Administrator

Administrator

እውቁ የትምህርት ባለሙያና የ95 ዓመት የእድሜ ባለፀጋው ዶ/ር አክሊሉ ሀብቴ ምስጋና ቀረበላቸው፡፡ የምስጋናና የእውቅና መርሃ ግብሩ
ባለፈው ማክሰኞ ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ጦር ሀይሎች አካባቢ በሚገኘው “ሊባዊ ኢንተርናሽና” ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥየተካሄደ ሲሆን የምስጋና መርሃ ግብሩበለባዊ አለም አቀፍ ት/ቤትና በተወዳጅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን አማካኝነት የተሰናዳ ነው፡፡
በእለቱ ልዩ ልዩ ኪነጥበባዊ መሰናዶዎች የቀረቡ ሲሆን ዶክተር አክሊሉ በስፍራው ተገኝተው ለለባዊ ት/ቤት መምህራንናተማሪዎች ልምዳቸውን በማካፈል እውቀትና ልምድ እንዲቀስሙ አድርገዋል፡፡ ዶ/ር አክሊሉ ሀብቴ በሀገራችን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ሲጀመር ከመጀመሪያዎቹ ምሩቃን
መካከል አንዱ ሲሆኑ ዩኒቨርስቲውንም በፕሬዚዳንትነትና በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ ዶክተሩ በሀገራችን የትምህር ዘርፍ ላይ የጎላ ሚና ከማከናወናቸውም በተጨማሪ በአለም ባንክ ውስጥም በትምህርት ዘርፍ ላይ ያገለገሉና የቀዳማዊ ሀይስላሴ ዩኒቨርስቲን(የአሁኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን) ታሪክ በ600 ገፅ በመጽሀፍ በማሳተምና ታሪክ በመሰነድ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡
 እኒህ የ95 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ለረጅም ዓመታት መኖሪያቸውን በሀገረ አሜሪካ ያደረጉ ሲሆን አልፎ አልፎ ወደ ሃገራቸው ኢትዮጵያ ብቅ እያሉ
ይመለሳሉም ተብሏል፡፡ የማክሰኞ እለቱ የምስጋናና የእውቅና መርሃ ግብርም ከአሜሪካ ተመልሰው ሀገራቸው በነበሩበትአጋጣሚ የተሰናዳና በአካል የታደሙበት ነውም ተብሏል፡፡ በእለቱ በርካታ እንግዶች የለባዊ እንተርናሽናል አካዳሚ ሀላፊዎች ተማሪዎችና መምህራን በታደሙበትዶ/ር አክሊሉ ሀብቴ ምስጋናና እውቅና ተሰጥቷቸው ተመስግነዋል፡፡

 32ኛው የአውደፋጎስ የመፅሀፍ ውይይት ክበብ “አደፍርስ ልቦለድ በሙዚቃ መንፈስ መፅሀፍነቱ ሲዳሰስ” በሚል ርእስ ነገ ታህሳስ7 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ቤተ መፃህፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ (ወ መዘክር) እደሚካሄድ አዘጋጆቹአስታወቁ፡፡ የውይይቱን የመነሻ ሀሳብ ከላይ በተገለፀው ርዕስ የምታቀርበው ትሬዛ ዮሴፍ ስትሆን ፍላጎት ያለውና የስነ ፅሁፍ ወዳጅ የሆነ በውይይቱ ላይ እንዲታደምና እውቀት
እንዲቀስም አዘጋጆቹ ጋብዘዋል፡፡

