Administrator

Administrator

   ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ልጅ ከት/ቤት ተመልሶ ወደ ቤቱ ይመጣል። እቤትም ሆኖ ክፉኛ ያለቅሳል።
አባት ከደጅ ሲመጡ ልጁ ሲያለቅስ ያዩትና፤
“ና አንተ አሽከር፣ ልጄ ምን ሆኖ ነው የሚያለቅሰው? እስቲ ሂድና ጠይቀኸው ና?” ይሉታል።
አሽከር እጅ ነስቶ የታዘዘውን ሊፈጽም ይሄዳል።
ልጁ ዘንድ ሄዶም፣
“ምን ሆነህ ነው የምታለቅሰው?”
ልጁም፤
“ምንም አልሆንኩም” ይላል።
አሽከር፣
“እንዲሁማ አታለቅስም፤ ዕውነቱን ተናገር” ይለዋል።
ልጅ፣
“የኔታ መትተውኝ ነው”
አሽከርም ወደ አባትዬው ተመልሶ ሲመጣ፣ አባትዬው፡-
    “እህስ ጠየከው?”
አሽከር- “አዎን ጌታዬ”
አባት- “ምን አለ?”
አሽከር- “የኔታ መትተውኝ ነው”አለ።
አባት “ለምን መቱት?”
አሽከር- “እሱን አልነገረኝም”
አባትዬው ተነስቶ ወደ ልጁ ሄደና “ልጄ ለምን ታለቅሳለህ?”
ልጅ- “የኔታ መትተውኝ ነው!” አለ።
አባት- “ለምን መቱህ?”
ልጅ-  “”ሀ” በል ቢሉኝ እምቢ ብዬ ነው”
አባት - “የሞትክ! ሰነፍ! “ሀ” ማለት አቅደህ ትገረፋለህ!”
ልጅ- “አይ አባዬ፣ የየኔታ  ጉዳቸው መች ያልቃል- “ሀ” ስል “ሁ” በል ዠይሉኛል፡፤ “ሁ” ስል “ሂ” በል ይሉኛል። “ሂ” ስል “ሃ” በል ይሉኛል። እንዲህ እያሉ እስከ “ፐ” ድረስ ሊያስለፉኝ እኮ ነው።” አላቸው ይገባል።
*   *   *
ወጣቶች እውቀትን ከሚሸሹበት ዘመን ይሰውረን። አንድ ያገራችን ገጣሚ እንዳለው፤
“… ዘመንና ዘመን እየተባረረ
ይሄው ጅምሩ አልቆ፣ ማለቂያው ጀመረ!”
ወጣቶች ለመማር ዝግጁነታቸውን እንዲያጠናክሩ
ሀ. ወላጆች
ለ. መምህራን
ሐ. ራሳቸውና ባልንጀሮቻቸው
ሊያበረታቷቸው ይገባል። አዲሱ አሮጌውን መውረሱ ከአበው ጊዜ ጀምሮ የሚነገር ሀቅ ነው። በፈረንጅኛው THE NEW IS  INVINCIBLE ይባላል። “አዲሱ አሸናፊ ነው” እንደማለት ነው። አንድ ስርዓት ተለዋዋጭ ትውልዶችን ያስተናግድ ዘንድ ግድ  ነው። አንጋፋው ለጎልማሳው፣ ጎልማሳው ለወጣቱ ማውረስ አለበት፡፡ ማውረስ ስንልም ጤናማና ያደገ ውርስ ማለታችን ነው! በትምህርት፣ በጤና፣ በመወያየት ባህል የጠነከረ ማህበረሰብ መገንባት ማለታችን ነው። ይህ ማህበረሰብ ወጣት ወንዶችና ወጣት ሴቶች ላይ የሚሰራና በትኩረት ነጋ-ጠባ የሚተጋ ኃይልን  የሚፈጥር መሆን አለበት። በዚህ ረገድ የመንግስት ሚና የማይናቅ ነው። መንግስት ቢሮክራሲ የፀዳ መሆንና የተቋማት መጠናከር ልዩ ትኩረትን ይጠይቃል። ዛሬም ከገጣሚ ገሞራው ጋር፣
    “… ነገሩ አልሆን ብሎ ሁኔታው ሲጠጥር
         ጠጣሩ እንዲላላ፣ የላላውን ወጥር…”
እንላለን። ሁሉም ጥብቅ ህብረተሰቡን የሚገነባ ነውና  ከተተገበረ ዋና ነገር ነው። ለዚሁም ብርታቱንና ጥናቱን ይስጠን!


