Administrator
የልማት ተነሺ ነዋሪዎች ሐሳብ ከራሳቸው አንደበት በዐጭር በዐጭሩ እነሆ።
የልማት ተነሺ ነዋሪዎች ሐሳብ ከራሳቸው አንደበት በዐጭር በዐጭሩ እነሆ።
እኔ በጣም ነው ደስ ያለኝ። በነበርንበት ሰፈር በየግቢው ሀያ ሠላሳ ቤተሰብ ሆነን ነበር የምንኖረው። የቤተሰብ ብዛት ሲታሰብ፤ በአንድ ግቢ ውስጥ መቶ ሁለት መቶ ሰው ይሆናል። አዲስ መኖሪያ ቤት፣ ሁሉም ቤተሰብ የየራሱ መታጠቢያ መጸዳጃ ቤት፣ የየራሱ ማድ-ቤት ሲያገኝ ደስ ይላል።
ዛሬ ደግሞ አይቼ የማላውቀውን አከባበር አይቻለሁ። በ65 ዓመት ዕድሜዬ፣ ከንቲባ በዐይኔ አይቼ አላውቅም። እዚህ መጥተው ሲያበረታቱን፣ ለጥያቄዎችም ጥሩ ምላሽ ሲሰጡን… በጣም ደስ ብሎኛ። በጣም ረክቻለሁ።
=======================
ክብርት ከንቲባ ቤት-ለእንቦሳ ሊሉን መጥተዋል። ባዶ እጃቸውን አልመጡም። ቡና አፍልተን የምንጠጣው ይዘውልን መጥተዋል። ለምግባችንም ሰርተን የምንመገበውን ስጦታ አበርክተውልናል።
====================
ከንቲባዋም እዚህ መጥተው ጠይቀውናል። እንዴት እንዴት እየሆናችሁ ነው ብለው ለመጠየቅና በአካል ለማየት ብለው ነው የመጡት። የሥራ ጊዜያቸውን አብቃቅተው እኛን ለመጠየቅ ስለመጡ ደስ ብሎናል። በጣም እናመሰግናለን።
========================
በጣም ደስ የሚል ሰፈር ነው የገባነው። አየሩ ራሱ ይመቻል። በተለይ ለእኛ ለሽማግሌዎች ጥሩ አየር ማግኘታችን ጥሩ ነው። አየሩ በጣም ተስማምቶኛል። መንገድ ነበር ችግሩ። አስፋልት አይደለም።
መንገዱን ቶሎ እንሠራዋለን ብለውናል። ትራንስፖርት እዚህ ስለማይደርስ ያስቸግራል። አውቶቡስ ይመደባል ብለው ቃል ገብተውልናል። በዚህ ደስ ብሎኛል።
=========================
በጣም ደስ የሚል ሰፈር ነው የገባነው። አየሩ ራሱ ይመቻል። በተለይ ለእኛ ለሽማግሌዎች ጥሩ አየር ማግኘታችን ጥሩ ነው። አየሩ በጣም ተስማምቶኛል። መንገድ ነበር ችግሩ። አስፋልት አይደለም።
መንገዱን ቶሎ እንሠራዋለን ብለውናል። ትራንስፖርት እዚህ ስለማይደርስ ያስቸግራል። አውቶቡስ ይመደባል ብለው ቃል ገብተውልናል። በዚህ ደስ ብሎኛል።
===========================
ጥራቱን የጠበቀ ቤት ውስጥ ነው የገባነው። መጸዳጃ ቤትም፣ ማድቤትም… ሁሉም ነገር የተሟላ ቤት ነው። ከተጎሳቆለ ጭቃ ቤት ተገላግለናል። ዕድለኛ ነን። ቅር የሚል ነገር የለም። ከዛ ክፉ ችግር ተላቅቄ እዚህ መድረሴ ትልቅ ነገር ነው። ያላሰብነውን ነው ያገኘነው።
እንደዚህ ዐይነት ዕድል ማን ያገኛል? ቦታው ሩቅ አይደለም። መሀል ከተማ ነው። መንገዱ ጭቃ የለው! ምን የለው! ምስጋና ይድረው።
=======================
አዲሱ ሰፈራችን ጥሩ ነው። የነበርንበት ሰፈር፣ ብዙ ችግሮች ነበሩብን። መጸዳጃ ቤት ሁል ጊዜ ችግር ነበር። ወረፋ ነው። ፍሳሽም አለ። የወዲህኛው ቤት ደህና ቢሆን፣ ከወዲያኛው ወይም ከጓሮ በኩል ፍሳሽ ይመጣል። በጣም ይረብሻል። ብቻ… ብዙ ችግር ነበር። ወደ አዲሱ ሰፈራችን ስንገባ አስተዳደሩ ጥሩ ድጋፍና አቀባበል አድርጎልናል። የዕቃ ለማጓጓዝ የከተማው አስተዳደር የጭነት መኪኖችን በነፃ ሰጥቶናል። የጫኝ የአውራጅ ወጪም አልነበረብንም። በከተማው አስተዳደር ድጋፍ በነፃ ነው።
ሌላው በጣም ደስ ያለኝ ነገር፣ የመኖሪያ ቤት አመዳደብ ነው። አካል ጉዳተኞችና በዕድሜ የገፉ አዛውንት፣ በመኖሪያ ሕንጻው እንዳይቸገሩ የታችኛው ፎቅ ላይ ተስማሚ ቤት አግኝተዋል። ጥሩ አስበውበታል። የሚመሰገን ተግባር ነው።
የልማት ተነሺ ነዋሪዎች ሐሳብ ከራሳቸው አንደበት በዐጭር በዐጭሩ እነሆ።
የልማት ተነሺ ነዋሪዎች ሐሳብ ከራሳቸው አንደበት በዐጭር በዐጭሩ እነሆ።
እኔ በጣም ነው ደስ ያለኝ። በነበርንበት ሰፈር በየግቢው ሀያ ሠላሳ ቤተሰብ ሆነን ነበር የምንኖረው። የቤተሰብ ብዛት ሲታሰብ፤ በአንድ ግቢ ውስጥ መቶ ሁለት መቶ ሰው ይሆናል። አዲስ መኖሪያ ቤት፣ ሁሉም ቤተሰብ የየራሱ መታጠቢያ መጸዳጃ ቤት፣ የየራሱ ማድ-ቤት ሲያገኝ ደስ ይላል።
ዛሬ ደግሞ አይቼ የማላውቀውን አከባበር አይቻለሁ። በ65 ዓመት ዕድሜዬ፣ ከንቲባ በዐይኔ አይቼ አላውቅም። እዚህ መጥተው ሲያበረታቱን፣ ለጥያቄዎችም ጥሩ ምላሽ ሲሰጡን… በጣም ደስ ብሎኛ። በጣም ረክቻለሁ።
=======================
ክብርት ከንቲባ ቤት-ለእንቦሳ ሊሉን መጥተዋል። ባዶ እጃቸውን አልመጡም። ቡና አፍልተን የምንጠጣው ይዘውልን መጥተዋል። ለምግባችንም ሰርተን የምንመገበውን ስጦታ አበርክተውልናል።
====================
ከንቲባዋም እዚህ መጥተው ጠይቀውናል። እንዴት እንዴት እየሆናችሁ ነው ብለው ለመጠየቅና በአካል ለማየት ብለው ነው የመጡት። የሥራ ጊዜያቸውን አብቃቅተው እኛን ለመጠየቅ ስለመጡ ደስ ብሎናል። በጣም እናመሰግናለን።
========================
በጣም ደስ የሚል ሰፈር ነው የገባነው። አየሩ ራሱ ይመቻል። በተለይ ለእኛ ለሽማግሌዎች ጥሩ አየር ማግኘታችን ጥሩ ነው። አየሩ በጣም ተስማምቶኛል። መንገድ ነበር ችግሩ። አስፋልት አይደለም።
መንገዱን ቶሎ እንሠራዋለን ብለውናል። ትራንስፖርት እዚህ ስለማይደርስ ያስቸግራል። አውቶቡስ ይመደባል ብለው ቃል ገብተውልናል። በዚህ ደስ ብሎኛል።
=========================