ፈተናውን ማለፍ ያልቻሉ መቋቋሚያ ተሰጥቷቸው ከስራ ይሰናበታሉ ተብሏል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስሩ ለሚገኙትና አዲስ የመዋቅራዊ ማሻሻያ አደረጃጀት ጥናት ባደረጉ ተቋማት ውስጥ ለሚገኙ ሁሉም ሠራተኞችና የስራ ኃላፊዎች የብቃት መመዘኛ ፈተና ሊሰጥ ነው ተባለ። ፈተናውን ያላለፉ ሰራተኞች መቋቋሚያ ተሰጥቷቸው ከስራ ይሰናበታሉ ተብሏል።
ከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ዘርፎች ለሰራኞቹ የብቃት ምዘና ፈተናውን የሚሰጥ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር የብቃት ምዘና ፈተናውን የሚወስዱት የቤቶች ልማት አስተዳደር ጽ/ቤት፣ የስራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት፣ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት፣ ህብረት ስራ ጽቤት የመሬት ልማት አስተዳደር ጽ/ቤት መሆናቸውም ታውቋል። የብቃት ምዘና ፈተናው የሚሰጠው በክፍለ ከተሞቹና በከተማ አስተዳደሩ ስር ባሉ መዋቅሮች እንደሆነም ታውቋል።
የብቃት ምዘና ፈተናውን የወሰዱ ሠራተኞች ፈተናውን ማለፍ ካልቻሉ ሁለት የውሳኔ አማራጮች የቀረቡ ሲሆን፤ አንደኛው አማራጭ ሰራተኛ ድልድሉ ከመደረጉ በፊት አጭር ስልጠና ተሰጥቷቸው ፈተናውን በድጋሚ እንዲወስዱ የሚደረግ ሲሆን ሌላኛው አማራጭ ደግሞ ወደ ሌላ ተቋም ተዛውረው ባላቸው የትምህርት ዝግጅትና በነበራቸው ደመወዝ እንዲመደቡ ይደርጋል ተብሏል። ከእነዚህ ውጪ የሆኑት ደግሞ የማቋቋሚያ ድጋፍ ተደርጎላቸው ከሥራ እንደሚሰናበቱ ተነግሯል። ከስራ እንዲሰናበቱ ያደርጋል ተብሏል። በሃላፊነት ደረጃ ላይ ተመድበው ሲሰሩ የነበሩና የብቃት ምዘና ፈተናውን ማለፍ ያልቻሉ ሠራተኞች ደግሞ ከነበሩበት የስራ መደብና ደመወዝ ዝቅ እንደሚሉ ተገልጿል።የብቃት ምዘና ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ሜያቸው ለጡረታ የደረሱና ጡረታ መውጣት የሚፈልጉ ሠራተኞች በፍቃደኝነት የጡረታ መብታቸውን ማስከበር እንደሚችሉም ታውቋል።
የአስተዳደሩ ሰራተኞች በከተማ አስተዳደሩ ተግባራዊ ሊደረግ ስለተዘጋጀው የብቃት ምዘና ፈተና የሚያውቁት ነገር እንደሌለና ዱብዕዳ እደሆነባቸው ምንጮች ጠቁመዋል። ፈተናው በቀጣዮቹ ሳምንታት ውስጥ እንደሚደረግና መጪው ጥር ወር በፊት እንደሚጠናቀቅ ታውቋል። የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ መርሻል ብርሃኑ ጁላ ሰሞኑን ለፋና ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ-መጠይቅ የድሮን ጥቃቱን አስመልክተው
ሲናገሩ “ድሮን እኮ የተሰራው ለጦርነት ነው፣ለውጊያ ነው የገዛነው ልንዋጋበት ነው እንጂ ድሮን አለን እያልን በሚዲያ ልንገልጸው አይደለም የጦር መሳሪያ ነው ልክ እንደክላሹ ክላሽ የአቅሙን ይሰራል ሌላውም የአቅሙን ይሰራል፣ ድሮንም የራሱን ስራ ይሰራል፡፡ ድሮን እኛ የምንጠቀመው ለስብስብ ዓላማ ነው፡፡ ለወታደራዊ ስብብ ኢላማ የሚባል ነገር አለ፡፡ ስብስብ ኢላማ ማለት የጠላት ጠንካራ ቋጠሮ ማለት ነው፡፡ የጽንፈኛ
ስብስብ ስናገኝ በድሮን እንመታለን”ብለዋል፡፡

•  በትግራይ የተከሰተው ድርቅ ከ77ቱ የከፋ ነው ተባለ  

•  25 ህፃናትን ጨምሮ 400 ሰዎች በረሃብ   ሞተዋል  

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በክልሉ   ከ2 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለረሃብ መጋለጡን ያስታወቀ ሲሆን፤ እስካሁንም 23 ህጻናትን ጨምሮ 400 ሰዎች በረሃብ መሞታቸውን ጠቁሟል፡፡

