Administrator

Administrator

የአገራችንን ሰሜናዊ ክፍል ውስብስብ የጂኦ-ፖለቲካዊ ተለዋዋጭነት፣ የማንነት ጥያቄዎችን እና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ደህንነት በምሁራዊ መንገድ የሚተነትነው አዲሱ መጽሐፍ ይመረቃል።

በደራሲ ዶ/ር ቹቹ አለባቸዉ አበበ የተጻፈው "የተከዜ ፖለቲካ፡ ኃይል፣ ማንነትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት" የተሰኘው መጽሐፍ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ በክብር ተጋብዘዋል።

መጽሐፉ ወቅታዊ የሆኑ የድንበር፣ የዜግነት እና የብሔር ፖለቲካ መገለጫዎችን በማንሳት፣ ለሀገር ሉዓላዊነት እና ለሰላም ግንባታ ሂደት የሚረዱ ወሳኝ የፖለቲካ እና የስትራቴጂካዊ ደህንነት ትንታኔዎችን ያቀርባል።

???? የምረቃ ፕሮግራሙ ዝርዝር፦

ቀን፦ ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም.
ቦታ፦ 4 ኪሎ፣ ኢክላስ ሕንጻ (ዋሊያ መጽሐፍት)
ሰዓት፦ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ
በዕለቱ በታዋቂ ምሁራን የሚደረግ የመጽሐፍ ዳሰሳና ጥልቅ የፓናል ውይይት ይኖራል!
???? በአዳራሹ ያለው ቦታ ውስን ስለሆነ አሁኑኑ ይመዝገቡ!
ለምረቃው ስነ-ስርዓት ቦታዎን ቀድመው ለመያዝ እና ለመመዝገብ ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ፦
???? https://readersget.com/event/untitled
ዕውቀት ለለውጥ!
ዶ/ር ቹቹ አለባቸዉ አበበ

የኬንያ ፕሬዝዳንት ይፋዊ የኢንተርኔት ድረ-ገጽ ቅዳሜ ዕለት በሳይበር ጠላፊዎች ጥቃት ደርሶበታል። ጠላፊዎቹ የድረ-ገጹን ዋና ገጽ በመቀየር የራሳቸውን መልዕክት የለጠፉ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅት 41 ሚሊዮን የኬንያ ሺሊንግ (5 ቢትኮይን ገደማ) የቤተ-ክህነት (የካሳ) ክፍያ ጠይቀዋል።

ጠላፊዎቹ የተሰጠው የጊዜ ገደብ ከመጠናቀቁ በፊት የጠየቁት ገንዘብ ካልተከፈላቸው፥ ስማቸው ያልተጠቀሱ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ይፋ እንደሚያደርጉ አስፈራርተዋል። የኬንያ ባለስልጣናት ስለ ጥቃቱ መረጃው እንዳላቸው ያረጋገጡ ሲሆን፥ የፕሬዝዳንት ቤተ-መንግስት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን ድረ-ገጹን ወደ ነበረበት ለመመለስና ስለ ሁኔታው ምርመራ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ይህ የሳይበር ጥቃት በ2025 ዓ.ም በርካታ የሀገሪቱን የመንግስት ድረ-ገጾች ኢላማ ካደረጉ ተመሳሳይ ጥቃቶች በኋላ የተከሰተ በመሆኑ፥ በኬንያ የመንግስት ዲጂታል መሠረተ-ልማት ደህንነት ላይ ያለውን ስጋት ዳግም እንዲቀሰቀስ አድርጎታል።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

"አፈሳ ይቁም፤ ሰላም ይስፈን" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ፣ በትግራይ ክልል ተወላጆች አማካኝነት የህወሓትን ህገ-ወጥ አፈና እና የጦርነት ቅስቀሳ በፅኑ ኮንኗል። የሰልፉ ተሳታፊዎች እንደገለጹት፣ የክልሉ እናቶች ካለፈው የሰሜኑ ጦርነት ጠባሳ ሳይፈወሱና ሁለት እና ሶስት ልጅ ያልቀበረች እናት በሌለችበት ሁኔታ፣ ድጋሚ ልጆቻቸውን ለጦርነት መገበር የለባቸውም።

ቡድኑ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በመጣስ ወጣቶችን ያለፍላጎታቸው እያፈሰ ወደ ጦርነት እያጋዘ መሆኑንና ከአፈሳ ለማምለጥ የሞከሩትም የጥይት ሲሳይ እየሆኑ መሆናቸውን ሰልፈኞቹ አጋልጠዋል።