በጣም ደስ የሚል ሰፈር ነው የገባነው። አየሩ ራሱ ይመቻል። በተለይ ለእኛ ለሽማግሌዎች ጥሩ አየር ማግኘታችን ጥሩ ነው። አየሩ በጣም ተስማምቶኛል። መንገድ ነበር ችግሩ። አስፋልት አይደለም።
መንገዱን ቶሎ እንሠራዋለን ብለውናል። ትራንስፖርት እዚህ ስለማይደርስ ያስቸግራል። አውቶቡስ ይመደባል ብለው ቃል ገብተውልናል። በዚህ ደስ ብሎኛል።
===========================
ጥራቱን የጠበቀ ቤት ውስጥ ነው የገባነው። መጸዳጃ ቤትም፣ ማድቤትም… ሁሉም ነገር የተሟላ ቤት ነው። ከተጎሳቆለ ጭቃ ቤት ተገላግለናል። ዕድለኛ ነን። ቅር የሚል ነገር የለም። ከዛ ክፉ ችግር ተላቅቄ እዚህ መድረሴ ትልቅ ነገር ነው። ያላሰብነውን ነው ያገኘነው።
እንደዚህ ዐይነት ዕድል ማን ያገኛል? ቦታው ሩቅ አይደለም። መሀል ከተማ ነው። መንገዱ ጭቃ የለው! ምን የለው! ምስጋና ይድረው።
=======================
አዲሱ ሰፈራችን ጥሩ ነው። የነበርንበት ሰፈር፣ ብዙ ችግሮች ነበሩብን። መጸዳጃ ቤት ሁል ጊዜ ችግር ነበር። ወረፋ ነው። ፍሳሽም አለ። የወዲህኛው ቤት ደህና ቢሆን፣ ከወዲያኛው ወይም ከጓሮ በኩል ፍሳሽ ይመጣል። በጣም ይረብሻል። ብቻ… ብዙ ችግር ነበር። ወደ አዲሱ ሰፈራችን ስንገባ አስተዳደሩ ጥሩ ድጋፍና አቀባበል አድርጎልናል። የዕቃ ለማጓጓዝ የከተማው አስተዳደር የጭነት መኪኖችን በነፃ ሰጥቶናል። የጫኝ የአውራጅ ወጪም አልነበረብንም። በከተማው አስተዳደር ድጋፍ በነፃ ነው።
ሌላው በጣም ደስ ያለኝ ነገር፣ የመኖሪያ ቤት አመዳደብ ነው። አካል ጉዳተኞችና በዕድሜ የገፉ አዛውንት፣ በመኖሪያ ሕንጻው እንዳይቸገሩ የታችኛው ፎቅ ላይ ተስማሚ ቤት አግኝተዋል። ጥሩ አስበውበታል። የሚመሰገን ተግባር ነው።
“ሐሳባችንን የሚረዳልን፣ ስሜታችንን የሚያውቅልን አገኘን”
“ከንቲባዋ ስጦታ ይዘው፣ በአካል መጥተው ጠይቀውናል፤ “ቤት ለእንቦሳ” ብለውናል!”… ወደ አዲስ ቤታቸው የገቡ የልማት ተነሺዎች።
“የካዛንችስ ነዋሪዎች ለከተማችን ልማት ባለውለታዎች ናቸው፤ በትዕግሥትና በአስተዋይነት ድጋፋቸውን ሰጥተውናል”… ከንቲባ አዳነች አበቤ።
የልማት ተነሺ ነዋሪዎች፣ ስለ ቀድሞው አኗኗራቸው፣ ስለ አዲሱ ቤታቸውና ስለ ከከተማ አስተዳደሩ ምን ይላሉ?
የአዲስ አበባ ከንቲባ፣ “እንዴት እየሆናችሁ ነው?” ብለው ነዋሪዎችን ለመጠየቅ በየቦታው ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
አዲሱ ቤታቸውን መልክ እያስያዙ ከአዲሱ ሰፈራቸው ጋር መላመድ የጀመሩት የልማት ተነሺዎች፣ የከተማዋ ከንቲባ እነሱን ለመጠየቅና ለመጎብኘት ይመጣሉ የሚል ግምት አልነበራቸውም። ለዚያውም ገና አንድ ቀን ሁለት ቀን ሳይሞላቸው ነው ለጥየቃ የመጡት።
ደግሞም፣ ከነባር የመኖሪያ ሰፈር ወደ መኖሪያ ቦታ የሚሄዱ የልማት ተነሺዎች፣ ወዲያውኑ ጠያቂና ጎብኚ ቢያገኙ ነው የሚጠቅማቸው። ከትንሽ ጊዜ በኋላማ፣ አዲሱን ሰፈራቸውን ይላመዱታል።
መንፈሳቸውን የሚያረጋጋና የሚያበረታታ ሰው የሚያስፈልጋቸው በመጀመሪያዎቹ ቀናት ነው። ከንቲባዋ ትክክለኛውን ጊዜ አውቀው በአካል እነሱን ለመጠየቅ መምጣታቸውን በማየት ብቻ የልማት ተነሺዎቹ ልብ ተነክቷል።
“በዚያ ላይ፣ ባዶ እጃቸውን አይደሉም የመጡት” በማለት ነዋሪዎቹ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።
ታዲያ፣ ምስጋናው ከአንድ አቅጣጫ ብቻ የተሰነዘረ አይደለም።
ከንቲባ አዳነች አበቤም የልማት ተነሺዎቹን ከልብ ማመስገን እፈልጋለሁ ብለዋል።
ድሮና ዘንድሮ፤ ያረጁ ቤቶችን አዲስ በተገነቡ ቤቶች መተካት
ከካዛንቺስ አካባቢ ለልማት የተነሱ ነዋሪዎች፣ በከተማዋ አስተዳደር ወደ ተሰጣቸው አዲስ መኖሪያ ቤት የተዛወሩት በዚህ ሳምንት ነው። በአብዛኛው፣ ለ50 ዓመታት ምንም ጥገናም ሆነ እድሳት ያልተደረገላቸው የቀበሌ የኪራይ ቤቶች ውስጥ ነበር የሚኖሩት።
ቤቶቹ አርጅተው የተጎሳቆሉ የጭቃ ቤቶች ናቸው። ግድግዳቸው ተቦርቡሮ በቆርቆሮ የተለጣጠፉ ናቸው - አብዛኞቹ። ጣሪያቸው በዕድሜ ብዛት እየዛገ፣ እየተበሳ ውኃ ያፈስሳል። አብዛኛው ጣሪያ የላስቲ ሸራ ተነጥፎበታል። በነፋስ እየተገነጣጠለ ተነቃቅሎ ለመብረር በትንሽ ሽውታ እየተወራጨ እንቅልፍ ይነሳል፤ ያስጨንቃል። ጣሪያ ላይ ብዙ ትልልቅ ድንጋዮች የሚታዩትም የዛገውን ቆርቆሮ ከነፋስ ለማስጣል ነው።
ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቀጥላ ቤቶች በቆርቆሮ እየተጨመሩበት ከሕዝብ ብዛት ጋር የቀድሞ መኖሪያ ሰፈሮች ተጨናንቀዋል። የውስጥ ለውስጥ መተላለፊያ መንገዶቹ ጠባብ ናቸው።
ብዙዎቹም የሰፈር ውስጥ መንገዶች፣ ለመኪና የሚታሰቡ አይደሉም። ከአንድ ከሁለት ሰው በላይ አያሳልፉም። በዚያ ላይ ፍሳሽ አለ። መጸዳጃ ቤትም፣ ብዙ ቤተሰብ በወረፋ የሚጠቀምበት ሲሆን ደግሞ፣ ለኑሮም ለጤናም የዕለት ተዕለት ፈተና ይሆናል።
ቢሆንም ግን፣ ያደጉበት ሰፈር፣ የኖሩበት ቤት ከነችግሩም ቢሆን፣ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ትልቅ ዋጋ አለው። የሚያናንቁት ነገር አይደለም። የተሻለ ሰፈርና መኖሪያ ቤት ካልተገኘም፣ “ይቅርብኝ” ብለው የሚያጣጥሉት አይሆንም።
ደግነቱ፣ ለልማት ተነሺዎች የተዘጋጁ መኖሪያ ቤቶች፣ ከቀድሞ መኖሪያ ቤቶች የተሻሉ ብቻ አይደሉም።