  የኮሮና ቫይረስ በወረርሽኝ መልክ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በመላው አፍሪካ 30 ሚሊዮን ያህል ሰዎችን ከስራ ገበታቸው በማፈናቀል ለስራ አጥነት መዳረጉንና ወረርሽኙ በፈጠረው ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ ሳቢያ በ2021 ብቻ 39 ሚሊዮን ያህል አፍሪካውያን ለከፋ ድህነት ሊጋለጡ እንደሚችሉ የአፍሪካ ልማት ባንክ አስታውቋል፡፡
የባንኩ ፕሬዚዳንት አኪንዉሚ አዴሲና ባለፈው ሰኞ ለሲኤንቢሲ እንደተናገሩት፤ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ እስከ 190 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ጥቅል የአገር ውስጥ ምርት ቅናሽ የገጠማት ሲሆን፣ የበጀት እጥረቷም ከቀውሱ በፊት ከነበረው 60 በመቶ ወደ 70 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡
ከ7.6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁባት አፍሪካ ከኮሮና ተጽዕኖ ማገገም የምትችለው በቂ ክትባት ስታገኝ ብቻ መሆኑን የጠቆመው ዘገባው፣ ከአህጉሪቱ ህዝብ ሙሉ ለሙሉ ለመከተብ የቻለው 2.5 በመቶው ብቻ መሆኑንና ይህ መጠን ከእስያ 25 በመቶ፣ ከደቡብ አሜሪካ 27 በመቶ እንዲሁም ከ40 በመቶ በላይ ከደረሰው የአውሮፓና አሜሪካ የክትባት ሽፋን አንጻር ሲታይ እጅግ በጣም ዝቅተኛ መሆኑንም አመልክቷል፡፡
በሌላ የአፍሪካ ኮሮና ዜና ደግሞ፣ የደቡብ አፍሪካ ተመራማሪዎች ራሱን በተደጋጋሚ የመቀያየር ባህሪይ ያለውና ሲ.1.2 የሚል ስያሜ ያለው አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ማግኘታቸውን የዘገበው ሮይተርስ፣ የስርጭትና የገዳይነት ደረጃውን ጨምሮ በቫይረሱ የተለያዩ ተፈጥሮዎች ዙሪያ ጥናት እየተደረገ እንደሚገኝ መነገሩን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በሁሉም የአገሪቱ ግዛቶች ታይቷል የተባለው ይህ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ አፍሪካን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓና እስያ ከተሞች ሰዎችን ማጥቃቱንም ዘገባው አመልክቷል፡፡

አንጋፋው ድምጻዊ አለማየሁ እሸቴ ባለፈው ሐሙስ ነሐሴ 27 ቀን 2013 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ላይ  ባደረበት የልብ ህመም ሳቢያ፣ በ79 ዓመቱ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ድምጻዊ አለማየሁ የተወለደው በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን እስከ ሦስት ዓመቱ ድረስ ከእናቱ ጋር ደሴ ነበር ያደገው።  የሦስት ዓመት ልጅ ሳለ አባቱ ወደ አዲስ አበባ አመጡት። ‘ክርስቲያን ትሬኒንግ ኢንስቲቲዩት’ አዳሪ ትምህርት ቤት ገብቶ ትምህርቱን ተከታትሏል፡፡ በትምህርት ቤቱ ቆይታውም መንፈሳዊ መዝሙሮችን  በእንግሊዝኛ ጭምር በመዘመር  ይታወቅ ነበር።
በዘመኑ ተወዳጅና እውቅ የነበሩ የምዕራባውያን ድምጻውያንን ሙዚቃ ማንጎራጎር ያዘ። በተለይ የሮክ የሙዚቃ ስልት ለአለማየሁ ነፍሱ ነበር። የአሜሪካውያኑን ድምጻዊያን ፓት ቦን፣ ቢል ሃሊይ እና ኤልቪስ ፕሪስሊን የእንግሊዝኛ ዘፈኖች አብዝቶ ይጫወት ነበር። የኤልቪስ ፕሪስሊን ሙዚቃ አብዝቶ በመጫወቱ፣ በፀጉር አበጣጠሩና ዘመናዊ አለባበሱ ‘ኢትዮጵያዊው ኤልቪስ’ የሚል ቅፅል ስምም ተሰጥቶት ነበር፡፡  
በዚህ እውቅናን እያተረፈ የመጣው አለማየሁ በጀነራል ዊንጌት፣ በዳግማዊ ምንሊክና በሌሎችም ትምህርት ቤቶች እየተጋበዘ ይዘፍን ነበር። በወቅቱ ለአማርኛ ዘፈን ብዙም ግድ አልነበረውም፡፡
