Administrator
Wednesday, 03 September 2025 18:25
ሆስፒታሉ የዓለም ጤና ድርጅትን ዕውቅና ማግኘቱን ገለጸ
"ላንድማርክ ኑሮውም ጉዞውም ከህብረተሰቡ ጋር ነው"
ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል "የአዲስ ዓመት ስጦታ" በሚል ከነሃሴ 26 ቀን ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2017 የሚዘልቅ የነጻ የጤና ምርመራ መርሃ ግብር እያካሄደ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የሆስፒታሉ አመራሮች ዛሬ ጠዋት ረፋዱ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በእነዚህ ቀናት ለ300 ያህል ሰዎች ነጻ የጤና ምርመራ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡ በዚህ መርሃ ግብርም የደም ግፊት፣ የስኳር፣ የጡት ካንሰር፣ የኤችአይቪና የአባላዘር በሽታዎች ነጻ ምርመራ የሚሰጥ ሲሆን፤ ወጪው በገንዘብ ሲሰላ ሩብ ሚሊየን ብር እንደሚደርስ አመራሮቹ ጠቁመዋል፡፡
በሌላ በኩል፤ ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል የዓለም ጤና ድርጅት "የታካሚ ደህንነትና ወገንተኝነት" መስፈርቶችን በማሟላት ዕውቅና እንደተሰጠው አመራሮቹ አስታውቀዋል፡፡
የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፕ/ር ከበደ ኦሊ በሰጡት ማብራሪያ፤ "ላንድማርክ በዓለም ጤና ድርጅት መስፈርት በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ብቸኛ ሆስፒታል ነው" ብለዋል፡፡
"ላንድማርክ ኑሮውም ጉዞውም ከህብረተሰቡ ጋር ነው" ያሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ የሆስፒታሉ የማስፋፊያ ግንባታ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ በቅርቡም ተጠናቆ አገልግሎት እንደሚጀምር ተነግሯል፡፡
ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ላለፉት 17 ዓመታት የህክምና አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ የግል ተቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 03 September 2025 18:15
ሚድሮክ በየወሩ እስከ 600 ሚ. ብር ደሞዝ ለሠራተኞቹ ይከፍላል
"ኢትየጵያን ከድህነት መንጋጋ ፈልቅቆ ማውጣት ግዴታዬ ነው"
የሼህ አል-አሙዲ ንብረት የሆነው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ከ74 ሺህ ለሚልቁ ሰራተኞቹ በየወሩ ከ500 - 600 ሚሊዮን ብር ደሞዝ እንደሚከፍል ምን ያህሎቻችን እናውቃለን?
ኢትዮጵያም የእናታቸው አደራ ሆናባቸው አል-አሙዲ በኢንቨስትመንት ለመሳተፍ በኢትዮጵያ ከተሰማሩበት ጊዜ አንስቶ በሶስት ምዕራፍ የፖለቲካ ትርጓሜ እየተሰጠባቸው ብዙ ውጣ ውረድ ገጥሟዋል፤ ሸራተን ሆቴል እስኪዘጋ ድረስ፡፡
አል - አሙዲን ከሳኡዲ ስለመጡ “ወሀቢያን ወደ ኢትዮጵያ ሊያስፋፋ ነው፤ የእስልምና አክራሪነትን ሊያመጣ ነው” በሚለው ጥርጣሬ ሸራተን ለጊዜው እንዲዘጋ ተወስኖ እና ሆቴል ሳይሆን መስጊድ ነው የሚል ወሬም ተናፍሶ ሆቴሉ ተዘግቶ ከተፈተሸ በኋላ ተረጋግጦ እንደገና ተፈቅዶ መከፈቱንስ እናውቅ ነበር?