አዲስ ናቸው። የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ፣ ማድቤት፣ መታጠቢያ፣ መጸዳጃ የተሟላላቸው ባለፎቅ መኖሪያ ቤቶች ናቸው።
የመኖሪያ ቤት አመዳደብ የተካሄደውም በዘፈቀደ አይደለም። የቀድሞ ጎረቤታሞችና የሰፈር ሰዎች ማኅበራዊ ግንኙነታቸው እንዳይበጠስና እንዳይበተን ታስቦበታል።
አንድ ሰፈር ላይ የነበሩ የልማት ተነሺዎች፣ ወደ አንድ አካባቢ እንዲዛወሩ ነው የተደረገው። ገሚሶቹ በአቃቂ ገላን ጉራ ወደተገነቡ መኖሪያ ቤቶች፣ ገሚሶቹ ደግሞ በቦሌ አራብሳ ወደተሠሩ አዳዲስ መኖሪያ ቤቶች ገብተዋል።
ይሁን እንጂ፣ ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ ነው ማለት አይደለም።
እንዴት እየሆናችሁ ነው? ብሎ የሚጠይቅና የሚያበረታታ ያስፈልጋል።
ምንም እንኳ፣ አዲሱ መኖሪያቸው በአሠራሩና በጥራቱ ከቀድሞው እጅግ የተሻለ ቢሆንም፣ ከነባር ቦታ በአንዴ መልቀቅ… ለጊዜውም ቢሆን መንፈስን ይረብሻል። ወደ አዲስ ሰፈር መግባትና መላመድ ለጊዜው ስሜትን ይፈታተናል። ሊያስጨንቅም ይችላል።
ለዚህም ነው፣ ከንቲባ አዳነች አበቤ “ይዋል-ይደር” ሳይሉ የልማት ተነሺዎችን በአካል ለማየትና ለመጠየቅ መምጣታቸው፣ ለነዋሪዎቹ ልዩ ትርጉም የነበረው።
ከንቲባ አዳነች አበቤ ወደ አቃቂ ገላን ጉራ ሄደው ነዋሪዎችን ጠይቀዋል። ወደ ቦሌ አራብሳ ሄደውም ጎብኝተዋል። ወደ ነዋሪዎች ቤት ጎራ እያሉ ከነዋሪው ጋር ቁጭ ብለው ተነጋግረዋል።
ቡና፣ የምግብ ዘይት፣ የዳቦ ዱቄት፣ የተማሪዎች ቁሳቁስ ይዘው ነው የልማት ተነሺዎችን ለመጠየቅ የሄዱት። ብዙ ነዋሪዎች ይህን እናያለን ብለው አልጠበቁም።
በከንቲባዋ ጉብኝት መደነቃቸውን የገለጹ ነዋሪዎች፣ በዚያ ላይ ስጦታ ይዘውልን ነው የመጡት ሲሉ ተናግረዋል።
ከሁሉም በላይ ግን፣ ከንቲባዋ እነሱን በማሰብ በቦታው ተገኝተው እነሱን ለማየት መምጣቸው ነው ነዋሪዎቹን ያስደሰታቸው።
ሐሳባችንን የሚረዳልን፣ ስሜታችንን የሚያውቅልን አገኘን የሚል መንፈስ ያደረባቸው ነዋሪዎች ከንቲባዋን ማመስገናቸው ለዚህ ነው።
ከንቲባዋም ግን የልማት ተነሺዎችን አመስግነዋል። የካዛንችስ ነዋሪዎች በትዕግሥትና በአስተዋይነት ከከተማዋ አስተዳደር ጋር በትብብር ሠርተዋል ሲሉ ከንቲባዋ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
የከተማችን ባለውለታዎች ናችሁ፤ ለከተማችን ልማት በበጎ መንፈስ ለሰጣችሁን ድጋፍ ከልብ ላመሰግናችሁ እፈልጋለሁ ብለዋል - ከንቲባዋ።
የልማት ተነሺዎች፣ ለኑሮ የሚያስፈልጉ አገልግሎቶች የተሟሉላቸው ንጹህ መኖሪያ ቤቶችን ማግኘታቸው መልካም ነው። መሆንም አለበት።
ለተማሪዎች በአቅራቢያቸው ትምህርት ቤት፣ ለነዋሪዎች የጤና ተቋማትና ፋርማሲ፣ የሸማቾች ሱቆች ተዘጋጅተዋል። ከዚህም በተጨማሪ፣ ለእናቶችና ወጣቶች የሥራ ዕድል የሚከፍቱ ሼዶች ተገንብተዋል። ውሃና መብራት ገብቶላቸዋል።
ችግሮች የሉም ማለት ግን አይደለም። በገላን ጉራ መኖሪያ ሕንጻዎች ላይ፣ መንደርን ከመንደር እንዲሁም ከዋና መስመር ጋር የሚያገናኙ መንገዶች ወደ አስፋልት ደረጃ አልተሻሻሉም። የትራንስፖርት ችግርም አለ።
ከንቲባ አዳነች አበቤ የገቡት ቃል
አስፋልት በፍጥነት ተሠርቶ የአውቶቡስ አገልግሎት እንደሚጀመር ለነዋሪዎች ገልጸዋል - ከንቲባዋ።
የተማሪዎች የክፍል ጥበት በማጋጠሙም አዲስ ትምህርት ቤት እንገነባለን ብለዋል። በደፈናው እንገነባለን አላሉም። ረዥም ቀጠሮ አልሰጡም።
አዲሱ ትምህርት ቤት 2 ወር ይጠናቀቃል ብለዋል።
ሴቶችን ተጨማሪ የሥራ ዕድል እንዲያገኙና በባለቤትነት ስሜት ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ፣ እንጀራ ማምረቻ ማእከል ግንባታ አስጀምረናል ሲሉም ለልማት ተነሺዎች ተናግረዋል።
በአዲሱ መኖሪያ ቤት፣ በከንቲባዋ ጉብኝትና በተቻለ ዐቅም ችግሮችን በፍጥነት ለማቃለል ቃል መግባታቸውን ሁሉ በመጥቀስ የልማት ተነሺዎች ምስጋናቸውን ገልጸዋል።
ከንቲባዋ በበኩላቸው፣ “በፍትሃዊነት እንሰራለን። ጊዜያዊ ችግሮችን ጨከንብለን በትብብር ሰርተን በፍጥነት እናልፋቸዋለን። ለከተማችን ልማት በሙሉ ልባችሁ እየደገፋችሁ ከጎናችን ሆናችሁ ስላበረታታችሁን አክብሮት እየገለጽኩ ከልብ አመሰግናለሁ” ብለዋል።
የተስፋዬ ቤት - ከማዕበል ማዶ
የመጽሐፉ ርዕስ -
ደራሲ -
ከማዕበል ማዶ
ተስፋዬ ማሞ
ዘውግ
ኢ-ልቦለድ (ቅይጥ ወይም የተስፋዬ መንገድ)
የገጽ ብዛት -
364
የኅትመት ዘመን -
2017
የዳሰሳው አቅራቢ -
ቢኒያም አቡራ
ቅይጥ ወይስ የተስፋዬ ቤት
የጋሽ ተስፋዬ ማሞ “ከማዕበል ማዶ” የተሰኘው መጽሐፍ፥ በስፍን ቅንብብ ለመታጠር ያልፈቀደ “አመጸኛ ጅረት” ነው። አሃዱ ብለን፥ “የአንድ ዕብድ ቀን ውሎ” ጋር ስንፋጠጥ፥ “ይሄ ነገር በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ግለ ሕይወት ታሪክ (auto-fiction) ነው እንዴ?” ያሰኘናል።
