
Administrator
አሰብ - ቀይ ባህርና ወደባችን በዚያን ጊዜ
“--ቢሆንም የዮሃንስ ተፈራ አጻጻፍ መንፈሱ በሕይወት ታሪክ ላይ ስለተመሰረተ፣ እንደ ሕዋስ
ቆዳን ዘልቆ ይገባል። ሌላው ጠንካራ ጎን የደራሲው የጽሁፍ ጥንቅር በግብዝነት ስላልተመሰረተ፣
ከታችኛው ማህበረሰብ ተናንሶ መብላት መጠጣቱ የምርም ‘ጥበበኛና ከንቲባ ከሕዝቡ ጋር ነው
መኖር ያለበት።’ የሚለውን ተለምዷዊ ብሂል ማሟላቱ መልካም ነው።--”
ጥንካሬ፦
ጠንካራው ጎኑ ስራው ብቸኛና አንጡራ የሚባል ነው። ስለ አሰብ የዚህ አይነት መጽሐፍ ተጽፎ አያውቅም። በልብወለድ ተደርጎ “ሄላ” የሚል መጽሐፍ አስታውሳለሁ። በኢ-ልብወለድ ግን ይህ መጽሐፍ ብቸኛው ነው። የዶ/ር ያእቆብ ኃ/ ማርያም “አሰብ የማናት” የሚለውም ቢሆን፣ የፖለቲካ ትንታኔ እንጂ እንዲህ ሰነድና ዋቢ መጻህፍት አልቦ ከሆነ፣ የህይወት ነጸብራቅ ላይ የተመሰረተ የእውቀት ብልጭታ አይደለም። የጽሁፍ ስራውን አድካሚ፥ መጽሐፉንም ወሳኝ የሚያደርገውም ይህ ነው።
የአሰብ ነዋሪዎችን ሕይወትና ውጣ ውረድ፥ የገቢ ምንጫቸውንና ባህሪያቸውን ለመሳል የተከፈለው ዋጋ፣ ከ400 ገጾች በላይ ያሉትን ኪታብ አል-አሰብ መስጠቱ ጥኡም ነው። የደራሲው ግልጽነትና አይኑን በRomanticism መነጽር ጋርዶ፣ ስለሌላው ጾታዊ ንሸጣው አልደበቀም። አንገቱ እስኪበጠስ እንደኔም ባያይ በአፋር ሴቶች መልክ መማረኩን አምኗል። Realism technic ተጠቅሞ መጻፉ ያስመሰግነዋል። ለምን? አኗኗራችን ንፍጥ ይበዛዋል።
ከአወቃቀር አኳያ ዘርፈ ብዙ (multi layered) ነው። ባህላዊ ዘውግም ማህበረሰባዊ ጠባይም አስተያይቶ ነው የጻፈው። ስለ ወደብ ጥቅሞች ይህ ትውልድ እንዲያውቅ የለፋበት ሂደት መልካም ነው። በርግጥ እዚህ ጋ ባለ ዳሰሳ፣ የ“አረናው” አስራት አብርሃም ባሳተመው፣ “ከሀገር በስተጀርባ” በሚለው፣ ህወሓትን በሚወግርበት መጽሐፉ፣ በአጭርና በእጭቅ ትንታኔ ገልጿል። ቢሆንም የዮሐሃንስ ተፈራ አጻጻፍ መንፈሱ በሕይወት ታሪክ ላይ ስለተመሰረተ፣ እንደ ሕዋስ ቆዳን ዘልቆ ይገባል። ሌላው ጠንካራ ጎን የደራሲው የጽሁፍ ጥንቅር በግብዝነት ስላልተመሰረተ፣ ከታችኛው ማህበረሰብ ተናንሶ መብላት መጠጣቱ የምርም ‘ጥበበኛና ከንቲባ ከሕዝቡ ጋር ነው መኖር ያለበት።’ የሚለውን ተለምዷዊ ብሂል ማሟላቱ መልካም ነው። ጠንካራ ግለሰቦች እንደ ኮማንደር ዘለቀ ቦጋለ፣ ጥናታዊ ፊልም ቢሰራባቸውና፣ በስማቸው መንገድ ብሎም የግንባታና የሀገርን መውደጃ ዝግጅቶች ላይ በስማቸው Conference Paper ቢቀርብ ጥሩ ነበር-ይህም የመጽሐፉ ትሩፋት ነው።
ድክመት፦
አንዳንድ ቦታ ላይ የሀሳብ ወጥነት ጉድለት ይታያል። ‘ስለምን የሀሳብ ወጥነት ጎደለው?’ ሊባል ይችላል። ይህም የሚከሰተው የጽሁፍ አባዜው እንደ ዛር ሲሰፍር ከሚመጣው የሃሳብ ግትልትል ናዳ ለማምለጥና ድምጹንና ምስሉን ከመፍራት ነው፡፡ ጽሁፉ ከውስጥ በግፊት መውጣት ሲጀምር፣ ምስሉና ድምጹ ከውጪ ኩልል እያለ ይመጣል፣ ይሄኔ ሰዎች ከውጪ የሚሰሙትን ድምጽ መበርገግ ይጀምራሉ። በዚህም የተነሳ በሰላሙ ጊዜ ሲታሰቡ የነበሩ ሀሳቦችን ማስገባት ይመጣል-(አላበድኩም ለማለት)። እንግዲህ ዛሩ ደግሞ ነጭናጫ ነገር ስለሆነ ትእግስት የለውም፤ ተቀይሞ እብስ ሲል ጸሃፊው በአእምሮው Mechanical ትግል ይጀምራል። ይሄኔ ቅልቅሉ ብቅ ይላል። የእርግጠኝነት ስሜት መጉደል፥ የእርማት ችግርና የዋቢ መጻሕፍት አሰዳደር መጽሐፉ ለአራተኛ ዙር ከታተመ ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው።
መጽሐፉ ባያልቅም እኛ ስንጨርስ፦
እንግዲህ- የድንቁርና ማሰሪያው ንባብ ነውና፤ መጽሐፉ ይነበብ ዘንድ የጥበብና የታሪክ ስንክሳር ያስገድዳል።
“ሁሉንም ዕንቁላልህን አንድ ቅርጫት ውስጥ አታስቀምጥ” “ገና ሳይፈለፈሉ ጫጩቶች መቁጠር አትጀምር”
ሁለት መንገደኞች ራቅ ወዳለ አገር ለመሄድ ጉዞ ጀምረዋል፡፡ ሁለቱም የተለያየ ጠባይ ያላቸው ናቸው፡፡
አንደኛው፤ በህይወቴ ሙሉ ዕውነት ፈፅሞ ተናግሮ የማያውቅ ነው፡፡
ሁለተኛው ደግሞ ዕድሜውን በሙሉ ውሸት የሚባል ነገር ፈፅሞ ተናግሮ የማያውቅ ነው፡፡
ሁለቱ መንገደኞች ብዙ ከተጓዙ በኋላ፣ ወደ ዝንጀሮዎች አገር ይደርሳሉ፡፡ የዝንጀሮዎቹ ንጉስ መንገደኞች መምጣታቸውን ይሰማና፣ ወደ ዙፋኑ እንዲቀርቡ ያዛል፡፡ ግርማ - ሞገሱንና ታላቅነቱን ይረዱ ዘንድ ዙፋኑ ላይ በክብር ይቀመጥና፣ ሌሎቹን ባለሟሎቹንና የበታች ሹማምንቱን በግራና በቀኝ እንዲኮለኮሉ ያደርጋል፡፡ ከግራ ከቀኙ የተደረደሩት ዝንጀሮዎች ረዥም መስመር ሰርተዋል።
መንገደኞቹ ዙፋኑ ፊት ቀርበው ለጥ ብለው እጅ ሲነሱ፤ የዝንጀሮዎቹ ንጉስ፤
“ረዥም መንገድ ላይ እንዳላችሁ ሰማሁ፤ ዕውነት ነው?” አሉ፡፡
ዕውነት የሚናገረው ሰውዬ፤
“አዎን ንጉሥ ሆይ፤ ገና ሁለት ቀንና ሌሊት ተጉዘን ነው ወደ አሰብንበት አገር የምንደርሰው” አለና መለሰ፡፡
“ለምን ጉዳይ ነው የምትሄዱት?”
