Administrator

Administrator

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን ባቀረበው አዲስ ጥናት መሠረት፣ ስፖርት፣ ባህል እና ኪነ-ጥበብ ለሀገሪቱ ዓመታዊ ኢኮኖሚ 380.40 ቢሊዮን ብር (2.521%) አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።
በጥናቱ ከተሳተፉት መካከል ዶክተር ሳምሶን ወንድይራድ እንደተናገሩት፣ የስፖርት ዘርፍ አክሳሪ ሳይሆን አትራፊ ነው፤ በዘርፉ ወጪ በሚደረግ በእያንዳንዱ 1 ብር ላይ 1 ብር ከ40 ሳንቲም ገቢ ይገኛል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካ ጥናቱ በቀጣይ 3 ዓመታት ስፖርቱን ለመምራት ላቀደው ስትራቴጂ ትልቅ ድጋፍ እንደሚሆን ገልጸዋል። ከኢኮኖሚ ጥቅም ባሻገር፣ የስፖርት እና የባህል ውድድሮች ህዝብን ከህዝብ በማቀራረብ እና ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆናቸውን ጥናቱ አመልክቷል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
አንድ ታዋቂ ሰዓሊ የሰራውን ስዕል ሰዎች በሚበዙበት አደባባይ ላይ አስቀመጠ። ከስዕሉም ስር "እባካችሁ የተበላሸ ቦታ ካየችሁ በኤክስ (X) ምልክት አድርጉበት" የሚል ፅሁፍ ለጠፈ። በማግስቱ ተመልሶ ሲመጣ ስዕሉ ሙሉ በሙሉ በኤክስ (X) ምልክት ተሸፍኖና ተበላሽቶ አገኘው።
በነገሩ በጣም አዝኖ ለጓደኛው ነገረው። ጓደኛውም፡ "በዚህ ተስፋ አትቁረጥ! ያንኑ ስዕል ድገምና በተመሳሳይ ቦታ አስቀምጠው። ነገር ግን በዚህኛው ስር 'የተበላሸ ቦታ ካለ በቀለሙና በብሩሹ አስተካክሉት' ብለህ ጻፍ" አለው። ሰዓሊውም እንደተባለው አደረገ። በማግስቱ ተመልሶ ሲመጣ ስዕሉ አንድም ቦታ ሳይነካ እንዳለ አገኘው!
ብዙ ሰዎች የሰውን ስህተት ለመንቀስና "ተበላሽቷል" ለማለት በጣም ፈጣኖች ናቸው። ነገር ግን ነገሩን ለማስተካከልና የተሻለ ነገር ለመስራት ሲባል፤ እውቀቱ፣ ጊዜው፣ ጉልበቱ ወይም ፍላጎቱ ያላቸው በጣም ጥቂቶች ናቸው።
ስለዚህ የሰዎች ነቀፌታ ተስፋ እንዲያስቆርጥህ አትፍቀድ፤ ከመንቀስ ባሻገር መፍትሔ የሚሰጡ ሰዎችን ብቻ አዳምጥ!
ኤርሚያስ በጋሻው ገሰሰ
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

ዋልያ መጻሕፍት “ሳይንስ እና ሳይንሳዊ አስተሳሰብ” በሚል ርዕስ ከዘርፉ ምሁራን ጋር የሚደረግ አጓጊ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል። በዕለቱ ታዋቂው ኢምሬተስ ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ “ሳይንስ እና ሳይንሳዊ አስተሳሰብ” በሚለው ርዕስ ላይ ጥልቅ ማብራሪያ የሚሰጡ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና በናሳ ተመራማሪና የዶክትሬት ተማሪ የሆነው አቶ ተስፋዬ ማሞ መኮንን ደግሞ “ፊዚክስ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን” በሚል ርዕስ ዙሪያ የዕውቀት ልውውጥ ያደርጋሉ።

ይህ ታላቅ የዕውቀት ማዕድ ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ከሰዓት ከ8፡00 ጀምሮ በ4 ኪሎ ኢክላስ ሕንጻ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት አዳራሽ ይካሄዳል። ሁለቱን ታዋቂ ምሁራን በአንድ መድረክ በማግኘት አዳዲስ ሃሳቦችን ለመረዳት እና ከእለት ተእለት ሕይወት ጋር ለማገናኘት ይህንን ዕድል ይጠቀሙበት።

በነፃ ሀሳብና በሰከነ መንፈስ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን በማድመቅ ላለፉት 14 ዓመታት የብዙዎችን ፍቅር ያተረፈው የ"ጦቢያ" መድረክ፣ በጀርመን መቀመጫውን ባደረገው "Hope for All" ግብረ ሰናይ ድርጅት አዘጋጅነት በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች አጓጊ ዝግጅቶቹን ሊያቀርብ ነው።