ጥቂት ፈቀቅ እንዳልን ግን ጥንቅቅ ያለ የግለ ሕይወት ታሪክ (autobiography) ቅርጽ ይመጣል። በራሱ ላይ ትኩረት ከመስጠቱ እና በራሱ ብዕር ከመተረኩ ባሻገር፥ በየዘመናቱ የደረሰበትን አስተሳሰብ እንደ ብር ጻሕል ዘርግቶ፥ ሥነ-ልቦናዊና ፍልስፍናዊ ቀለማትን እንደ ወርቅ እንኮይ ያቀርባቸዋልና፥ “ይሄማ ደንበኛ ግለ ሕይወት ታሪክ (autobiography) ነው!” እንድንል ይገፋፋናል። ለአብነትም ያህል ከመጽሐፉ ውስጥ ይሄን መመልከት እንችላለን፡- “… ከሰዎች ጋር ለመግባባት ምንም ያህል ጊዜ አይፈጅብኝም። ግልጽነቴም ለአንድ የፖለቲካ ሠራተኛ ከሚያስፈልገው ቁጥብነት የሚያልፍም ይመስለኛል። ችኩልነትም አያጣኝም። አንድን ነገር ለማድረግ ካሰብኩ ይዋል ይደርን አላውቅም፤ አደርገዋለሁ። ቡቡ ነገርም ነኝ። ለደስታም ለኀዘንም ትንሽ ይበቃኛል። ይህ ባሕርዬ የከፋ ጉዳት ባያደርስብኝም አልፎ አልፎ የሰው የሆኑ ጥቃቅንም፣ ትልልቅም ስህተቶችን ያሠራኛል። በአጠቃላይ እነዚህ ባሕርይዎቼ ተደማምረው ብዙ ጊዜ ለጥቃት አጋልጠውኛል።” (ገጽ 122)
ግና … ቅደም-ተከተላዊ (chronological) ተረክ ጥሶ፥ ከገጠመኞቹ መካከል ሊያስተምሩ ይገባል ያላቸውን ብቻ መርጦ፥ ከድርጊቱ ይልቅ ለድርጊቱ ያለው አተያይ አድልቶ ወደ ግለ ማስታወሻ (memoir) የአጻጻፍ ምኩራብ ላይ ተሰይሞ እናገኘዋለን። ለምሳሌ፡- 2006 ላይ ሲቆዝም ያስነብበን እና 15 ዓመት ወደ ኋላ ይወስደናል፥ ከዚያ በድጋሚ ወደ 2006 ያመጣንና ከመቅጽበት ወደ 1949 ዓ.ም የኋላ ሽምጥ ያስጋልበናል። በተጨማሪም ከገጠመኞች መካከል ሊያስተምሩ ይገባል ያላቸውን መርጦ በማስፈር ረገድ፥ ወደ ግለ ማስታወሻ (memoir) አጻጻፍ ያደላበትን ለአብነት ያህል እንጥቀስ። የማክሲም ካፌን እና የእያሱ በርኼን ተረክ ካወጋን በኋላ፥ ከዚህ ዘመን ኩነት ጋር ነጽሮ ትዝብቱን እንዲህ በማለት ያጋራል፡- “ሁልጊዜ ከሚያስቆጩኝ ነገሮች መካከል አዲስ አበባ ይህንን ጥሩ ባሕል ማጥፋቷና ማምከኗ ነው። ሊበረታታ፣ ሊያድግ፣ ሊስፋፋ፣ የሚገባው ነገር በፖለቲካዊ ተጽዕኖዎችና ፍላጎቶች ምክንያት ከስሞ ወጣቶች ከአርአያዎቻቸው ጋር በቅርብ የሚተያዩበትና ተምሳሌት የሚፈጥሩበትን ዐውድ ማጣቷ የሚያስቆጭ ነው። አዲስ አበባ ዐዳዲስ ወጣቶችን በማፍራትና የኪነጥበብ ሰዎች እንደየዝንባሌያቸው በነጻነት የሚገናኙበት ቦታ የሌላት መሆኑ ያሳዝናል። ዛሬም ከሠራቻቸውና ከምትኩራራባቸው በርካታ ሜጋ ፕሮጄክቶች ፓርኮች፣ አደባባዮች መናፈሻዎችና ጊዜ ማሳለፊያዎች ባለፈ እንዲህ ዓይነት ጥበባዊ ልምምዶች በነጻነት የሚካሄዱባቸውን ቦታዎች አለመሥራቷ ኪሳራዋ ይመስለኛል።” ገጽ 269
የተስፋዬ ብዕር አመጸኛ ጅረት ነውና በዚህ አያከትምም። ወደ ትዝታ (reminiscence) ጎሬ ውስጥም ጎራ ይላል። ነባር የተሰነዱ የሕይወት ዘገባዎችን ግልጋሎት ላይ ሳያውል፥ በትዝታ ብቻ ወደ ኋላ ሽምጥ ጋልቦ፥ በአሁናዊ ኹኔታ የሚታወስን ድርጊት በሌሎች ላይ አተኩሮ ይጫጭራልና።
የጋሽ ተስፋዬ ብዕር በሕግ እና በደንብ መቀንበብን ያልፈለገች ነጻ ልሳን ናት። ሕግን የምታውቅ ግን ለዛ ባለው መንገድ የደንቡን ኮረብታ የምትነድል ብዕር። የስፍን መጋረጃን ለመቅደድ የፍንገጣ መቀስ የሰደደች ብዕር። የዚህን መጽሐፍ ስፍን፥ “ቅይጥ” ከማለት ይልቅ “የተስፋዬ ቤት” ወይም “የተስፋዬ መንገድ” ልንለው እንችል ይሆን? ከማዕበል ማዶ ለግለ ሕይወት ታሪክነት (autobiography) ያደላ አጻጻፍ መኾኑን አለማመን ግን እብለት መኾኑን ልብ ይሏል።
ከማዕበል ማዶ vs የአንጋፋዎቹ ግለሰቦች ታሪክ
ከማዕበል ማዶ ከታሪክ ሰነድነት አኳያ፥ የየካቲት 66 የፖለቲካ ትምህርት ቤት ቁመና ኾነ፥ የፓዊ-መተከል ሠፈራ ጣቢያ ውስጥ ያለው ሐተታ ከየኔታ ተመስገን ገብሬ (ሕይወቴ) የፋሺስት ጭፍጨፋ የዓይን እማኝነት ጋር አይጋጠምምን? … የባለታሪኩን ሙያ በማተት ረገድ የሕክምና፥ የፊልም እና የድራማን እንዲሁም የማስታወቂያን ሙያን ከፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ (አንዳፍታ ላውጋችሁ) የካታሎግ አሠራርን፥ የአተረጓጎም ሥልት ሐቲትን አይተዝትምን? …እንደ ትዳር ያለ እጅጉን ግላዊ ነገር አደባባይ ላይ በግልጸኝነት በማውጋት በኩል፥ ከጋሽ በቀለ ወልደ ኪዳን (ጣልቃ እየገባ) ያንስ ይኾን? … ልጅነትን፥ የቅርብ ዘመድን ቤተሰብን በመተረክ ረገድ ከአብዬ መንግሥቱ ለማ (ደማሙ ብዕረኛ) የተዋሰ ይኾንን? … ወቅትን፥ ዘመንን ከራስ ተረክ ጋር ገምዶ ወሽኔ በኾነ ሥነ ጽሑፍ በመከተብ በኩል፥ ከብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ (ትዝታዬ ስለራሴ የማስታውሰው) መጽሐፍ ጋር ትከሻ ለትከሻ ለመለካካት ይንደረደር ይኾን? … በሀብተ-ቋንቋ ረገድ፥ ከዮሐንስ አድማሱ (ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ) ጋር አይቀራረብምን? … እንደ ኤርትራዊቷ አደይ ያሉ የግለሰቦችን ዘዬ በመከሰት ረገድ፥ መጽሐፈ ትዝታ ዘ አለቃ ለማ ኃይሉን አያስተዝትምን? … በአንድ ጉዳይ ላይ አድምቶ በመጻፍ ረገድ እንደ ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት (ኦቶባዮግራፊ) ያለ ልፋት አይታይምን? … ኢ-ቅደም-ተከተላዊ አሰዳደር በማንበር በኩል፥ የፍቅረ ማርቆስ ደስታ (የሚሳም ተራራ) ጥላ የረበበ አይመስልምን? … የራስን የአጻጻፍ ዘይቤ ለማሥረጽ፥ እንደ አሰፋ ጫቦ (የትዝታ ፈለግ፣ 2008) ያለ ጥረት አይታይምን? … በታሪክ አጋጣሚ በሕይወት ሰርጥ ውስጥ ስላገኛቸው ጉምቱ ሰዎች ሲያወጋ የእነ-ጋሽ ተክለጻዲቅ መኩሪያ (የሕይወቴ ታሪክ) ቀለም አይታይምን?