በክልሉ ያጋጠመውን የድርቅ አደጋ ለመከላከል ያለመ፣ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ  22 አባላት ያሉት "አፋጣኝ ምላሽ ለትግራይ" የተሰኘ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እንቅስቃሴ መጀመሩም ተነግሯል፡፡

የ"አፈጣኝ ምላሽ ለትግራይ" ግብረ ሃይል ሰብሳቢ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ   በዛሬው ዕለት  ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ በአሁኑ ሰአት ለረሃብ አደጋ የተጋለጠውን ከ2 ሚሊዮን በላይ ትግራዋይ ህይወት ለመታደግ በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኝ የክልሉ ተወላጅና ወዳጅ እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።  “ሰብዓዊነት የሚሰማው ሁሉ” የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋም ጠይቀዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ኮሚሽን ኮሚሽነር ገብረሕይወት ገ/እግዚአብሔር (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ድርቁ በአምስት የትግራይ ክልል ዞኖች ተከስቷል ብለዋል።


“በትግራይ የከፋው ድርቅ የተከሰተው በ1951 እና በ1977 ነበር፤ አሁን ያጋጠመን ከዚያም በላይ ነው፤ በዚህ ድርቅ ምክንያት 2 ሚሊዮን ሕዝብ ተርቧል። 400 የሚሆኑ ሰዎች ባለፈው ወር ብቻ  በረሃብ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል” ብለዋል፤ ኮሚሽነሩ፡፡

የ"አፈጣኝ ምላሽ ለትግራይ" ግብረ ሃይል ድጋፍ ማሰባሰቢያ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች የሚከተሉር ናቸው፡-

* አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ፡-00112180095-49

* ወጋገን ባንክ፡- 1001077411101

* የኢትዮጵያ  ንግድ ባንክ፡- 1000592420809

”አርቲስት ሀናን እንደምትጠቅመን አምነንበታል” -ድርጅቱ-

አርቲስት ሀናን ታሪክ፤ ድሪመር ፉድ ማኑፋክቸሪንግ ከተሰኘ ታዋቂና ግዙፍ የቻይና ኩባንያ ጋር የብራንድ አምባሳደር ለመሆን በዛሬው ዕለት በስካይላይት ሆቴል  ከስምምነት ላይ የደረሰች  ሲሆን፤ ለድርጅቱ የሁለት ዓመት የብራንድ አምባሳደር ለመሆን 10 ሚሊዮን ብር ተከፍሏታል፡፡

ኩባንያው በኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ኢንቨስትመንት የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ያቋቋመ ሲሆን ፤ ‹‹ኤስ›› በሚል ብራንድ ያልተለመዱና አዳዲስ የታሸጉ የኬክ ወይንም የጫፋጭ ምግቦችን እያመረተ በመላው አገሪቱ እያከፋፈለ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡



ድርጅቱ ይህንን ‹‹ኤስ›› የተሰኘ ብራንድ ምርቶቹን በስፋት ለማስተዋወቅና ስርጭቱን ለማሳደግ የአንድ አመት የኮርፖሬት ብራንድ ፕሮሞሽን እቅድ ማውጣቱን ገልጿል፡፡ በዚህ እቅዱ ውስጥም ታዋቂዋን አርቲስት ሀናን ታሪክን ማካተቱን አስረድቷል፡፡

 ‹‹የኤስን ብራንድ ፕሮሞሽን ውጤታማና ስኬታማ ለማድረግ አርቲስት ሀናን እንደምትጠቅመን አምነንበታል›› ብሏል፤ ድርጅቱ በሰጠው መግለጫ፡፡

የቴሌግራም ቻናልችንን  በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ያዘጋጀውና የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አካል የሆነው “የኛ ምርት” የተሰኘ አውደ ርዕይና ባዛር በዛሬው ዕለት ረፋዱ ላይ በስካይ ላይት ሆቴል ተከፈተ፡፡

