Administrator

Administrator

Sunday, 07 November 2021 18:04

የዘላለም ጥግ

• በዝናብ ውስጥ መጓዝ እወዳለሁኝ፤
ምክንያቱም ማ ንም ሰ ው ሳ ለቅስ
አያየኝም፡፡
ሮዋን አትኪንሰን
• እንባ ከእግዚአብሔር የተበረከተልን
ስጦታ ነው። ቅዱስ ጠበላችን፡፡
ሲፈስ የሚፈውሰን።
ሪታ ሺያኖ
• ፀሃይ ስታዘቀዝቅ አታልቅስ፤
ምክንያቱም እንባህ ክዋክብትን
እንዳትመለከት ይጋርድሃል።
ቫዮሌታ ፓራ
• አስከፊው ዓይነት ስቃይ እንባህ
እንዳይፈስ ለማቆም ፈገግ ስትል ነው።
ሒሮ ማሺማ
• ለማልቀስ ምርጡ ሥፍራ የእናት
ክንድ ነው።
ጆዲ ፒኮልት
• እንባ መጻፍ የሚገባው ቃላት ነው።
ፓውሎ ኮልሆ
• መንግስተ ሰማያት የተሰበረ ልብን
እንባ አይዘነጋም።
ቶባ ቤታ
• ሳሙና ለሰውነታን ፣ እንባ ለነፍሳችን።
የአይሁድ አባባል
• እንባ የሚመነጨው ከአዕምሮ ሳይሆን
ከልብ ነው።
ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ
• በእንባችን ፈጽሞ ማፈር የለብንም።
ቻርለስ ዲከንስ
• እንባህን ጥረገው፤ እና ህይወት
መቀጠል እንዳለበት ለራስህ ንገረው።
• ማልቀስ ችግር የለውም፤ ሰማይም ያለቅሳልና።
• ያለ ደስታ እንባ የለም፤ ያለ እንባ ደስታ የለም።
• በየቀኑ ከትላንቱ የበለጠ ጠንክረህ ከእንቅልፍህ ተነሳ።
• ፍርሃትህን ተጋፈጠው፤ እንባህን ጥረገው።
• እንባ የተሰራው ከ1% ውሃና ከ99%
Sunday, 07 November 2021 18:02

የፖለቲካ ጥግ

 • ዘር የሚባል ነገር የለም። ፈፅሞ።
ያለው የሰው ዘር ብቻ ነው- በሳይንስም
በአንትሮፖሎጂም።
ቶኒ ሞሪሰን
• ዓይንን ላጠፋ ዓይኑን የሚለው መርህ፣
ዓለምን እውር ያደርጋታል። ማሃትማ ጋንዲ
• ዘረኛ በሆነ ህብረተሰብ ውስጥ ዘረኛ
አለመሆን ብቻ በቂ አይደለም። ፀረ-
ዘረኛ ልንሆን ይገባል።
አንጄላ ዴቪስ
• ሰላምን ከነፃነት ልትለየው አትችልም፤
ምክንያቱም ማ ንም ሰ ው ነ ፃነቱን
ካልተቀዳጀ በ ቀር ሰ ላም ሊ ያገኝ
አይችልም።
ማልኮልም ኤክስ
• ዘረኝነት በትናንሽ ጭንቅላቶች የሚፈጠር
ትልቅ ችግር ነው።
ጊል ጎንዛሌስ
• እውነተኛ ወታደር የሚዋጋው ከፊት
ለፊቱ ያለውን ስለሚጠላ ሳይሆን፤
ከኋላው ያለውን ስለሚወድ ነው።
ጂ.ኬ.ቼስቴርቶን
• አገር ጥሩ ወታደሮች ይኖሯት ዘንድ፣
ሁልጊዜ በጦርነት ላይ መሆን አለባት።
ናፖሊዮን ቦናፓርቴ
• ወታደር ነኝ፤ በታዘዝኩበት እዋጋለሁ፤
በተዋጋሁበትም አሸንፋለሁ።
ጀኔራል ጆርጅ ኤስ.ፓቶን
• ወዳጅን ይቅር ከማለት ጠላትን ይቅር
ማለት ይቀላል።
ዊሊያም
• አሜሪካ ያለ ወታደሮቿ፣ እግዚአብሔር
ያለ መላዕክቶቹ እንደ ማለት ነው።
ክላውድያ ፔምበርተን
• አንድ ሰው የሚሞትለትን ነገር ካላገኘ፣
ለመኖር ብቁ አይደለም።
ማርቲን ሉተር ኪንግ ጄ.አር
• ወታደራዊ ሃይል ውጊያን ያሸንፋል፤
መንፈሳዊ ሃይል ግን ጦርነትን ያሸንፋል፡፡
ጆርጅ ሲ. ማርሻል
• ዕድል ሁሌም ለጀግኖች ታደላለች። ቴሬንስ
• ነፃነት ፈጽሞ በነፃ አይገኝም።
ያልታወቀ ሰው

