አንድ መጽሐፍ እዚህ አውደ ርዕይ ላይ ለአንባቢያን እንዲደርስ አድርገናል ። ባለታሪኩ አቶ ታምራት ተመስገን ይባላል ። ከሊስትሮ እስከ የኮንስትራክሽን ድርጅት ባለቤት የሆነ ሰው ነው ። " ምስጉኑ ሰው " በሚል ርእስ ደራሲው አስጠርዞታል። መጽሐፍ በጃዕፋር ፣ በክብሩ ፣ እና በጦብያ ( መኮንን ፈንታው ) መጻሕፍት መደብሮች ታገኙታላችሁ ። ከሌላው ህይወት በማንበብ መማር ዝግጁ ለሆነ አንባቢ " ምስጉኑ ሰው " ዳጎስ ያለ ጉርሻ ነው ። ታነቡት ዘንድ እንጋብዛለን መልካም ንባብ !
