Administrator

Administrator

  ከሰሞኑ በጊኒ የተገኘውና አንድ ሰው ለሞት የዳረገው ማርበርግ የተሰኘ ኢቦላ መሰል አደገኛ ቫይረስ በስፋት በመሰራጨትና በወረርሽኝ መልክ በመከሰት ብዙዎችን ሊገድል ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩንና የአለም የጤና ድርጅት ቫይረሱን በቁጥጥር ስር ለማዋል የተጀመረውን ጥረት ለመደገፍ ወደ አገሪቱ መጓዛቸውን አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል፡፡
እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ክትባትም ሆነ ፈዋሽ መድሃኒት እንደሌለውና ከኢቦላ ቫይረስ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው የተነገረለት ማርበርግ ቫይረስ፣ ከሁለት ሳምንታት በፊት በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከስቶ ለሞት ከዳረገው ሰው ጋር ንክኪ አላቸው የተባሉ አራት ሰዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ መደረጉን ዘገባው ጠቁሟል፡፡
የመግደል አቅሙ እስከ 88 በመቶ ይደርሳል የተባለው ይህ አደገኛ ቫይረስ ከፍተኛ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ ድካምና በአይንና በጆሮ በኩል የሚፈስስ ደምን ጨምሮ የተለያዩ ምልክቶች እንዳሉት የተነገረ ሲሆን፣ በንክኪ የሚተላለፈው ቫይረሱ ከዚህ በፊትም በአንጎላ፣ ኮንጎ፣ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካና ኡጋንዳ ቢከሰትም በምዕራብ አፍሪካ አገራት ሲከሰት ግን ይህ የመጀመሪያው መሆኑንም አስታውሷል፡፡
በሌላ የጤና ዜና ደግሞ፣  እስካለፈው ረቡዕ ድረስ በመላው አፍሪካ የኮሮና ክትባት የወሰዱ ሰዎች ከ51 ሚሊዮን ማለፉንና በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥርም ከ7 ሚሊዮን በላይ መድረሱን የዘገበው ኦልአፍሪካን ኒውስ፣ የሟቾች ቁጥር ወደ 179 ሺህ ሲጠጋ ያገገሙት ቁጥር ደግሞ 6.2 ሚሊዮን መድረሱን አመልክቷል፡፡
በተያያዘ ዜናም፣ በጊኒ የኮሮና ክትባት መውሰዳቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያልያዙ ዜጎች ወደ ስራ ገበታቸው እንዳይገቡ በአገሪቱ መንግስት መከልከላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በመላ አገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች የኮሮና ክትባት መውሰዳቸውን የሚያረጋገጥ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ እስካልቻሉ ድረስ ወደስራ ቦታቸው መግባት እንደማይችሉ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ ከሰሞኑ ባወጡት መግለጫ ማሳወቃቸውን ነው ዘገባው ያመለከተው፡፡

Monday, 09 August 2021 16:25

የዘላለም ጥግ

ሁሉም ነገር ውበት አለው፤ ሁሉም ሰው ግን አያየውም።
     ኮንፉሺየስ
= ሁሉም ነገር በራሱ መንገድ ውብ ነው።
     ሬት ስቲቨንስ
= ውበት መልክ አይደለም፤ የልብ ብርሃን ነው።
     ካህሊል ጅብራን
= ብርሃን በሌለበት ውበት የለም።
     ሩቢ ሮስ ውድ
=የሴት ውበት ዋጋ የማይዋጣለት ሃብት ነው።
    ሱዬ ዳይ
= ውበትን ማፍቀር ጣዕም ነው፤ ውበትን መፍጠር ጥበብ ነው።
    ራልፍ ዋልዶ ኢመርሰን
= ውበት የደስተኛነት ተስፋ ነው።
    ኢድመንድ ቡርኬ
= ውበት፤ እንደ እውነትና ፍትህ፣ በውስጣችን ያለ ነው።
   ጆርጅ ባንክሮፍት
= ውበት በውስጣችሁ የሚሰማችሁ ስሜት ነው፤ በዓይኖቻችሁም ይንጸባረቃል፡፡ አካላዊ አይደለም።
     ሶፍያ ሎረን
= እውነተኛ ውበት፣ ለራስ መታመን ነው።
    ላቲቲያ ካስታ
= ውጭያዊ ውበት ይመስጣል፤ ውስጣዊ ውበት ግን ይማርካል፡፡
     ኬት አንጄል


Monday, 09 August 2021 16:24

የጥበብ ጥግ

እያንዳንዱ አርቲስት መጀመሪያ አማተር ነበር።
    ራልፍ ዋልዶ ኢመርሰን
 ስዕል፤ ቃላት አልባ ሥነ ግጥም ነው።
   ሆራስ
 ፊትህን በመስተዋት ውስጥ፣ ነፍስህን በጥበብ ውስጥ ታያለህ።
   ጆርጅ በርናርድ ሾው
 ውበት ዓለምን ይታደጋታል፡፡
   ፊዮዶር ዶስቶቭስኪ
 ጥበብ የባህል ድንበሮችን ሁሉ ይሻገራል።
   ቶማስ ኪንካዴ
 የጥበብ ሥራ የነፃነት ጩኸት ነው።
   ክሪስቶ
 ነፃነት በሌለበት ጥበብ የለም።
   አልበርት ካሙ
 የጥበብ ዓላማ ጊዜን ማቆም ነው።
   ቦብ ዳይላን
 መፍጠር የምንጀምረው፣ መፍራት ስናቆም ብቻ ነው።
   ጄ.ኤም.ደብሊው.ተርነር
 ሰዓሊ ዓይኑን ብቻ ሳይሆን ነፍሱንም ማሰልጠን አለበት።
   ዋሲሊ ካንዲንስኪ
 ፈጠራ ፅናትን ይጠይቃል።
   ሔነሪ ማቲሴ
 አበቦችን የምስለው እንዳይሞቱ ብዬ ነው።
   ፍሪዳ ብህሎ


Monday, 09 August 2021 16:21

የስኬት ጥግ


 ሻምፒዮን መሸነፍን ይፈራል። የተቀረው ደግሞ ማሸነፍን ይፈራል።
    ቢሊ ዣን ኪንግ
 ድል አንድ ሺ አባቶች ሲኖሩት፤ ሽንፈት ግን ወላጅ አልባ ነው።
   ጆን. ኤፍ. ኬኔዲ
 ስኬታማ ለመሆን ልብህ በሥራህ ላይ፤ ሥራህም በልብህ መሆን አለበት።
   ቶማስ ጄ.ዋትሰን
 ስኬት ስኬትን ይወልዳል።
   ሞያ ሃም
 ትምህርት ከቀሰምንበት፣ ውድቀት ስኬት ነው።
   ማልኮልም ፎርብስ
 ስኬት፤ ዘጠኝ ጊዜ ወድቆ በአስረኛው መነሳት ነው።
   ጆን ቦን ጆቪ
 ዝግጁ መሆን፣ የድሉ ግማሽ ነው፡፡
   ሚጉል ዲ ሰርቫንቴስ
 ዕድል እስኪፈጠር ድረስ አትጠብቅ፤ ዕድሉን ፍጠረው።
    success.com
 ስኬት ፈፅሞ ድንገት የሚከሰት ጉዳይ አይደለም።
   ጃክ ዶርሴይ
 ከእያንዳንዱ ስኬታማ ግለሰብ ጀርባ፣ ብዙ ስኬታማ ያልሆኑ ዓመታት አልፈዋል።
   ቦብ ብራውን
 እውነተኛ ስኬታማ ሰው ማለት፣ ራሱን የፈጠረ ነው።
   አል ጎልድስቴይን
 ከምንም ነገር በፊት ለስኬት ቁልፉ ዝግጅት ነው።
    አሌክሳንደር ግራሃም ቤል
 ስኬታማነት አቋራጭ መንገድ የለውም።
   ቦ ቤኔት

     የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ፣ የአገሪቱ መንግስት እ.ኤ.አ ከ1977 አንስቶ ሲያደርገው የነበረውን የዳቦ ዋጋ ድጎማ ለማንሳት ማሰቡን ከሰሞኑ በይፋ ማስታወቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የአገሪቱ መንግስት በየአመቱ ለዳቦ የሚያደርገውን 44.8 ቢሊዮን ፓውንድ ያህል ድጎማ ማንሳቱ በዳቦ ዋጋ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪና ተቃውሞን ያስከትላል የሚል ስጋት መፍጠሩን የጠቆመው ዘገባው፤ በአሁኑ ወቅት 60 ሚሊዮን ያህል ግብጻውያን መንግስት በሚያደርግላቸው የዋጋ ድጎማ አንድ ዳቦ በ0.05 የግብጽ ፓውንድ ሂሳብ እየገዙ እንደሚገኙና አንድ ሰው በየዕለቱ አምስት ዳቦዎችን መግዛት እንደሚፈቀድለት አክሎ ገልጧል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ማክሰኞ አንድ የምግብ ፋብሪካን ሲመርቁ ባደረጉት ንግግር፤በአገሪቱ 20 ዳቦዎች በአንድ ሲጋራ መግዣ ዋጋ እየተሸጡ መገኘታቸው እጅግ አስገራሚ መሆኑን ጠቁመው፤ከአራት አስርት አመታት በላይ የዘለቀውን የዳቦ ዋጋ ድጎማ ማንሳት እጅግ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ማስታወቃቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡
የዳቦ ዋጋ ጉዳይ በአገሪቱ ለተቃውሞ መነሾ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ ሲሆኑ ፕሬዚዳንቱ ግን #የዋጋ ጭማሪ እናደርጋለን ስንል ያን ያህል የከፋ ጭማሪ እናደርጋለን ማለታችን አይደለም; ሲሉ አበክረው ለህዝባቸው ቃል ቢገቡም፣ ግብጻውያን በዚያው ዕለት ብቻ በትዊተር ላይ ከ4 ሺህ በላይ የተቃውሞ መልዕክቶችን ማስተላለፋቸው ተጠቁሟል፡፡
በአገሪቱ ለመጨረሻ ጊዜ የዳቦ ዋጋ ጭማሪ የተደረገው ከ43 አመታት በፊት በፕሬዚዳንት አንዋር ሳዳት ዘመን እንደነበር ያመለከተው ዘገባው፤ጭማሪው በወቅቱ በአገሪቱ ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣና ተቃውሞ ቀስቅሶ እንደነበር አስታውሷል፡፡


  - አለማቀፉ የኮሮና ሟቾች ቁጥር ከሚነገረው በ1 ሚሊዮን ይበልጣል ተባለ
                     - በጤና ተቋማት ጥቃቶች ከ2700 በላይ ባለሙያዎችና ታካሚዎች ተገድለዋል


              በአፍሪካ አህጉር በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለሞት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ባለፈው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ በ89 በመቶ ያህል መጨመሩንና ለዚህም በምክንያትነት የተጠቀሰው ዴልታ የሚል ስያሜ የተሰጠውና በፍጥነት በመሰራጨትም ሆነ በገዳይነት የከፋ እንደሆነ የሚነገርለት አደገኛው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በስፋት መሰራጨቱ መሆኑን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
በአለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ የክትባት ቢሮ ሃላፊ የሰጡትን መግለጫ ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፣ ባለፈው ወር በአህጉሪቱ የተመዘገበው የቫይረሱ ሟቾች ቁጥር 24 ሺህ 987 ሲሆን ይህም ከአንድ ወር በፊት ከተመዘገበው የ89 በመቶ ብልጫ አሳይቷል፡፡ በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ሟቾች ቁጥር እስካለፈው ሳምንት በነበሩት ያለፉት አራት ተከታታይ ሳምንታት በሚገርም ሁኔታ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን በሃምሌ አጋማሽ ከፍተኛው የአህጉሪቱ የቫይረሱ ሟቾች ቁጥር 6 ሺህ 343 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
በአፍሪካ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር እስካለፈው ረቡዕ ከ6.8 ሚሊዮን ማለፉን፣ የሟቾች ቁጥር ደግሞ 173 ሺህ  መድረሱን የዘገበው ኦል አፍሪካን ኒውስ፤ እስከተጠቀሰው ዕለት ድረስ በአህጉሪቱ በድምሩ ከ48.3 ሚሊዮን በላይ ክትባቶች መሰጠታቸውን ጠቁሟል፡፡ በተያያዘ ዜና፤ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ በመላው አለም በቫይረሱ ሳቢያ ለሞት የተዳረጉት ሰዎች ቁጥር በይፋ ከሚነገረው በ1 ሚሊዮን ያህል እንደሚበልጥ ከሰሞኑ የወጣ አንድ ጥናት አመልክቷል፡፡
የእስራኤሉ ሂብሩ ዩኒቨርሲቲ በ103 የአለማችን አገራት ላይ የሰራውን ጥናት መሰረት አድርጎ ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ሪፖርት እንዳለው፣ በመላው አለም በኮሮና ሳቢያ ለሞት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 4.22 ሚሊዮን ያህል ነው ቢባልም፣ ትክክለኛው ቁጥር ግን ከተባለው ከአንድ ሚሊዮን በላይ እንደሚበልጥ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
አንዳንድ መንግስታት፣ የኮሮና ቫይረስ ሟቾችን ቁጥር ሆን ብለው ቀንሰው ስለሚያሳውቁና አንዳንዶቹ ደግሞ የሟቾችን ቁጥር በአግባቡ ለመመዝገብ ባለመቻላቸው ሳቢያ፣ አለማቀፉ የቫይረሱ ሟቾች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተቀንሶ እንደሚነገርም ዩኒቨርሲቲው ባወጣው ጥናት አመልክቷል፡፡
በሌላ በኩል፤ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለሁለት ዙር የወሰዱ ሰዎች ካልተከተቡ ሰዎች ጋር ሲነጻጸር በቫይረሱ የመያዝ ዕድላቸው በግማሽ ያህል ያነሰ እንደሆነ በብሪታኒያው ኢምፔሪያል ኮሌጅ ኦፍ ለንደን የተሰራ አንድ ጥናት ማረጋገጡን ፎርብስ መጽሄት ዘግቧል፡፡
በሌላ የጤናው መስክ ዜና ደግሞ፣ እስካለፈው የፈረንጆች አመት 2020 በነበሩት ያለፉት 3 አመታት፣ በአለም ዙሪያ በሚገኙ የጤና ተቋማት ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች፣ ከ2700 በላይ የጤና ባለሙያዎችና ታካሚዎች መገደላቸውን አንድ አለማቀፍ ሪፖርት አመልክቷል፡፡
የአለም የጤና ድርጅት ባለፈው ማክሰኞ ይፋ ባደረገው ሪፖርት እንዳለው፣ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ700 በላይ የጤና ባለሙያዎች ሲገደሉ፣ ከ2ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ለማረጋገጥ ተችሏል።