Sunday, 07 November 2021 17:42

የጥበብ ጥግ

 • ሁሉም ሰው ጭምብል እያጠለቀ
ነው። እውነተኛ ህይወት የሚገኘው
በሥነፅሁፍ ውስጥ ነው። በልብወለድ
ጭምብል ውስጥ ነው እውነቱን
መናገር የምትችለው።
ጋኦ ዚንግጂያን
ከሥነጽሁፍ የምታገኘው መልስ
በምታቀርባቸው ጥያቄዎች ይወሰናል።
ማርጋሬት አትውድ
የሥነ-ጽሁፍ ዘውድ ሥነ-ግጥም ነው።
ዊሊያም ሶመርሴት ሟም
የሥነጽሁፍ ማሽቆልቆል የአገርን
ማሽልቆል ያመለክታል፡፡
ጆሃን ዎልፍጋንግ ቮን ገተ
ቅኔ የላቀ የሥነጽሑፍ ዓይነት ነው።
አልፍሬድ ሂችኮክ
ሥነፅሁፍ ዜና ሆኖ የሚቆይ ዜና ነው።
ኢዝራ ፓውንድ
ህይወት ከሥነጽሁፍ ውጭ ገሃነም
ነው።
ቻርለስ ቡኮውስኪ
የእያንዳንዱ ሰው ትውስታ የግሉ
ሥነጽሁፍ ነው።
አልዶዩስ ሃክስሌይ
እኔ ሥነፅሁፍ ብቻ ነኝ፤ ሌላ ልሆን
ወይም ለመሆን ፈቃደኛ አይደለሁም።
ፍራንዝ ካፍካ
ቋንቋ የሰዎች ልብ መክፈቻ ቁልፍ
ነው።
አህመድ ዲዳት
ሥነፅሁፍ ሞትን ለማሸነፍ ምርጡ
መንገድ ነው።
አይላን ስታቫንስ
ሥነጽሁፍ የኖረው ዓለም በቂ
ባለመሆኑ ነው።
ፈርናንዶ ፔሶአ
ሥነፅሁፍ የኒዩክሌር ቦምብ ተቃራኒ
ነው።
አሩንድሃድ ሮይ
ሥነጽሁፍ የምናባዊ ሰዎች እውነተኛ
ህይወት ነው።
ስቴፋኖስ ሊቮስ
የሥነፅሁፍ ታሪክ የሰው ልጅ ታሪክ
ነው።
ዊልያም ሂክሊንግ ፕሬስኮት

ውድ ፕሬዚዳንት ባይደንና ምክትል
ፕሬዚዳንት ካሚላ ሃሪስ፡-
ሲድኒ ካርሎ እባላለሁ፡፡ 9 ዓመቴ
ሲሆን የምኖረው ፍሎሪዳ ነው፡፡ በምርጫው
ማሸነፋችሁን ስሰማ አልቅሻለሁ፡፡
ሁለታችሁም ድንቅ ሰዎች ናችሁ፡፡ አገራችንን
አንድ ለማድረግ ተግታችሁ እንደምትሰሩ
አውቃለሁ፡፡ በት/ቤታችን ምርጫ ላይ እኔ
ድምጼን የሰጠኹት ለእናንተ ነው፡፡ እኔም
እንደናንተ ሳድግ አገሬን መርዳት እፈልጋለሁ፡
፡ አሜሪካ ታላቅ አገር ናት፤ እናንተ ግን በእጅጉ
የተሻለች አድርጋችኋታል፡፡
ሲድኒ፤ ዕድሜ-8
ውድ ፕሬዚዳንት፡-
ለእኔ ጥሩ ፕሬዚዳንት ማለት፡-
1. ጦርነትን የሚከላከል
2. ህይወትን የሚጠብቅ ነው፡፡
እኔ ፕሬዝዳንት ብሆን ኖሮ፣ ዋይት ሃውስን
ቀይ ቀለም እቀባው ነበር፡፡
ሳሚ፤ ዕድሜ-5
ውድ ዶናልድ ትራምፕ፡-
ከጠብመንጃ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ህጎች
ለውጥ ያስፈልጋቸዋል ብዬ አስባለሁ፡፡
አሜሪካ ነፃ አገር ናት፤ነገር ግን በጠብመንጃ
አያያዝ ላ ይ ገ ደብ መ ደረግ እ ንዳለበት
አምናለሁ፡፡ እ ባክህን ሰ ዎች ከ ባድ
መሳሪያዎችን እ ንዲይዙ አ ትፍቀድላቸው፡
፡ ጠብመንጃ ለመያዝ በቂ ምክንያት ሊኖር
ይገባል ብዬ አስባለሁ፡፡ አንድ ሰው በሚኖረው
የጠብመንጃ ብዛት ላይ ገደብ መኖር ያለበት
ይመስለኛል፡፡ በሳንዲ ሁክ ከተከሰተው መማር
ይገባናል፡፡ እኔ በሆነው ነገር በጣም ነው
ያዘንኩት፡፡
ግራንት፤ ዕድሜ -9
ውድ ፕሬዚዳንት ትራምፕ፡-
ይህን ደብዳቤ የፃፍኩት አንተና ቤተሰብህ
ለሁሉም ሰዎች ፍቅርና ደግነት እንድታሳዩ
እንዲሁም የሁሉም አሜሪካዊያን ፕሬዚዳንት
እንድትሆን ለመጠየቅ ነው፡፡ እባክህ ዘራቸውና
ሃይማኖታቸው ምንም ይሁን ምንም ለሰዎች
ርህራሄና ደግነት አሳያቸው፡፡ በምርጫ
ዘመቻህ ላይ ቃል በገባኸው መሰረት የሁሉም
አሜሪካውያን ፕሬዚዳንት ትሆናለህ ብዬ
ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ማይክ፤ ዕድሜ-8
ውድ ሚስተር ኦባማ፡-
ውቅያኖሱን ንፁህ እንድታደርገውና
እንስሳት በህይወት እንዲኖሩ እፈልጋለሁ፡
፡ እባክህ ህፃናት እንስሳትን ተንከባከባቸው፡፡
እኮራብሃለሁ፡፡
ጆሲ፤ ዕድሜ-6
ውድ ፕሬዚዳንት ኦባማ፡-
በጣም ቀጫጫ ትመስላለህ፡፡ ብዙ ምግብ
መብላት አለብህ፡፡ እነዚህን ነው መብላት
ያለብህ፡-
1. ፒዛ
2. አይስክሬም
3. ሃምበርገር
4. ሆት ቸኮሌት
5. ሆትስ ዶግ
6. ፍሬንች ፍራይስ
ሰሎሞን፤ ዕድሜ-5