የ”ከማዕበል ማዶ ፋይዳ”
አንደኛ፡-
ፒየር ማሻሪ “ሥነ ጽሑፍ ለተጻፈበት ዘመን ጥበባዊ አንደበት ነው!” ይላል። የግለሰብ ታሪክ ሲሆን ደግሞ ይብሱን ልሳንነቱ ይተባል። በዚህ ረገድ ጋሽ ተስፋዬ ዘመናቸውን “በፊደላት ስዕል” አንብረውታል። ከማዕበል ማዶ ዐዲስ የአጻጻፍ ይትባሕል ለመፍጠር በመታተር ሂደት ውስጥ ቢኾንም እንኳ የዘመን መስታየትነቱን አልነፈገም። ዘመንን በማኅበራዊ፥ በኢኮኖሚያዊ፥ በፖለቲካዊ እንዲሁም በታሪካዊ ሁኔታዎች በመዳሰስ በኩል ለምሉዕነት ቀርቧል። ስለጓድ ደበላ ዲንሳ ብንል ስለእትየ ዓመለ-ወርቅ (የፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም እህት)፥ ስለባለቅኔው ሙልጌታ ተስፋዬ ብንል ስለሁለገቧ አርቲስት አዳነች ወልደገብርኤል፥ ስለኢንጂነር ካሳ ገብሬ ብንል ስለኢያሱ በርኼ፥ ስለጋሽ ሥዩም ተፈራ ብንል ስለሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን … በስም ወጭት የግብር እና የሰነድ ወጣወጥ በዓይነት በዓይነቱ የቀረበ የታሪክ ብፌ ነው ብል ማጋነን አይኾንብኝም። የአዲስ አበባን ልብና ኩላሊቷን መርምሮ፥ በየዘመኑ የነበራትን መልክ ከትቧል። አሥመራን የበዓሉ ገጸሰብ እንደ ነበረው ጸጋዬ ኃይለማርያም በብዕሩ ስሏታል። ባሕርዳር፥ መተከል፥ ፓዌ፥ መንዱራ፥ ጣና በለስ፥ ሠፈራ ጣቢያዎችን ጅማትና ቅልጥማቸውን ለያይቶ ጽፏል። የመጽሐፉ ቁልፍ ቃላት ናቸው ብዬ ባልፍ ይሻለኛል። በአጭሩ ሠፈራ ጣቢያን በሚመለከት እንደ መጀመሪያ የታሪክ ምንጭ የሚጠቀስ ሰነድ በመኾን የዘመን መስታወትነቱን ያንጸባርቃል። በታሪካዊ አንደበትነት ረገድ እጅግ ብዙ አበርክቶት የሰነቀ ጥራዝ በመኾኑ ምክንያት የመጽሐፉ ፋይዳ ንሯል።
ሁለተኛ፡-
መካከለኛው የፊልም ዘመን በኢትዮጵያ እና የተከታታይ ድራማ አጀማመር በኢትዮጵያ ላይ የነበረ የአሠራር መንገድ፣ ተግዳሮት እና ዕድሎች ማጥናት ለሚሻ ሰው ትልቅ ፋይዳን የሚሰጥ መጽሐፍ ነው። ስለ መንትያ፥ የንዋይ ሰለቦች፥ ትዝታ፥ ፊርማ፥ ምርጫ፥ ይቅርታ፥ አጋጣሚ፥ መላ ... የተሰኙ ሥራዎቹን ከቅድመ-ቀረጻ እስከ ድኅረ-ቀረጻ የነበረውን በማተቱ በኩል የኢትዮጵያ የፊልም፣ የድራማ ታሪኮችን ለሚሰንድ የጥናት ባለሙያ አንዱ ዋቢ የሚሆን ቅምጥ ጽሑፍ ማዘጋጀቱ ትልቅ አበርክቶት ነው። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት ለወደፊቱ ታሪኩን ሲሰንድ ኹነኛ ማጣቀሻ የሚኾን መጽሐፍም ነው።
ሦስተኛ፡-
የጋሽ ተስፋዬ የማስታወቂያ ሥራ አጀማመሩ፣ አካሄዱ እና ዕድገቱን በማካተቱ ወደዚህ ሥራ ለሚገቡ ሰዎች ቀላል የማይባል ጥቁምታ ሰጪ ነው። ባለታሪኩ ከምንም ተነስቶ እዚህ መድረሱ በራሱ፣ በቀቢጸ-ተስፋ ለሚናውዘው የሀገራችን ወጣት “ዝሆንም በልጅነቱ ትንሽ ነበር!” ብሎ እንዲነሳሳ የማድረግ አቅሙ ላቅ ያለ ነው።
አራተኛ፡-
በሀገራችን ያለው የግለሰብ ታሪክ አጻጻፍ የረጋ ሐይቅም አይደል? ልክ እንደ ሰዋሰው ባለቤት፥ ተሳቢና ግስ። ተወለደ፥ አደገና ሞተ የግለሰብ ታሪክ የአጻጻፍ ቀኖና መስሎ ነበር። ጋሽ ተስፋዬ ዐዲስ በኾነ የአጻጻፍ መንገድ መከሰቱ ለሀገራችን ሥነጽሑፍ አንድ ትልቅ ዕምርታ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ጥናትና ውይይትን ይሻል።
አምስተኛ፡-