ከአለማየሁ እሸቴ የሙዚቃ ሥራዎች መካከል "ስቀሽ አታስቂኝ"፣ "እንደ አሞራ ክንፍ አውጥቼ ልብረራ"፣ "ማን ይሆን ትልቅ ሰው"፣ "ምሽቱ ደመቀ"፣ "አዲስ አበባ ቤቴ"፣ "የወይን ሃረጊቱ"፣ "የሰው ቤት የሰው ነው"፣ "ደንየው ደነባ"፤ "ትማርኪያለሽ"፣ "ወልደሽ ተኪ እናቴ"  እና "ተማር ልጄ" በዋነኝነት ይጠቀሱለታል፡፡
የድምፃዊውን ድንገተኛ ህልፈት ተከትሎ የመንግስት ባለሥልጣናትና አርቲስቶች እንዲሁም አድናቂዎቹ ሀዘናቸውን እየገለፁ ይገኛል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት የሃዘን መልዕክት፤ ሃገራችን ካፈራቻቸው ታላላቅ ድምጻውያን አንዱ በሆነው በአለማየሁ እሸቴ ዜና እረፍት እጅግ አዝኛለሁ ብለዋል፡፡
‘‘የአለማየሁ ዘመን ተሻጋሪና ቁም ነገር አዘል ግጥምና ዜማዎቹ በኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ ለዘለዓለም ይኖራሉ’’ ሲሉም  አስፍረዋል፤ በመልዕክታቸው። ለድምጻዊው ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብም መጽናናትን ተመኝተዋል።
አዲስ አድማስ ጋዜጣ በድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ  ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ፤ ለቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል።


    በኢትዮጵያ በቴሌው ዘርፍ 8.5 ቢሊዮን ዶላር ድረስ ፈሰስ የማድረግ ዕቅድ አለው

         ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቴሌኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ በመጪው የፈረንጆች ዓመት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ገለፀ። ኩባንያው በኢትዮጵያ በቴሌው ዘርፍ እስከ 8.5 ቢሊዮን ዶላር ፈሰስ  ለማድረግ ዕቅድ አለን ብሏል።
የኩባንያው ኃላፊዎች ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተገለጸው፤ ኩባንያው በኢትዮጵያ የቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ፍቃድ አግኝቷል። የኩባንያው ዋና ስራ አስኪጅ ፒተር ኔድግዋ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ ዕድገት እያላየች ያለች አገር በመሆኗ በዚህች አገር ውስጥ ስራ መጀመሩን ለእኛ ከፍተኛ ዕድል ነው ብለዋል። ኩባንያው በመጪው ፈረንጆች አዲስ ዓመት ወደ ስራ ሲገባ ዘመናዊ የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎቶችን ተደራሽ እንደሚያደርግም ተጠቁሟል።

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ፣ ታጣቂዎች በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ በፈጸሙት ጥቃት እስረኞችን አስመልጠው በርካታ የፖሊስ አባላትን ማቁሰላቸው ተነገረ።
ቢቢሲ ከአካባቢው ነዋሪዎችና ከሆስፒታል ምንጮች ማረጋገጥ እንደቻለው፣ ጥቃቱ የተፈጸመው ማክሰኞ ነሐሴ 25 ቀን 2013 ዓ.ም ነው። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር እያለ የሚጠራውና ከወራት በፊት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪ ድርጅትነት የተፈረጀው፣ መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ጥቃቱን ስለመፈጸሙ አስታውቋል።
በሳሲጋ ወረዳ የጋሎ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንድ ግለሰብ ጥቃቱን በተመለከተ ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ ማከሰኞ ረፋድ 3፡30 አካባቢ በከተማዋ የተኩስ ድምጽ መሰማት እንደጀመረ ገልጸዋል።