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ባለፉት 22 ወራት በመላው አለም ለሞት የዳረጋቸው ሰዎች ቁጥር በሳምንቱ መጀመሪያ ከ5 ሚሊዮን ማለፉን መረጃዎች ቢጠቁሙም፣ ትክክለኛው ቁጥር ግን ከተባለው እስከ ሶስት እጥፍ ሊበልጥ እንደሚችል የአለም የጤና ድርጅት ማስታወቁን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
ከ250 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ያጠቃው ቫይረሱ በመላው አለም ለሞት ከዳረጋቸው ሰዎች መካከል ብዛት ያላቸው ሰዎች የሞቱት በአሜሪካ መሆኑንና በአገሪቱ እስካለፈው ሰኞ ድረስ ከ740 ሺህ በላይ ሰዎች ለሞት መዳረጋቸውን የጠቆመው ዘገባው፤ ብራዚል በ607 ሺህ፣ ህንድ በ458 ሺህ ሟቾች በሁለተኛና በሶስተኛ ደረጃ እንደሚከተሉም አመልክቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት ኮሮና ከልብ ህመምና ከስትሮክ ቀጥሎ በአለማቀፍ ደረጃ ለበርካታ ሰዎች የሞት ምክንያት የሆነ 3ኛው ገዳይ በሽታ እንደሆነ የጠቆመው ዘገባው፤ በቫይረሱ ሳቢያ ለሞት የተዳረጉት ሰዎች ከ5 ሚሊዮን በላይ ነው ቢባልም ከመመርመር አቅም ማነስና በኮሮና መያዙ ሳይታወቅና ሳይመዘገብ በየቤቱ የሚሞተው ሰው እጅግ በርካታ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ቁጥሩ ከተባለው በእጅጉ እንደሚበልጥ መነገሩንም አመልክቷል፡፡
አብዛኞቹ ያደጉ አገራት የኮሮና ቫይረስ ክትባቶችን በስፋት በማዳረስ ብዙ ዜጎቻቸውን ለመከተብ መቻላቸውን ያመለከተው ዘገባው፤ ክትባት በስፋት መዳረሱ የሞት መጠኑን በተወሰነ መልኩ ሊቀንሰው ችሏል መባሉንም ጠቁሟል፡፡
ኮሮና ከ8.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ያጠቃባትና ከ218 ሺህ በላይ ሰዎችን ለሞት የዳረገባት አፍሪካ፣ ከመላው አለም እጅግ አነስተኛ ክትባት የተዳረሰባት አህጉር መሆኗንና ከ1.3 ቢሊዮን ህዝቧ ውስጥ መከተብ የቻለችው 5 በመቶውን ብቻ እንደሆነም ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡

 አለቃ ገብረ ሃና ከዕለታት አንድ ቀን መንገድ እሄዳለሁ ብለው ይነሳሉ፡፡
“ማዘንጊያ” ይላሉ ሚስታቸውን
“አቤት” ይላሉ ሚስት
“መንገድ ልሄድ አስቤያለሁ”
“ወዴት?”
“ወደ ቆላ ወርጄ የታመመ ጠይቄ፣ የተጣላ አስታርቄ እመለሳለሁ!”
“እንግዲያው ባዶ ሆድዎን አይሄዱም፤ ቆይ ቁርስ ደርሷል፡፡”
“ባዶ ሆዳችንን አደል የተፈጠርን?”
“ቢሆንም ወንድ ልጅ የሚገጥመው ስለማይታወቅ ባዶ ሆዱን አይወጣም”
“ሴትስ የሚገጥማት ታጣለች ብለሽ ነው? ካልሽ እንግዲህ ቶሎ አቅርቢልኝና ፀሃዩ ሳይገርር ልነሳ”
ወ/ሮ ማዘንጊያ ጉድ ጉድ ብለው ቁርስ አቀረቡና አብረው በልተው ተሰነባብተው ተለያዩ፡፡
አለቃ ቆላ ወርደው የታመመ ጠይቀው፣ የተጣሉትን ሁለት ሰዎች ሊያስታርቁ ግቢያቸው ሲደርሱ ጭራሽ ተጋግለው ቡጢ ሊቀማመሱ ግራ ቀኝ ሲሉ ያያሉ፡፡ ከሰዎቹ አንደኛው የተማረና አዋቂ የሚባል ነው፡፡
ሌላኛው ምንም ያልተማረና መሀይም ነው፡፡ መሀይሙ የተማረውን፡-
“አንተ ደንቆሮ! ዶሮ ራስ!” ይለዋል፡፡
“አፍህን ዝጋ ነግሬሃለሁ!” ይላል የተማረው
“ደንቆሮ! ደደብ! ቆርቆሮ!” ይላል መሀይሙ፡፡
“ምንም ልሁን አፍህን ካልዘጋህ ዋጋህን ታገኛለህ!” ይላል የተማረው
አለቃ፤  “ተው እንጂ፤ ተው አይሆንም!” ይላሉ ሊገላግሉ መካከል ገብተው፡፡
መሀይሙ አሁንም፤ “ደንቆሮ! አለቃ፤ ይሄኮ ደደብ ነው!” ይላል፡፡
አለቃ፤ ሁለቱንም በተለያየ አቅጣጫ ገፍተው ይለያዩዋቸዋል፡፡
ይሄኔ አንድ መንገደኛ ድንገት ይደርሳል፡፡ አለቃን ያውቃቸዋል፡፡ ወደሳቸው ቀረብ ብሎ፤
“አለቃ ምን እያደረጉ ነው?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡
አለቃም፤ “ስድብ ቦታውን ስቶብኝ፤ ቦታ ቦታው እየመለስኩ ነው!” አሉ፡፡
* * *
በሀገራችን ቦታውን የሳተ ብዙ ነገር አለ፡፡ ዲሞክራሲ ቦታውን ስቷል፡፡ ዲሞክራቱ አፉን ዘግቶ ተቀምጦ ሐሳዊ - ዲሞክራቱ ከጣራ በላይ ይጮሃል፡፡ የተማረው ፀጥ ብሎ መሀይሙ ያለ እኔ ማን አለ ይላል፡፡
“ምሁሩ ስፒከር ነገር የለው፣ መሀይሙ ባለ አምፕሊፋየር ነው፤” እንደተባለው ነው፤ ይሄ ክፉ
እርግማን ነው፡፡ የሀገራችን ፀሐፌ ተውኔትና ገጣሚ ፀጋዬ ገ/መድህን፤
“ከመርገምት ሁሉ የከፋ መርገምት
ቋንቋ ለቋንቋ መጠፋፋት!” ይለናል፡፡ ቋንቋ ለቋንቋ ከመጠፋፋት ይሰውረን፡፡ ቋንቋ ለቋንቋ ካልተደማመጥን፣ ቋንቋ ለቋንቋ ካልተግባባን ለፍትሕ አንመችም፡፡ ቋንቋ ለቋንቋ ካልተናበብን ለሃይማኖት፣ ለጐሣ፣ ለእርስ በርስ ግጭት እንዳረጋለን፡፡
ተወያይተን መፍታት የምንችላቸውን ነገሮች፣ ተጋጭተን ወይም ተዋግተን ካልፈታን ብለን ያዙኝ ልቀቁኝ እንላለን፡፡ ከዚህ እርግማን ይሰውረን፡፡ አንድን ነገር ባንድ ጥሞና መፈፀም ሲገባን፣ ሁለት ሶስት ነገር ካልፈፀምን ብለን ስንራኮት አንዱንም ሳንጨብጥ እንቀራለን፡፡
“ራስ ሴላስ መስፍነ ኢትዮጵያ” የተባለው መጽሐፍ እንዲህ ይለናል፡-