“የምንሄድበት አገር ያሉት ሰዎች እጅግ የሰለጠኑ ናቸው ይባላል፡፡ እኛ ገና አላየናቸውም። ከነሱ ትምህርት በመውሰድ ያገኘነውን አዲስ ነገር፣ ወደ አገራችን አምጥተን እኛም እንደነሱ ለመሰልጠን አስበናል” አለ፡፡
ንጉሱም፤ “መልካም፡፡ ሃሳባችሁ የተቀደሰ ነው፡፡ ጥሩ ነገር እንዲገጥማችሁ እመኛለሁ፡፡ አሁን ያስጠራሁዋችሁ ስለ እኔና ስለ ባለሟሎቼ ምን እንደምታስቡ እንድትነግሩኝ ነው”
ይሄኔ ውሸት የመናገር ጠባይ ያለው መንገደኛ፤
“ንጉሥ ሆይ፤ ማንም እርስዎን ያየ ሰው እጅግ የተከበሩና ኃያል ንጉስ መሆንዎን አይስተውም።”
“ባለሟሎቼንና ሹማምንቴንስ እንዴት ታያቸዋለህ?”
“እነሱማ አንዳቸውም ከእርሶ ጋር አይተካከሉም፡፡ እርሶ እዚያ አናት ላይ፤ እነሱ ደግሞ እዚህ ታች እግርጌ ናቸው፡፡ የጌታቸውን ክብርና አዋቂነት ይፈራሉ”
የዝንጀሮዎቹ ንጉስ በጣም ተደሰተ፡፡ መደሰቱ እስከሚታወቅበት ድረስ እየተቅበጠበጠ በባለሟሎቹ ፊት ወዲያ ወዲህ ሲል ቆይቶ፤
“እንዳንተ፤ ሁሉ ሰው ዕውነቱን ቢያውቅ የት በደረስን፡፡ እንዳንተ ያሉ ሰዎች ይህቺን ዓለም ቢሞሉዋት የእኛ ሀገር ብቻ ሳትሆን፣ ጎረቤቶቻችንና ከዚያም የራቁት ሀገሮች የት በደረሱ፡፡ በል እንካ ይህን የከበረ ስጦታ ውሰድ፡፡ ስለተናገርከው እውነት ማስታወሻ ይሁንህ” አለና ስጦታውን አበረከተለት፡፡
ይህንን ያስተዋለው ሁለተኛው መንገደኛ በሆዱ እንዲህ አሰበ፡-
“ጌታው፤ አንተስ ስለእኔና ስለባለሟሎቼ ያለህ አስተያየት ምንድን ነው? እንዴት አገኘኸን?” ዕውነት ተናጋሪው መንገደኛም፤
“ንጉስ ሆይ እርሶ ግሩም ነዎት፡፡ ባለሟሎዎችም ግሩም ናቸው፡፡ በምንም አትተናነሱም፡፡ በምንም አትበላለጡም፡፡ ሁላችሁም አንድ አይነት ናችሁ” አለ፡፡
የዝንጀሮዎች ንጉስ ቱግ አለ፤ ተቆጣ፡፡ እጅግ ከመናደዱም የተነሳ፤
“በዝንጀሮዎቹ ጥፍር እየተቧጠጠ እየተሰቃየ እንዲሞት!” ሲል ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
***
ንጉሶች፣ መሪዎችና አለቆች ሁሌም ከሌሎች ባለሟሎችና አጋሮቻቸው እንዲሁም የሥራ ባልደረቦቻቸው እኩል ናችሁ እንዲባሉ አይፈልጉም፡፡ የተለዩ መሆናቸውን፣ የተሻሉ መሆናቸውን፣ ከሁሉ በላይ መሆናቸውን የሚነግራቸውን አማካሪ ነው የሚወዱት፡፡ በጊዜና በታሪክ አጋጣሚ እንጂ እነሱም እንደማናቸውም ባለሟል እንደነበሩ፤ ይዘነጋል፡፡ አንገረ ፈላስፋ፤ “ሸክላ ሲሰበር ገል ይሆናል፤ መኳንንትም ሲሻሩ ያው እንደማንኛውም ሰው ይሆናሉ” የሚለውን ይረሱታል፡፡ እንደ ዕውነቱ ከሆነ ሲሾሙና ሥልጣን ሲይዙ ራሳቸውን ከጥንት ወዳጆቻቸው የተለየ ፍጡር አድርገው ባያዩ፤ ከሥልጣን ሲወርዱ የተዋረዱ አድርገው ራሳቸውን ከህዝብ እንዳይሸሽ በጠቀማቸው ነበር። በእርግጥም፤ ራሳቸውን የተለየ ፍጡር አድርገው ማየት፤ የተለየ እንክብካቤ፤ የተለየ ጥቅም፣ የተለየ ከበሬታ ወደመፈለግ እንዲያመሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን፣ በአንደኛው ቴያትሩ ውስጥ “የዘመኑ ተራማጅ፤ ሥልጣን በሸተተው ማግሥት አካሄዱ፣ አረማመዱ ሁሉ እንደ ድመት ኮርማ ይሆናል” ይላል፡፡ በመሰረቱ ማናቸውም ሥልጣን ላይ የሚቀመጥ ሰው የዚያ ወንበር ተሸካሚ፣ የዚያ ኃላፊነት አገልጋይ እንጂ በዚህ ሥልጣን ተገልጋይና የግል ጥቅሙን አሳዳጅ፣ የግል ወገናዊነቱን ተግባሪ ሊሆን አይደለም፡፡ ራስን ልዩ አድርጎ ማስቀመጥ ተነጥሎ መታየትን ብቻ ሳይሆን ዒላማ መሆንን ያስከትላል ይሏልና፤ በዚህም ረገድ ቢሆን አደገኛ ነው፡፡ ዛሬ ያልነውን ነገ መሻር ተዓማኒነትን ያሳጣል፡፡ በምንም ረገድ፤ በምንም ዘዴ ተጠቅመን እናስተባብለው ታዳሚው በልቡ ፅላት እንደሚፅፈው አለመርሳት ነው፡፡ ታዳሚ ጆሮ የገባ ነገር በዋዛ አይፋቅም፡፡ ይህን ምንጊዜም ማስተዋል ይበጃል፡፡ አንዴ ተዓማኒነትን ካልጣን መልሰን ማግኘት ዘበት ነው፡፡ አንድ ሁለት ግለሰቦችን ቡድኖችን ማታለል ይቻል ይሆናል፤ ህብረተሰብን ግን ማታለል አይቻልም። ይህን እንደዋና መመሪያ ከመያዝ ዋና ነገር ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ግን የምንመራውን ህዝብ ምንም ያህል መልካም ፖሊሲ ብንቀርፅለት፤ ጊዜና ቦታ ለይተን፤ መጠንና ልክ አውቀን፤ ባህል ልምዱን አጣጥመን፤ ካላቀረብንለት ከየትም ከየትም ከምእራብም ከምስራቅም ያሰባሰብነው መመሪያና ደንብ እንዲሁም መተዳደሪያ፤ ባንድ ጊዜ እናስውጥ ብለውን ተርፎ የሚፈሰው፣ ሳይጨበጥ የሚሰበረው፣ ለአደጋ የሚያጋልጠው ይበዛና ካሰብነው ቦታ እንዳንደርስ እንሆናለን። ይኼ በየዘመኑ ደጋግመን አይተናል፡፡ በአንፃሩ ስለተጠነሰሰ ብቻ የማይጠመቅ ብዙ ጠላ አለ፡፡ ስለተወራ ብቻ የልብ የማያደርስ ብዙ ደጋግ እቅድ አለ፡፡ ከወረቀት የማያልፍ አያሌ ህግና ደንብ አይተናል፡፡ የማስፈራሪያ ያክል የሚጮህበት አያሌ መሬት ያላረፈ መፈክር ታዝበናል፡፡ (የቀድሞ መሪ አብዮቱ በፈነዳው በስምንተኛ አመቱ “የምንለውን ብለናል፤ የምናደርገውን እንጀምር” ማለታቸውን ልብ ይለዋል፡፡) ለፖለቲካዊ ልዩነቶች ሁሉ ወታደራዊ እርምጃዎችን እንደብቸኛ መፍትሄ መውሰድ ለአገርም ለመንግስትም ለህዝብም አይበጅም፡፡ ጦርነት ከአንዱ ክልል ወደ ሌላው ክልል ማሻገር አይመከርም ዘላቂ መፍትሄም አያመጣም፡፡
“ሁሉንም እንቁላልህን አንድ ቅርጫት ውስጥ አስቀምጥ” የተባለውን ያህል፤ “ገና ሳይፈለፈሉ ጫጩቶችህን መቁጠር አትጀምር” እንደሚባል አለመርሳት ታላቅ ነገር ነው፡፡ ሁሉንም አባልህን በአንድ አሸንዳ እንዲፈሱ አታድርግ፡፡ የሃሳብ ልዩነትህን ውደድ፤ አስተናግድ፡፡ ሁሉንም ወዳጆችህን ለአንድ ጉዳይ አታውል፡፡ ሁሉንም ተከታይህን የአንድ ሀሳብ ቁራኛ አታድርግ ማለትም ያስኬዳል፡፡
“የጋሞ ህዝብ ጥያቄ በክላስተር የመደራጀት ሳይሆን ራስን በራስ የማስተዳደር ነው”
የጋሞ ህዝብ ጥያቄ በክላስተር የመደራጀት አይደለም ያለው የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጋዴፓ)፤ህዝቡ ለረዥም ጊዜ ሲጠይቅ የቆየው ራሱን በራሱ የማስተዳደርና በክልል የመደራጀት ህገመንግስታዊ መብቱ እንዲከበርለት ነው ብሏል፡፡
የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራሮች፣ ዛሬ ከሰዓት በኋላ 8 ሰዓት ላይ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ጽ/ቤት አዳራሽ ውስጥ፣ በአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች አደረጃጀት ዙሪያ መንግሥት እያደረገ ካለው እንቅስቃሴ ጋር በተገናኙ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
አዲሱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመሰረቱት የጌዲኦ፣ የወላይታ፣ የጋሞ፣ ጎፋ፣ የኮንሶ፣ የደቡብ ኦሞ ዞኖች እንዲሁም የቡርጂ፣ የአማሮ፣ የደራሼ፣ የባስኬቶ እና የአሌ ልዩ ወረዳዎች መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የጋሞ ዞን በክላስተር የክልል አደረጃጀት ውስጥ መካተቱን እንደማይቀበለው ይገልጻል፡፡ የጋሞ ህዝብ ጥያቄ በክላስተር ልደራጅ የሚል አይደለም ያለው ፓርቲው፤ ህዝቡ ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ-መንግሥታዊ መብቱ እንዲከበርለት ነው የጠየቀው ብሏል፡፡
”የጋሞ ዞን ህዝብ ጥያቄ ከማዕከልነት ጋር የተያያዘ ወይም የከተማ አመዳደብ ኢ-ፍትሃዊነት ጉዳይ አይደለም“ ያሉት የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ቡንካሾ ሀንጌ፤የህዝቡ ጥያቄ የክልልነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ ነው ብለዋል፤ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ በሰጡት ማብራሪያ፡፡
“የጋሞን ህዝብ በክላስተር መደራጀት ይጎዳዋል የምንለው ያለምክንያት አይደለም” የሚሉት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው፤ “የጋሞ ህዝብ በፊት አዋሳ መጥቶ ነበር አገልግሎቶችን የሚያገኘው፤ በአዲሱ አደረጃጀት ግን አገልግሎት ለማግኘት ዲላ ድረስ መምጣት አለበት፤በዚያ ላይ ከአንድ ማዕከል አገልግሎቶችን ማግኘት የማይቻልበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡“ ሲሉ አስረድተዋል፡፡
“በክላስተር መደራጀትን የተቃወምነው አርባምንጭ በአዲሱ የክልል አደረጃጀት ዋና መቀመጫ ሳትሆን በመቅረቷ ነው ብለው የሚያወሩ አንዳንድ ወገኖች አሉ፤ ይሄ ግን ሃሰት ነው፡፡” ያሉት የፓርቲው የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ኤልያስ ዛለ በበኩላቸው፤ ህዝቡ ያቀረበው የማዕከልነት ጥያቄ ሳይሆን፣ “ክልላችን ጋሞ፣ ማዕከላችን አርባምንጭ” የሚል ነው ብለዋል፡፡
ፓርቲያቸውም ሆነ የጋሞ ህዝብ የማዕከልነትን ጥያቄ እንዳላነሱ የገለጹት የፓርቲው ም/ፕሬዚዳንት አቶ ዳሮት ጉምአ ጉጌ፤ “በክላስተር አደረጃጀት ማዕከል የሚባል ነገር ያለ አይመስልም፤ እኛ የጠየቅነው የጋሞ ክልላዊ መንግሥትን የመመሥረት ህገ-መንግስታዊ መብታችንን ነው፤ ማዕከሉንም አርባምንጭ ማድረግ፡፡” ሲሉ በመግለጫው ላይ ተናግረዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ፤ “የጋሞ ሕዝብ በክልል የመደራጀትና ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ-መንግሥታዊ መብቱ ይከበር፤ሕዝቡ ያቀረበው ህጋዊ ጥያቄም ሕገ-መንግሥታዊ መልስ ይሰጠው!” በሚል መሪ ቃል፣ ጋዴፖ ባለ 7 ገጽ የአቋም መግለጫ በዛሬው ዕለት አውጥቷል፡፡
”የጋሞ ሕዝብ ከላይ እስከ ታች ባሉት መንግሥታዊ መዋቅሮቹና ምክር ቤቶቹ አጽድቆ ያቀረበው የጋሞ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የክልልነት ጥያቄ ሕገ-መንግሥታዊ ምላሽ ባላገኘበት ሁኔታ፣ በብልጽግና ካድሬዎች የሸፍጥ አሠራር የመጣን ክላስተር የክልል አደረጃጀት” እንደማይቀበለው በመግለጫው የጠቆመው ጋዴፓ፤“መንግሥት ይህን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ የማሻሻያ እርምጃ እንዲወስድ” በአጽንኦት ጠይቋል፡፡
“መንግሥት የጋሞን ሕዝብ ክልላዊና ሀገራዊ መብት፣ ጥቅምና ክብር በሕገ-መንግሥታዊ መንገድ ያላከበረውን የአዲሱን የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምሥረታ ሒደት ከማጣደፍ እንዲቆጠብ” ያሳሰበው ፓርቲው፤ “ይልቁንም የጋሞ ሕዝብን በጉዳዩ ዙሪያ ከላይ እስከ ታች የሚያወያይበትን አካታችና አሳታፊ መድረኮች በአስቸኳይ እንዲፈጥር“ በዚሁ መግለጫው ጠይቋል፡፡
አዲሱን አደረጃጀት በመቃወም ለነሐሴ 4 ቀን 2015 ዓ.ም በዞኑ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶ እንደነበር ያስታወሰው ጋዴፓ፤ ነገር ግን የዞኑ አስተዳደር ወታደራዊ ሃይል በማሰማራት፣ ለሰልፍ ከወጡት 400 ያህሉን ማሰሩን ጠቁሞ፣ የጋሞ ሕዝብ ኃሳቡን በነፃነት የመግለጽ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱን የረገጡት የጋሞ ዞን አስተዳደርና የጋሞ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ፣ በሕግ እንዲጠየቁና፣ ይህም መተግበሩን መንግስት ለሕዝብ እንዲገልጽ አሳስቧል፡፡
“ቀንጢቻ ማይኒንግ“ በመጪው መስከረም ወር ሥራ ይጀምራል ተባለ
• “ድርጅቱ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር፣ አገሪቱ በዓመት 1.2 ቢ. ዶላር
የውጭ ምንዛሪ ታገኝበታለች”
• “ቀንጢቻ ማይኒንግ”፣ ለሰባቦሩ ወረዳ አስተዳደር የ2 ሚ. ብር ድጋፍ አድርጓል
በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን፣ ደርሚ ወረዳ፣ ቀንጢቻ አካባቢ የሚገኘውና የሊትየም ማዕድን ለማምረት የተቋቋመው ቀንጢቻ ማይኒንግ ኃ.የተ.የግ.ማህበር፤ በመጪው መስከረም ወር ሥራ እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡
ይህ የተገለጸው በዛሬው ዕለት የድርጅቱ አመራሮችና ባለአክሲዮኖች፣ የፕሮጀክቱን ሂደትና የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁም 150 ሚሊዮን ብር የወጣበት የሊትየም ማዕድን ማውጫ ወደ ኢትዮጵያ እያስገባ መሆኑን በተመለከተ በሸራተን አዲስ ሆቴል፣ ለባለድርሻ አካላትና ለጋዜጠኞች ማብራሪያ በሰጡበት መርሃግብር ላይ ነው፡፡
ባለፈው ሳምንት፣በምሥራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው ነው የተባለ የሊትየም ማዕድን ማውጫ ማሽነሪ፣ በቀጣይ ሳምንታት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገባ፣ የቀንጢቻ ማይኒንግ ኃ.የተ.የግ.ማህበር መሥራችና ከፍተኛው የአክሲዮን ባለድርሻ የሆኑት ሀጂ አሊ ሁሴን፣ ከሳኡዲ አረቢያ በስካይፒ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማስታወቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