 ከዕለታት አንድ ቀን አንድ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ክንዱ ላይ ክርኑን በጣም ያመውና ለጓደኛው "..ምን ባደርግ ይሻለኛል?.."  ይልና ይጠይቀዋል፡፡
ጓደኛውም፤  "..አንድ ዋሻ ውስጥ የሚኖር አዋቂ ሰው አለ። እሱ ጋ ሄደህ ችግርህን ብታስረዳው መፍትሔ ይፈልግልሃል.." አለው፡፡
"ስንት ያስከፍለኛል?.."
"አስር ብር ብቻ፡፡.."
"ምን ምን ዓይነት ምርመራ ያደርግልኛል?." ሲል ጠየቀ ታማሚው፡፡
"የሽንት ምርመራ ብቻ ነው የሚያደርግልህ፡፡ ዋሻው በራፍ ላይ በዕቃ ሽንትህን ታስቀምጣለህ፡፡ እሱ ይደግምበታል፡፡ ይመሰጥበታል፡፡ ከዚያ መድኃኒቱን ይነግርሃል፡፡ አለቀ፡፡"
ታማሚው፣ ጓደኛው እንዳለው፣ ዋሻው ደጃፍ ላይ ሽንቱን በዕቃ ያኖርና አብሮ አስር ብር ያስቀምጣል፡፡ በሚቀጥለው ቀን ወደ ዋሻው ደጃፍ ሲሄድ አንድ ማስታወሻ ተጽፎለት ያገኛል፡፡
እንዲህ ይላል፡-
"በሜዳ ቴኒስ ጨዋታ ምክንያት ክንድህ ላይ ክርንህን ተጎድተሃል፡፡ ስለዚህ ክንድህን ለብ ያለ ውኃ ውስጥ ከተህ ታቆየዋለህ፡፡ ከባድ ዕቃ አታንሳ፡፡ በሁለት ሳምንት ውስጥ ይሻልሃል.. ታማሚው ማታ ቤቱ ገብቶ ነገሩን ሲያስበው፤ "የገዛ ጓደኛዬ ቢሆንስ ማስታወሻውን የጻፈው? ከዚያ አስር ብሬን ወስዶ አታሎኝ ቢሆንስ?.." ደጋግሞ አሰበበትና በሚቀጥለው ቀን ወደ ዋሻው ደጃፍ ይሄዳል፡፡ አሁን ግን የራሱን የሽንት ዕቃ ሳይሆን የሚስቱንና የወንድ ልጁን የሽንት ምርመራ ናሙና፣ የውሻውን ፀጉርና የቧምቧ ውሃ ደባልቆ፤ በአንድ ዕቃ ዋሻው ደጃፍ ላይ ከአስር ብር ጋር ያስቀምጣል፡፡
ከዚያም ወደ ጓደኛው ይሄድና እንደገና ወደ ዋሻው ደጃፍ ሄዶ የሽንት ናሙና በትልቅ ብልቃጥ እንዳስቀመጠ ይነግረዋል፡፡ ጓደኛውም፤
"አሁን ደግሞ ለምን አስቀመጥክ?." ብሎ ይጠይቀዋል፡፡
"ጤንነት አይሰማኝምና እንዳለፈው ጊዜ መፍትሔ እንዲሰጠኝ ፈልጌ ነው.." ይለዋል፡፡
ጓደኝዬውም፤ "ጥሩ፡፡ እንግዲያው ነገ ሄደህ የምርመራውን መልስ ካወቅህ በኋላ እናወራለን.." ብሎት ይለያያሉ፡፡
በነጋታው ታማሚው ሰው ወደ ዋሻው ደጃፍ ሲሄድ፣ እንደጠበቀው ሌላ ማስታወሻ ያገኛል፡፡ እንዲህ የሚል ጽሑፍ ይነበባል፡-
"የቧምቧህ ውሃ በጣም ወፍራምና ከባድ ነው፡፡ ስለዚህ የሚያቀጥነውና የሚያሳሳው ኬሚካል ግዛ፡፡ ውሻህ የሚያሳክክ ቅንቅን አለበት፡፡ ስለዚህ ቪታሚን ገዝተህ ስጠው፡፡
ወንድ ልጅህ የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቂ ሆኗል፡፡ ስለዚህ ከዚህ አባዜ እንዲላቀቅ ወደ ማገገሚያ ማዕከል ወስደህ ለተወሰነ ጊዜ እዚያ እንዲቆይ አድርገው፡፡ ሚስትህ አርግዛለች። ያውም መንታ ልጆች ነው ያረገዘችው፡፡ ልጆቹ ግን ያንተ አይደሉም፡፡ ስለዚህ ጠበቃ ግዛ። እንዲህ ስትጠራጠርና በራስህ ስትቀልድ የክርንህ ህመም እየባሰብህ ነው የሚሄደው፡፡"
* * *
በአጠራጣሪ ሁኔታ ውስጥ መኖርና ኮስተር ብሎ ጉዳይን አለመጨበጥ ሌላ ጉድ ያሰማል፡፡ "አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል.." እንዲሉ፡፡ በአጠራጣሪ ዓለም እየኖርን ዕቅዶች ስናወጣ፣ ዕቅዶችም አጠራጣሪ ይሆናሉ፡፡ ለዚያውም ነገን በማናውቅበት ዓለም፡፡ ውዲ አለን የተባለው ኮሜዲያን "ሰው ሲያቅድ እግዚሃር ይስቃል.." (when man plans God laughs እንዲል) ታዋቂው ሳይንቲስት አልበርት አነስታይን ደግሞ "በተጨባጭ ዓለም ውስጥ እየኖረ ..ዕውነትና ዕውቀት ላይ ፍርድ ሰጪ ዳኛ ነኝ የሚል ሰው፤ መርከቡ፤ አማልክቱ ሲስቁ ትንኮታኮታለች.." ይለናል፡፡ ማንም ፍፁም ነኝ አይበል ነው ነገሩ፡፡ በገዢና በተገዢ መካከል ያለው ግንኙነት፣ ፍፁምና ንፁህ ስምምነትና መተማመን መሆን አለበት ብሎ ግትር ማለት ቢያዳግትም፣ በመተማመን ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይገባዋል፡፡ በተለይ "እናቱ የሞተችበትም፣ እናቱ ወንዝ የወረደችበትም እኩል የሚያለቅስበት አገር." ከሆነ አለመተማመንና መጠራጠር የታከለበት እንደሆነ፣ በቡሃ ላይ ቆረቆር ይሆናል። ከዚህ ይሰውረን!
ቲ ኤስ ኢሊየት ያለንን አለመርሳት ነው። Oh my soul…be prepared for him
Who knows how to ask questions ("..ነብሴ ሆይ ተዘጋጂ አደራ አውጪኝ ከዛ ጣጣ ጥያቄ መጠየቅ የሚችል ሲመጣ..." እንደማለት ነው፡፡)
ዛሬ በሀገራችን ስለተጠያቂነት ብዙ ይነገራል፡፡ ከዚህ ተነጣጥሎ የማይታይ ግን ቸል የተባለው ጉዳይ ግን "ጠያቂውስ ማነው?.." የሚለው ነው፡፡ ታሪክ፣ ጊዜና ህዝብ ናቸው ቢባል መልሱን ይጠቀልለዋል፡፡ እንጠየቃለን ብሎ አለመስጋት፣ ማናለብኝን ያስከትላል፡፡ ማናለብኝ ደሞ ኢ-ዲሞክራሲያዊ፣ ኢ-ፍትሐዊ  ነው፡፡
ጥርጣሬ አገር ጐጂ እክል ነው፡፡ እርስ በርስ አለመተማመንና ኑሮን አለማመን ያስከትላልና፡፡ ፖለቲካዊም ኢኮኖሚያዊም መረጋጋትን ያጫጫል፡፡ የሩሲያው መሪ ጆሴፍ ስታሊን፤ የጥርጣሬ መናኸሪያ ነበር ይባላል። ሁሉንም ሰው፤ ሌባና አጭበርባሪ፤ ሁሉንም ሰው፣ ክፉና መጥፎ አድርጐ የማየት ባህሪ ነበረው፡፡ ሁሉን በመጥፎ ስለሚፈርድም ራሱን ጥሩ አድርጐ ይደመድማል፡፡ መጥፎዎቹ ሁሉ በእኔ ላይ ይነሳሉ የሚል ጥርጣሬ ይወርረዋል፡፡ ስለዚህም ብዙ ሰው ላይ ግፍ እንዲፈጽም ይገደዳል፡፡ ፀረ-ዲሞክራሲ ተግባራቱ በይፋ ታይተዋል፡፡ ሩሲያ ለሆነችው ሁሉ ትልቅ አሉታዊ አስተዋጽኦ አድርጓል፤ ከዚህም ይሰውረን፡፡