“ዐባይን ከምንጩም ከመድረሻውም በአንድ ጊዜ ለመጨለፍ አይቻልም፡፡ የእናትየው አበባ ሳይረግፍ ልጅ እንቡጥ ትታቀፋለች፡፡ አባትየው ዓለምን ለመተው ዝግጁ ሳይሆን ልጅ እውስጥ ገብቼ ልፈትፍት ይላል፡፡ በአንድ ጊዜ ደግሞ ለሁለት ትውልድ ቦታ የለም!”
አባት ታጋይ ቦታውን ለመልቀቅ ዝግጁ ሳይሆን ተተኪ ትውልድ ቦታውን ልውረስ ይላል እንደ ማለት ነው፡፡ መተካካት ቀላል የማይሆነው ለዚህ ነው፡፡ ወጉ እንጂ ግብሩ ሩቅ ነው፡፡ የ60ዎቹ ዓመታት ታጋዮች፣ በየትኛውም መልኩ ተደራጅተው ይታገሉ የነበሩት ጊዜው የፈቀደውን ያህል ብስለት ነበራቸው፡፡ ትምህርቱ፣ ዕውቀቱ፣ ቅን ልቦናው ነበራቸው፡፡
ትግላቸው ዛሬ አቁሟል? ወይም ነገም ይቀጥላል? የትላንቱ ታሪክ የት ጋ ቆሞ አዲሱ ታሪክ የት ጋ ጀመረ?
ታሪክ ተመራማሪዎች ይፈትሹት፡፡ አንድ ዕውነት ግን አለ፡፡ ያ የዱሮው አስተሳሰብ ዛሬ፤ ሁሉም
ጥላውን ያጠላባቸዋል፡፡ የትግል ልምዳቸው ያው የትላንትናው ነው፡፡
“የነቃ፣ የተደራጀ፣ የታጠቀ ኃይል ያሸንፋል!” ነው የሁሉ ነገር መፍትሔያቸው፡፡ ለዚህ ሳይሆን አይቀርም፤ ዛሬ ቋንቋ ለቋንቋ መግባባት ያቃተው፡፡ ከንግግር ከውይይት ይልቅ ጦር መነቅነቅ ይቀናናል (Not the word but the sword እንደሚሉት ነው ፈረንጆቹ፡፡) ያደግነው በህቡዕ ትግል (Clandestine Struggle) ውስጥ ነውና በሁሉም ወገን ያለን ፖለቲከኞች፤ በሰላም አገርን እናስብ ሲባል የባቢሎንን ግንብ እንደምንገነባ ሁሉ ቃል ለቃል መግባባት እርም ይሆንብናል፡፡ ፅንፍ መለየት (Polarization) ብቻ መፍትሄ ይመስለናል፡፡
ለሀገር ስንል ግማሽ መንገድ እንኳ አብረን እንሂድ መባባል ሽንፈት ይመስለናል፡፡
ገጣሚው እንዳለው፤
“ከዋሸህ ሽምጥጥ፤
ከመታህ ድርግም!”
የሚል ፅንፈኛ መርህ ብቻ ሆኗል የሚገዛን! ትላንት ያልነውን ዛሬ ለመሻር ከቶም ዐይናችንን አናሽም፡፡ ለእለት ፖለቲካ እስከበጀን ድረስ መካድና መካካድ አይገደንም። ዋሽተን ማጣፊያው ሲያጥረን “ፖለቲካ እኮ ነው!” እንላለን፡፡ የመዋሸት ሊቼንሳ አለን እንደማለት፡፡
መንግስትም፣ ፓርቲም፣ ተቃዋሚም፣ ደጋፊም ይሄ ሊቼንሳ ያለው ነው የሚመስለው፡፡ አገር ያጠፋው አገር አለማሁ ይላል፡፡ ሙሰኛው የፀረ ሙስና ህግ አውጪ ይሆናል፡፡ ግፈኛው ስለ ፍትሕ ይሰብካል፡፡
መሀይሙ የተማረውን ቀጪ ተቆጪ ይሆናል፡፡ ቦታ ቦታው ያልተመለሰ አያሌ ወንጀለኛ በናጠጠባት አገር ዕድገት ማምጣት ከባድ ፈተና ነው፡፡ መንግሥት ይዋሻል ወይ? ሙሰኛ አለ ወይ? ፓርቲ ይሰርቃል ወይ?
ተቃዋሚ በአገር ላይ ያሴራል ወይ? ወዘተ ብሎ የሚጠይቅ አይጠፋም፡፡ መልሱ፤
"አያ፤ የብሳና ዛፍ ይሸብታል ወይ?” ቢለው  “ለዛፍ ሁሉ ያስተማረው ማን ሆነና ነው” አለው፤ የሚለው ተረት ነው፡፡ ከ1 ሚሊዮን በላይ ተፈናቅለዋል
                                  