ትግራይ በአሁኑ ወቅት የሚያስፈልጋት ጥይት ሳይሆን ልማትና ሰላም መሆኑን ያሰመሩበት ሰልፈኞቹ፣ ይህ የህዝብ ሰቆቃ በአስቸኳይ እንዲያበቃ ጠይቀዋል። ይህ የተደገሰው የጥፋትና የሞት ድግስ ዳግም እንዳይከሰት የትግራይ ተወላጆች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተባበረ ክንድ ሊታገሉትና በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

fmc-

በአሶሳ ከተማ ያደገው የ19 ዓመቱ ታምረኛ ወጣት ኃይሌ አዳነ፣ እጅግ አስቸጋሪ የሚባሉ 11 የአሜሪካ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎችን የነፃ ትምህርት ዕድል ውድድር በአስደናቂ ሁኔታ ማሸነፍ ችሏል። ኃይሌ ገና ከጅምሩ በራሱ ተነሳሽነት በኢንተርኔት የዌብሳይት ማበልጸግ (Web Development) የተማረ ሲሆን፣ የክረምት ወቅቶችን በመጠቀም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት (በአሜሪካና ዚምባቡዌ) የተሰጡ የኮዲንግ እና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ስልጠናዎችን በተግባር ቀስሟል።

ይህን ያገኘውን ዕውቀት በመጠቀምም፣ የአየር ንብረት ድርቅን በ95% ትክክለኛነት አስቀድሞ መተንበይ የሚችል የAI ሞዴል የፈጠረ ሲሆን፣ በተጨማሪም ከ20 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያገለገለ የሚገኘውን ethioexam.et የተሰኘ የፈተና ዝግጅት መተግበሪያ ማበልጸግ ችሏል። ይህ ድንቅ ብቃቱ በጠቅላላው የ4.1 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው የነፃ ትምህርት ዕድል ያስገኘለት ሲሆን፣ እንደ ፕሪንስተን እና ፔንስልቬንያ ያሉ ትልልቅ ተቋማት ቢፈልጉትም እርሱ ግን የመጨረሻ ምርጫውን በቴክኖሎጂ ዘርፍ የዓለማችን ቁጥር አንዱ በሆነው MIT ላይ አድርጓል።

በመጪው ሐምሌ ወር ወደ አሜሪካ በማቅናት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ከፍተኛ ትምህርቱን የሚጀምረው ኃይሌ አዳነ፣ በቁርጠኝነትና በትጋት ለሚሰሩ የኢትዮጵያ ወጣቶች በማንኛውም የዓለም አቀፍ መድረክ ላይ መወዳደርና ማሸነፍ እንደሚቻል ትልቅ ማረጋገጫና የሀገር ኩራት ሆኗል።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ማህበረሰብ ትምህርት ቤት (AAU-MCS) በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ1ኛ-7ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል። ምዝገባው ከሐምሌ 14 እስከ ሐምሌ 21 /2018 ዓ.ም በ5 ኪሎ የቴክኖሎጂና ቢዩልት ኢንቫይሮንመንት ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር E04 የሚከናወን ሲሆን፣ የመመዝገቢያ ክፍያው 1,000 ብር ነው።

ትምህርት ቤቱ ራሱ 5 ኪሎ በሚገኘው በቀድሞው ድህረ ምረቃ/ፋርማሲ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ ለልጆችዎ ምቹና ተደራሽ የትምህርት አካባቢን ያረጋግጣል።

ለመመዝገብ ሲመጡ የተመዝጋቢውን የልደት ካርድ፣ የቀድሞ ትምህርት ቤት ሰርተፊኬት፣ 2 የወላጅ እና 4 የልጅ ፎቶግራፍ፣ የመመዝገቢያ ክላሰር እና የክፍያ ደረሰኝ ይዘው መቅረብ ይኖርብዎታል።

በተጨማሪም ወላጆች ከሚሰሩበት የሰው ሀብት (HR) ቢሮ ህጋዊ አሳዳጊ መሆናቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው። ትምህርት ቤቱ ቅድሚያ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ልጆች ዕድል የሚሰጥ ቢሆንም፣ ባለው ክፍት ቦታ መሠረት ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ውጭ ላሉ ተማሪዎችም በውድድር ተደራሽ የሚሆን መሆኑን ተገልጧል።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