አንድ ፀሐፊ እንዳለው፤ "ዕድገት ማለት ለውጥ ማለት ነው፡፡ ለውጥ ቢያዋጣም ባያዋጣም ደፍሮ መግባትን ይጠይቃል፡፡ ይህም ማለት ከሚታወቀው በመነሳት ወደማይታወቀው ዕመር ብሎ እንደመግባት ነው.."
ለውጥ ለማምጣት አያሌ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስዋዕቶችን ይጠይቃል፡፡ ለዚህ ነው ለውጥ በተግባር እንጂ በአፍ አይገባም፤ የሚባለው፡፡ በተጨባጭ ከየት ተነስተን የት ደርሰናል? የሚል ጥያቄ መነሳት አለበት፡፡ የትምህርት ጉዳይ፣ የጤና ጉዳይ፣ የፍትህ ጉዳይ፣ የግንባታ ጉዳይ፣ የንግድና የግብር ጉዳይ፣ የሰላምና ደህንነት ጉዳይ-- የዚህ ሁሉ ድምር የኑሮ ጉዳይ፣ የት ደርሷል መባል አለበት፡፡
ጭቦ አትናገሩ ይላሉ አበው፡፡ ነገ በራሳችሁ ይደርስባችኋል ለማለት ነው፡፡
የሌለውን አለ፣ ያላደገውን አድጓል፣ የደረቀውን አልደረቀም በማለት ልንከላከለው ብንሞክር "ሆድን በጐመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል.." ነው ውጤቱ፡፡ የዕውነቱ ዕለት ማነከሳችን ይታያልና። በሀገራችን በተደጋጋሚ የምናየው ሌላው አባዜ ተቻችሎ አለመኖር ነው፡፡ አለመቻቻልን ለመሸፈን የምናደርገው ጥረትም ሌላው ተጨማሪ አባዜ ነው፡፡ እኔ ፃድቅ ነኝ ለማለት ሌላውን መኮነን የሚመጣው እዚህ ላይ ነው፡፡ ተግባብቶ ሳይጠላለፍ መኖር የሚያቅተውም ለዚህ ነው፡፡ ሔንሪ ቫን ዳይክ እንዲህ ይለናል፤ "ኤደን ገነት ዳግመኛ ብትሰጠን እንኳ በትክክል አንኖርም፣ ተስማምተን አንዝናናባትም ወይም ለዘለዓለም አንቆይባትም..
ይህ አባባል በእኛም ሳይሠራ አይቀርም፡፡ እንዲህ ኢኮኖሚያችን ቆርቁዞ፣ በጦርነት እርስ በርስ እየተቆራቆዝን ቀርቶ ..ለምለሟን..፣ ..የዳቦ ቅርጫቷን..፣ ..የአፍሪካ ኩራቷን.. ኢትዮጵያን ብናገኝ በትክክል አንኖርባትም፣ ተስማምተን አንዝናናባትም አንቻቻልባትም እንደማለት ነው፡፡
በታሪክ እንደሚነገረው፤ ታሊያርድ የተባለው የፈረንሳይ ዲፕሎማት በየስብሰባው ላይ "ቢዝነስ የምትሠሩ ሰዎች እጃችሁ ንፁህ መሆን አለበት.." ይል ነበር አሉ፡፡ ንፁህ ያልነበረው እጅ ግን የሱ የራሱ ነው፡፡ ያንን በመናገሩ ሌሎች ንፁህ እንዳልሆኑ ጥርጣሬን ይፈጥራል፡፡ አለመተማመንን ያሰፍናል፡፡ መፈራራትንና ሥጋትን ያሰለጥናል፡፡ ጥርጣሬን ይፈጥራል፡፡ እሱ  ግን ከጥርጣሬው በላይ ተረጋግቶ ይቀመጣል፡፡ በጥርጣሬ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ለፍርሃት፣ ላለመረጋጋት፣ በዕቅድ ላለመኖር፣ ለሙስና፣ ምሬትን ለማመቅ፣ በኑሮ ተስፋ ለመቁረጥ እጅግ የተጋለጡ ናቸው፡፡ ይሄን ሁኔታ የሚፈጥሩ ወገኖች ደሞ በአጋጣሚው ለመጠቀም ወደ ኋላ አይሉም፡፡ ወትሮም ሰበብ ይፈልጋሉና ባገኙት ቀዳዳ ይገለገላሉ፡፡ ሙስናቸውን ያስፋፋሉ፡፡ ያለ ገንዘብ ንቅንቅ የማይሉ ቢሮክራቶችን ይፈለፍላሉ፡፡ እየቦረበሩ ስለ ድል ያወራሉ፡፡ በአሸበረቁ ፖሊሲዎች ይምላሉ ይገዘታሉ፡፡ ብዙ ግብረ አበሮችን በመረብ ያደራጃሉ፡፡ የማይቀለበስ ደረጃ ደረስን ይላሉ ከአጋጣሚ አጋጣሚን ይወልዳሉ፡፡ እንኳንስ ነጠላ አግኝታ ዱሮም ዘዋሪ እግር አላት ይሏል እኒህ ናቸው፡፡   የአንድ  ሰፈር  ሰዎች ወደ ጦርነት ሊሄዱ ለረጅም ጊዜ በዝግጅት ላይ ከርመዋል። በዝግጅቱ ወቅትም የማይፎክሩት ፉከራ፣ የማያቅራሩት ቀረርቶ፣ የማይደነፉት ድንፋታ አልነበረም። ገና ሳይዘመት ይዘፈናል፣ አታሞ ይደለቃል፣ ዳንኪራ ይረገጣል። ዘማቾቹም ለህፃን ለአረጋውያኑ ጀግንነታቸውን እያስረዱ ከድል በኋላ ምን አይነት ሹመት እንደሚሾሙ ሳይቀር ይተነብያሉ። በተለይም አለቃቸው ጠላትን እንዴት ድባቅ እንደሚመታና የተማረኩትንም እጅ-እግራቸውን ጠፍሮ አስሮ መንደር ለመንደር እያዞረ እንደ ላንቲካ እንደሚሳያቸው፣ከዚያም እስከ አንገታቸው ድረስ ከነህይወታቸው መሬት ቀብሮ ከብት እንደሚያስነዳባቸው ዲስኩር ያደርጋል። አንድ ነገሩ ያላማራቸው አዛውንት፤
“ተው ልጆቼ፣ ሲሆን እርቁ ነበር እሚበጀን፤ እምቢ ብላችሁ ጦር ውስጥ ከገባችሁ ደግሞ ፉከራውና አስረሽ ምቺው ቢቀርባችሁ? ለእሱ ስትመለሱ ያደርሳችኋል” ቢሉ፤ ሰሚ ጆሮ አጡ።
ፉከራው ይቀጥላል። ዘፈኑ ይቀልጣል። በመካያው ለዚያ አለቃ ፈረስ ተዘጋጀለትና ሌሎቹ ጋሻ ጃግሬዎች በእግራቸው፣ እሱ በፈረስ ዘመቱ። ብዙ ጊዜ አለፈ። የጦርነቱን ወሬ ግን አየሁም ሰማሁም የሚል ወሬ-ነጋሪ ጠፋ። መንደሩ ተጨነቀ። አሸነፉም ተሸነፉም የሚል ወሬ በሀሜት መልክም እንኳ ሳይሰማ ይከርማል…
 በመጨረሻም ከሩቅ አንድ ሰው በፈረስ ሲመጣ ይታያል። አቧራው ይጨሳል። የመንደሩ ሰውም፤ “መጡ-መጡ” እያለ ለመቀበል ይወጣል።
ቀድሞ የደረሰው ያ የዘመቻው መሪ ነበር። ከፈረሱ ወርዶ ሰዉን #እንዴት ከረማችሁ;  ካለ በኋላ፣ እኒያ ተዉ ይሉ የነበሩ አዛውንት፤
 “እንደው ልጄ አገር ያስባል አትሉም እንዴ? አንድ መልዕክተኛ አጥታችሁ ነው ሳትልኩብን የቀራችሁት? ለመሆኑ ጦርነቱ እንዴት ነበር?” ብለው ይጠይቁታል።
ያም የዘመቻው መሪ፤ “አይ፤ እንደፈራነው አይደለም። እኔ በደህና በሰላም ተመልሻለሁ!!” ብሎ መለሰ።
*   *   *
