Administrator

Administrator

“5ኛው “ደስታ ለእናቴ 2005” የእናቶች ቀን፣ ነገ በካፒታል ሆቴል ከዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ እንደሚከበር “ሱባ 16 ኢቬንትስ” አስታወቀ፡፡ በበዓሉ ላይ ታላቅ ሥራ የሰሩ ኢትዮጵያውያን እናቶች ሽልማት እንደሚበረከትላቸውና በተለያዩ ስፍራዎች በችግር ላይ ያሉ እናቶችን ለመደገፍ እንደታሰበ ተገልጿል፡፡

በኩል ፊልም ፕሮዳክሽን የተሰራው “አይራቅ” የተሰኘ ሮማንስ ፊልም፤ ነገ በአዲስ አበባና በአዳማ ከተሞች ይመረቃል፡፡ ፊልሙ በመጪው ሰኞ በአዲስ አበባ አቤል ሲኒማ በ11 ሰዓት እንደሚመረቅም አዘጋጆቹ ጠቁመዋል፡፡ በፊልሙ ሥራ ላይ ደራሲ በሀይሉ ዋሴ (ዋጄ)፣ ፕሮዲዩሰርና ዳይሬክተር ፍቅረየሱስ ድንበሩ የተሳተፉበት ሲሆን ማህደር አሰፋ፣ ሚካኤል ሚሊዮን፣ መስፍን ኃይለየሱስ እና ሌሎችም ተውነውበታል፡

ለሦስት ወራት በተለያዩ የላቲን ዳንሶች የሰለጠኑ የቡድን ዳንሰኞች፤ ዛሬ በክለብ H2O እንደሚመረቁ የማሰልጠኛ ማዕከሉ ኃላፊ ቢ-ላቲኖ አስታወቀ፡፡ የዳንስ ተመራቂዎቹ በጠቅላላ 156 ሲሆኑ ምረቃው ለ26ኛ ጊዜ የሚካሄድ እንደሆነ ታወቋል፡፡

34ኛው ግጥም በጃዝ የፊታችን ረቡዕ ከ11፡30 ጀምሮ በራስ ሆቴል እንደሚቀርብ አዘጋጆቹ አስታወቁ፡ ገጣሚ ነቢይ መኮንን፣ አርቲስት ተፈሪ አለሙ፣ አርቲስት ግሩም ዘነበ፣ ገጣሚ በረከት በላይነህና ሌሎችም ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ የመግቢያ ዋጋ በነፍስ ወከፍ 50 ብር ነው፡፡

    በደራሲ ገብረክርስቶስ ኃይለስላሴ የተዘጋጀው “የሉሲ ከዋክብትና ሌሎችም” የተሰኘ የልጆች መልካም ሥነምግባር ማስተማርያ መፅሐፍ ታትሞ ለንባብ በቃ፡ አንጋፋው ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ በመጽሐፉ ጀርባ ላይ በሰጠው አስተያየት፤ “በየምዕራፉ የተካተቱት ጣፋጭ ታሪኮች ለልጆችም ሆነ ለአዋቂዎች ሰፊ ትምህርት ይሰጣሉ፡፡ ግብረገባዊነትንና መልካም ዜግነትንም ያላብሳሉ” ብሏል፡፡ “ቀደም ሲል ከጓደኛቸው ጋር ያሰናዱት “ናብሊስ” የተሰኘ የመልካም ሥነምግባር መጽሐፍ፤ ከ5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች፣ የሥነምግባርና የሥነ ዜጋ ትምህርት ማጣቀሻ ሆኖላቸዋል” ብለዋል - ደራሲው በአዲሱ መጽሐፋቸው መግቢያ ላይ፡፡ መጽሐፉ በ30 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲ ገብረክርስቶስ፤ ከዚህ ቀደም “ቅንጅት ከየት ወደየት”፣ “እምዬ” የተሰኘ የረዥም ልብወለድ፣ “በፈተናና በጥረት የታጀበ ስኬት” የሚል የህይወት ታሪክ እና “መቀናጆ” የሚል ርዕስ ያለው የግጥም መድበል ለአንባቢያን አቅርበዋል፡፡