ያኔ የኢህአዲግ መንግስትን ይቃወሙና ተችተው ይጽፉ የነበሩ እንደ እነ ጋሽ ጻውሎስ ኞኞ ያሉትን ሼሁ ጀርመን ልከው ማሳከማቸው፤ ቀጥሎም አርቲስቶቹን እነ ታማኝ በየነና ፀሀዬ ዮሀንስ ላይ ከመንግስት ሹሞች ጫና ሲበዛባቸው አላሙዲን አሜሪካ ወስደው መደገፋቸውን ተከትሎ፣ በመንግስት በኩል ጥርጣሬው መባሱን፤ በዚህ ሳያበቃም - አፍቃሬ ደርግ ተብለው እንደነበርም በሚድሮክ በጣም መረጃ ሰጪ ዶክመንተሪ ላይ ተጠቅሷል፡፡
“አፍሪካ ከልቤ ብትሆንም - ኢትዮጵያ ግን የእናቴ አደራ ናት አሉ” - ቢሊየነሩ ሼህ መሀመድ አላሙዲን፡፡
ለኢህአዲግ መንግስት ሼህ አላሙዲን በ1997 ምርጫ ድጋፍ ሁነት ላይ መገኘታቸውን ተከትሎ ብዙ ሰው ሚድሮክ የህወሀት ነው፣ የወያኔና የአዜብ መስፍን ነው እስከሚለው ድምዳሜ ድረስ የዘለቀው ነቆራ ሚድሮክን ከፖለቲካ ፓርቲ ጋር አላጥፎ በባለሀብቱና በድርጅቶቹ ላይ ከፍተኛ ፈተና ደቅኖም ማለፉን ዶክመንተሪው ከትቦታል፡፡
በሚድሮክ ዶክመንተሪ ላይ እንደ ወግ በጣም ቀልብን በሚገዛ ሁነት ማብራሪያውን የሚሰጡት አቶ ጀማል አህመድ እንዲህ ሲሉ በአጽንኦት ያነሳሉ - “አላሙዲ ለኢትዮጵያ ስላላቸው በጎ ሕልም በህዝቡ ዘንድ በቂ ግንዛቤ አልተያዘውም፤ እናም አሁንም ድረስ ፈተና ሆኖ የቀጠለው አብዛኛው የሼሁን የሀገር ወዳድነት ውስጠታቸውን አልተረዳውም”
መንግስት በደንብ ያመናቸው በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ነው ይሉና የሚድሮኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሲያብራሩ - “በዚህ ወቅት ሀገሪቱ ከባድ የፋይናንስ ማጥ ውስጥ ነበረችና አልአሙዲ የተጠየቁትን ድጋፍ ሁሉ በደስታ በማድረግ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን በቁርጠኝነት ቆመዋል”፡፡
የሚያደርጉት ድጋፍ ሼህ አላሙዲን የማህበራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት የሀገር ውለታ የዋሉ ሰዎችን መደገፍ መውደዳቸው ግን በአንዳንድ ፖለቲከኞች በበጎ ጎን አለመታየቱ ፈተና አመጣባቸው በማለት በቁጭት የሚያነሱት ስራ አስፈጻሚው አቶ ጀማል፤ ለካ ደግነትም ፈተና መሆኑን ያወቅሁት በእሳቸው ነው በማለት በአግራሞት በምልሰት ሄደው ያወሱታል፡፡
ሌላው በሚድሮክ የውስጥ ድርጅት የአስተዳደራዊ ልቅ አሰራር ችግርና ሙስና ብሎም የገንዘብ ብክነትና ስርቆትን ተከትሎ ኩባንያዎቹ የመውደቂያ ቀናቸውን የሚቆጥሩ ነበሩና ከግራ አጋቢ ሁኔታ የገባው ሚድሮክ የራሱን customized መዋቅር አበጅቶ በስሩ ያሉ 45 ድርጅቶች በ6 ዘርፎች ተጣምረው በ2012 ዓ.ም መጨረሻ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ መፈጠሩ ይነገራል፡፡
ከወሎዋ ወልዲያ ትውልዳቸውን አድርገው ደሴ ወ/ሮ ስህን ት/ቤት ተከታትለው - የስራን ልምድ ከአንድ ስዊድን ካለ ትልቅ ኩባንያ ተቀጥረው ስለቢዝነስ ተሞክሮ ጨብጠዋል፡፡ አውሮፓ ላይ ሀብት ቢያፈሩም፣ ወደ ኢትዮጵያ ግን መጥተው አያውቁም ነበር፡፡ ይሁንና አንድ ቀን ግን እናታቸው የጤና አያያዛቸው አላምር አላቸው፤ እንግሊዝ ሀገር ለህክምና ከመሄዳቸው በፊት ግን ኢትዮጵያ ውሰዱኝ አሉ፡፡
ኢትዮጵያ መጥተው መርካቶን ጭምር ጎበኙ እና “ልጄ አደራህን!” አሉ ለሼህ አላሙዲን - “አደራ ሀገርህን ኢትዮጵያን አግዝ!” የሚል አደራ ተቀበሉ - ይህ የእናቲቱ አደራ አላሙዲንን ከበዳቸው፡፡