አምባገነን መሪዎች ከራሳቸው በዕብሪት የተሞላ ፍላጎት ውጪ፤ እንኳን ለሚገዙት ህዝብ ለገዛ ግብረ-አበሮቻቸውም ቁብ የላቸውም። ለማንም አያዝኑም። ሰብአዊነት አልፈጠረባቸውም። ዋናው የእነሱ ደህንነት ነው።  ዋናው የእነሱ ሥልጣን ነው። ዋናው የእነሱ ሰላም ነው። ዋናው የእነሱ ቅዠት እውን መሆን ነው። ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው፡፡ ለዚያ ደግሞ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ ይደነፋሉ፡፡ ያስፈራራሉ፡፡ ህዝብ ለዘመቻ ይቀሰቅሳሉ፡፡ ጦርነት ያውጃሉ፡፡ አስገድደው ያዘምታሉ። ህዝባቸውን ያለ ርህራሄ ለሞት ይገብራሉ። የሺዎች ህይወት እየተቀጠፈና፣ የሺዎች ኑሮ እየተፈታ እነሱ ፍላጎታቸውን ማርካት እንጂ እልቂቱ ደንታቸው አይደለም።
በታሪክ የሚታወቀው የሮማ ንጉሥ ኔሮ /ሉሺየስ ዶሚቲየስ አሄኖባርበስ/ የሥልጣኑ ጣዕምና ግዛት ሲያሰክረው እናቱንም፣ ሚስቱንም፣ ጓደኞቹንም ገድሎ በገዛ ፍላጎቱ ብቻ እየተመራ ሮማ ስትቃጠል፣ እሱ ይደንስ የነበረና በመጨረሻም አመፅ በአመፅ ላይ እየተደራረበ ሲመጣበት፣ ራሱን ለመግደል የበቃ አምባገነን ንጉስ ነበር።
እንዳለመታደል ሆኖ በአህጉራችንም ሆነ በአገራችን ሥልጣንና ጥቅም ያሰከራቸው አምባገነኖችን አላጣንም፤ ከጥንት እስከ  ዛሬ።
የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመሰንዘር የጦርነቱን ክብሪት የጫረው አምባገነኑ የህውኃት ቡድን፣ ወደዚህ እኩይ ድርጊቱ የገባው #ከሁለት አሰርት ዓመታት በላይ እንደ ርስት ከያዝኩት የመንግስት ሥልጣን ለምን ተገፋሁኝ; በሚል ቁጭትና እብሪት ነው ቢባል ኩሸት አይሆንም፡፡ ድንገት ከእጁ ያመለጠውን ሥልጣን መልሶ ለማግኘትም ብቸኛው አማራጭ ነፍጥ ነው ብሎ ያሰላው ህወኃት፤ ለሦስት ዓመታት ያህል ራሱን ለጦርነት ሲያዘጋጅ ከረመ - ለትግራይ ህዝብ "ዙሪያህን ተከበሃል" የሚል በፍርሃትና በስጋት የሚቀፈድድ  ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳ በመስበክ፡፡  
የመከላከያ ሰራዊት የህግ ማስከበር ተልዕኮውን ለመወጣት ወደ ትግራይ ሲዘምት ቡድኑ ምን እንደተሰማው በእርግጠኝነት ለማወቅ ያዳግታል፡፡ ነገር ግን እንደ ማንኛውም አምባገነን፣ በመቶ ሺዎች በሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶች መስዋዕትነት ህልሙን ለማሳካት ተፈጥሞ እንደነበር በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡
ከላይ በታሪኩ እንደተጠቀሰው፣ በጦርነቱ ዋዜማ ያልተፎከረ ፉከራ፣ ያልተደነፋ ድንፋታ፣ ያልተደለቀ አታሞ አልነበረም፡፡ ጦርነት ግን ድንፋታና ፉከራ አይደለም፡፡ ህይወት ያስገብራል፡፡ እልቂትና ፍጅት ያስከትላል፡፡ ጥፋትና ውድመት ያመጣል፡፡
የመከላከያ ሰራዊቱ የመቀሌ ከተማን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተቆጣጠረ፡፡ ሂደቱ አልጋ በአልጋ ግን አልነበረም፡፡ ይሆናል ተብሎም አይጠበቅም፡፡ መስዋዕትነትን ያስከፍላል፡፡ በጦርነቱ ብዙ ሺህ የትግራይ ወጣቶች አልቀዋል፡፡ ከቡድኑ አመራሮች መካከልም አብዛኞቹ ሲገደሉ፣ ከፊሎቹ በቁጥጥር ስር ውለው ወህኒ ወርደዋል፡፡  
ከሞት የተረፉት በጣት የሚቆጠሩ የህውኃት አመራሮች መቀሌ ሲገቡ ምን አሉ? እንደ ዘመቻ መሪው፤ “አይ! እንደፈራነው አይደለም። በደህና በሰላም ተመልሰናል!” ነው ያሉት፤ ግብረ አበሮቻቸው በሙሉ ቢገደሉባቸውም፡፡ ከዚም የውሸት ድል አከሉበት፡፡ የፌደራል መንግስቱ በራሱ ጊዜ የተናጥል የተኩስ አቁም አውጆ ሠራዊቱን ከመቀሌ ቢያስወጣም፣ እነሱ ግን “አሸንፈን ነው ያስወጣናቸው” ሲሉ በዕብሪት ተሞልተው ደነፉ፡፡
ደጋግመው ያስተጋቡትን ውሸት እውነት ነው ብለው አመኑና፣ መቀሌን በተቆጣጠሩ ማግስት፣ ሌላ ዙር የጦርነት አዋጅ አወጁ፡፡ በአማራም በአፋርም በኤርትራም በኩል ጥቃት እንደሚሰነዝሩ ምለው ተገዘቱ፡፡ "ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ሲኦል መግባት ካለብንም እንገባለን" ብለው ተፈጠሙ፡፡ እንደተለመደው ብዙ ብዙ ድንፋታዎች፣ ብዙ ብዙ  ዛቻዎች ተሰሙ፡፡
ይኸኔ ነው የትግራይ ህዝብ ሰቆቃና መከራ እንደ አዲስ የጀመረው።
ወጣቶችና አዛውንት ለሌላ ዙር ጦርነት በውድም በግድም እየተመለመሉ ይዘምቱ ጀመር፡፡ ቡድኑ ዕድሜያቸው ያልደረሰ ህፃናትን ለጦርነት በመጠቀም ዓለምን ጉድ አሰኘ፡፡ በሁለት ሳምንታት ውስጥ  በአፋርና በአማራ በኩል በተደረጉ ጦርነቶች ብዙ ሺ የትግራይ ታዳጊዎችና አዛውንቶች ማለቃቸው ተሰምቷል፡፡ አሁንም ግን የህወኃት ቡድን በጦርነቱ ቀጥሎበታል፡፡ በየጦርነት አውድማው ድል እንደቀናው እየደሰኮረም ነው፡፡
በዚህ መሃል ከ1.2 ሚሊዮን በላይ የትግራይ ህዝብ ለረሃብ አደጋ መጋለጡ እየተነገረ ነው፡፡ በትግራይ ስልክ የለም፡፡ መብራት የለም፡፡ የባንክ አገልግሎት የለም፡፡ ትራንስፖርት የለም፡፡ ሥራ የለም፡፡ ደሞዝም የለም፡፡ በጀትም የለም፡፡ እንዲያም ሆኖ የህወኃት ቡድን አሁንም ድል ማድረጉን እየደሰኮረ ነው፡፡
አምባገነኖች መቼም ይሁን የትም ሽንፈትን አምነው ተቀብለው አያውቁም። አልፈው ተርፈውም ለህዝባቸውም ዋሽተውና ጦሱ ተርፎት፣ ህዝቡ ጭምር በነሱ ቅኝት እንዲዘፍን ያስገድዱታል፡፡ “ጥፋ ያለው ከተማ ነጋሪት ቢጎሰም አይሰማ” ማለት ይኸው ነው። ከዚህ ይሰውረን!