የቀንጢቻ ማይኒንግ መሥራችና በኢትዮጵያ የአፍሪካ ማይኒንግና ኢንጂነሪንግ ተወካይ የሆኑት ሀጂ አሊ ሁሴን በዛሬው የሸራተን አዲስ መርሃ ግብር ላይ በሰጡት ማብራሪያ፣ ከፍተኛ መዋዕለንዋይ የፈሰሰበት ይኸው የሊትየም ማሽን፣ ከደቡብ አፍሪካ ወደ ኢትዮጵያ በመርከብ የተጫነ ሲሆን፤ በመጪው መስከረም ወር ወደ አገር ውስጥ እንደሚገባና ድርጅቱም ሥራ እንደሚጀምር አስታውቀዋል፡፡
ሁለት ተጨማሪ አቅም ያላቸው የሊትየም ማውጫ ማሽነሪዎች ከ2023 የፈረንጆች ዓመት ማገባደጃ በፊት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚያስገቡ የገለጹት ሀጂ አሊ ሁሴን፤ይህም በጠቅላላው በሰዓት 270 ቶን ሊትየም የማምረት አቅም እንደሚሰጣቸውና በዓለም ላይ በጣት ከሚቆጠሩ ጥቂት የሊትየም አምራች አገራት ጎራ እንደሚያሰልፋቸው ጠቁመዋል፡፡
ቀንጢቻ ማይኒንግ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባና የሊትየም ማዕድን ከሀገራችን ከርሰ ምድር ወጥቶ ለዓለም ገበያ ሲቀርብ፣ ኢትዮጵያ በዓመት 1.2 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ታገኝበታለች ያሉት የድርጅቱ መሥራች፤ ከዚህም ባሻገር ለ500 ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል እንደሚፈጠርላቸውና መንግሥትም ከፍተኛ የታክስ ገቢ እንደሚያገኝበት አክለው ገልጸዋል፡፡
ቀንጢቻ ማይኒንግ ኃ.የተ.የግ.ማህበር፣ በአጠቃላይ በ80 ቢሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ወደ ሥራ መግባቱን ያስታወቁት የድርጅቱ መሥራች፤ በዓለም ላይ አሉ የተባሉ የማዕድን ፍለጋ ባለሙያዎችን አሰማርተው ለተጨማሪ ኢንቨስትመንት እየተዘጋጁ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡
“በቀጣይነትም ሊትየም፣ የባትሪ ምርት ዋነኛ ግብአት በመሆኑ፣ ማዕድናችንን እየላክን የበዪ ተመልካች እንዳንሆን፣ የሊትየም ባትሪ ፋብሪካ ለመክፈትም፣ ጥናቱን አጠናቅቀን በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡” ብለዋል፤ሀጂ አሊ ሁሴን፡፡
በዛሬው መርሃግብር ላይ የቀንጢቻ ማይኒንግ ፕሮጀክቶችን አጠቃላይ ሂደት የሚያሣይ የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን ለዕይታ የቀረበ ሲሆን፤ ኤግዚቢሽኑ በባለድርሻ አካላትና በክብር እንግዶች ተጎብኝቷል፡፡
በሌላ በኩል፣ ቀንጢቻ ማይኒንግ ፈቃድ ወስዶ ፕሮጀክቱን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ከፍተኛ አስተዋጽኦና ድጋፍ ያደረጉ አካላት የዕውቅና ሽልማት በድርጅቱ የተበረከተላቸው ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ የፌደራል ማዕድን ሚኒስቴር፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት፣ የሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ የቆንጢቻ ቀበሌ ይገኙበታል፡፡
ከዕውቅና ሽልማቱ በተጨማሪ፣ ቀንጢቻ ማይኒንግ ኃ.የተ.የግ.ማህበር፣ ለሰባቦሩ ወረዳ አስተዳደር የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ቀንጢቻ ማይኒንግ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ባዘጋጀው በዛሬው የፕሮጀክት ሂደት ማብራሪያ መርሃግብር ላይ ባለድርሻ አካላት፣ አምባሳደሮች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የባንክ ተወካዮች፣ አባ ገዳዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ጋዜጠኞች ተገኝተዋል፡፡
ስካር ይለቃል፤ ድድብና አይለቅም!
“…ከመሰላሉ ማውረድ አለባቸው የሚላቸውን ሰዎች ዝንተ አለማቸውን ስማቸውን እንደ ተራራ ሲቆለል የኖረ ነው” የሚል የፅሁፍ መግቢያ ያደረገውን… የፅሁፉም ርእስ … “ደራሲ ብሎ ጠቢብ አይታየኝም” … የሚል ነበር፡፡ በእኔ በኩል ፀሃፊ ከመግቢያውም መስተካከል አለበት እላለሁ፡፡ ለዚህም የማነሳው ሃሳብ እነዚህ ሰዎች… ወደ መሰላሉ እንዴት ወጡ? ማን አወጣቸው? የሚለውን ማየት ያስፈልጋል። በመጀጨመሪያ ደረጃ ሰዎቹን ወደ መሰላሉ ያወጣቸው ስራቸው በማስከተለም ህብረተሰቡ ነው፡፡ ህብረተሰቡ ወደ ላይ ለመውጣቱም ሆነ ወደ ታች ለመውረድ ከፍተኛውን አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡ ስለሆነም ማህበረሰቡ ወደ መሰላሉ ማውጣት ብቻ ሳይሆን እንድትመላለስ የሚያደርግህ ዝም ብሎ አይደለም፡፡ ይህም ሲባል ጠቃሚ የሆነ ምርምር በህክምና፣ በእርሻ፣ በሳይንስ፣ በፍልስፍና እንዲሁም በስነ ፅሁፍ በድርሰት… በግጥም… በቅኔ… ህይወትን መምራት የምትችልበትን ቀመር በመቀመር ህብረተሰቡ… አንድ … ሁለት… እርምጃ ቀድመህ ስትገኝ ህብረተሰቡ እራሱ እዛ መሰላል ላይ ያስቀምጥሀል፡፡ ምክንያቱም ሁሌም ማህበረሰቡ ለህይወቱ ተሞክሮውን፣ መፍትሄ፣ ብሎም ብርሃንን አግኝቶበታል፡፡
ኤፍራጠስ፤ አንተ እንዳልከው ላንተ ማዳም ሲጁ ወከር ትበልጥብሃለች …. ይሁን ስራዋ ለውጫዊ ውበት ይጠቅማልና… ለውስጣዊ ውበትህስ ማንን? ወይስ ለውስጣዊ ውበት አትጨነቅም? አለኝ ካልክስ ከየት አመጣኸው?... እንደው ለማለት ያህል ማህበረሰቡም የራሱ የሆነ ውስጣዊ ውበት አለው፡፡ በእኔ እምነት ስነፅሁፍ ድርሰት፣ ግጥም፣ ቅኔ ብሎም ፍልስፍና አለ ሊባል የማይችል ውስጣዊ ውበት ወይም ንቃተ ህሊና ፍላጎትን እና ጉጉትን እያንዳንዱ ግለሰብ ውስጥ ይፈጥራሉ፡፡ ይህ ደግሞ ምን አይነት እንደሆነ ከጊዜ በፊት ለማስረዳት ጊዜ መፍጀት ይመስለኛል፡፡
እዚህ ላይ እኔ ከነዚህ ሰዎች አልተጠቀምኩም ማለት ሌላ ነገር ነው፡፡ አይጠቅሙም ማለት ግን ትንሽ አስገዳጅነት ባህሪ አለው፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን የተጠቀሙትን መንካት፣ የናንተን አፍሩስና በእኔ አይነት ገንቡ እንደ ማለት ነው። … እኔ በበኩሌ የዚህ አይነቱን አቀራረብ አልጣመኝም፡፡ እስቲ ሳነብ ያገኘሁትን ላካፍልህ።
“የሰው ልጅ ጌጡ ጥበብ ነው እና ለጠቢባን እውቀትን ያበዙ ዘንድ መናገር ተገቢ ነው፡፡”
ጠቢብ እንዲህ አለ፡- “በጭለማ ማየት እችላለሁ…” የጠቢቡን አባባል ያልተረዳ ሰነፍ ደግሞ ጠየቀ፡-
“በጨለማ ማየት ከቻልክ ታዲያ ለምን መብራት ይዘህ ትሄዳለህ?” ጠቢቡ ከሰነፍ የሚጠብቀው ጥያቄ ነውና ሳይደነቅ መለሰለት፡- “እንደ አንተ አይነት በጨለማ ማየት የማይችል መጥቶ እንዳይገጨኝ ነው” አለው፡፡ ጠቢብ መሆን ባይቻል፣ የጠቢብን ብርሃን ማየት ይቻላል፡፡ ስለሆነም ብርሃኑን በመጠቀም ለህይወት የሚጠቅመውን (የሚበጀውን) ማየት የተመረጠ ይሆናል ብዬ ነው፡፡