ለምን መንግስት ብቻ - የግል ባንክ ለምን አይኖርም፣ ኢኮኖሚው እንዲያድግ መንግስት መደገፍ አለበት የሚለው ሌላ የተሳሳተ የፖለቲካ ስሌት አስነስቶባቸው - ስማቸውንም የጠለሸበት አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር - ከበጎ ምክር ይልቅ ጥርስ አስነከሰባቸው - በዚህ መዘዝ የስራቸው ቀዳሚ የነበረው የመጀመሪያውን ሼራተን ሆቴል ታሽጎባቸው ነበር፤ የተሳሳተ ስሌቱም ስማቸውን አጠለሸባቸው፡፡
እኔ የተሸለምኩት መንግስት ኢትዮጵያ ሀገርህ ናት - ናና አልማ ስባል ነው - ለነገሩ የተወለድኩባትን እናት ሀገሬን እንዴት ነው የምረሳው ብለው ነበር፤ በአንድ ሽልማት ስነ ስርአት ላይ ባደረጉት ንግግር፡፡
ለበርካታ ወገኖች ስራ እድል በመፍጠር ኢትየጵያን ከድህነት መንጋጋ ፈልቅቆ ማውጣት ቅድሚያ ግዴታዬ ነው ይላሉ ዛሬም ድረስ ሼህ አል-አሙዲን፡፡
የሻይና ቡና ተክል ልማት ላይ በመሰማራት ኢትዮጵያን በዚህ ዘርፍ በአለም ቀዳሚ ረድፍ ላይ ማሰለፍ ህልማቸው ነበር፡፡
ሁሌም በተስፋ ይስተካከላል፤ የጊዜ ጉዳይ ነው ይሉኝ ነበር በማለት አቶ ጀማል የሼሁን ጨለምተኛ አለመሆን ይገልፁና፣ አሁን ያለው ፈተና ደግሞ ሳኡዲ ውስጥ ካለ ችግር ጋር የተያያዘ እና ከዛ ሀገር እንዳይወጡ በመደረጉ ድርጅቶቻቸውን ተከታትለው እንዳይመሩ እንደሆነ በቅሬታ ያነሳሉ፡፡ ይሁንና አሉ አቶ ጀማል - “አልአሙዲን ሁሌም ይፈተናሉ፤ አላህምዱሊላሂ ሁሌም ግን ፈተናውን ያልፉታል”፡፡
መንግስት ትኩረት የሰጣቸው የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ መዋቅር (home grown economic reform pillars) ከሚባሉት ከአይቲ በስተቀር በአራቱ ስለምንሳተፍ ትኩረቱ ለእኛ ጠቃሚ ነው ባይ ናቸው ከፍተኛው አመራር፡፡
ለ22 አመታት በኪሳራ የኖረው ኤልፎራ በዶሮ ዝርያ ከምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚውን ስፍራ ስለመያዙ ተጠቅሷል፡፡ ጫጩትን ከውጭ ለምታስመጣው ኢትዮጵያ መድህን ሊሆን ጥረት ላይም ይገኛል፡፡ የሻይ ቅጠል ምርትን ከኬንያ እያስመጣች የነበረችው ኢትዮጵያ አሁን በሚድሮክ ፍላጎቷን የሚሞላ አቅርቦትና የውጭ ምንዛሪ ገቢም እየተገኘበት ነው፡፡
የአፍሪካ ቢዝነስ ሊደርሺፕ ኦርጋናይዜሽን የአመቱ ምርጥ ዋና ስራ አስፈጻሚ “CEO of the Year” በሚል ሚድሮክ የእውቅና ሽልማት እና በቅርቡም እንዲሁም የአፍሪካ መሪዎች በተገኙበት ሌላ የእውቅና ሽልማት አንስቷል፡፡
ፋብሪካዎቹ ጋ ሲኬድ - እኛ የዚህ ድርጅት ባለቤቶች ነን - የዚህ ድርጅት እድገት በእኛ ይወሰናል - የሚል አባባል አለ - ሆራይዘን ጋ የነበሩ ሰራተኞች የፈጠሩት መሪ ቃል ነው - ሌሎቹም ተጋሩትና ቀጠሉ - ጀማል አዝዞት የሆነ አይደለም፡፡
ሚድሮክ ባለፉት አስር አመታት ሰርቶ አምርቶ ካመጣው የሽያጭ ገቢ በላይ የዘንድሮ አንድ አመቱ ውጤት እጅግ ያስከነዳልም ተብሏል፡፡
በውጭ አልሚነት የተመዘገቡት ሼህ አላሙዲን ብዙ ሚሊዮን ዶላር ወደ ኢትዮጵያ ይዘው መጥተው ድርጅቶች ከፍተው አምርተው በውጭ ምንዛሪም ሸጠው ከፍተኛ ገቢም አግኝተዋል፤ ግን አንድ ዶላር ከሀገር አውጥተው አያውቁም ተብሎላቸዋል፡፡
የዚህን እውነትነት ለማረጋገጥ አሉ አቶ ጀማል በዶክመንተሪው - “የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክም ጋ ሄዶ ማረጋገጥ ይቻላል፤ ከእኛ ብር ይወስዱ ስላልነበር፤ ማበረታቻ ቲፕ የሚሰጡት እንኳ በዩሮ ነበር፡፡
(Via:- ጋዜጠኛ እሸቱ ገለቱ)
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ህብረተሰብ