 ቢጂአይ ኢትዮጵያ፤ በጉራጌ ዞን የጋሶሬ ቀፍ 1 እና 2 ከተማን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የሚስችል ድጋፍ አደረገ፡፡
ድርጅቱ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ባለስልጣን ሆሳዕና ቅርንጫፍ ቢሮ የጋሶሬቀፍ 1 እና 2 ከተማ ነዋሪዎች ያለባቸውን የኤለክትሪክ ኃይል ችግር ለመቅረፍ የሚያስችልና ከ1500 በላይ አባውራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
በወልቂጤ ከተማ በተካሄደው በዚሁ የድጋፍ አሰጣጥ ፕሮግራም ላይ  የተገኙት የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ እንዳለ ገ/መስቀል እንደተናገሩት፤ ድርጅቱ ማህበረሰቡ በተደጋጋሚ የሚያነሳውን የኤሌክተሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር ለመፍታት የሚያስችል ድጋፍ በማድረጉና አፋጣኝ ምላሽ በመስጠቱ  መመስገን ይገባዋል ብለዋል፡፡
የወልቂጤ ከተማ ፀጥታ ቢሮ ሀላፊው አቶ ክንፈ ሀብቴ በበኩላቸው፤ ሕብረተሰቡ ችግሮቹን ለመንግስት ቢያሳውቅም መንግስት ባለበት የአቅም ውስንነት  ምክንያት፣ ጥያቄው ምላሽ ሳያገኝ ቆይቷል። ቢጂአይ ኢትዮጵያ፤ ይህንን የህብረተሰቡን ተደጋጋሚ ጥያቄ ተቀብሎ ችግሩ እንዲፈታና ማህበረሰቡ የኤሌክተሪክ ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆን በማድረጉ ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል፡፡ በዚህ ድጋፍ በርካታ እናቶችና አባቶች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ በተለይም ልጆቻችን  ራሳቸውን ከወቅቱ ቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር፣ ውጤታማ ለመሆን እንዲችሉ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የቢጂአይ ኢትዮጵያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገብረስላሴ ስፍር በዚህ የድጋፍ አሠጣጥ ፕሮግራም ላይ እንደተናገሩት፤ ድርጅቱ ፋብሪካዎቹ በሚገኙባቸው አካባቢዎች ሁሉ  የነዋሪዎቹን ህይወት ለመለወጥና ለማሻሻል የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸው የጋሶሬ  ቀፍ 1 እና 2 ከተማ ነዋሪዎችን  የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል የትራንስፎርመር መግዣና ማስተከያ 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል። ይህ ድጋፍ ድርጅቱ በተለያዩ አካባቢዎች እየተወጣ ያለው የማህበራዊ ኃላፊነት ተግባር እንዱ አካል እንደሆነም አመልክተዋል፡፡
በሆሳዕና ከተማ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ባለስልጣን ዳሬክተር አቶ ዘመነ ዳንኤል እንደተናገሩት ከወልቂጤ ከተማ በ50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የጋሶሬ ቀፍ 1 እና 2 ከተማ የመብራት ችግርን ለማስወገድ ባለስልጣን መ/ቤቱ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በመደገፍ አስፈላጊ የሆነውን ትራንስፎርመር ለመግዛትና ለማስተከል ብሎም ህብረተሰቡ የተመኘውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለማግኘት እንዲችል ቢጂአይ ኢትዮጵያ ያደረገልን የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡ የትራንስፎርመሩ ግዢና ተከላ ስራ በአፋጣኝ ተጠናቆ ህብረተሰቡን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ ቀን ከሌሊት እንሰራለን ሲሉም ቃል ገብተዋል፡፡