ነገረ መጻሕፍት!
ተጋባዥ እንግዳ:- ሲሳይ ንጉሡ
የተመረጠው መጽሐፍ:- ሣልሳዊ ልደት
አዘጋጅና አቅራቢ:- እንዳለጌታ ከበደ
አሰናጅ:- ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ
የዝግጅት ቦታ:- FSS. አዳራሽ
በዝግጅቶቻችን ላይ በአካል በመገኘት መሳተፍ ለምትፈልጉ አድራሻችን:- ቀበና፣ ካቶሊክ፣ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን አቅራቢያ፣ ወደ ሳንፎርድ ትምህርት ቤት በሚወስደው መንገድ፣ ባማ አዲስ ሕንፃ አጠገብ፣ FSS አዳራሽ ሲሆን፣ የመገኛ ቦታው Google Map link:-
ለበለጠ መረጃ:- 0976066720
0900651010
በአክሱም ከተማ በቅርቡ በመኖሪያ ቤታቸው ላይ የተኩስ ጥቃት (የግድያ ሙከራ) የተፈጸመባቸው አቡነ ናትናኤል እና አቡነ አረጋዊ፣ በአሁኑ ወቅት ከመኖሪያ ቤታቸው መውጣትም ሆነ መግባት ተከልክለው በቁም እስር ላይ እንደሚገኙ የቅርብ ሰዎቻቸውን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።
ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅዳሜ ዕለት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው በከባድ ወንጀል መጠርጠራቸው ተገልጾ ለእያንዳንዳቸው 300 ሺህ ብር ዋስትና ከተጠየቀ በኋላ ቢለቀቁም፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ግን ስልኮቻቸው እንዳይሰሩ ተደርጎ ከማንኛውም ሰው ጋር እንዳይገናኙ ተከልክለዋል።
የመንበረ ሰላማ ካሳቴ ብርሃን ላዕላይ ቤተ ክህነት በአባቶቹ ላይ የተፈጸመውን የተኩስ ጥቃት "የግድያ ሙከራ" ሲል የገለጸው ሲሆን፣ የአክሱም ፖሊስ በበኩሉ ከክስተቱ ጋር በተያያዘ ሦስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። ይሁን እንጂ ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ከክልሉ ባለሥልጣናት ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ሳይሳካ የቀረ ሲሆን፣ የቀረቡትን ክሶችም ከተለያዩ ገለልተኛ ምንጮች ማረጋገጥ እንዳልቻለ አክሎ ገልጿል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
በሸገር ሬድዮ "ማንን ምን እንጠይቅልዎ?" ፕሮግራም ላይ የቀረበውና በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 2 የተፈጸመው አሳዛኝ ክስተት፣ ከቀላል የአጥር ማጠር ጉዳይ ባለፈ የዜጎችን መሠረታዊ መብትና የሥልጣን ወሰንን ጥያቄ ውስጥ የሚጥል እጅግ አሳሳቢ ድርጊት ነው።
ጉዳዩ ቀደም ሲል በወረዳው አመራር ይሁንታ ተሰጥቶት የፈረሰ፣ በኋላም ይቅርታ ተጠይቆበትና በባለቤቱ ኪሳራ በድጋሚ እንዲታጠር የተደረገ ቢሆንም፣ የደንብ ማስከበርና የጸጥታ አካላት በድጋሚ የፈጸሙት ነገር ህገ-ወጥነት የነገሠበት ሆኗል።
አጥሩ በድጋሚ የፈረሰው ዓርብ ቀን ከምሽቱ በ4:00 ሰዓት፣ በበርካታ መኪኖች በመታጀብ ፖሊሶች መሣሪያ ይዘው መጥተው፣ ከቤት ውስጥ ሰው አፍነው ወስደው፣ መኪና ውስጥ አስገብተው በዱላ ደብድበው መሆኑ ነው። በዚያ ላይ ጎረቤት ሲወጣ ተመለስ እያሉ እያስፈራሩ ይመልሱ ነበር ተብሏል።
ይህ ድርጊት ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት በኋላ ወደ ግል ይዞታ መግባትን የሚከለክለውን የሕግ አሠራር በግልጽ የጣሰ ከመሆኑም በላይ፣ ጥፋት እንኳ ቢኖር በጠራራ ፀሐይ ሕግን ተከትሎ መሥራት ሲቻል በምሽት ተደብቆ መምጣት ምን ዓይነት አሠራር እንደሆነ አጥብቆ ያጠያይቃል።
የክፍለ-ከተማውና የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች ለጉዳዩ ፈጣን ምላሽ ከመስጠት በመሸሽ ዝምታን መምረጣቸው፣ የአመራሩን ተጠያቂነትና የሕግ የበላይነትን ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል። እንዲህ ዓይነቱ አምባገነናዊና ኢ-ሰብአዊ የኃይል እርምጃ በከተማችን ላይ ስጋት የሚደቅንና በገጠር የሚሰሙት የጸጥታ መደፍረሶች በሕጋዊ አካላት ስም ወደ ዋና ከተማዋ እንዳይገቡ "ሳይቃጠል በቅጠል" ልንከላከለው የሚገባ አደገኛ ምልክት ነው።