Tagged under
Wednesday, 03 September 2025 18:14
የሴቶች የመሬት ባለቤትነት ሽፋን 60 በመቶ ደርሷል ተባለ
በኢትዮጵያ የሴቶች የመሬት ባለቤትነት ሽፋን 60 በመቶ መድረሱ ተገለጸ፡፡
የሴቶችን የመሬት ባለቤትነት ለማረጋገጥ ከግብርና ሚኒስቴርና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሠራ እንደሆነ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ ተናግረዋል።
ሚኒስትሯ በግብርናው ዘርፍ የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያሳድግ ፕሮግራም በአዲሱ ዓመት ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል።
በጋምቤላ ክልል ሙከራው ተጀምሮ ወደ ሌሎች ክልሎች የሚስፋፋው ይህ ሮግራም፤ የአምስት ዓመት ቆይታ ይኖረዋል፡፡
ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ 90 በመቶ የሚሆኑ የገጠር ሴቶች ከቀበሌ ጀምሮ ባሉ አደረጃጀቶች የራሳቸውን ሃብት እያፈሩ እንደሆነም ለሀገር ውስጥ ሚዲያ መግለጻቸውን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 03 September 2025 18:12
ትራምፕ የቻይናን ፕሬዚዳንት በአሜሪካ ላይ በማሴር ወነጀሉ
• ክሬምሊን የትራምፕን ውንጀላ አጣጥሎታል
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የቻይና አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ከሩሲያና ሰሜን ኮሪያ መሪዎች ጋር በጥምረት በአሜሪካ ላይ እያሴሩ ነው ሲሉ ወንጅለዋል፡፡
ትራምፕ ይህንን ያሉት ቻይና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጃፓን ላይ ድል የተቀዳጀችበትን 80ኛ ዓመት መታሰቢያ አስመልክቶ ታላቅ ወታደራዊ ትዕይንት ዛሬ ረቡዕ ማካሄዷን ተከትሎ ነው።
በዚህ ታላቅ የወታደራዊ በዓል ላይ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡንን ጨምሮ 26 መሪዎች ተገኝተዋል።
ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ለሺ ጂንፒንግ፤ "በአሜሪካ ላይ በጋራ እያሴራችሁ ላላችሁት ለቭላድሚር ፑቲንና ለኪም ጆንግ ኡን ሞቅ ያለ ሰላምታ አቅርብልኝ" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ትራምፕ አክለውም፤ አሜሪካ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ለቻይና የሰጠችውን ከፍተኛ "መስዋዕትነት" አውስተዋል።
"በርካታ አሜሪካውያን ለቻይና ድልና ክብር ሲሉ ሞተዋል። ለጀግንነታቸውና መስዋዕትነታቸው በትክክል እንደሚከበሩና እንደሚታወሱ ተስፋ አድርጋለሁ" ብለዋል፤ ባሰፈሩት መልዕክት፡፡
ክሬምሊን በበኩሉ፤ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡትን የማሴር ክስ ውድቅ አድርጎታል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያ፣ የቻይናና የሰሜን ኮሪያ መሪዎች በአሜሪካ ላይ እያሴሩ ነው በማለት የሰነዘሩትን ውንጀላ ያጣጣለው ክሬምሊን፤ በአሜሪካ ላይ የማሴርን ጉዳይ "ያሰበ እንኳ ማንም የለም” ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…


Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 03 September 2025 18:11
"ቻይና ሁሉም ሀገራት ከታሪክ እንደሚማሩ ተስፋ ታደርጋለች"
በምድር ላይ ያለ ሁሉም የሰው ልጅ በሰላም አብሮ ሊኖር ይገባል ያሉት የቻይናው ፕሬዚዳንት፤ የሰው ልጅ ወደ ቀድሞ ህይወትን የማቆየት ስርዓት መመለስ እንደሌለበት በ80ኛ ዓመት የድል በዓል አከባበር አቀባበል ላይ ተናግረዋል፡፡
ቻይና ሁሉም ሀገራት ከታሪክ እንደሚማሩ፣ ለሰላም ዋጋ እንደሚሰጡና በጥምረት ለሰው ልጆች የተሻለ መጪ ጊዜ እንደሚፈጥሩ ተስፋ ታደርጋለች ብለዋል - ሺ ጂንፒንግ፡፡
ፕሬዚዳንቱ፤ ቻይና ሁሌም ለዓለም ሰላም፣ መረጋጋትና እድገት መሪ ኃይል ትሆናለች ሲሉም ናግረዋል፡፡
ሁሉም ሀገራት ሰብዓዊ እሴቶችንና ዓለም አቀፍ ፍትህን እንዲያስከብሩም የቻይናው ፕሬዚዳንት ጥሪ ማቅረባቸውን ስፑትኒክ ጠቁሟል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 03 September 2025 18:10
ሩሲያን ለመርዳት ሁሉንም ነገር እናደርጋለን - የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት
የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት ከፑቲን ጋር በቤጂንግ ባደረጉት ውይይት፣" ሩሲያን ለመርዳት ሁሉንም ነገር እናደርጋለን፤ ይሄንንም እንደ ወንድማዊ ግዴታ እንቆጥረዋለን።" ብለዋል።
ኪም ጆንግ ኡን፣ የሩሲያና የሰሜን ኮሪያ ግንኙነት በሁሉም መልኩ እየተጠናከረ ነው ሲሉም ጨምረው ገልፀዋል።
ፑቲን በበኩላቸው፤ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በሩሲያ ኩርስክ ግዛት ከዩክሬን ጋር በተደረገው ፍልሚያ በጀግንነት ተዋግተዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ለመላው የሰሜን ኮሪያ ሕዝብ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 03 September 2025 18:09
"የሐይማኖት አባቶችን መግደል ያልተጻፈ ሕግ ኾኗል"
እናት ፓርቲ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሐይማኖት አባቶችን መግደል ያልተጻፈ ሕግ ኾኗል ሲል አዲስ ባወጣው መግለጫ ከሷል።
ፓርቲው፣ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን፣ ሮቤ ወረዳ፣ የመሰራንጄ ኦዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የ78 ዓመቱ መምሬ ንጉሤ ወልደ መድኅን በታጣቂዎች በግፍ መገደላቸውን ሰሞኑን ገልጿል።
በተለይ የአርሲ ዞን የደም መሬት ኾኗል ያለው ፓርቲው፣ የሐይማኖት አባቶች ግድያ ወደመለመድ ደረጃ ደርሷል ብሏል።
ዕሁድ'ለትም በቦሌ ክፍለ ከተማ የጎጆ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የድጓ መምህር አፈወርቅ አበባው በጥይት መገደላቸውን ፓርቲው ጠቅሷል።
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎትም ይህንኑ ግድያ ማረጋገጡን ዋዜማ በዘገባዋ አመልክታለች፡፡
Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 03 September 2025 18:07
"በኢትዮጵያ የከተማ ልማት ፕሮግራም ከ1 ሚ. በላይ የስራ ዕድሎች ተፈጥረዋል"