 ከቀን ወደ ቀን የጤናዬ ሁኔታ  በትንሽ በትንሹ መሻሻል ማሳየት ቀጠለ፡፡ ትንሽ ትንሽ ፈሳሽም መውሰዴን ቀጠልኩ፡፡ በፊት ያስከፉኝ የነበሩትን አብዛኛዎቹን የህክምና ሂደቶችን እየተቀበልኳቸውና እየለመድኳቸው መጥቻለሁ፡፡ ኮሎስ ቶሚ ባግና ካቲተር መቀየር፣ የመኝታ አቅጣጫዎችን በየሁለት ሰዓት ልዩነት መለወጥ፣ ሰውነትን በሌላ ሰው እርዳታ መታጠብ ፣ልብስን በሰው እርዳታ መቀየር፣ በዊልቸር መንቀሳቀስ፣ ከአልጋ ወደ ዊልቸተር ከዊልቸር ወደ አልጋ በሰው እርዳታ መመላለስ ወዘተ…. ማድረግና መቀበል መማር ጀምርኩ፡፡ እኔ ብቻ ሳልሆን ቤተሰቦቼና ጓደኞቼም ይህንኑም መቀበልና መማር ጀመሩ፡፡
ያለሁብት ሁኔታ የመቀበል ሂደቱ እንዲህ እንደማወራው ቀላል አይደለም፡፡ ብዙ ህመምና መተናነቅ አለው፡፡ በመጀመሪያ መጽሐፌ ላይ ከሌሎች ታሪኮች ጋር በማያያዝ ፅፌዋለሁ፡፡ ይህንን ለሚያነብ ሰው አስረግጬ መናገር ይፈልግ ግን፣ ደስተኛ መሆን የጀመርኩት ያለሁበትን ሁኔታ መቀበል ስጀምር ነው፡፡ ማንነቴን፣ እኔነቴን፣ ያለሁበትን ሁኔታ፣ የደረሰብኘኝን አደጋና ሌሎች እውነታዎችን መቀበል መጀመሬ፣ የደስታ በር  ቁልፍን በቶሎ እንዲያገኝ ረድቶኛል፡፡ መደስት መጀመሬን ደግሞ፣ የውስጡን ቁስሌን ማሻልና ማዳን አሰችሎኛል፡፡ የውስጥ ቁስሌ መዳን ደግሞ፣የውጭውን አካላዊ ቁስል ቶሎ እንዲያድን አድርጎታል፡፡ ትልልቅ የሚመስሉት ችግሮችም፣ በመቀበል ብቻ ወደ ትንንሽ ተግዳሮቶች መቀየር ጀመሩ፡፡ ድፍን ጨለማ ከመሰለው ችግር ላይ ትንንሽ ብርሀናትን ማየትን ጀመርኩ፡፡
የእኔ ደስተኛ መሆን መጀምር ነርሶቼን፣ ጓደኞቼንና ቤተሰቦቼን ደስተኛ ማድረግ ጀመረ፡፡ እኔ ማገዝ፣መርዳና አብሮኝ መሆን የበለጠ ደስታ የሚሰጣቸው ነገር ሆነ፡፡ ብዙ ጓደኞቼም እየተፈራረቁ እየገቡ ያጫውቱኝ፣ ያዋሩኝ፣ መዝሙር ይከፍቱልኝ፣ መጽሀፍ ቅዱስ ያቡልኝና ይፀልዩልኝ ጀመር። ሙሉቀን፣ መላከ፣ አሰግድ፣ በኤኔዘር፣ ስጦታው፣ ወሰን፣ ታግለህ፣ ህሊና፣ ብሩክታየት፣ አሌክስ፣ ሙና፣ ኩኩ፣ ውድድ፣ ፀጋ፣ ሉሲ፣ ናርዶስ፣ ፍፁም ሌሎችም ብዙ ጓደኞቼ እየመጡ ያጫውቱኛል፡፡
ሁኔታዎች እንደዚህ መስተካከል ሲጀምሩ፣ ሀኪሞቸና ነርሶቼ ከሆስፒታል መውጣትና በቤት ሆኜ ህክምና መከታተል ስለምችልበት ሁኔታ ሀሳብ ማምጣት ጀመሩ፡፡ ይህም በሌላ ቋንቋ “በደንብ ተሽሎኸል” ማለት ስለሆነ፣ አምላኬን አመሰገንኩት፡፡ በጣም ከምወዳትና ሲመደቡልኝ ደስተኛ ከሚያረጉኝ ነርሶች መካከል አንዷ ፅጌ እንዲህ አለችኝ፡፡
“ዳጊ አሁን በደንብ እየተሻለህ ነው። በህይወትህ  የሚያሰጉ ነገሮች በሙሉ አሁን የሉም፡፡ አንተ ከፈለክና ሁኔታዎች የሚመቻቹ ከሆነ፣በቤትህ ሆነህ ህክምናህን መከታተል ትችላለህ፡፡ እዚህ የሚደረጉልህን አብዛኞቹን ህክምናዎች በቤት ውስጥ ነርስ ተቀጥሮልህ  ወይም ቤተሰብ በኩል ሊደግልህ ይችላል፡፡ ደግሞም ብፁህ ዶ/ር ናት፤ ናቲ ነርስ ናት  እነሱ ቤት ውጥ በደንብ ቢከታተሉህ ይችላሉ፡፡ አንደኛ ብዙ ወጪ ማትረፍ ትችላለህ፡፡ ሁለተኛ እዚህ ሆስፒታል በመቆየት  ሊይዙህ የሚችሉ ኒሞኒያ የመሳሰሉ ተላላፊ በሽታዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ፣ከእነሱም ትድናለህ። ደግሞም ይሔ ሁሉ ቤተሰብና ጓደኛ ከአዋሳ እዚህ ድረስ እየተመላለሰ ከሚቸገር፣ አንተ እዛው ብትሆን የተሻለ ነው፡፡ ምናልባት ቤት መሆንን ከፈራህ ወይም ካልተመቸህም፣ሀዋሳ ላይ ጥሩ ሆስፒታል ሆነህ ክትትልህን  መቀጠል ትችላለህ። እስኪ ከቤተሰቦችህ ጋር ተነጋገሩ፡፡”  አለችኝ፡፡
እኔ በሀሳቡ ስለተስማማሁ ለቤተሰቦቼ ነገርኳቸው፡፡ በሀሳቡ ዙሪያ እንዲመካከሩበትና  የተሻለ ሀሳብ እንዲያመጡ አሳሰብኳቸው፡፡ ከጓደኞቼም ጋር በሀሳቡ ዙሪያ  በደንብ ተነጋገርንበት። ነገር ግን በሆስፒታል ለመውጣት ሲታሰብ ፊት ለፊት ያሉ ብዙ ችግሮች ነበሩ። አንደኛው ወደ ቤት ከሄድኩ በኋላ፣ የምተነፍስበት የብረት ትቦ በድንገት ቢታፈን በምን ሊፀዳ ይችላል?  ለዚህ ደግሞ የመምጠጫና የማጽጃ ማሽን (ሳክሽን ማሽን) ማግኘት የግድ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ማሽን የማይኖር ከሆነ ወደ ቤት መሄዱ ትርፉ ሞት ነው፡፡ ሁለተኛው ችግር ኦክሲጅን ነው፡፡ በእርግጥ ምንም ዓይነት  ኦክስጅን መጠቀም ካቆምኩ ወር አልፎኛል፡፡   ስለዚህ  ኦክስጅን አያስፈልገኝም፡፡ ነገር ግን ምናልባት የአየር እጥረት ቢፈጠርብኝ  መዘጋጀት ስለሚያስፈልግ፣ ስለ ኦክስጅንም ማሰብ ነበረብኝ፡፡ ከዚህም ካለፈ በቅርቤ ካሉት የህክምና ባለሙያዎች በተጨማሪ ቤት መተው የሚንከባከቡ የጤና ባለሙያዎችን መቅጠር እንችላለን፡፡ ሌሎችም ችግር ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን እያነሳሁ፣ከሆስፒታሉ ከመውጣቴ በፊት ቀድመን ለማስተካከልና ለማዘጃገት ጥረታችንን ቀጠልን፡፡
በዚህ ሁኔታ ላይ እያለሁ ነበር ያ በመጀመሪያው መፅሀፌ ላይ የጠቀስኩት ዶ/ር፤ ከእንቅልፌ ቀስቅሶ ያናገረኝ፡፡ ንግግሩ እስከ ዛሬ ድረስ ትዝ ይለኛል፡፡ “ዳጊ ስላለው ነገር ለፋዘር ነግሬያቸዋለሁ፡፡ አልነገሩህም? ከዚህ በኋላ እድናለሁ ብለህ ብዙም ተስፋ አታድርግ፡፡ እጅህ  እግርህ እንደበፊቱ መሆን አይችልም፡፡ ምናልባት በወዲያኛው ዓለም ካልሆነ እዚህ ያለኸው ሌሎች ቁስሎችን ለማከም እንጂ፣ ዋናውን የአለርጂ ችግር ለማከም አይደለም፡፡ ለእሱም በዙም ተስፋ አታድርግ፡፡” ነበር ያለኝ፡፡ በነበረኝ ተስፋ፣ ደስታና መነሳሳት ላይ ቀዝቃዛ ውሃ የሚቸለስ ንግግር ነበር፡፡