የተኩስ ልውውጡም በአካባቢው በነበሩ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና ታጣቂዎቹ መካከል መሆኑንና ይህም እስከ እኩለ ቀን መቀጠሉን ይናገራሉ። ታጣቂ ቡድኑ ጥቃት የፈጸመው በሳሲጋ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ሲሆን በዚህም ጥቃት እስረኞችን ማስመለጡን ነዋሪው ይገልጻሉ።
“ከእስር ቤቱ ያመለጡ ስድስት ሰዎች እኔ ወደ ምሠራበት ቦታ ሸሽተው ገብተው ነበር። ክፍት በር ሲያገኙ ነው ዘልቀው የገቡት። ከዚያ በኋላ ወጥተው ሄዱ። እኔም የሥራ ቦታዬን ዘግቼ ከአካባቢው ሄድኩ” በማለት የገጠማቸውን  ገልጸዋል።
የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ በተረጋገጠው የትዊተር ገጽ ላይ፣ ቡድኑ በሳሲጋ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ስለመፈጸሙ አስፍሯል። በዚህም ጥቃት “ከ100 በላይ የፖለቲካ እስረኞች ተለቀዋል” ብሏል።
ቢቢሲ ከእስር ያመለጡ እስረኞችን ትክክለኛ ቁጥር ከገለልተኛ ወገን ማጣራት አልቻለም።
ጥቃቱን ተከትሎ በቁጥር ከ40 በላይ የሚሆኑ የአካባቢው የፖሊስ አባላት፣ የተለያየ ጉዳት ደርሶባቸው ለሕክምና ወደ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል መምጣታቸውን ከሆስፒታሉ ማረጋገጥ ተችሏል።
ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ስድስት የፖሊስ አባላት ቀዶ ሕክምና እንደተደረገላቸውና ሌሎች ስምንት የፖሊስ አባላትም የቀዶ ሕክምና እንደሚደረግላቸው  የሆስፒታሉ ሠራተኛ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተጨማሪም “ስድስት ሰዎች ደግሞ ወደ አዲስ አበባ ሪፈር ተብለዋል” በማለት ለተጨማሪ ሕክምና ወደ ሌላ የጤና ተቋም የተላኩ የፖሊስ አባላት መኖራቸውንም ጨምረው ተናግረዋል። በዚህ ጥቃት ሕይወቱ ያለፈ የፖሊስ አባል ስለመኖሩ እስካሁን ማወቅ አልተቻለም።
የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው፤ “እኔ አላውቅም። በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ የለኝም” በማለት ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥተዋል።
(ቢቢሲ አማርኛ)

      በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ስር ወዳለችው ቡለን ወረዳ፤ ሰሞኑን  በባጃጅ ሲጓዙ የነበሩ አምስት ሚሊሺያዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። የክልሉ የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት አልቦሮ፤ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የጉሙዝ ታጣቂዎች አምስት ሚሊሺያዎችን መግደላቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል።
ሚሊሺያዎቹ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው “ለአካባቢ መጠበቂያ የሚሆን [ትጥቅ] ሊታጠቁ ወደ ከተማው ማዕከል በመጓዝ ላይ እያሉ” መሆኑን አቶ አብዮት ገልጸዋል። በመተከል ዞን ከምትገኘው ዶቤ ቀበሌ እንደተነሱ የተነገረላቸው ሚሊሺያዎች፤ ወደ ቡለን ከተማ ሲጓዙ የነበረው በሶስት ባጃጆች ተሳፍረው ነበር ተብሏል።
ታጣቂዎቹ ጥቃቱን የሰነዘሩት በአንደኛው ባጃጅ ውስጥ በነበሩ ሰባት ሚሊሺያዎች ላይ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስረድተዋል። በጥቃቱም አምስት ሚሊሺያዎች ሲገደሉ፤ ሁለቱ መቁሰላቸውን በቡለን ወረዳ የሚኖሩ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የመንግስት ሰራተኛ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