                 በአማራ ክልል በሚደረገው ጦርነት ምክንያት ከ6 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለረሃብ አደጋ መጋለጡን የአማራ ክልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ።
በህውኃት ወራሪ ሃይል ጦርነት በተሳተፈባቸውና በወረራ በተያዙ የክልሉ የረሃብ አደጋ ማንዣበቡን ነው የክልሉ አደጋ መከላከል ኮሚሽን መረጃ ያመለከተው።
በተለይም አሁንም ጦርነት እየተካሄደ ባለበት የዋግህምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዝቋላና  ጋዝጊብሳ ወረዳዎች ብቻ በምግብ፣ በመጠጥ ውሃና መድኃኒት  እጥረት፣ 13 ሰዎች መሞታቸውን የኮሚሽኑ  መረጃ ይጠቁማል።
የህውኃት ወራሪ ሃይል በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳን በያዘበት ወቅትም 90 ሰዎችና 13 ወላድ እናቶች በመድኃኒትና በሌሎች ግብአቶች እጥረት ህይወታቸው እንዳለፈ፤ ጦርነቱን በመሸሽ ከቤት ንብረቱ የሚፈናቀለው ሰው ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን፤ በዚህም በአሁኑ ወቅት የተፈናቃዮች ቁጥር ከ1 ሚሊዮን መብለጡን ነው መረጃው ያመለከተው። አብዛኛው ተፈናቃይም በተደጋጋሚ መፈናቀል ያጋጠመው መሆኑን አንዳንዶችንም እስከ 4 ጊዜ ድረስ ለመፈናቀል መገደዳቸውን ኮሚሽኑ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ አመልክቷል።
የአማራ ክልል በወረራው ምክንያት በነዋሪዎች  ላይ የተጋረጠውን አደገና በ6 ሚሊዮን ዜጎች ላይ ረሃብ ማንዣበቡን በተመለከተ በኢትዮጵያ ለአሜሪካ ኤምባሲ፣ ለዓለም ህፃናት አድን ድርጅት፣ ለዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ለአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት፣ ለተባበሩት  መንግስታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያና ለአለማቀፍ ቀይመስቀል ማህበር በተደጋጋሚ ቢያመለክትም እስካሁን ምላሽ አለማግኘቱን አስታውቋል።