Saturday, 10 May 2014 13:11

አዳዲስ መፃህፍት

የመፅሃፉ ርዕስ - የግንኙነት ጥበብ ሥነ-ልቦናዊ ገፅታ
ደራሲ - አለማየሁ ፀሃዬ
የምረቃ ሥፍራ - የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፃህፍት ኤጀንሲ
ሰዓት - ጠዋት 3፡30  
*            *            *
የመፅሃፉ ርዕስ - አቤቶ ኢያሱ፤ አነሳስና አወዳደቅ
ደራሲ - አጥናፍሰገድ ይልማ
የምረቃ ሥፍራ - ጣይቱ ሆቴል
ሰዓት - ከጠዋቱ 3 ሰዓት
*            *            *
የመፅሃፉ ርዕስ - ሁለት ሶስት መልክ
ደራሲ - ሮዝ መስቲካ
ጭብጥ - እርግዝናና ልጅ ማሳደግ
የምረቃ ሥፍራ - ብርሃን ባህላዊ መዝናኛ ማእከል
ሰዓት - ከጠዋቱ 4 ሰዓት
*            *            *
የመፅሃፉ ርዕስ - የሙስና ወንጀልና የክርክር ሥነ-ሥርአት
ደራሲ - አበበ አሳመረ
ጭብጥ - ሙስናና የክርክር ስነ-ስርአቶች
ዋጋ - 59 ብር ከ 90

ህገወጥ መድሃኒቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል መሣሪያ ለጤና ጥበቃ ሚ/ር አበርክቷል
በህክምና፣ በመድሃኒትና በኬሚካል ዘርፍ አዳዲስ ምርቶችን በማቅረብ የሚታወቀውና ዋና መ/ቤቱ በጀርመን አገር የሆነው መርክ የተሰኘው ድርጅት በኢትዮጵያ ሥራ ጀመ፡፡ ይህ በአዲስ አበባ ከተማ የተከፈተው አዲስ ድርጅት ሱዳንን፣ ኢትዮጵያንና ፈረንሳይኛ ተናጋሪ የሆኑ የአፍሪካ አገሮችን የሚየገለግልና በቀጠናው የመጀመሪያው ማዕከል ነው ተብሏል፡፡
ድርጅቱ በትሮፒካል አካባቢዎች እምብዛም ትኩረት ባልተሰጣቸውና እንደ ቢልሀርዚያ ያሉ አደገኛ በሽታዎችን ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም የድርጅቱ ሃላፊዎች ከትናንት በስቲያ በሸራተን አዲስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል፡፡
ድርጅቱ በመሠረተው የዓለም አቀፍ ፋርማ ሄልዝ ፈንድ ፕሮግራም ስር ሁለት አነስተኛ ላብራቶሪዎች ለጤና ጥበቃ ሚ/ር ያበረከተ ሲሆን መሣሪያዎቹ ህገወጥና የጥራት ደረጃቸውን ያልጠበቁ መድሃኒቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡
መርክ በጀርመን አገር በ1968 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰራ በህክምና፣ በመድሃኒትና በኬሚካል ዘርፍ የተሰማራ አንጋፋ ኩባንያ ነው፡፡

Saturday, 10 May 2014 12:32

ውሀና ጠቀሜታዎቹ

ከመተኛትዎ በፊት አንድ ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ፡፡ ስትሮክን እና የልብ ህመምን ለመከላከል ይረዳዎታልና
ጠዋት ከእንቅልፍዎ እንደተነሱ 2 ብርጭቆ ውሃ ከጠጡ ውስጣዊ የሰውነት አካላትዎን ለማነቃቃት ያግዝዎታል፡፡
ሻወር ከመውሰድዎ በፊት አንድ ብርጭቆ ውሃ የሚጠጡ ከሆነ ከፍተኛ የደም ግፊትን ለመከላከል ይጠቅሞታል፡፡
ከምግብ በፊት አንድ ብርጭቆ ውሃ መጠጣት ለምግብ መንሸራሸር ይረዳል
ምግብ ከመመገብዎ 30 ደቂቃ በፊት በቂ ውሃ ይጠጡ፡፡ ብዙ ባለመመገብ የሰውነት ክብደትዎን ለመቀነስ እንዲችሉ ያግዞታል፡፡

የጓደኛዎን ወይም የጐረቤትዎን የፌስቡክ “ፓስወርድ” ለማግኘትና ገመናውን ወይም ሚስጥሯን መበርበር ይፈልጋሉ?