ይህ መጽሐፍ በጋሽ ተስፋዬ ዘመን ለነበሩ ጉምቱ የዘመን ጓዶች የራሳቸውን ታሪክ እንዲጽፉ ተነሳሽነትን የሚፈጥር ነው ብዬ አምናለሁ። ጉምቱ ሰዎቻችንን ባጣን ቁጥር ለቀብር ቀን የሚነበብ የሟች የሕይወት ታሪክ ጽሑፍ እስከማጣት መድረስ እንደ ዓመት በዓል በየዓመቱ የምንደጋግመው የሲሲሰፈስ እርግማን ኾኖብናል። ታላላቆቻችንን ባጣን ቁጥር እዝራ እጅጉ ወደ ሚያዘጋጀው “መዝገበ አእምሮ” እና ወደ መዓዛ ብሩ “የጨዋታ እንግዳ” መርሐግብር” የምናማትረው በዚህ ምክንያትም አይደል? ይህ መጽሐፍ ጉምቱ ሰዎቻችን በተለይም የጋሽ ተስፋዬ የዘመን ጓዶች እንዲጽፉ የሚያነሳሳ ነው። ሁሉም የራሱን መልክ በጽሑፍ ከገበረ ደግሞ የዘመን ምስል እና የሀገር ቁመና ይከስትልናል። ጋሽ ተስፋዬ የራሱን ፊት እስከነቡጉሩ በማሳየት “ኑ አብረን የዘመን እና የሀገርን መልክ ለዚህኛውና ለሚመጣው ትውልድ እናሳይ” የሚል ትልቅ ቀጨምታን (inspiration) ገብሯል፤ ለዘመን ጓዶቹ።
ስድስተኛ፡-
ከዚህ በኋላ ለሚጻፉ የግለሰብ ታሪኮች በእነዚህ ምክንያት ደንበኛ ማጣቀሻ የመኾን ዕድል ያለው ይመስለኛል። እጅጉን ግላዊ የሚባለው ነገር ለሰዎች ትምህርት ይኾን ዘንድ ሊሰዋ እንደሚገባ፥ ከታሪኮች መሃል የተሻለውን መርጦ መከተብ የመጽሐፉን አቅም እንደ ሚወስን፥ የራስ ታሪክ የሚደምቀው በሌሎች ታሪክ መሃል መኾኑን፣ የሌሎችን ታሪክ ስናስገባ ዐውዱን በጠበቀ መልኩ እና በልክ መኾን እንዳለበት መጽሐፉ በጉልህ ይናገራል።
ሥነ ጽሑፋዊ ውበት፥ ቋንቋ፥ ሥርዓተ ነጥብ፥ ሰዋሰው እጅግ ውብ በመኾኑ ከዚያ ውስጥ ሕጸጽ ለማውጣት መሞከር “ከቁንጫ ሌጦ” ማውጣትን የሚጠይቅ አድርጎብኛል።
***
ከአዘጋጁ፡-
ጸሃፊው፤ “የባለቅኔዋ ሶሪት” እና “ወደ ፍቅር ጉዞ” መጻሕፍት ጸሐፊ ሲሆን በኢሜይል አድራሻው፡
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ማግኘት ይቻላል፡፡
የግጥም ጥግ
እንዲያው ማሳዘኑ!
ተበዳዩ ጨቋኝ. . .
በዳዩ ተጨቋኝ. . .
የተገላቢጦሽ ኾኗል ነገሩማ፤
ፍትሕ ተዘንብላ
ስትወድቅ በአፍጢሟ
የድረሱልኝ ጥሪ ሩቅ ስታሰማ፤
ሮሮዋን ሰምቶ - አዝኖ ቀረበና
ሊያነሳት ቢሞክር ተበዳዩ ጨቋኝ፤
አልተቻለው ከቶ ቢለፋ ቢሞክር
ከወደቀችበት ሽቅብ ቀና እንድትል
ማድረጉ ተሳነው የቱን ያህል ቢጥር።
ሞት አፋፍ ላይ ኾና ጣርን ስታጣጥር
ጩኸትና ዋይታ አብዝቶ ተሰማ
ከተበዳይ ጨቋኞች ከምስኪኖች ዘንዳ።
የኩኔዎች ባልተቤት በዳዩ ተጨቋኝ
ፍትሕን ፈላጊ እሷኑኑ አዳኝ
መስሎ ቀረበና. . .
በደስታ - በተድላ - በአሸናፊነት ስሜት
በወኔም ተሞላ በድል አድራጊነት!
ዳግም ላታበራ የወደቀችውን ገድሎ ቀበረና
ደግሞም ላዩ አዝኖ ብሎም ጆሮ ዳባ
ዓይኑን በጨው አጥቦ የአዞ እንባ እያነባ
ቀርቦም ተጭቁኖች፣ ተገፊዎች ዘንዳ
በመርዛም ምላሱ መስሎም ለዘብተኛ
ይነዛ ጀመረ የአይዟችሁ ጥሪ
በዳዩ ተጨቋኝ የፍትሕ ቀባሪ!
እንዲያው ማሳዘኑ. . . .
(በዒምራን ዑመር
ምን ዓይነት እናት ነሽ?
ምን ዓይነት እናት ነሽ?
አንዱ ልጅሽ ሲያለቅስ፣
አባብለው ብለሽ፣
ከሌላው (ከሌለው) ቀምተሽ፣
እንባውን እያበሽ፣
አይዞህ ብለሽ ሰጥተሽ።
ደግሞ ሌላው ልጅሽ፣
ተበደልኩኝ ብሎ ሲመጣ ወደ አንቺ፣
ሌላውን በድለሽ ችግር የምትፈቺ፣
በ”ተበዳይ” እና በ”በዳይ” አዙሪት፣
እየተሽከረከርሽ የማትሄጂ ወደፊት፣
ምን አይነት እናት ነሽ?