ጥቃቱ የተፈጸመበት፤ በዶቤ ቀበሌ የሚገኘው በተለምዶ “እሪ በከንቱ” ተብሎ የሚጠራው አካባቢ፤ ከዚህ በፊትም ስጋት ያለበት እና ለትራንስፖርት የማይመች እንደሆነ የሚጠቅሱት ሌላ የቡለን ከተማ ነዋሪ፤ የዛሬው ጥቃት የተፈጸመው “በተጠና መልኩ” ሳይሆን እንደማይቀር ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። ለዚህም በማስረጃነት የሚያቀርቡት፤ በቡለን ወረዳ የነበረው የመከላከያ ሰራዊት ትላንት ማምሻውን አካባቢውን ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ ጥቃቱ መሰንዘሩን ነው።
በቡለን ወረዳ የነበረው የመከላከያ ሰራዊት ለሌላ ግዳጅ ወደ ጉባ ወረዳ አልመሃል አካባቢ ከተንቀሳቀሰ በኋላ፤ አሁን በስፍራው የሚገኙት የሲዳማ ልዩ ኃይል እና የፌደራል ፖሊስ ብቻ መሆናቸውን ነዋሪው አብራርተዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ግን ጥቃቱ ከኃይል እንቅስቃሴው ጋር የተያያዘ “ሊሆንም፤ ላይሆንም ይችላል” ብለዋል።
“ኃይል እንደ አስፈላጊነቱ ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ ሊንቀሳቀስ ይችላል” ያሉት አቶ አብዮት፤ በአሁኑ ወቅት በአካባቢው የልዩ ኃይል አባላት፣ ሚሊሺያዎች እና የታጠቁ ግለሰቦች መኖራቸውን ገልጸዋል። “በአካባቢው የኃይል እጥረት ካለ ከሚመለከተው አካል ጋር ተነጋግሮ የኃይል እጥረቱ አንዲቀረፍ ማድረግ ይቻላል” ሲሉም የአካባቢው ነዋሪዎች ስጋት ሊገባቸው እንደማይገባ አስገንዝበዋል።
እርሳቸው ይህን ቢሉም፤ የአካባቢው ነዋሪዎች ግን የመከላከያ ሰራዊት ስፍራውን ለቅቆ በመውጣቱ ገና ከአሁኑ ችግሮች መስተዋል መጀመራቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስረድተዋል። በቡለን ከተማ በባጃጅ ሹፌርነት የሚሰራው ሀብታሙ ደሬሳ፤ ከወንበራ እና ሌሎች አካባቢዎች የመጡ በርካታ ሰዎች በስጋት ምክንያት ወደ ሌሎች ቦታዎች መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ ተናግሯል።
ሰዎቹ ወደ ቡለን ከተማ የመጡት፤ በመከላከያ ሰራዊት ታጅበው በአማራ ክልል ወደምትገኘው ቻግኒ ከተማ ለመጓዝ እንደነበር የጠቆመው ሀብታሙ፤ ሰራዊቱ አካባቢውን ለቅቆ በመሄዱ መሄጃ ማጣታቸውን አብራርቷል። “እንኳን ያለ አጃቢ [መንቀሳቀስ]፤ ዱር ወጥቶ አንድ ፍየል ይዞ መምጣት አይቻልም” ሲልም በአካባቢው ያለውን የስጋት ደረጃ ገልጿል።
የቡለን ወረዳ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ላለው የጸጥታ ስጋት እና ዛሬው ለተፈጸመው ጥቃት ተጠያቂ የሚያደርጉት የጉሙዝ ታጣቂዎችን ነው። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊም “ጥቃቱን የፈጸሙት የጉሙዝ ታጣቂዎች ናቸው” ሲሉ ወንጅለዋል።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

  በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ያለው የህልውና ዘመቻና ጦርነት ሀገሪቱ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ገቢ የመሰብሰብ አቅምን እና የታክስ መሰብሰቢያ ማእከላትን በማስፋፋት እየተሰራ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትር ዴኤታው በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በተዘጋጀው ሳምንታዊ መግለጫ ላይ የሀገሪቷን ወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በወቅቱ እንደገለፁትም ጦርነቱ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል የገቢ መሰብሰብ አቅም እንዲጨምር ተደርጓል፡፡
አሸባሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነት በቅርቡ ለምግብና ለሌሎች ወጪዎች 9 ቢሊየን ብር ወጪ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ በሃገር ውስጥና በውጪ የሀገር ህልውና ዘመቻን አጀንዳው ማድረጉም ያለውን የትብብር መንፈስ ያጠናከረና የችግር ግዜን ለመውጣት ያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ በቅርቡ ያደረገችውና ሚሊየኖች የተሳተፉበት ምርጫም የሃገራዊ አንድነትን አመላካች ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይ አመት ኢኮኖሚውን የማነቃቃት ስራ ይቀጥላል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ የገቢ ማሰባሰብ አቅምን ማሳደግ፣ ምርታማነትንና የካፒታል ገበያን ማስፋፋት፣ ፕራይቬታይዜሽን ተጠናክረው ይቀጥላሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
(ዋልታ)

 በወረባቦ ወረዳ ሰርጎ ገብቶ የነበረው ቁራጭ የህወሓት  ሃይል እየተደመሰሰ መሆኑን የወረዳው አስተዳደር የህዝብ ሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ መሃመድ ሰይድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ተንቀዥቅዦ ወደ ወረዳው ገብቶ የነበረው ቡድን በመከላከያ፣ በአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላትና በማህበረሰቡ እየተደመሰሰ ነው፡፡
ቡድኑ  ወረዳውን ለቆ መሸሹን የገለጹት ሀላፊው÷ የጸጥታ ሃይሉ በገባበት እየተከተለ እየቀበረው መሆኑን ነው የገለጹት።  በየትኛውም በኩል ማምለጫ የሌለው የጁንታው ሃይል፣ አማራጩ መደምሰስ ብቻ መሆኑን አቶ መሃመድ ተናግረዋል።
 ወጣቶች በግንባር ለሚገኘው የጸጥታ ሃይል ከኋላ ደጀን በመሆን ከከተማው ማህበረሰብ ምግብ በማሰባሰብ ግንባር ድረስ በማድረስ ለሰራዊቱ ያለውን ደጀንነት በተግባር እያሳዩ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም ከጠላት ሃይል ጋር በሚደረገው ፍልሚያ የወረዳው ወጣቶች በከፍተኛ ወኔና ተነሳሽነት ያላቸውን መሳሪያ በመያዝ በጦር ግንባር ድረስ በመግባት ከጠላት ሃይል ጋር እየተፋለመ ይገኛል፡፡
በተመሳሳይ ዜና፤ በከሃዲው ጄኔራል ምግበይ ሀይለ እየተመራ በማይጠብሪ ግንባር በደባርቅና ዳባት ወረዳዎች አዋሳኞች በጫንቅ፣ ጭና እና ወቅን አካባቢዎች የመጣው የአሸባሪው የህወሓት ቡድን ተደመሰሰ፡፡ የመከላከያ ሰራዊት መረጃ እንዳመለከተው፤ ይህ ወራሪና ዘራፊ የህወሓት ቡድን የእነ ወዲ ረዳን ሒሳብ የማወራረድ ስሌት ይዞ የመጣ ነው፡፡
ከግንባሩ አዛዦች መካከል አንዱ ኮሎኔል ሀብታሙ ምህረቴ እንደገለጹት፤ በሠራዊታችን አባላት መሪነት በግንባሩ ከተሰለፈው የወገን ሀይል ጋር በሳምንቱ ጠላት የከፈተውን ተደጋጋሚ ጥቃት በመመከትና ወደ ማጥቃት በመሸጋገር የመጣውን ጠላት ለመደምሰስና ድል ለመቀዳጀት ተችሏል፡፡
በወቅን ጭና የተሰለፈው የወገን ሀይል በወሰደው እርምጃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የህወሓት ሀይል የተደመሰሰና የተማረከ ሲሆን÷ ፀረ-ታንክ፣ ዲሽቃ ፣ ብሬን፣ ላውንቸር እና ስናይፐርን ጨምሮ የተለያዩ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳሪያዎች ፤ ከ15 ሺህ 600 በላይ የተለያዩ ጥይቶች፣ የመገናኛ ሬዲዮና የእጅ ስልኮች እንዲሁም የብር ኖቶች ከጠላት ተማርከዋል፡፡
(ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት)            መንግሥት ከአገር ውስጥና ከውጭ አበዳሪ ምንጮቹ ላለፉት ዓመታት የተበደረው ውዝፍ የዕዳ መጠን 2.4 ትሪሊዮን ብር ደረሰ። የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ውዝፍ ዕዳ እ.ኤ.አ. እስከ ጁን 30 ቀን 2021 ድረስ 2.4 ትሪሊዮን ብር ሆኖ መመዝገቡን ይፋ ያደረገው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ሰሞኑን ያወጣው የዕዳ መግለጫ ሰነድ ነው።