በገጣሚ ምስራቅ ተረፈ መስራችነት የሚመራው ይህ መድረክ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ኦገስት 9 በአምስተርዳም፣ ኦገስት 16 በኑረንበርግ፣ ኦገስት 23 ፍራንክፈርት፣ ኦገስት 30 ኮለን እንዲሁም ሴፕቴምበር 5 በሙኒክ ከተሞች ለታዳሚዎች ይደርሳል።

ይህ የኪነጥበብ ጉብኝት ከእጅግ ውብ መዝናኛ ባለፈ በትውልድ ሀገራቸው ለሚገኙ ወጣት ሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ትልቅ የበጎ አድራጎት ዓላማ ሰንቋል። አዘጋጆቹ በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የዝግጅቱ ታዳሚዎች እየተዝናኑ ለተቸገሩ ወገኖቻቸው እንዲደርሱ በህብረት እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

የሆርን ሪቪዩ መጽሔት ባወጣው የደህንነት ሪፖርት መሠረት፣ በሰሜን ኢትዮጵያ አዲስ ግጭት ለመቀስቀስ በህወሓት እና በኤርትራው ህግደፍ አመራሮች መካከል ምስጢራዊ ስምምነት ተደርጓል።
ከሰሞኑ በዛላምበሳ ከተማ በተደረገው በዚህ ስብሰባ ላይ እነ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር (ሞንጀርኖ) እና ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል። የስምምነቱ ዋና ዓላማ በኢኮኖሚ ተቋማት፣ ገበያዎች፣ ሆስፒታሎችና የእምነት ቦታዎች ላይ የቦምብ ጥቃት በመፈጸም፣ ጥቃቱን በፌደራል መንግሥቱ ላይ በማሳበብ ሕዝቡን ለዓመፅ ማነሳሳትና ማዘጋጀት እንደሆነ ሪፖርቱ ገልጻል።
ይህንን እቅድ ለማስፈጸምም የሕዝቡን ስሜት የሚቀሰቅሱ የሐሰት መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨት ተጀምሯል። ሪፖርቱ እንደሚለው፣ በ2020-2022 ጦርነት ወቅት በትግራይ ሕዝብ ላይ ከተፈጸሙት በደሎች 76 በመቶ የሚሆነው በኤርትራ ሠራዊት የተፈጸመ ቢሆንም፣ አሁን ግን ህወሓት ከዚሁ አካል ጋር በመተባበር ሕዝቡን እንደ መሣሪያ ለመጠቀም እየሠራ ነው። በተጨማሪም የ1988ቱን የሐውዜን ጥቃት ትዝታ በመጠቀም ሕዝቡ በፌደራል መንግሥቱ ላይ እንዲያምፅ ሥነ-ልቦናዊ ጫና እየተፈጠረ እንደሆነ የሆርን ሪቪዩ ዘገባ ያመለክታል።
በወታደራዊ በኩል ህወሓት በራያ፣ ዞብል፣ ዋጃ፣ ኮረምና በሱዳን ባሉ ኃይሎቹ በኩል የጦር ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። በዚህ ስጋት ምክንያት በአላማጣ፣ ቆቦ እና ኮረም አካባቢ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የተስተጓጎለ ሲሆን፣ ብዙ ነዋሪዎችም ስጋት ስለገባቸው ወደ ሌሎች ቦታዎች በመፈናቀል ላይ ናቸው። የሆርን ሪቪዩ ሪፖርት እንደሚያስጠነቅቀው፤ መንግሥት የሕዝቡን ደኅንነት የመጠበቅ፣ የሐሰት መረጃዎችን የመመከት እና ሰላምን የማስከበር ትልቅ ኃላፊነት አለበት።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
ሪያል ማድሪድ ኮትዲቯራዊውን አማካይ ያን ዲዮማንዴ ከአርቢ ላይብዢግ ለማስፈረም መስማማቱን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
በአሁኑ ሰዓት ተጫዋቹ በኦስትሪያ የቅድመ ውድድር ዝግጅት እያደረገ ሲሆን በቀጣይ ሰዓታት ለጤና ምርመራ ወደ ማድሪድ የሚያቀና ይሆናል።
ሪያል ማድሪድ ለጀርመኑ አርቢ ላይብዢግ በተከታታይ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ቢሆንም፤ በመጨረሻ ያቀረበው 125 ሚሊዮን ዩሮ ጥቅማጥቅሙ 140 ሚሊዮን ዩሮ የሚደርስ ዋጋ ተቀባይነት አግኝቷል።
ያን ዲዮማንዴ ላይብዢግን ከተቀላቀለ በኋላ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ባደረጋቸው 36 ጨዋታዎች 13 ግቦችን አስቆጥሮ፣ 10 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።