(ነሐሴ 26 ቀን 2012 ዓ.ም፤ዮናስ ታረቀኝ)
“ፕሬዚዳንቱ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ መሆን ይጠበቅባቸዋል”
አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የቀድሞዋን ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴን በመተካት የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ሆነው ከተሾሙ
ሳምንት አለፋቸው። አምባሳደሩ ለፓርላማው ባቀረቡት ንግግር የተለያዩ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡፡ የቀድሞዋ ፕሬዚዳንት
አሸኛኘትም አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የትግራይ ክልል አስተባባሪ አቶ ጊደና መድሕን
የቀድሞዋ ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ ስለተሸኙበት መንገድና ስለአዲሱ ፕሬዚዳንት የፓርላማ መክፈቻ ንግግር ሃሳብና
አስተያየታቸውን እንደሚከተለው አጋርተውናል፡፡
የቀድሞዋ ፕሬዚዳንት ስለተሸኙበት መንገድ--
በመጀመሪያ በጣም ነው የማመሰግነው። በመንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመቅረብ ዕድል የሌለን ሰዎች ሃሳባችን እንዲሰማ፣ ሕዝቡም ዘንድ እንዲደርስና ሚዛናዊነት እንዲጠበቅ ለምታደርጉት ጥረት ታላቅ ክብር አለኝ። የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የትግራይ ክልል አስተባባሪ ነኝ። ቀደም ሲል በትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ዋና ጸሐፊ፣ ከዚያም የትንሳዔ ሰብዓ ዕንደርታ ፓርቲ መስራችና ምክትል ሊቀ መንበርም ነበርኩ። አሁን በኢሕአፓ ውስጥ ነው የምገኘው።
እንደ እኔ አተያይ -- አይደለም ስድስት ዓመት ያገለገሉ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት ይቅሩና ለማንም ሰው -- ክብር ሊኖረን ይገባል። ኢትዮጵያውያን ራሳችን ሳንከባበር ማንም ሊያከብረን አይችልም። ክብርት ፕሬዚዳንቷ የፈለጉት ዓይነት የፖለቲካ አቋም ሊኖራቸው ይችላል፤ በመጨረሻም በራሳቸው የማሕበራዊ ትስስር ገጽ ያስተላለፉትን መልዕክት የምናውቀው ነው። ማንኛውም ሰው የፈለገውን የፖለቲካ አቋም ያራምድ፣ ኢትዮጵያ የሁላችንም እስከሆነች ድረስ፣ አንድ ዓይነት አስተሳሰቦችን ብቻ ሳይሆን፤ የተለዩ ሃሳቦች መንሸራሸር አለባቸው የሚል አቋም ነው ያለኝ፡፡ ፕሬዚዳንቷም ስላገለገሉበት ጊዜ በክብር ሃሳባቸውን ገልጸው፣ ፓርላማውም ሃሳባቸውን ሰምቶ በክብር ሊሸኛቸው ይገባ ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ የተሄደበት መንገድ የፖለቲካ ልሂቆቻችን ልዩነትን የሚያስተናግዱበት መንገድ ምን ያህል ደካማ እንደሆነ ነው ያሳየኝ። እንደ አንድ ፖለቲከኛ በጣም ያዘንኩበትና በጣም ቅር ያለኝ ጉዳይ ነው፡፡ ድሮ በስድሳዎቹ በነበሩት ፖለቲከኞች የምናያቸው ችግሮች አሁንም እንዳልተፈቱ ነው ያየሁት። ይሄ ኢትዮጵያን እየመሩ ያሉ ሰዎች ልዩነትን የማስተናገድ አቅማቸው ወይም ትችትን የሚሸከመው ትከሻቸው ምን ያህል ለስላሳና ደካማ እንደሆነ ነው የሚያሳየው።
ስለ አዲሱ ፕሬዚዳንት ንግግር--
እንግዲህ ለእኔ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ማለት ገለልተኛ ናቸው፤ ከማንም ጋር የማይወግኑ፡፡ ለእያንዳንዱ 120 ሚሊዮን ለሚገመት ደቂቅ ኢትዮጵያዊ አባት ናቸው። መሪ ናቸው። ስለዚህ ሁላችንንም በእኩል ዓይን ማየት አለባቸው፡፡ ነገሮችን ፖለቲካዊ ቀለም ከመቀባባት ይልቅ የማቻቻል፣ ወደ መፍትሔና አንድነት የማምጣት ትልቁን ሚና መጫወት ያለባቸው ክቡር ፕሬዚዳንቱ ናቸው ብዬ ነው የማስበው። በአንዳንድ ሚዲያዎች እንደሰማሁት ከሆነ፣ አዲሱ ፕሬዚዳንት ጦርነቱ እንደሚቀጥልና የመሳሰሉ ወደ አንድ ጽንፍ፣ በተለይም ወደ ገዢው ፓርቲ ጥግ የሄደ አቋም ነው ያየሁባቸው።
በእርግጠኝነት፣ እኔ ከአንድ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት የምጠብቀው ዓይነት ንግግር አይደለም፡፡ ወደ አንድ ወገን፣ ወደ አንድ ጽንፍ፣ ወደ አንድ አቅጣጫ የሄዱ ነው የሚመስለኝ፡፡ ይህንን ከእርሳቸው የምጠብቀው አይደለም። እርሳቸው ይበልጡኑ የክብር ፕሬዚዳንት ናቸው። ተምሳሌት ናቸው። የክብር ስራዎችን ነው የሚሰሩት። ለምሳሌ፦ የሌሎች አገራት አምባሳደሮች ሲመጡ መቀበል፣ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የእኛን አምባሳደሮች መሸኘት፣ ጄኔራሎች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲቀርቡ የመሾም የመሳሰሉት ተግባራት አገርን ከፍ፣ ሕዝብን ደግሞ አንድ የሚያደርጉ በይበልጥ ተምሳሌታዊ የሆኑ ናቸው። ከየትኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ሁሉንም ኢትዮጵያዊ -- ተፎካካሪውንም፣ ገዢውንም --- በአንድ ዓይን መመልከት አለባቸው። ምናልባት ይህንን በቀጣይ ያስተካክሉት ይሆናል። በተለይ እየተዋጉ ያሉ ሃይሎችን ወደ ዕርቅና አንድነት በማምጣት ረገድ ተምሳሌታዊ ሚና ይጫወታሉ ብዬ ነው የማስበው።
ከአዲሱ ፕሬዚዳንት የምጠብቀው---
አሁን በፕሬዚዳንትነት የተሾሙት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምሕዳር ውስጥ ከወጣትነታቸው ጀምረው በለሳ ላይ ነፍጥ ይዘው የኢሕአፓ ታጋይ ሆነው የተዋጉ፤ ከእነ አቶ በረከት ስምዖን፣ ኢሕዴን ከመሆናቸው በፊት፣ ከእነ አቶ አዲሱ ለገሰ ጋር የነበሩ የኢሕአፓ ታጋይ ናቸው። በደንብ ፖለቲካን የሚረዱ፣ የሚያውቁ በተለይ ከ1960ዎቹ ጀምሮ የነበረውን ፖለቲካ መረዳት ብቻ ሳይሆን፣ እራሳቸውም ተሳታፊ የነበሩ ሰው ናቸው። ከዚያም ቀጥለው ከ1984 ጀምረው በኢሕአዴግ መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ሃላፊነት የነበራቸው፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ዋና ዲፕሎማት ሆነው ያገለገሉ ናቸው፡፡ ምናልባት ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ይረዳሉ ብዬ ከምጠብቃቸው ጥቂት ሰዎች አንዱ ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ በጣም የዳበረ የዲፕሎማሲና የፖለቲካ ልምድ ያላቸው ሰው ናቸው። ይህ ሰብዕናቸው ለነገይቱ ኢትዮጵያ ትልቅ ሚና ይጫወታል ብዬ አምናለሁ፡፡ በተለይ ትግራይ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ችግር ይታወቃል። አማራ ክልል ያለውም ችግር ይታወቃል። ኦሮሚያ ውስጥም እንዲሁ። ሰላም ከራቀን ቆይቷል። ምንም እንኳን ስልጣናቸው የተገደበ ቢሆንም፣ እኒህን ችግሮች ከመፍታት አንጻር ፕሬዚዳንቱ በጎ ተጽዕኖ ማሳደር ይችላሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡
የኢትዮጵያ ብር ደካማ ከሚባሉት ገንዘቦች ተርታ ተመደበ
የኢትዮጵያ ብር ከሰሃራ በታች ደካማ ከሚባሉት ገንዘቦች ተርታ መመደቡን የዓለም ባንክ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። የዓለም ባንክ አፍሪካ ፐልስ ሪፖርት ላይ እንደተገለጸው፣ ከኢትዮጵያ ብር ባሻገር የናይጄሪያ ናይራ እና የደቡብ ሱዳን ፓውንድ በቀጣናው “እጅግ ደካማ” ከሚባሉት ገንዘቦች መካከል ተመድበዋል፡፡