በኢትዮጵያ የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (UIIDP) እ.ኤ.አ ከ2018 እስከ 2024 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ1.15 ሚሊዮን በላይ የስራ ዕድሎችን መፍጠሩን የዓለም ባንክ አስታወቀ።
ከእነዚህ ውስጥ 915 ሺ የሚሆኑት የጊዜያዊ፣ 237 ሺ የሚሆኑት ደግሞ ቋሚ የስራ መደቦች ናቸው ብሏል።
ባንኩ አዲስ ባወጣው ሪፖርት፤ የኢትዮጵያ የከተማ ነዋሪ ቁጥር እ. ኤ. አ በ2012 ከነበረው 15 ሚሊዮን ወደ 42 ሚሊዮን ሊጠጋ እንደሚችል ገልፆ፤ ይህም በመሰረተ ልማት፣ በአገልግሎት አቅርቦትና በስራ ዕድል ላይ ተግዳሮት ሊፈጥር እንደሚችል አመልክቷል።
የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም፤ የተቋማትን አቅም ለማጠናከርና በመሰረተ ልማት አማካኝነት የስራ ዕድል ለመፍጠር በሀገሪቱ ባሉ 117 ከተሞች ተግባራዊ ተደርጓል ተብሏል።
እንደ ዓለም ባንክ ሪፖርት፣ ፕሮግራሙ የከተማ አስተዳደሮች ተቋማዊ ግንባታ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። በዚህም ምክንያት፣ ጠንካራ የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓቶችን በመዘርጋት፣ የአስተዳደር ሂደቶችን በማሻሻልና በጊዜው ኦዲት በማድረግ፣ ከተሞች በራሳቸው እድገት ላይ ቁጥጥር እንዲኖራቸው አስችሏል ማለቱን የዘገበው አዲስ ስታንዳርድ ነው፡፡


Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 03 September 2025 18:06
በአዲሱ የትምህርት ዘመን የመምህራን ዝውውር በኦንላይን ይፋ ይደርጋል
ከመምህራን ዝውውር ጋር ያለውን አሠራር ግልጽነት ለማስፈን የመምህራንን ዝውውርን በኦንላይን ይፋ እንደሚገረግ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ከዚህ ቀደም መምህራን ከቦታ ቦታ ዝውውር ሲያደርጉ አሠራሩ ግልጸኝነት የጎደለው ነው።
በአዲሱ የትምህርት ዘመን ግን የኦንላይን ዝውውር አሠራርን በመፍጠር ግልፅ የሆነ ምክንያት በመጥቀስ እና የግምገማ ውጤት በማስቀመጥ ይከናወናል ብለዋል።
በሲስተሙ መሠረት ዝውውሩ ሲደረግም መምህራን በሞባይል ስልካቸው በግልፅ የሚመለከቱት አሠራር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
መምህራንም ዝውውሩን በስልካቸው አማካኝነት በኦንላይን እንዲከታተሉ ሀላፊው ጠቁሟል።
Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 03 September 2025 18:04
ጳጉሜን 2 ምሽት ላይ ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ ይከሰታል፡- ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር)
በቢሊዮኖች ይታያል ተብሎ የሚጠበቀው ታላቅ ክስተት ጳጉሜን 2 ቀን 2017 ዓ.ም እሁድ ምሽት ላይ ይከሰታል፤ በዚህም ጨረቃ ደም መስላ ትታያለች ሲሉ የሥነ ፈለክ ተመራማሪው ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
በመላው ኢትዮጵያ ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀው የጨረቃ ግርዶሹ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት፣ በእስያ እና በአውስትራሊያ እንደሚታይም ነው በተለይ ለኢቢሲ ዶት ስትሪም የተናገሩት።
Published in
ዜና
Tagged under