በትግራይ ክልል «ሰባ ካሬ» የተፈናቃዮች ማዕከል ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በተከሰተ ከባድ ዝናብ እና ኃይለኛ ንፋስ ከ20 በላይ ጊዜያዊ መጠለያዎች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተዘግቧል፡፡ አውሎ ነፋሱ መጠለያዎቹን ለኑሮ የማይመቹ በማድረግ የነዋሪዎችን ንብረት ያወደመ ሲሆን፤ አረጋውያንን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና ተቋማት ተወስደዋል።
ይህ አስከፊ አደጋ ቀድሞውንም አስቸጋሪ ሕይወት ለሚመሩት ተፈናቃዮች ተጨማሪ ከባድ ፈተና ሆኗል። «ጽላል» የተባለው የምዕራብ ትግራይ የህብረተሰብ ድርጅት፣ ሰብአዊ ድርጅቶች አስቸኳይ እርዳታ እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፤ የችግሩ እውነተኛ ዘላቂ መፍትሔ ተፈናቃዮች በሰላም ወደ ቀያቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንደሆነ አፅንኦት ሰጥቷል።
AS-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በየዓመቱ ሐምሌ 29 ቀን ከሚያከብረው የበጎ አድራጎት ቀን ጋር ተያይዞ፣ በመቄዶንያ ማዕከል ለሚገኙ አረጋውያን እና አቅመ ደካሞች ከ600,000 ብር በላይ የሚገመቱ የምግብ ፍጆታዎችን፣ የዊልቸር፣ የዋከር፣ የአልባሳት እና የፅዳት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል።
በመከላከያ ሚኒስቴር የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ሁሉሀገርሽ ድርስ አማካኝነት ለአረጋውያኑ ልዩ የምሳ ግብዥ የተደረገ ሲሆን፣ ሠራዊቱ የሀገርን ህልውና ከመጠበቅ ባሻገር ለወገኑ ቀዳሚ ደራሽ መሆኑን በማስመስከር ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
የማዕከሉ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ብንያም በለጠ ሠራዊቱ ሕይወቱን አሳልፎ ከመስጠት ባለፈ ወገኖቹን በፍቅር በመጎብኘቱ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል፤ በማዕከሉ የሚገኙ አረጋውያንም ለሠራዊቱ ያላቸውን ፍቅር በምርቃት ገልጸዋል። በመጨረሻም የማዕከሉን የቀሩ የግንባታ ስራዎች በፍጥነት ለማጠናቀቅ ኅብረተሰቡ አሁንም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወጣቶች ይህንን ክረምት ከንቱ እንዳያሳልፉ አሳስበው፣ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኮርሶች ሥልጠና በነጻ እየተሰጡ መሆኑን ገለጹ። ቀደም ሲል 5 ሚሊዮን ሰዎች መመዝገባቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አሁን ደግሞ ተራው የሌሎች ወጣቶች መሆኑን በመጥቀስ ጥሪ አቅርበዋል።
በቴክኖሎጂ ዘርፍ አቅምን ለመፍጠር ትልቅ ዕድል የሆነውን ይህንን ሥልጠና ወጣቶች እንዲጠቀሙበት ያሳሰቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ መማር የሚፈልጉ ሁሉ በድርጅቱ ድረ-ገጽ (ethiocoders.et) በመግባት አሁኑኑ እንዲመዘገቡ አሳስበዋል።
ኤር ኢንዲያ በአቪዬሽን ዘርፍ ሰፋ ያለ ልምድ ያላቸውን ኢትዮጵያዊውን አቶ ተወልደ ገብረማሪያም የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አድርጎ መሾሙን አስታውቋል። አቶ ተወልደ በአዲሱ ኃላፊነታቸው አየር መንገዱ ያጋጠሙትን የፋይናንስ እና የአሠራር ፈታኝ ሁኔታዎች የመምራት እና የመወጣት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።
በፍቃዳቸው ኃላፊነታቸውን የለቀቁትን የኤር ኢንዲያ የቀድሞ ኃላፊ ካምፕቤል ዊልሰንን በመተካት፣ አቶ ተወልደ ከመጪው መስከረም መጨረሻ ጀምሮ አዲሱን ሥራቸውን ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Page 1 of 817