በዚሁ ሪፖርት ላይ “እ.ኤ.አ. በነሐሴ 2024 የኢትዮጵያ ብር፣ የናይጄሪያ ናይራ እና የደቡብ ሱዳን ፓውንድ በቀጣናው እጅግ በጣም ደካማ አፈጻጸም ካላቸው ገንዘቦች መካከል ነበሩ” ሲል ይገልጻል። በአንፃሩ ግን እንደ ኬንያ ሽልንግ ያሉ ገንዘቦች ከነበሩበት ደካማነት የማገገም ምልክቶችን አሳይተዋል ተብሏል፡፡
እ.ኤ.አ. በነሐሴ 2024 በዓመት እስከ 21 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ማስመዝገባቸውን ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡ “ይህ መሻሻል ቢታይም፣ የብዙ አፍሪካ አገራት ምጣኔ ሃብት የውጭ ምንዛሪ ተግዳሮቶች እየገጠመው ነው” ተብሏል። በዚሁ ሪፖርት መሰረት፤ ናይጄሪያ ከሌሎች የቀጣናው አገራት ጋር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ዕጥረትና የምንዛሪ ተመን ጫና እያጋጠማት እንደሆነ ተብራርቷል።
ናይጄሪያ የውጭ ምንዛሪ ገበያ ማሻሻያን ብትተገብርም፣ የአገሪቱ ገንዘብ አሁንም እየታገለ መቀጠሉን ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ገበያ ማሻሻያ ተፅዕኖው ገና አልታየም። ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በጁላይ 2024 የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን የተገበረች ሲሆን፣ ይህም በገንዘቧ የመግዛት አቅም ላይ ከፍተኛ መዳከም ማስከተሉ ይታወቃል፡፡
በሌላ በኩል፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ 26 ሃገራት ባለፉት ሁለት ዐሥርተ ዓመታት ውስጥ የከፋ የብድር አዘቅት ውስጥ እንደሚገኙ የዓለም ባንክ ይፋ አድርጓል። የተጠቀሱት ሃገራት እጅግ ደካማ ኢኮኖሚ እንዳላቸው ተገልጧል። በዋናነት የኮቪድ 20 ወረርሽኝ መቀስቀስና ግጭቶች የአገራቱን ኢኮኖሚ ይበልጥ ማድቀቃቸውም ተጠቁሟል።
ለቱሪዝም ዘርፍ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና ተቋማት ተሸለሙ
የኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማህበር፣ የ2024 የዓለም ቱሪዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ፣ የመጀመሪያውን የቱሪዝም የመገናኛ ብዙኃን የሽልማት ፕሮግራም ከትላንት በስቲያ ጥቅምት 7 ቀን 2024 ዓ.ም አካሂዷል፡፡
የዘንድሮ የቱሪዝም ቀን “ቱሪዝም እና ሰላም” በሚል መሪ ቃል የሚከበር ሲሆን፤ ማህበሩ ባለፈው ሐሙስ ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሙዚየም ቅጥር ግቢ ባካሄደው የሽልማት መርሃ ግብር፣ በሚዲያው ዘርፍ ቱሪዝሙ ላይ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት፣ፎቶግራፈሮች እንዲሁም የቱሪዝም ባለሙያዎችና ድርጅቶች ዕውቅና ሰጥቷል፡፡
ለማህበሩ የመጀመሪያው በሆነው በዚህ የሽልማት መርሃግብር 10 ተቋማትና ግለሰቦች ዕውቅና ያገኙ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (በሚዲያ ዘርፍ)፣ አንድነት ፓርክ (በመዳረሻ ልማት ዘርፍ)፣ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲቲዩት (በቱሪዝም ተቋማት ዘርፍ)፣የኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ግሩፕ (በሆቴልና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ)፣ ቴዎድሮስ ደርበው (በቱሪዝም ባለሙያ ዘርፍ)፣ ሄኖክ ያሬድ (በጋዜጠኝነት ዘርፍ)፣ ጸሃይ ተፋረደኝ (በጋዜጠኝነት ዘርፍ)፣ አንቶኒዮ ፍዮሮንቴ (በፎቶግራፍ ዘርፍ)፣ ህሊና ታፈሰ (በፎቶግራፍ ዘርፍ) እና አርቲስት ኪሮስ ኃ/ሥላሴ (በልዩ ተመስጋኝ ዘርፍ) ተሸልመዋል፡፡
ከትላንት በስቲያ በተካሄደው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሽልማት መርሃግብር ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ታዋቂ የዘርፉ ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች ታድመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማህበር፣ የኢትዮጵያን ተፈጥሮአዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ መስህቦች የሚያስተዋውቁ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ያቋቋሙት የሙያ ማህበር ነው፡፡
በአማራ ክልል ዳኞችን ያለአግባብ ማሰር ቀጥሏል ተባለ
ከ35 በላይ ዳኞች ያላግባብ ታስረው ተፈተዋል
በአማራ ክልል ከ35 በላይ ዳኞች ያለአግባብ ታስረው መፈታታቸውን ያመለከተው የአማራ ክልል ዳኞች ማሕበር፤ በክልሉ ዳኞችን ያለአግባብ ማሰር መቀጠሉን አስታውቋል፡፡
ማሕበሩ ከትላንት በስቲያ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ የዳኝነት ነፃነት አንዱ መገለጫም ዳኞች ከማንኛውም አካል ጣልቃ ገብነትና ተፅዕኖ ነፃ ሆነው በሕግና በሕሊናቸው ብቻ እንዲሰሩ ማድረግ መሆኑን አስታውሶ፤ “በአማራ ክልል ውስጥ ዳኞችን ያለአግባብ ማሰርና ማዋከብ የተለመደና ከአንድ ዓመት ወዲህ ደግሞ ተባብሶ የቀጠለና ሞትንም እስከማስከተል የደረሰ ሆኗል።” ብሏል፡፡
ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች ከ35 በላይ ዳኞች ያለአግባብ ታስረው መፈታታቸውን ያመለከተው ማሕበሩ፤ ዳኞቹ በዋናነት እየታሰሩ የሚገኙት “ከስራቸው ጋር በተገናኘ” ምክንያት መሆኑን ጠቁሟል፡፡ “በወንጀል የሚፈለጉ እንኳን ቢሆን በሕግ አግባብ ምርመራ አጣርቶ መያዝ ሲገባ፣ ከሚያስችሉበት ችሎት ጭምር በአደባባይ በሚያገለግሉት ህዝብ ፊት እየተያዙ የሚታሰሩበት ሁኔታ እጅግ አደገኛና የተቋሙንም ነጻነት ጨርሶ እያጠፋ የሚገኝ ነው።” ሲል ማሕበሩ ተችቷል፡፡
ይኸው እስር “ዳኞች ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩ እንቅፋት የሆነና ክብራቸውንም የሚነካ ነው፡፡ ሁሉም ዳኛ ለሙያው ያለው ፍቅር እንዲቀንስና የስራ ሞራልን እየጎዳ ያለ ተግባር ነው” ያለው መግለጫው፤ “እስካሁን ባለው ሂደትም የማሕበሩ አመራሮች በተለያየ እርከን ከሚገኙ የፍርድ ቤት አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን ችግሩ በንግግር እንዲፈታ ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ ቢሆንም፣ ችግሩ አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል።” ሲል አመልክቷል።
በእስር ላይ ከሚገኙ የፍርድ ቤት ዳኞች መካከል፣ የባሕር ዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለት ዳኞች፣ የባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ሁለት ዳኞች፣ በሰሜን ሸዋ ዞን፤ በቀወት ወረዳ ፍርድ ቤት ሁለቱ የስራ ሂደት አስተባባሪ ዳኞችና በሸዋ ሮቢት ወረዳ ፍርድ ቤት አንድ ዳኛ እንዲሁም በደቡብ ወሎ ዞን፣ ደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት አንድ ዳኛ መታሰራቸውን ማሕበሩ በመግለጫው ዘርዝሯል። የአማራ ክልል፤ ዳኞቹ “በአስቸኳይ” እንዲፈቱ እንዲያደርግ፣ በቀጣይም በዳኞች ላይ የሚፈጸም “ያልተገባ” እስር እንዲቆምና ይህን ተግባር በሚፈፅሙ የጸጥታ አካላት ላይ አስተማሪ እርምጃ እንዲወሰድ ሲል ማሕበሩ አሳስቧል፡፡
የአማራ ክልል ዳኞች ማሕበር በ2012 ዓ.ም. ተመስርቶ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወስ ነው።