በመሆኑም፣ ይህ በዜጎች ሰላም፣ መብትና ንብረት ላይ የተፈጸመው በደል "ነግ በኔ" የሚያሰኝ በመሆኑ በጥቃቅን ስህተቶች ሰበብ የሕዝብን እምነት የሚያጠፉና የቤተሰብን ፀጥታ ያወኩ አካላት ላይ አፋጣኝ የስነ-ስርዓትና የሕግ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል።
አዲስ አበባ ነዋሪዎቿ በሰላምና ያለስጋት የሚኖሩባት ከተማ እንድትሆን፣ በፖሊስና በጸጥታ አካላት በኩል የተጀመሩ መልካም እንቅስቃሴዎች በእንዲህ ዓይነት ድርጊቶች መበላሸት የለባቸውም። በመጨረሻም፣ ይህንን እጅግ አሳሳቢ የመብት ጥሰትና የአሠራር ጉድለት አውጥቶ ለሕዝብ ድምፅ ለሆነው ለጋዜጠኛ ግርማ ፍስሐና ለሸገር ሬድዮ የላቀ ምስጋና ይገባቸዋል።
Get Toughe Zer ·
ከዝግጅት ክፍሉ፡- ጽሁፉ ከኦሪጂናሉ በመጠኑ አጥሮና ኤዲት ተደርጎ የቀረበ ነው፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
በሊንክድኢን (LinkedIn) ማኅበራዊ ገጽ ላይ ዕውቀትን በማጋራት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠርና በፈጠራ ሥራዎቻቸው የላቀ አሻራ እያሳረፉ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ዕውቅና የሚሰጠው የመጀመሪያው “ሊንክድኢን ቼንጅሜከርስ አዋርድስ ኢትዮጵያ” በመጪው ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ በድምቀት ይካሄዳል።
በጉሩጂ ኤር ኢትዮጵያ መሥራች በአብስራ መካሻ አነሳሽነት የተመሠረተውና ከዥማ ሚዲያና ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር የሚዘጋጀው ይህ መድረክ፤ በሕዝብ ጥቆማ፣ በድምፅ አሰጣጥና በባለሙያዎች ጥብቅ ምዘና ውስጥ ያለፉ ምርጥ ባለሙያዎችን፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችንና የኢንዱስትሪ መሪዎችን በአንድነት ያገናኛል።
ይህ ታላቅ የሽልማት መድረክ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በጤና፣ በሥራ ፈጠራና በሌሎች ዘርፎች የተሰማሩ የኢትዮጵያ ባለሙያዎች በዲጂታል ዓለም የሚያበረክቱት አስተዋፅዖ በአገር አቀፍ ደረጃ ዕውቅና እንዲያገኝ ለማድረግ ያለመ ነው። ፕሮግራሙ ጠቃሚ ይዘቶችን የሚያጋሩና ወጣቶችን የሚያማክሩ እውነተኛ የለውጥ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን የሚያበረታታ ሲሆን፣ በአገሪቱ እየተገነባ ላለው የዲጂታል ሽግግር ስትራቴጂም ትልቅ ግብዓትና ለሌሎችም አርአያ እንደሚሆን ይጠበቃል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
በቡና ማቀነባበር ዘርፍ ታዋቂ የሆነው የቻይናው ሁዪቺዋን ዩንግዩ ኩባንያ በኢትዮጵያ የተቀናጀ የቡና ኢንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት ፍላጎት እንዳለው በመግለጽ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ እስካሁን በአብዛኛው ያለ እሴት ማሻሻያ (ጥሬውን) ወደ ውጭ የምትልከውን የቡና ምርት በቴክኖሎጂ በመደገፍና ጥራቱን በመጨመር፣ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝና በዓለም ገበያ ይበልጥ ተወዳዳሪ እንድትሆን ትልቅ በር ይከፍታል።
ከ2019 ጀምሮ በቻይና ሄናን ግዛት የኢትዮጵያን ቡና ለቻይና ገበያ ሲያቀርብ የቆየው ይህ ኩባንያ፣ አሁን ላይ በቀጥታ በኢትዮጵያ ኢንቨስት በማድረግ ተሳትፎውን ለማሳደግ መዘጋጀቱን ገልጿል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንም ለፕሮጀክቱ ስኬታማነት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ ማረጋገጡ ተዘግቧል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Page 8 of 818