ቀላል ነው፡፡ አንድ መስመር በማትሞላ ጽሑፍ የልብዎን ማድረስ ይችላሉ፡፡ አንድ ደቂቃ አይፈጅም፡፡ “ኮፒ” ከዚያ

“ፔስት” ማድረግ ብቻ ነው ከእርስዎ የሚጠበቀው። ከሁለት ሰዓት በኋላ፤ የጓደኛዎ ወይም የጐረቤትዎ ፓስወርድ እጅ

ይገባል…
በኢንተርኔት የተሰራጨው መልዕክት አጭርና ግልጽ ነው፡፡ በዚሁ መልዕክት የተማረኩ ብዙ ህንዳዊያን ወጣቶች በሁለት

አቅጣጫ የሚመነዘር ትርጉም እንዳለው ልብ አላሉትም፡፡ የሰዎችን ፓስወርድ በቀላሉ መስረቅ ትችላለህ - ይሄ አንደኛው

ትርጉም ነው፡፡ ሌሎች ሰዎች ያንተን ፓስወርድ በቀላሉ መስረቅ ይችላሉ፡፡ ይሄንን ሁለተኛ ትርጉም ልብ ለማለት ጊዜና

ፍላጐት ያልነበራቸው በሺ የሚቆጠሩ ህንዳዊያን፤ የጓደኞቻቸውን ወይም የስራ ባልረቦቻቸውን ገመና ለመበርበር

ቸኩለዋል። እውነትም ነገርዬው ቀላል ነው - “ኮፒ - ፔስት”… “ኮፒ - ፔስት”
በእርግጥም፤ ያቺ አንድ መስመር የማትሞላ ፅሁፍ የዋዛ አይደለችም፡፡ ፓስወርድ ለመስረቅ ተብላ የተቀመመች ናት፡፡

ግን…እዚህ ላይ ነው፤ ታሪኩ ድንገት የሚታጠፈው - “ሰርፕራይዝ” እንደሚባለው፡፡
“ኮፒ - ፔስት” ቀላል ቢሆንም፤ ኮምፒዩተራቸው ምን እያደረገ እንደሆነ አያውቁም። ፓስወርድ እየተሰረቀ ቢሆንም፤

ከሌላ ሰው ተሰርቆ እየመጣላቸው አይደለም፡፡ ከሁለት ሰዓት ጥበቃ በኋላ ምን እንደሚፈጠር ለማየት ነው የሚጠብቁት።

የራሳቸው ኮምፒዩተር፤ የራሳቸውን የፌስቡክ ፓስወርድ አፈላልጐ ለማግኘት፤ ከዚያም ያንን ፓስወርድ ወደሌላ ሰው

አድራሻ ለመላክ ትንሽ ጊዜ ያስፈልገዋል፡፡ ለካ፣ የሌላ ሰው ፓስወርድ ለመስረቅ ሳይሆን፣ የራሳቸው ፓስወርድ እንዲሰረቅ

ነው በፈቃደኝነት የተባበሩት፡፡ “አጭር ምጥን ብላ የተቀመመችና የተራቀቀች ስርቆት” ይሉሃል እንዲህ ነው፡፡ አንድ ሰው

የሆነ ጊዜ ላይ የፈጠራትና ያሰራጫት ዘዴ ናት፡፡ ከዚያ በኋላማ የሆነ ቦታ ሆኖ፣ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በሺ የሚቆጠሩ

የፌስቡክ ፓስወርዶች በአድራሻው እየተላኩ ፓስወርዶችን መሰብሰብ ነው፡፡
ከጥቂት ወራት በፊትም በተመሳሳይ የማታለያ ዘዴ የፓስወርድ ስርቆት እንደተካሄደ የገለፀው ገልፍ ኒውስ እንደሚለው፤

100ሺ ያህል የፌስቡክ ደንበኞች ፓስወርድ ተሰርቆባቸዋል፡፡ ቁምነገሩ ግን፤ እበላለሁ ሲሉ መበላት፤ እነጥቃለሁ ሲሉ

መነጠቅ ይኖራልና እንጠንቀቅ የሚል ነው፡፡
ከሰሞኑ ከወደ ፊሊፒንስ የወጣውም ጉድ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል፡፡ በፌስቡክ አለም፤ ማን ምን እንደሆነ በእርግጠኛነት

ለማወቅ ያስቸግራል። ለዚያም ነው፤ በእውነተኛው አለም በሰው ፊት የማንናገራቸውና የማናደርጋቸው ነገሮች፤ በፌስቡክ

አለም ለመናገርና ለማድረግ ብዙዎች የሚደፋፈሩት። ስኮትላንዳዊው ታዳጊ፣ በፌስቡክ የአንዲት ቆንጅዬ ፎቶ በማየት

ተማርኮ ነው ጓደኝነት (ግንኙነት) የጀመረው፡፡ ብዙም ሳይቆይ የግል ወሬ ማዘውተር መጣ፡፡ ፎቶዎችን ተራ ፎቶ ሳይሆን

ከላይም ከታችም አጋልጠው የሚያሳዩ ፎቶዎችን ተለዋውጠዋል። መኝታ ቤት ውስጥ በወሲብ ጊዜ የሚያጋጥሙ አይነት

ወሬዎችንም ለምደዋል፡፡
ይሄ ሁሉ የሆነው በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ለታዳጊው ስኮትላንዳዊ ሰማይ ምድሩ የተገለባበጠበትም በአጭር ጊዜ