 “ለኢትዮጵያውያን የቀረበው ወቅታዊ ምርጫ ነፃነት ወይም ሞት ነው”
                                     አለማየሁ አንበሴ


                ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለክብራቸው ለነፃታቸውና ለሃገራቸው አንድነት መጠበቅ የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው አሸባሪውና ሃገር አፍራሹ ህወኃት ላይ በሚወሰደው እርምጃ ግንባር ቀደም ተካፋይና የታሪክ ባለቤት እንዲሆኑ እናት ፓርቲ ጥሪ አቀረበ፡፡
እናት ፓርቲ “በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ፍላጎትን በሃይል እጭናለሁ ብሎ ማሰብ እብደትም እብሪትም ነው፤ ህዝብም በተባበረ ክንድ ይመክተዋል” በሚል ርዕስ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ፤ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ የጦር ክተት ጥሪ አቅርቧል፡፡
“ሃገራችን ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ ተፈትና ይሆናል እንጂ ወድቃ ተሸንፋ አታውቅም” ያለው የፓርቲው መግለጫ እንዲያውም በመከራው  ፅናት እንደ እንቁ አብርታና ዕልፍ ጀግኖቿን ወልዳ ለራሷም ለአለምም መኩሪያ ሆናለች፤አሁንም ሃገር ለማፍረስ የተነሱ ሃይሎችን የኢትዮጵያውያን ብርቱ ክንድ ምላሽ ይሰጣቸዋል” ብሏል፡፡
ህወኃት ከፍጥረቱ ጀምሮ ጥፋት የተጣባውና ባለፉት 27 ዓመታት በምኒሊክ ቤተ መንግስት ተቀምጦ እንደ ቅኝ ገዥ ሲኖር የነበረ መሆኑን ያመለከተው እናት ፓርቲ፤ አሁንም እኔ ያልገዛኋት ሃር ለማንም አትሆንም ትበተን በሚል ቅዠት ህዝብን ለዳግም ባርነት፣ ስደት ማኮላሸትና ግድያ ቋምጦ እየተፍጨረጨረ ይገኛል ብሏል፡፡
“ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ወቅታዊ ምርጫው ነፃነት ወይም ሞት ነው “ያለው ፓርቲ መልሱ ግን ነፃነት መሆኑ ላይ ምንም ጥርጥር የለውም፤ሆኖም ነፃነት በችሮታ አይመጣም፤ ለነፃነት በመሞት እንጂ፤ ስለሆነም መላው ኢትዮጵያውያን ፊታችን በዚህ እኩይ ቡድን ላይ እንድናዞር፣የተባበረ ክንዳችንንም እንድናሳርፍና የአባቶቻችንን የነፃነት ገድል ዳግም እንድንፅፍ ጥሪያችንን  እናቀርባለን” ብሏል  በመግለጫው፡፡
የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ሁሉ ሃገርን የመታደግ ተግባርን እንዲቀላቀሉና ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ፣ ለፌደራል መንግስቱ ባስተላለፈው ለጦርነቱ ግልፅ ግብ ከማስቀመጥ ጀምሮ ትኩረት ከሚበትኑ ጉዳዮች በመራቅና አካሄዱን  ደግሞ በእውቀት በጥበብና ተጠያቂነት ባለበት መልኩ እንዲመራ፣ መረጃዎች ለህዝብ በመደበኛነት እንዲቀርቡ፣የቀድሞ የጦር ጠበብቶች ሙያዊ እገዛ የሚያደርጉበት መንገድ እንዲመቻች የጠየቀ ሲሆን በተጨማሪም የአፋርና የአማራ ክልሎች በጀታቸውን በሙሉ ለጦርነቱ ማዋላቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ የፌደራል መንግስቱ የባጀት ሽግሽግ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንደ አንድ ልብ መካሪ ሆነው፣ ለዚህ ሀገር የማዳን ጥሪ እንዲሰለፉ ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል፡፡