እብደት ማለት ምን ማለት ነው? ለእኔ እብደት ማለት … አንድ ሰው ካለው ማህበረሰብ ወጣ ያለ አስተሳሰብ ሲኖረው ነው… ሰዎች ያ ሃሳብ ከራሳቸው በላይ በሆነ ጊዜ አበድን ይላሉ… ግን ያበደው ማን ይሆን? ኤፍራጠስ፤ በፅሁፍህ ላይ “ግማሹ አብዶ ነው የሚሞተው” ብለሀል። ለዚያም የጠቀስከው አማኑኤል ካንትን ነው። ምን አልባት ‘አማኑኤል’ እንደ ‘ባህሉ’ ሆኖ ሊሆን ይችላል፡፡ ባህሉን የቱንም ያህል በጥበብ ቢበስል፣ በዚሁ ምክንያት የሚደርስበትን አደጋ ፍራቻ ጥበብን በእብደት መጋረጃ ሸፍኖት ነበር። ለዚሁም ምሳሌ፡-
አንድ ቀን ባህልን ከንጉስ መቀመጫ ተቀምጦ ተገኘ፡፡ በዚህ ምክንያት ወታደሮቹም ቆዳው እስኪላጥ ሲገርፉት… ጩኸቱን የሰማው ንጉስ፣ መጣና ወታደሮቹን “እናንተ እብዶች፣ ባህሉን እብድ መሆኑን አታውቁም” አላቸው፡፡
ባህልሉን “ንጉስ ሆይ ወታደሮችህን ተዋቸው፤ እኔን ያስለቀሰኝ ሌላ ነው” አለ፡፡ በዚህ ንግግር የተደነቀው ንጉስ ምን ለማለት እንደፈለገ ጠየቀው… ባህሉንም አለው፡- “እኔ አንድ ቀን ለተቀመጥኩበት ይሄን ያህል ከሆንኩኝ፣ አንተማ ለሀያ አመታት የተቀመጥከው… ያንተ ስቃይና መከራ ትዝ ብሎኝ ነው” አለው፡፡ ንጉስ ለአመታት ያላየውን እውነት እብዱ ባህሉን አሳየው፡፡ ንጉስም አለ “ከእብደት፤ ሚስጥር የእውነት ምንጭ ይገኛል፡፡”
ሌላው የጠቢባኑን የግል ሰብእና ከሚሰጡን እውቀት፣ ጥበብ፣ ብርሃን ጋር በመደባለቅ ማየት አግባብ አይመስለኝም፡፡ ለዚሁም አንድ ሻማ ሲበራ መጠቀም ያለብህ፣ ሻማው የሚሰጠውን ብርሃን በመንተራስ ሌላ ጥበብ… ምርምር… ሌላ እውቀትን ለህብረተሰቡ ሊሰጡና መሰላል ሊያወጡ የሚችሉ የህይወት ቀመሮችን በመቀመር ነው፡፡ አለዚያ ግን ይሄኛው ጥቁር ሻማ… ያኛው ነጭ… ቀይ… እያልን ጊዜያችንን ስናባክን ብርሃኑን በአግባቡ ሳንጠቀም ያልፈናል። ስለሆነም ከውስጣቸው የሚፈሰውን ከኔና ካንተ ውስጥ የሌለውን እውቀት፣ ብርሃን፣ … ጥበብ … መቅሰም ይጠቅማል ባይ ነኝ። ስብሃት ስካር ሲነጋ ይለቃችኋል፣ የኔና ያንተ ደደብነት ግን ዝንታለም አይለቀንም፡፡
ስለዚህ እኔ በበኩሌ ከዚህ አይነቱ ሀጥያት ይሰውረኝ ብያለሁ፡፡ ለምን ቢሉ አለማወቅን የመሰለ ሀጥያት የለምና… ለእኔ፡፡
ሌላው አንድ የጠየከው ጥያቄ ነበር። ዳኛቸው ወርቁ፣ በአሉ ግርማ፣ አቤ ጉበኛ… ብለህ ጠርተህ “ለዚህ ህዝብ አንድ ቀን እንጀራ አብስለውለታል?” ብለህ ጠይቀህ ነበር፡፡ አንዱና ዋናው ችግር ይህ ነው፡፡ ለምንድን ነው ህይወታችን በሌላ ሰው ላይ የሚመሰረተው ወይም እንጀራችንን ሰው እንዲጋግርልን የምንፈልገው? ማን ነው የራሱን ትቶ የሰው እንጀራ የሚጋግረው? የቱ ነው የጠቀስከው ሰው፣ ለሰው ብሎ የሚሰራ? ዶክተር? ነርስ? … መሃንዲስ ነው ድልድይ ለሰው የሚሰራ? እኔ የሚመስለኝ… ምን አልባት ይሻገርበት ስለፈለገ… አለዚያ ደግሞ ወደ ቀጣዩ ሌላ እንጀራ እንደሚያሻግረው አስቦ ለራሱ ሲል ነው የሚሰራው፡፡ እዚህ ላይ አንድ የሰማሁት የፈረንሳዮች አባባል ልጥቀስ “ሁሉም ለራሱ፣ እግዜር ለሁሉም”
ስለዚህ ሁልጊዜ ምን ምን ሰራሁ? እኔ ማን ነኝ? ለሀገሬስ በምን መልኩ አስተዋፅኦ አደረኩ ብሎ እራስን መጠየቅ በራሱ እውቀት (ብርሃን) የሚያመጣውን የመጀመሪያ ደረጃ መድስ ማለት ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ደግሞ የምትመከረው ወይም የምትለመነው የማይጠቅምህን ሁልጊዜ መተው ነው፡፡ ለምሳሌ ሬዲዮንን ስለጋሽ ስብሃት ማውራት ሲጀምር መዝጋት ወይም መስመርን መለወጥ እንዲሁም በETV ሲመጡህ አሁን አሁን በጣም ተመስገን ነው ወዲያው … TV Africa … መለወጥ የተሻለ ዘዴ በመሆኑም፣ ይህን በመጠቀም የሚያደናቁርህን መሸወድ ትችላለህ፡፡ ስለዚህ ላንተ ያልተፃፈውን አለማንበብ ለምን ቢባል አይጠቅምህም እና… ጊዜና ወቅቱ ሲደርስ ላንተ የሚሆን… ሲፃፍ ማንበብን… ትመከራለህ፡፡ ለዛሬ መፅሀፍ ሳነብ ባገኘሁት ጥቅስ ልሰናበትህ።
“If your mind is not open, keep your mouth shut too” “Let’s hear what you have to say"
“እኔም ብርሃን ከጨለማ እንደሚበልት እንዲሁም ጥበብ ከስንፍና እንደሚበልጥ አየሁ”
መክ፡13
“የሰው ልጆች ደስታ እና ጥበብ የሚከማቹት በመፅሃፍ ውስጥ ነው…
… ምንጊዜም እያንፀባረቁ ፍሬዎቻቸውም በማሰራጨት ለዘመናት አያሌ ሃሰሳቦችን እና ተግባሮችን ያመነጫሉ፡፡
(ምንጭ፡- አድማስ ሃምሌ 5 ቀን 1995)
“ጦርነት መፍትሄ አይኾንም፤ ከትናንት እንማር”
”--ጦርነት መፍትሄ አይኾንም፤ ከትናንት እንማር፤ ችግሮችን በውይይት እንፍታ፤ በሀገራችን ሰሜናዊ ክፍል ለሁለት ዓመታት የተካሄደው ጦርነት ካደረሰብን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ገና በቅጡ እንኳ ባላገገምንበት በዚህ ወቅት፣ ዳግም ወደ ሌላ መጠነ ሰፊ የእርስ በርስ ግጭት መግባት፣ በሕዝባችን ላይ የሚያደርሰው ማኀበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ስነ ልቡናዊ ጉዳት በእጅጉ የሚያሳስብ ነው። ጦርነት ከፍተኛ መጠን ያለው ሰብኣዊ እልቂትንና ቁሳዊ ውድመትን ከማስከተል በቀር፣ ለችግሮቻችን መፍትኄ እንደማያስገኝ ከቅርብ ጊዜው ተሞከሯችን መማር አለመቻላችን እጅግ አሳዛኝ ነው። በሀገር ውስጥ የሚካሄድ ጦርነት፣ የሀገር አንድነት ፀንቶ የቆመባቸውን የእሴት አምዶች በማፍረስ፣ የሕዝባችንን አንድነት የሚንድ በመኾኑ፣ ሁሉም አካላት ሁኔታውን ከማባባስ ተቆጥበው፣ ወደ ውይይት መምጣት የሚቻልበትን መላ ያፈላልጉ፡፡ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ፤ እጅግ አውዳሚና አክሳሪ ከኾነው ጦርነት፣ የችግር መፍትኄን ከመጠበቅ ይልቅ፣ በአስቸኳይ ወደ ውይይት ይምጡ።--”
(የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሰሞኑን ካወጣው መግለጫ የተወሰደ)
የቁጫ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፤ በመንግሥት አመራሮች በተቀሰቀሰ ግጭት ተፈጸመ ያለውን ጥፋትና ውድመት አወገዘ
አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ከነባሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሥልጣን መረከቡን ተከትሎ፣ ከክልሉ ዋና ከተሞች አመራረጥ ጋር በተያያዘ በቁጫ የምርጫ ክልል በተቀሰቀሰ አመጽና ረብሻ፣ ከፍተኛ ጉዳትና ውድመት መድረሱን የጠቆመው የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁሕዴፓ)፤ ይሄንኑ በመንግሥት አመራሮች የተቀሰቀሰና የተመራ ነው ያለውን አመጽና ረብሻ በጽኑ አውግዟል፡፡
ከደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ክልል አደረጃጀትና ምስረታ ሂደት ጋር ተያይዞ፣ በቁጫ ምርጫ ክልል የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር አስመልክቶ የቁሕዴፓ አመራሮች፣ ትላንት ከሰዓት በኋላ 8 ሰዓት ላይ፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ጽ/ቤት አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በየጊዜው ሀገራችን የሚገጥማትን የፀጥታ ችግር እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ የቁጫ ምርጫ ክልል ሕዝብን እረፍት የሚነሱ ኃይሎች ላይ መንግስት የህግ የበላይነትን እንዲያሰፍን ፓርቲው ጠይቋል፡፡
ባለፉት ዓመታት በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፣ በተለያዩ ዞኖች ሲነሳ ለቆየው የክልል አደረጃጀት መንግስት ምላሽ እየሰጠ መሆኑን የሚገልጸው ፓርቲው፤ በዚህም ነባሩ ደቡብ ክልል ከአራት በላይ በሆኑ አዳዲስ ክልሎች እንዲዋቀር ተደርጓል ይላል፡፡
”ከእነዚህ አራቱ ክልሎች አንዱ የሆነውና በአሁኑ ወቅት በምስረታ ሂደት ላይ የሚገኘው “የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ክልል”፣ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በተደረገው ሕዝበ ውሳኔ በተመዘገበው አብላጫ ውጤት፣ 6ቱ ዞኖች እና 5ቱ ልዩ ወረዳዎች በአንድነት በጋራ ክልል ለመተዳደር የወሰኑት ድምፅ በፌዴሬሽን ም/ቤት በመፅደቁ፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፣ ክልል ም/ቤት፣ ከሐምሌ 28 እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ የም/ቤት ጉባኤ፣ ለአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ክልል የስልጣን ርክብክብ አድርጓል፡፡” ብሏል፤ ፓርቲው፡፡
ም/ቤቱ፤አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ክልልን በ6 ክላስተር ከተሞች የአገልግሎት ተቋማትን ሸንሽኖ በተመረጡ ከተሞች የተደለደሉ የመንግሥት ተቋማትን ዝርዝር ይፋ ማድረጉን ያወሱት የፓርቲው አመራሮች፤ ይሄን ተከትሎም፣ ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም፤ “አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ክልል አደረጃጀት የጋሞ ሕዝብን ጥቅም የሚነካ በመሆኑ አንቀበልም” በማለት በቁጫ ምርጫ ክልል፣ በቁጫ ወረዳና በቁጫ ሰላምበር ከተማ አስተዳደር፣ በመንግስት አመራሮች የተመራ የረብሻና አመፅ ቅስቀሳ መደረጉን ይገልጻሉ፡፡
የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚና የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የሆኑት የተከበሩ ረ/ፕሮፌሰር ገነነ ገደቡ፣ በአካባቢው የመንግስት አመራሮች የተቀሰቀሰና የተመራ ነው ባሉት አመፅና ረብሻ ስለደረሱት ጥፋቶች ሲያስረዱ፤”የቁጫ ሕዝብን ከወላይታ ዞን፣ ከጎፋ ዞንና ከደቡብ ኦሞ ዞን ሕዝብ ጋር የሚያገናኘውን የፌደራል አስፓልት መንገድ በመዝጋትና የሕዝብን ነፃ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ ወደ ቁጫ ሰላምበር ከተማ ቅዳሜ ገበያ የመጣው ገበያተኛ እንዲበተን፣ የፀጥታ ሃይሎች፣ በገበያተኞች ላይ ወከባና ድብደባ ፈጽመዋል” ብለዋል፡፡
”በረብሻው ያልተሳተፉ የሰላምበር ከተማ ነዋሪዎች በብሔር እየተለዩ፣ በቁጫ ብሔረሰብ አባላትና በቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች የንግድ ተቋማትና መኖሪያ ቤቶቻቸው ላይ በተፈፀመው የድንጋይ ውርወራ ውድመት ደርሷል” ያሉት የም/ቤት አባሉ፤ ”በረብሻው ከተሳተፉ ወጣቶች መካከልም የአንዱ ህይወት ማለፉ ተረጋግጧል፤ሌሎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ ሰዎች ላይ በአካባቢው የፀጥታ ኃይሎችና በረብሻው በተሳተፉ ወጣቶች እንዲሁም በመንግስት አመራሮች ጥቃት ተፈጽሟል” ብለዋል፡፡
በቁጫ ምርጫ ክልል በመንግሥት ሃላፊዎች የተቀሰቀሰውንና የተመራውን የአመጽና ረብሻ እንቅስቃሴ ፓርቲያችን በፅኑ ያወግዛል ያሉት አመራሮቹ፤በአካባቢው ከፍተኛ ግጭትና ውድመት እንዲደርስ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ ከቁጫ ሕዝብና ከፓርቲያችን ለክልሉና ለፌዴራል ፀጥታና ተጠሪ ተቋማት በቀረበው ጥቆማና አቤቱታ፣ የፌዴራል ፀጥታ ኃይል ወደ አካባቢው በፍጥነት ደርሶ ሕዝቡን ታድጎታል ብለዋል፡፡
”የተገኘው አንፃራዊ መረጋጋት አስተማማኝ ደረጃ እስኪደርስና አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ክልል ምስረታ ተካሂዶ በአካባቢው ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እስኪሰፍን ድረስ፣ የፌዴራል ፀጥታ ኃይል የሕዝብን ሰላምና ደህንነት እንዲያስጠብቅ በመንግሥት በኩል ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው እንጠይቃለን” ብለዋል፤ አመራሮቹ በመግለጫቸው፡፡
አመፅና ረብሻው በቁጫ ወረዳና በቁጫ ሰላምበር ከተማ አስተዳደር እንዲነሳ የተፈለገው ያለ ምክንያት አይደለም የሚሉት የፓርቲው ም/ፕሬዚዳንት አቶ ሃብታሙ ኃ/ሚካኤል፤ የቁጫን ህዝብ ማህበራዊ ዕረፍት በመንሳት ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ምስቅልቅል ለመዳረግና አካባቢውን የግጭት ማዕከል በማድረግ፣ የሕዝብን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመቀልበስ ነው ብለዋል፡፡
የአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናት ከሌሎች አካባቢዎች ያመጧቸውን ወጣቶች ሳይቀር በዚህ ግጭትና ረብሻ ውስጥ አሳትፈዋቸዋል ያሉት ም/ፕሬዚዳንቱ፤ ግጭቱን በቁጫ የምርጫ ክልል እንዲነሳ ያደረጉትም በቁጫ ብሔረሰብ እንዲሁም በፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ላይ ጥቃት ለመፈጸም በማለም ነው ሲሉ ወንጅለዋል፡፡
ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም፣ በቁጫ ወረዳና በቁጫ ሰላምበር ከተማ፣ በመንግሥት አመራሮችና በአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች እንዲሁም በፖሊስ አባላት በተመራው አመፅና ረብሻ፣ የቁጫ ሕዝብን ከወላይታ፣ ከጎፋና ከደቡብ ኦሞ ዞን ሕዝቦች ጋር የሚያገናኘውን የፌዴራል አስፓልት መንገድ ዘግተውት እንደነበር ያስታወሱት የፓርቲው ም/ፕሬዚዳንት፤ በዚህም ሰላም ወዳዱን የቁጫ ሕዝብ ለዘመናት ጥብቅ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ከፈጠሩ፣ በአንድነትና በፍቅር ከሚኖሩ አጎራባች ሕዝቦች ለመለየትና እነዚህ አካባቢዎች በቁጫ ህዝብ ላይ እንዲነሳሱ በማድረግ፣ ከግጭት ለማትረፍ ታቅዶ የተፈፀመ ነው ብለዋል፡፡
ከክልል በታች ያሉ አደረጃጀቶች፣ ከአዲሱ ክልል ምስረታ በኋላ ምላሽ እንደሚያገኙ በፌዴሬሽን ም/ቤት አቅጣጫ መቀመጡን ያመለከተው ቁሕዴፓ፤ የቁጫ ሕዝብ ብሔር ማንነትና ራሱን በራሱ የማስተዳደር ህገመንግስታዊና ዴሞክራሲያዊ ጥያቄው ለዘመናት የቆየና ጥያቄው ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ በክልል ደረጃ ምላሽ ማግኘት የሚገባው ጊዜ በማለፉ በይግባኝ ለፌደሬሽን ም/ቤት ቀርቦ ለምላሽ የተለያዩ ጥናቶች ሲደረጉ የቆየበት ከመሆኑ አንጻር፣ ከክልል አደረጃጀት ጥያቄ አስቀድሞ ምላሽ ሊሰጠው ይገባ ነበር ብሏል፤ ፓርቲው፡፡
በአጠቃላይ በቁጫ ሕዝብ ላይ ተጭነው ለቆዩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች የፌዴሬሽን ም/ቤት በራሱ ሥልጣንናና ተግባር ስር የነበረውን ኃላፊነት፣ በህግ አግባብም በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መመለስ አለመቻሉ በፈጠረው አጋጣሚ የቁጫ ሕዝብ ህገመንግስታዊ መብቶች ተጥሰው፣ በሌላው ወገን ፈላጭ ቆራጭነት፣ ህዝብን ለማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መጎሳቆል ከመዳረጉም በላይ፣ በራሱ መልክዓ ምድር ሠርቶ፣ ነግዶ፣ አርሶና አርብቶ እንዳይኖር ለተለያዩ ችግሮችና መከራዎች አጋልጦታል፤ ብሏል በመግለጫው፡፡
ፓርቲው በመግለጫው ለፌዴሬሽን ም/ቤት ባስተላለፈው መልዕክት፤የቁጫ ብሔረሰብ ማንነትና የራስ አስተዳደር የዞን መዋቅር ህገመንግስታዊና ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች፣ በህገመንግስቱ በተቀመጠው አግባብ፣ መሰረት ፈጣን ምላሽ እንዲሰጠው አበክሮ ጠይቋል፡፡
በሌላ በኩል፤የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ክልል ምስረታን ተከትሎ፣ በቁጫ የምርጫ ክልል በመንግሥት አመራሮች በተነሳው ረብሻና አመፅ፣ ለሰው ህይወት ጥፋትና የንብረት ውድመት ተጠያቂ የሆኑና የቁጫ ምርጫ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ከመረጣቸው ሕዝብ ጋር እንዳይገናኙ በማድረግ ጥቃት ፈጽመውባቸዋል የተባሉ አካላት ተጣርተው ለህግ እንዲቀርቡ ቁሕዴፓ በመግለጫው ጠይቋል፡፡
ፓርቲው አክሎም፤ የመንግሥት አካላት በመሩት ሁከት፣ የሰው ሕይወት ለጠፋበት የሟች ቤተሰብና በብጥብጡ የአካልና የንብረት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች፣ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ፣ ተገቢው ካሣ እንዲከፈልና የወንጀሉ ፈፃሚዎችም በቁጥጥር ሥር ውለው ለሕግ እንዲቀርቡ ጠይቋል፡፡
የወቅቱ ጥቅስ
“--በአሉታዊ-መነሻ ሳይሆን በአዎንታዊ-መነሻ ላይ ቆሜና የሀገሪቱን መዳን አስቀድሜ፣ እንዴት ልጓዝ? ብሎ የማሰብ ሆደ-ሰፊነት እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ የተመቻቸ ሁኔታ አይፈጠርልኝም ብሎ የተስፋ-ቆራጭ መንገድ ከማሰብ የግድ መንገዱን መፍጠር አለብኝ ብሎ ቆርጦ መነሳት፤ ህዝብን ወደ በለጠ አዘቅት ከመምራት፣ አገርንም ይበልጥ ወደ ተወሳሰበ አደጋ ከመግፋት የሚገታ ብስለት ይሆናል፡፡--”
“ብላ ያለው ተጋግሮ ይጠብቀዋል ተሸከም ያለው ታስሮ ይጠብቀዋል”
በአንድ መንደር የሚኖር አንድ ድመት ያለው ሰው አለ፡፡ ድመቱ በመንደሩ እየተዘዋወረ በርካታ የድመት ወዳጆችና ውሽሞች አፈራ፡፡ አንድ ቀን አንዷ ድመት ዘንድ፣ ሌላ ቀን ሌላ ድመት ዘንድ እየተዘዋወረ ሲወሰልት ከረመ፡፡ በውጤቱም የመንደሩ ድመቶች ሁሉ አረገዙ፡፡ አያሌ ተፈለፈሉ። የሰፈሩ ሰው ሁሉ በድመቶች ብዛት ተጨናነቀ፤ መረረውና እድሩ ተሰበሰበ፡፡ ይሄንኑ ምሬቱን ተወያየ። በመካያው የአገር ሽማግሌዎች ተመርጠው ወደ ባለድመቱ ሄዱና እንዲህ አሉ፡-
“ጌታዬ፣ መቼም አንተ አስበህ ለተንኮል ያደረግኸው አይመስለንም፡፡ ሆኖም ችግሩ መፈጠሩ አልቀረም”
ሰውዬውም እንዲህ ለምድር ለሰማይ የከበዱ ሰዎች ላይ ምን ችግር ፈጠርኩባቸው በሚል ተሽቆጥቁጦ፤
“ምን ጥፋት አገኛችሁብኝ ጌቶቼ?” ሲል ጠየቀ፡፡
የሽማግሌዎቹ ተወካይም፡-
“አየህ ያንተ ድመት በሰፈሩ አንዲትም የቀረችው ድመት የለች፡፡ የድመት ማቲ ተፈለፈለ ተፈለፈለና በዚህ ምክንያት መንደሩ ሁሉ በድመት ተወረረ፡፡ አሁን ድመትህን ታስርልን ዘንድ ልንጠይቅህ ነው የመጣነው፡፡”
ሰውዬው፡-
“ታዲያ ምን ችግር አለ? እኔ እንደሚሆን አደርጋለሁዋ!” አለ፡፡ አመስግነውት ይለያያሉ፡፡
ባለድመቱ ሲያወጣ ሲያወርድ ይቆይና በመጨረሻ ውሳኔ ላይ ይደርሳል፡፡
ከጊዜ በኋላ በመንደሩ አንድ አደገኛ የእንስሳት ወረርሽኝ ይገባል፡፡ የሰፈሩ ትናንሽ ድመቶች በሙሉ ይረፈረፋሉ፡፡
ጭንቅ መጣ- ምክንያቱም አይጥ ደግሞ በተራው መንደሩን ወረረው፡፡ ሳሎን ከጓዳ የአይጥ መናኸሪያ ሆነ፡፡ የአገሩ ሽማግሌዎች እንደገና ወደ ባለ ድመቱ ይመጣሉ፡፡
ባለድመቱ፡- “አሁን ደግሞ ምን ተፈጠረ አባቶቼ?”
የሽማግሌዎቹ ተወካይም፡- “አንድ ችግር ገጠመን ወዳጄ፡፡ ያ የአንተ ድመት ከቤቱ መውጣት ካቆመ በኋላ አይጥ አላስቀምጥ አለን፡፡ አንድ ጊዜ ደግመህ ብትቸገርልንና ድመቱን ብትለቀው?”
ባለ ድመቱ፡- “አባቶቼ ያንንማ ለማድረግ ከእንግዲህ አልችልም፡፡”
የሽማግሌዎቹ ተወካይ፡- “ለምን ወዳጄ?”
ባለ ድመቱ፡- “ለአንዴም ለሁሌም እንዳያስቸግራችሁ ብዬ አኮላሸሁት!”
ሁሉም ጭንቅላታቸውን ያዙ፡፡ አዝነው መንገዳቸውን ሲቀጥሉ፣ ባለድመቱ ተጣራና አንድ ተስፋ ሰጣቸው፡-
“ጌቶቼ ሆኖም ድመቴ ስራ አልፈታም፡፡ ሊያግዛችሁ ይችላል”
ቆም ብለው፡- “በምን መንገድ ይረዳናል?”
ባለ ድመቱ፡- “የአማካሪነት አገልግሎት ስራ ጀምሯል- Consultant ሆኗል!!!”