ብሔራዊ ባንክ ላለፈው አንድ ዓመት ባደረገው የብር ምንዛሪ ተመን ለውጥ ምክንያት የብር የመግዛት አቅም በከፍተኛ ደረጃ በመውረዱ፣ አጠቃላይ የአገሪቱ ውዝፍ ዕዳ በ221.5 ቢሊዮን ብር እንዲያሻቅብ ምክንያት እንደሆነም ሰነዱ ያመለክታል። አጠቃላይ የአገሪቱ የዕዳ መጠን በውጭ ምንዛሪ ሲሰላ 55.6 ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰም ሰነዱ ያመለክታል።
ከአጠቃላይ ውዝፍ ዕዳ ውስጥ የአገር ውስጥ አጠቃላይ ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.14 ትሪሊዮን ብር ሲሆን፣ የአገር ውስጥ የዕዳ መጠን ባለፈው ዓመት 918.9 ቢሊዮን ብር ነበር።
በተመሳሳይ ከውጭ የተበደረው አጠቃላይ ውዝፍ ዕዳ መጠን ወደ 1.29 ትሪሊዮን ብር ያሻቀበ ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ ተመዝግቦ የነበረው የውጭ የዕዳ መጠን 1.01 ትሪሊዮን ብር እንደነበር ሰነዱ ይገልጻል።
መንግሥት ከአጠቃላይ የውጭ ውዝፍ ዕዳውን ለማቅለል በዘንድሮው በጀት ዓመት መዝጊያ ድረስ 73.1 ቢሊዮን ብር ወይም 1.8 ቢሊዮን ዶላር ለውጭ አበዳሪዎቹ ከፍሏል። ይህም ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከከፈለው 64.03 ቢሊዮን ብር ከፍ ያለ ቢሆንም፣ በወቅቱ በነበረው የምንዛሪ ተመን መሠረት ግን ሁለት ቢሊዮን ዶላር በመሆኑ ባለፈው ዓመት የከፈለው የዕዳ መጠን ብልጫ አለው።
በሌላ በኩል መንግሥት ዘንድሮ 1.4 ቢሊዮን ዶላር በተጨማሪ ከዓለም ባንክ ተበድሯል። ነገር ግን በዚሁ ዓመት 1.8 ቢሊዮን ዶላር የዕዳ ክፍያ በማድረጉ ምክንያት የተጣጣው የብድር ገቢ፣ በዓመቱ መጨረሻ ዜሮ ወይም በዓመቱ ከተገኘው የውጭ ብድር ፍሰት በ432 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ ያለው ገንዘብ ለዕዳ ክፍያ ውሏል።
የዛሬ አምስት ዓመት ማለትም እ.ኤ.አ. በ2016/17 የነበረው የአገሪቱ አጠቃላይ የውጭ የብድር ዕዳ መጠን 23.3 ቢሊዮን ዶላር፣ ወይም በወቅቱ የብር ምንዛሪ ተመን 539.5 ቢሊዮን ብር እንደነበር መረጃው ያመለክታል።
ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የውጭ የዕዳ መጠኑ ከ23.3 ቢሊዮን ዶላር ወደ 29.5 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል፡፡ ይሁን እንጂ በሰኔ ወር 2013 ዓ.ም. በነበረው የብር ምንዛሪ ተመን ሲሰላ ግን 1.29 ትሪሊዮን ብር እንደሆነ መረጃው ያስረዳል።
በተመሳሳይ የዛሬ አምስት ዓመት የነበረው አጠቃላይ የአገር ውስጥ የዕዳ መጠን 522.8 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፣ በሰኔ ወር በ2013 ዓ.ም. ላይ የዕዳ መጠኑ ከእጥፍ በላይ በመጨመር 1.14 ትሪሊዮን ብር ደርሷል።
የዛሬ አምስት ዓመት የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ዕዳ መጠን 1.06 ትሪሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፣ በአምስት ዓመታት ውስጥ ወደ 2.4 ትሪሊዮን ብር አሻቅቧል።
ከአጠቃላይ የዕዳ መጠን ውስጥ 1.29 ትሪሊዮን ብር የሚሆነው የዕዳ መጠን በዶላር ተመንዝሮ ለውጭ አበዳሪዎች የሚመለስ በመሆኑ፣ የአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ማሻሻል ከተቻለ አሳሳቢ እንደማይሆን ባለሙያዎች ያስረዳሉ።
(ሪፖርተር)


Saturday, 28 August 2021 14:42

ከፌስቡክ ገጾች በጨረፍታ

      አሜሪካ ልክ ልካችንን ነገረችን!