ባለፈው ረቡዕ  አዲስ አበባ የገቡት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፈር ፌልትልማን ከምክትል ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን፣ ከመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይና  ከገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ጋር ተወያዩ፡፡
በሰሜን ኢትዮጵያ ለተፈጠረው ጦርነት መፍትሔ ለማፈላለግ ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የተባሉት ፌልትማን ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በተጨማሪ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ጋርም በጉዳዩ ላይ መምከራቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ አስታውቀዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ከባለስልጣናቱ ጋር በዝርዝር የተወያዩበት ጉዳይ አልተገለጸም፡፡
ፌልትማን አንደኛ ዓመቱን ያስቆጠረው የሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ  ሲሆን በሰሜኑ የአገራችን ክፍል እየተካሄደ ከሚገኘው ጦርነት ጋር በተያያዘ ሁሉም የተፋላሚው ወገኖች የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ልዩ መልዕክተኛው ከአፍሪካ ህብረትና ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር  ባካሄዱት ውይይት ጦርነት በሚቆምበት ጉዳይ ሳይመክሩ እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡
የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ ሁሉም ወገኖች ወደ ውይይት እንዲመጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡


      የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የአገርን ህልውና እና ሉዓላዊነት እንዲሁም የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን፡-
1. በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል መከላከያ ኃይልን ወይም የትኛውንም ሌላ የፀጥታ አካል በማሰማራት ሰላምና ፀጥታ እንዲያስክብሩ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል፤
2. እድሜያቸው ለወታደራዊ አገልግሎት የደረሱና የጦር መሳርያ የታጠቁ ዜጎች ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱ፣ ወታደራዊ ግዳጅ እንዲቀበሉ ወይም ይህን ማድረግ የማይችሉ ሲሆን በአማራጭ ትጥቃቸውን ለመንግሥት እንዲያስረክቡ ሊያዝ ይችላል፤
3. የሰዓት ዕላፊ ገደብ ሊወሰን ይችላል፤
4. ማናቸውም የሕዝብ የመገናኛና የሕዝብ መጓጓዣ ዘዴ እንዲዘጋ ወይም እንዲቋረጥ ሊያዝ ይችላል፤
5. ከሽብር ቡድኖች ጋር ይተባበራል ብሎ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ የተጠረጠረ ማንኛውንም ሰው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቁጥጥር ሥር ለማድረግ፣ ይህ አዋጅ ተፈጻሚ ሆኖ ባለበት ጊዜ ድረስ ይዞ ለማቆየት ወይም በመደበኛ ሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ ይችላል፤
6. ከሽብር ቡድኖች ጋር ይተባበራል ብሎ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ የተጠረጠረ ማንኛውንም ሰው ወይም ድርጅት ንብረት የሆነን ማንኛውንም ቤት፣ ህንጻ፣ ቦታ፣ መጓጓዣ ለመበርበርና እንዲሁም ማንኛውንም ሰው ለማስቆም፣ ማንነቱን ለመጠየቅ፣ ለመፈተሽ ይችላል፤ በብርበራ ወይም በፍተሻ የተያዙ የጦር መሳሪያዎችን መውረስ ይችላል፤
7. ለተወሰነ ጊዜ መንገዶችን፣ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ለመዝጋት እንዲሁም ሰዎች ለጊዜው በተወሰነ ቦታ እንዲቆዩ፣ ወደ ተወሰነ አካባቢ እንዳይገቡ ወይም ከተወሰነ ቦታ እንዲለቀቁ ለማዘዝ ይችላል፣
8. ከፍተኛ የፀጥታ ችግር እና ስጋት በተፈጠረባቸው የአገሪቱ ክፍሎች የአካባቢ አመራር መዋቅርን በከፊልም ሆነ በሙሉ፣ ማገድ፣ መለወጥና በሲቪልም ሆነ በወታደራዊ አመራር መተካት ይችላል፤
9. በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የሞራልም ሆነ የቁስ ድጋፍ ያደርጋል ብሎ የሚጠረጥረውን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት እንቅስቃሴ በሚመለከተው ባለሥልጣን በኩል እንዲታገድ ወይም ፍቃዱ እንዲሰረዝ ሊያዝ ይችላል፤
10. በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የሞራል ድጋፍ ያደርጋል ብሎ የሚያምነውን የመገናኛ ብዙኃንን ወይም ጋዜጠኛ በሚመለከተው ባለሥልጣን በኩል እንዲታገድ ወይም ፍቃዱ እንዲሰረዝ ሊያዝ ይችላል፤
የተከለከሉ ተግባራትና ግዴታዎች
1. ሁሉም ሰው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ በአዋጁ መሰረት የሚያወጣቸውን መመሪያዎችና የሚሰጣቸውን ትዕዛዞች የመቀበል ግዴታ አለበት።
2. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙን እንቅስቃሴና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አላማ የሚቃረን፣ የሚቃወምና ለሽብር ቡድኖች አላማ መሳካት አስተዋፅኦ የሚያደርግ፣ የሽብር ቡድኖችን የሚያበረታታ፣ ሰላማዊ ዜጎችን የሚያሸብር ንግግር በማንኛውም መንገድ ማድረግ ወይም ማሰራጭት የተከለከለ ነው።
3. በየትኛውም መንገድ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የገንዝብ፣ የመረጃ፣ የቁስም ሆነ የሞራል ድጋፍ ማድረግ የተከለከለ ነው።
4. አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙ በተዋረድ ውክልና ከሰጣቸው አካላት ፈቃድ ውጪ ማንኛውንም የአደባባይ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የተከለከለ ነው።
5. ከመከላከያ፣ ከፌዴራል ፖሊስ ወይም ሌሎች ፈቃድ ከሚሰጣቸው የፀጥታ አካላት ወይም ከእነዚህ አካላት እውቅና እና ፈቃድ ውጭ ማናቸውንም የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።
6. በከተሞች አካባቢ የነዋሪ መታወቂያ የመንጃ ፈቃድ፣ የሠራተኛ መታወቂያ፣ ፓስርፖርት ወይም ከእነዚህ ተመጣጣኝ የሆነ መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። [ዜጎች እነዚህን ሰነዶች የሚያገኙበት መንገድ ተመቻችቷል]
7. ማንኛውንም ወሳኝ በሆነ የአገልግሎት ዘርፍም ሆነ በምርት ሂደት ላይ የሥራ ማስተጓጎል ወይም የኢኮኖሚ አሻጥር መፈፀም የተከለከለ ነው።
8. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም ሰበብ በማድረግ የግል ጥቅም ለማግኘት ስልጣንን አላግባብ መጠቀም፣ ምክንያታዊ የሆነ ጥርጣሬ ሳይኖር ሆን ብሎ ዜጎችን ማሰር ወይም መሰል እርምጃ መውሰድ የተከለከለ ነው።
የወንጀል ተጠያቂነት
1. የዚህን አዋጅ ድንጋጌዎችና በአዋጁ መሰረት የወጡ መመሪያዎችን ተላልፎ የተገኘ ማንኛውም ሰው እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም እንደጥፋቱ ክብደት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል።
2. የዚህን አዋጅ ድንጋጌዎችና በአዋጁ መሰረት የወጡ መመሪያዎችን በመተላለፍ የተፈፀመው ወንጀል በሌሎች ሕጎች ከዚህ ከፍ ያለ ቅጣት የሚያስከትል ከሆነ የከበደው ቅጣት ተፈጻሚ ይሆናል።
3. በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት የተፈፀሙ የአዋጁና በአዋጁ ማዕቀፍ የወጡ መመሪያዎች ጥሰቶች የአዋጁ ተፈጻሚነት ጊዜ ቢያበቃም፣ የሚያስከትሉት የወንጀል ተጠያቂነት በመደበኛው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ መሰረት ይቀጥላል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም  ጀምሮ  ለስድስት ወራት የሚቆይ ነው።

Page 8 of 566