***
የአማካሪው ዓይነት በበዛ ቁጥር ማ በጤና፣ ማ ተስፋ በቆረጠና በተኮላሸ አቋም እንደሚያማክር ለመለየት ያስቸግራል፡፡ አማካሪው ከግራ ከቀኝ መሯሯጡ ሲበዛ ማ “የመጣው ይምጣ!” በሚል እንደሚያቅድ፣ ማ በአቦ-ሰጡኝ እንደሚመራ፣ ማ አለቃውን የሚያስደስት መፈክር ማስገር እንደሚሻ፣ ማ እንደበቀቀን ከላይ የተነገረውን ብቻ በመደጋገም አዋቂ ለመምሰል እንደሚፍረመረም አበጥሮ ለማየት እጅግ ያዳግታል፡፡ በመንደር በሰፈሩ አንድ ሽለ-ሙቅ አጥቂ (fertile) ድመት ብቻ መኖሩንና የተፈለፈሉ ድመቶች እንደ አሸን መፍላት አሳሳቢ ሁኔታ መፍጠሩ፤ የትኩረቱን አቅጣጫ ሁሉ ከአይጦች መምጣት አንፃር እንዳይታይ አደረገው፡፡ ሁኔታው የአገር የቀዬውን አይን ማወሩ የሚገርመውን ያህል፣ የባለድመቱ ድመቱን የማኮላሸት ፈጣን እርምጃ ይብስ አስደንጋጭነቱን ያጎላዋል፡፡ ያ ሳይበቃ የመንደሩ ሰዎች፤ አይጦች መፈልፈል ሲጀምሩ፣ “እኛ እንዴት አይጦቹን ልናስወግድ እንችላለን?” የሚለውን ጥያቄ አላነሱም፡፡ የተለመደውን የድመቱን ጌታ እንደ መፍትሄ በማሰብ ወደሱዉ ያመሩት ሽማግሌዎች ብቸኛው መልስ አለመኖሩን ሲረዱ፣ የደረሰባቸው የሀሞት መፍሰስም፤ የማሳቁን ያህል፣ የድመቱ የአማካሪነት አገልግሎት ደግሞ ከተፍ አለ፡፡ “ባላጋባ ማጫፈር ያቅተኛል ወይ?” ዓይነት ተሳትፎ መሆኑ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ የሀገራችንን የችግር መፍትሔ አሰጣጥ፣ የዕቅድ አወጣጥ፣ ድቀት አፈረጃጀትና አፈታት (Crisis management) ምን እንደሚመስል፣ ሌሎችንም ሁናቴዎች የሚያመላክት ሁኔታ ነው፡፡ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ምስቅልቅል ሂደቶች እንደተለመደው በሹም-ሽር (appoint-demote) ፈጣን እርምጃ እንዳንገላገለው “ወተት ያጠጧት ውሻ፣ ቅቤ ሳትቀቡኝ አልሄድም ትላለች” እንዲሉ፤ የውስጥ አዋቂነትና ጠላት የማብዛት ስጋት መንገዶችን ሁሉ እያቆላለፉ መራመጃ ያሳጡ ይመስላሉ፡፡ ምንም እንኳ የምሩ ሰዓት አይቀሬ ቢሆንም፣ ጊዜያዊ መረጋጋትን (temporary stability) የሚሰጡ ሁኔታዎችን በማሰላሰል “አንገብጋቢ አይደለም” ብሎ እንደማለፍ ያለ አደገኛ መፍትሄ የለም፡፡ ዛሬ የሚፈጠርን ችግር ነገ እናስብበታለን ብለን አንዘልቀውም፡፡ ጉድጓዱን ሳይደፍኑ አይጢቱን የማሳደድ ዓይነት ብልሀት ሙስናን እንደማያስወግድ ሁሉ፤ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መሰረተ-ጉዳዮች ውስጥ ያሉ ጉድጓዶችን በቀና ልቡና ሳይደፍኑ መረጋጋት፣ መቻቻል፣ በራስ መተማመን በዋዛ የሚገኙ ነገሮች አይሆኑም፡፡ ከሁሉም ቀዳሚው አርቆ ማስተዋል ነው፡፡ የቤት ስራን ለመስራት የምንተጋውን ያህል፣ ኃላፊነትን ለመወጣት ሌት-ተቀን እንፍጨረጨራለን የምንለውን ያህል፣ አርቆ አስተዋይነትን በተገቢው መጠን መያዝ ይኖርብናል፡፡ ከዚህ ወይም ከዚያ እርምጃ ሀገር ምን ትጠቀማለች ማለትን ግንዛቤ ውስጥ ልናስገባ ያሻናል፡፡ ከምሁራንና ከረዥም ዕድሜ የልምድ ባለቤቶች የሚገኘውን ዕውቀት እንዴት በአግባቡ ለሀገር በሚበጅ ፈርጁ መጠቀም ይገባል ብሎ በብልህ ልቡና ማሰብ ይገባል፡፡
የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች የመፏከቻና የመሻኮቻ መድረክ መፍጠር ሳይሆን፣ ያልተሄደበትን መንገድ እንዴት እናግኘው የማለትን ብልሀት መሻት ያስፈልጋል፡፡ በአሉታዊ-መነሻ ሳይሆን በአዎንታዊ-መነሻ ላይ ቆሜና የሀገሪቱን መዳን አስቀድሜ፣ እንዴት ልጓዝ? ብሎ የማሰብ ሆደ-ሰፊነት እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ የተመቻቸ ሁኔታ አይፈጠርልኝም ብሎ የተስፋ-ቆራጭ መንገድ ከማሰብ የግድ መንገዱን መፍጠር አለብኝ ብሎ ቆርጦ መነሳት፤ ህዝብን ወደ በለጠ አዘቅት ከመምራት፣ አገርንም ይበልጥ ወደ ተወሳሰበ አደጋ ከመግፋት የሚገታ ብስለት ይሆናል፡፡ “የሞኝ ጀርባ ሲመታ የአስተዋይ ጀርባ ያመዋል” ይሏልና፤ ከህመማችን ተነስተን፤ የአተያያችን አቅጣጫ ቀናና አዎንታዊ መሆን እንደሚገባው አበክሮ ማስተዋል ነው፡፡
የሀገራችንን ሁኔታ “አንዴ ካመጣው ምን ይደረግ” በሚል ህሊና ለማለፍ አዳጋች ነው፡፡
“አይጣል ይሏል እንጂ ከጣለ ምን ይሏል
ከመቀነት ወጥቶ ብር ይኮበልላል”
ብለን ያላሳብ ለመተኛት የሚቻል ቢሆን መታደል ነበር፡፡ ሆኖም በተጨባጭ አካልንም አዕምሮንም የሚኮሰኩስ ሳንካ በየቢሮው፣ በየበሩ፣ በየማጀቱ ይጎረብጣልና ዐይንን መግለጥ ወይም ማፍጠጥ ብቸኛ አማራጭ ይሆንብናል፡፡ ለማንኛውም ተኝቶ ማደር አለመቻሉን ነው የምናጤነው፡፡
ስለ ተግባራዊ ዲሞክራሲያዊነት፣ ስለ እውነተኛ ፍትሀዊነት፣ ስለ ልባዊ መልካም አስተዳደርና ዕብለት-አልባ ስለሆነ የሀገር ዕድገት የምናወራ ከሆነ፤
“ብላ ያለው ተጋግሮ ይጠብቀዋል
ተሸከም ያለው ታስሮ ይጠብቀዋል”
ለሚል ዓይነት አሰራርና ተጨባጩን ሂደት እድል ለሚያስመስል ወገናዊ አካሄድ፣ ከቶም ቦታ ልንሰጠው አይገባም፡፡
ፈሳሽ ስዕል
ወንዜም ሞላ ቦይ
ምንጬም አትጉደይ
ከስሬ ስትፈልቂ
ራሴን እንዳይ
ምስሌ ይፍሰስብሽ
ፀድተሸ ብታጠሪኝ
ወንዜ ፍሰሽልኝ፡፡
ፍሰሽልኝ ወንዜ፤
ተቀላቅሎ ይኑር
ወዝሽና ወዜ፡፡
ጥያቄ ነን
ጥያቄ ነን
ለራሳችን
መልስ የሌለን፡፡
በሴኮንዶች ተጀምረን
በአመታት የምናድግ
በግዜ ጎርፍ
የምንጓዝ የምንከንፍ
መነሻ እንጂ
መድረሻ የለሽ ፍጡራን
ሄደን ሄደን…ሄደን
ጀማሪዎች የምንሆን
አውቀን አውቀን
መሃይማን፤
አድገን አድገን-
ህፃናት ነን!
ጥያቄ ነን!