የዚያን ቀን ተረኛ ሆኖ አጠገቤ ያደረው ጓደኛዬ ታግለህ ነበር፡፡ ገና ንግግሩን ሲሳማ መላ ሰውነቱ በቁጣ ተንቀጠቀጠ፡፡ እኔ ፊት ምንም  ላለማድረግና ላለመናገር እንደምንም ራሱን ለመቆጣጠር ሲሞክር ይታየኛል፡፡ ዐይኞቹ ደም መስለው የግንባሩ ደም ስሮች ሲወጣጠሩ ይታየኛል፡፡ አንዴ እኔን አንዴ ዶክተሩን ያያል፡፡ ከንዴቱ የተነሳ ግንባሩን ማላብ ጀመረው፡፡ ዶክተሩ ግን ማስተላለፍ የፈለገውን መልዕክት ጨረሶ ወደ ውጪ መውጣ ጀመረ፡፡ ቀና በዬ ታግለህን አየሁትና
“ወንድሜ ለምንድን ነው የተበሳጨኸው? ዶክተሩ ያለውን ሰምተህ ነው? አይዞህ እኔ አልሰማሁምትም፡፡ አንተም አትስማው። ከእሱ ቃል ይልቅ እኔን ነው የማምነው እግዚአብሔር ነው፡፡ “አልኩት ረጋ ብዬ፡፡
(“ከማዕዘኑ ወዲህ” ከተሰኘው ዳግማዊ አሰፋ መጽሃፍ የተቀነጨበ)
“እሺ አልሰማውም” አለኝና ፈጠረኖ ካጠገቤ ሄደ፡፡ ዶክተሩን ተከትሎ ወደ ውጭ ሲወጣ አባቴ፣ እናቴ ወንድሜና ቤቢ በር ላይ አገኙት  እጅግ በጣም ተቆጥቶ በንዴት በግኗል፡፡ እነሱም ሁኔታን አይተው ስለደነገጡ፣ የተፈጠረውን ጠየቁት፡፡ እሱም በንዴት እንባ እየተናነቀው ዶክተሩ ያለኝን ነገር ነገራቸው፡፡ አካባቢው ተደበላለቀ፡ ሁሉም ተቆጡ፡፡ ሀኪሙን ጠርተው በቁጣ አናገሩት፡፡ የሆስፒታሉ አስተዳደር ድረስ ክስ አስገቡ፡፡ ፈፅሞ  አጠገቤ እንዳይደርስ  አመለከቱ፡፡ ከቤተሰቦቼና ከጓደኞቼ አልፎ ነርሶቼን በሀኪሙ ንግግር በጣም ተበሳጩ። አውቆም ይሁን ሳያውቅ አስቦትም ይሁን ሳያስብ በተናገረው ነገር ሁሉንም ሰው አሳዘነ፡፡ የሁሉንም ሰው ስሜት የጎዳ የሁሉንም ተስፋ አጨለመ፡፡
ነገሩ የሰመማ ሰው ሁሉ እየተፈራረቀ እየመጣ ምንም እንዳይሰማንና ተስፋ እንዳልቆርጥ አጽናናኝ፡፡ የሰይጣን ፈተና መሆኑን እየነገሩ እንደልሸነፍ መከሩኝ፡፡ በተቻላቸው መጠን ሁሉ ከጎኔ መሆናቸውን ነገሩኝ፡፡ የሁሉም ሰው ጭንቀት ገብቶኛል፡፡ በሀኪሙ ንግግር ተስፋ ቆርጬ እንዳልሸነፍ ነው፡፡ ወይም ደግሞ ካለሁበት ችግር ወደ ከፋ በስጭት፣ሀዘንና ተስፋ መቁረጥ እንዳልገባ ነው፡፡
ውስጤ ግን በተቃራኒው ነበር፡፡ እንዴት እንደሆነ ባልገባኝ ሁኔታ ምንም ዓይነት መከፋት ማዘንና ተስፋ መቁረጥ አልተሰማኝም፡፡ እንዲያውም ሀኪሙ ያንን ሲናገር እዚያው ነበር የሳኩት፡፡ የተናገረውን ንግግር በጆሮዬም ሰማሁት እንጂ አንዱም ቃል ወደ ውስጤ አላስገባሁትም፡፡ በፍፁም ልቤን ለሀዘን፣ውስጤንም ለመከፋፋት አልከፈትኩም፡፡
እንዲያውም ሀኪሙን ንግግር እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ለመሆኑ እንደ ማረጋገጫ አድርጌ ወሰድኩት። ምክንያቱም ፈተናና መከራ ሲበዛ፣ እግዚአብሔር የፈተነውን ሰው ለመርዳት ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደሚቀርብ አውቃለሁ፤ አምናለሁም፡፡ በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ከተፃፉት የተፈተኑ ለሚፈተኑ ሰዎች እግዚአብሔር ቅርብ እንደሆነ ነው። ለዚህ ብዙ ማሳያ የሚሆኑ  ታሪኮች መጥቀስ ቢቻልም፣ መጀመሪያው መፅሀፌ ላይ ስላካተትኩት ያንን እንዲያነቡበ አጋባዛለሁ።
በሁለተኛ ደረጃ የተረዳሁት ነገር ሰይጣን የሚችለውን ሰይፍ ሁሉ ወደ እኔ እየወረወረ እንደሆነ ነው፡፡ በመጀመሪያ መፅሐፌና ከዚያም በላይ ባሉት ምዕራፎች እንደገልጽኩት ከስድስት ጊዜ በላይ ለሞት ያበቁ ሁኔታዎች ተከስተውብኝ ነበር፡፡ በእግዚአብሔር እርዳታ አምልጫለሁ፡፡
ሰይጣንም በተለያየ መንገድ ሊገድለኝ የሞከረው መንገድ አልተሳካም፡፡ የአሁኑን የሀኪሙን ንግግር ደግሞ ተስፋዬንና መንፈሴን ለመግደል እንደተወረረ ሰይፍ ቆጠርኩት፡፡ ለዚህ መድሃኒቱ ደግሞ ንግግሩን ችላ ብሎ ወደ እግዚአብሔር በመጠጋትና እርዳታ መለመን ነው፡፡ እኔም አደረኩት፡፡
በሶስተኛ ደረጃ ለራሴ ፈተናው የሚበዛው ጠንካራ ስከሆንኩ እንደሆነና መሸነፍ እንደሌለብኝ ደጋሜ ነገርኩት። ምንም ቢመጣ በህይወት እስካለሁ ደረስ መጋፈጥና መታገል ብሎም ማሸነፍ እንደለብኝ ነገርኩት፡፡ አቅሙ እንዳለኝና ይልቁንም ይህን ፈተና አሸንፌ ወጥቼ ሀኪሙ ፊት በእግሬ መምጣት እንደለብኝ ራሴን አሳመንኩት።
እግዚአብሔር እስከረዳኝ፣ እኔም አስከበረታሁና እስካልተሸነፍኩ ድረስ የማይታለፍ ፈተና፣ የማይናድም ተራራ እንደሌለ ውስጤን አሳመንኩት፡፡ እንዲያውም ትግል የሚበዛበት ጠንካራ ሰው ብቻ እንደሆነ ለራሴ እየነገርኩ ውስጤን አጠነከርኩት፡፡ ከዚያም ያለቀሱ ዐይኖቿን ጠራርጋ ልታበረታተኝ የመጣቸው እናቴን እንዲህ አልኳት፡፡
“አይዟችሁ አትበሳጩ፡፡ ይሄ የሰይጣን ፈተና እንደሆነ ገብቶኛል፡፡ የሀኪሙ ንግግር ዓላማው ሁለት ነው፡፡ ከተሳካ እኔን ተስፋ ማስቆረጥና ጥንካሬዬን መግደል ነው። ውስጤ ከተሸነፈና ብርታቴ ከወደቀ ደግሞ፤ ሞትኩኝ ማለት ነው፡፡ ይህ ካልተሳካ ደግሞ፤ እናንተ ተቆጥታችሁ ሆስፒታሉን እንድትበጠብጡ ወይም ሀኪሙን እንድትደበደቡና እኔ ከሆስፒታሉ እንድባረር ነው፡፡
እንደዚያ ከሆነ ደግሞ ሌላ ሆስፒታል ለመፈለግ ላይ ታች  ስንል ሰይጣን ሌላ አደጋ ይፈጥርና ድጋሚ ሊገድለኝ ይሞክራል ማለት ነው፡፡ የዶክተሩ ንግግር ዓላማ ይሄ ነው፡፡ እኔ ምንም አልተሰማኝም። ያለውንም አልሰማሁትም። እናንተም አትበሳጩ

Page 9 of 546