                       ዘውድአለም ታደሠ


           (አማን መዝሙር)
አሜሪካ በኤምባሲዋ በኩል “ልካችሁን እወቁ” ብላናለች። «እናንት መናጢ ድሆች» ብላ ሰድባናለች። ወገን ተዋርደናል።
ሲያንቀለቅለን “USAID ለህዝቡ እያለ ጁንታውን ይቀልባል” ብለን ከሰን ነበር። ምነው አፋችንን በቆረጠው። አሜሪካ ዛሬ በፌስቡክ ገፅዋ አስገባችልን። (ኩሩው የጦቢያ ህዝብ ሆይ፤ ስድብህን እነሆ ወደ አማርኛ ተርጉሜልሀለሁ፡-)
«እናንት ንገሩኝ ባይ ችስቶች። እናንት ረሃብተኞች። ወልዳችሁ የትም የጣላችኋቸውን ድሆች ባበላን እጃችን አመድ አፋሽ ሆነ ማለት ነው? የኢትዮጵያን 7% ህዝብ የምንቀልበው እኛ መሆናችንን ምነው ረሳችሁት? በርግጥ ጁንታው ከምንወስደው ምግብ ላይ ሰርቆ ሊበላ ይችላል። እና ጁንታው ይበላል ተብሎ ህዝብ በረሃብ ይለቅ ወይ? እናንት ዘላለማችሁን ከጦርነት አትወጡ። ወይ ጠግባችሁ አትዋጉ። ዘላለማችሁን የኛ ሸክም ናችሁ። ሰው እናድርጋችሁ ብለው አውሮፓውያኑ በቅኝ ግዛት ቢይዟችሁ ነፃነት ይሻለናል ብላችሁ ገፋችኋቸው። ከዚያ እነሱ ሲለቋችሁ እርስ በርስ ትገዳደሉና የድል ቀን ታከብራላችሁ። ጦርነቱ ጋብ ሲልላችሁ ደግሞ ረሃብ ይገድላችኋል። ምን አፍ አለን ብላችሁ ነው ምታወሩት። ክፍት አፎች። በሐገራችሁ ሀፍረት የሚባል ነገር የለም ወይ? በማያገባን ገብተን 7 ፐርሰንቱን ድሃችሁን የምናበላው´ኮ ከፈጣሪ እናገኘዋለን ብለን ነው። እናንተ ግን ስንዴያችንን ጥርግ አርጋችሁ እየበላችሁ እኛኑ ሴጣን ታረጉናላችሁ። ወይ ነዳጅ ፣ ወይ አልማዝ በሌለው ደረቅ መሬት ምክኒያት ትዋጉና “አሜሪካኖች አዋጉን” ትላላችሁ። ለሃጢአታችሁ ሰይጣንን ለጠባችሁ ደግሞ አሜሪካን እስከ መቼ ሰበብ እያደረጋችሁ ትኖራላችሁ? ሼም የለም እንዴ?  ደግሞኮ እየሰደባችሁንም እርዳታችንን ትሻላችሁ። አልበዛም እንዴ? “እፀድቅ ብዬ ባዝላት ተንጠልጥላ ቀረች” አለች አሉ፤ ሂላሪ ክሊንተን»Page 11 of 553