ውስጥ ነው። “ገንዘብ ካላመጣህ፤ ያ ሁሉ ያወራነውን ነገር በኢንተርኔት በፌስቡክ እለቀዋለሁ” የሚል ማስፈራሪያ

ደረሰው፡፡
“በጓደኝነት የፌስቡክ ግንኙነት የፈጠረው፤ ቆንጅዬ ፎቶ በማየት ከተማረከላት ሴት ጋር አይደለም፡፡ ሰዎችን

በማስፈራራት ገንዘብ ከሚዘርፉ የፌስቡክ ማፍያዎች ወጥመድ ውስጥ አስገብተውታል፡፡
የተጠየቀውን ገንዘብ ቢከፍል እንኳ አይለቁትም። በማፍያዎቹ ወጥመድ ተይዘው በማስፈራሪያ ገንዘብ የከፈሉ በርካታ

የፊሊፒንስ ወጣቶች፤ በአንድ ጊዜ አልተገላገሉም፡፡ እንደገና ገንዘብ እንዲያመጡ ይጠየቃሉ፡፡ ብዙዎቹ ሦስት አራቴ

ከከፈሉ በኋላ ነው፤ ማስፈራሪያው ማብቂያ እንደሌለው ገብቷቸው ለፖሊስ የተናገሩት፡፡ የፊሊፒንስ ፖሊስ ወደ 60

ገደማ የፌስቡክ “ማፊያዎችን” በመያዝ ሰሞኑን ፍ/ቤት አቅርቧል፡፡

የቀን እንጀራቸው 7 ነገሮችን ነካ ነካ ማድረግ ብቻ ሆኗል

ከባድና የተከበረ፣ ህፃናት የሚመኙትና ወላጆች የሚኮሩበት የፓይለት ሙያ፣ ተረት ሆኖ ሊቀር እየተቃረበ ነው።

በእርግጥ፣ የጎበዝና የሰነፍ ፓይለት ልዩነት፣ የበርካታ ሠዎች የሕይወትና የሞት ጉዳይ መሆኑን ከማሌዢያው አደጋ

መመልከት ይቻላል። በዚያ ላይ፣ የትርፍና የኪሳራ ጉዳይም ነው። ሉፍታንዛ በቅርቡ ያጋጠመውን ችግር አላያችሁም?

5500 ፓይለቶች ያሉት ሉፍታንዛ፤ በየእለቱ በ1400 በረራዎች ወደ 150ሺ የሚጠጉ መንገደኞችንና በርካታ ጭነቶችን

በማጓጓዝ ይታወቃል።
ይሄን ሁሉ የሚሠራው በአንድ ቀን ነው። በያዝነው ወር መባቻ ግን፣ ብዙዎቹ ፓይለቶች ለሦስት ቀን የሥራ ማቆም

ለማድረግ በመወሰናቸው፣ ሉፍታንዛ ችግር አጋጠመው።  በሦስት ቀናት ውስጥ ወደ 4ሺ ገደማ በረራዎች ተሰርዘው፣ ወደ

ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ መንገደኞች ሲጉላሉ አስቡት። ታዲያ እንዴት ነው፤ የፓይለት ሙያ ተረት ለመሆን የተቃረበው?
ኒው ኤሌክትሮኒክስ መፅሔት እንደዘገበው፤ አውሮፕላኖች ያለ ፓይለት መንገደኞችን እንዲያጓጉዙ ለማድረግ የሚያስችል

ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንደ ልብ ተትረፍርፏል። ቴክኖሎጂዎቹ ሥራ ላይ ውለው በተደጋጋሚ ውጤታማነታቸው

ከመታየቱም በተጨማሪ፣ የመንገደኞች አውሮፕላን ያለ ፓይለት ከለንደን ስኮትላንድ ደርሶ መልስ 800 ኪሎ ሜትር

እንዲያርፍ የተደረገው ሙከራም ስኬታማ ሆኗል። እናም ወደፊት የፓይለት አስፈላጊነት እየተረሳ መምጣቱ አይቀርም።
ዛሬም ቢሆን፣ የፓይለቶች የዘወትር ሥራ እንደድሮው አይደለም። ለአውሮፕላኖችና ለአብራሪዎች የብቃት ማረጋገጫ

በመስጠት ቀዳሚውን የተቆጣጣሪነት ስፍራ የያዘው ኤፍኤኤ እንዳለው፤ ዛሬ ዛሬ የፓይለቶች ስራ ኢምንት እየሆነ ነው።

ከለንደን የተነሳውን አውሮፕላን አትላንቲክ ውቅያኖስን ተሻግሮ፣ እስከ ኒውዮርክ ከተማ ድረስ ከ5ሺ ኪ.ሜ በላይ

ሲጓዝ፣ ፓይለቱ ምን ይሰራል? ወንበሩ ላይ ቁጭ ብሎ ከአጠገቡ የሚገኙ ቁልፎችንና ማርሾችን ስንት ጊዜ ይነካካል? 7

ጊዜ ብቻ! ይሄው ነው፣ የፓይለቱ እለታዊ መደበኛ ሥራ? ለዚህም ነው ሙያው ተረት ለመሆን ተቃርቧል የሚባለው።