አውደ ርዕዩና ባዛሩ “ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” በሚል መሪ ቃል፣ እስከ ታሕሳስ 7 ቀን 2016 ዓም ድረስ እንደሚቆይ  ተገልጿል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በመክፈቻው ላይ ባደረጉት ንግግር፤ አምራቹን ዘርፍ ለማነቃቃት የተለያዩ ንቅናቄዎች ተጀምረው ለውጥ ማስመዝገብ ተችሏል፤ የዚህ ንቅናቄ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኤግዚቢሽንና ባዛር፣ አምራቾችን ከሸማቾች ጋር በማገናኘት፣ የሀገር ውስጥ ምርትን በማስተዋወቅና የኑሮ ውድነቱን በማረጋጋት ሰፊ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።


የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው፤ አምራች ዘርፉን መደገፍ ኢትዮጵያ ለምታደርገዉ የብልጽግና ጉዞ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ አውደ ርዕይና ባዛር ላይ ከ85 በላይ የሀገር ዉስጥ አምራች ኢንተርፕራይዞች የተሳተፉ ሲሆን፤ ከ50 ሺ በላይ ሰዎች እንደሚጎበኙት ይጠበቃል ተብሏል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር አሰራርን ለማዘመን፣ የቴክኖሎጂ ሶሉሽኖችን ለማቅረብና ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሻሻል የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሙን አስታወቀ፡፡

 
 ኢትዮ ቴሌኮም፤ ከዚህ ቀደም የሚኒስቴር መ/ቤቱን አሰራር ለማዘመን የሚያስችሉ ልዩ ልዩ የቴክኖሎጂና ዲጂታል ሶሉሽኖችን ለማቅረብ የሚያስችሉ በርካታ ሥራዎችን ማከናወኑን ጠቁሞ፤ በቀጣይም የተለያዩ የቴክኖሎጂ ሶሉሽኖችን በስፋት ለማቅረብና የስራ ፈጠራን ለማበረታታት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ድጋፎችን በማድረግ፣ የዜጎችን ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት የፊርማ ሥነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት መከናወኑን በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራሮች መካከል ከዚህ ቀደም ስትራቴጂካዊ አጋርነትን የበለጠ ለማሳደግና ውስጣዊ አቅሞችን ለአገራዊ ተልዕኮ አቀናጅቶ ለመጠቀም የጋራ ስምምነት ላይ መደረሱን ተከትሎ፣ ኩባንያው  ወደ ውጭ ሃገራት ዜጎችን የሚልኩ ህጋዊ ኤጀንሲዎች ፍቃድ ለማውጣትና ተዛማጅ ክፍያዎችን በቴሌብር አማካኝነት ለመፈጸም የሚያስችላቸው አሰራር  ተግባራዊ ማድረጉን አስታውሷል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም አክሎም፤ ወደ ውጭ ሃገራት ለሥራ የሚሄዱ ዜጎች በተዘጋጀላቸው የሮሚንግ አገልግሎት አማካኝነት በያዙት የሃገር ቤት ሲም ካርድ የቴሌኮም አገልግሎት እንዲያገኙ እንዲሁም በቴሌብር ሃዋላ አማካይነት ገንዘብ ወደ ሃገር ቤት ለሚልኩ የማበረታቻ ልዩ ጥቅሎች ዝግጅት ማጠናቀቁን ጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ኩባንያው፣ የሚኒስቴር መ/ቤቱን አሰራር ለማዘመን የሚያስችሉ ልዩ ልዩ የቴክኖሎጂና ዲጂታል ሶሉሽኖችን ለማቅረብ የሚያስችሉ በርካታ ሥራዎችን ማከናወኑን የጠቆመ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ የሚኒስቴር መ/ቤቱን የዳታ ሴንተር ማዕከላት የማዘመን፣ ቅርንጫፎችን ከማዕከልና እርስበርስ በፈጣን ኢንተርኔት የማስተሳሰር፣ እንዲሁም የጥሪ- የግንኙነት ማዕከል አገልግሎት ለማቋቋም የሚያስችሉ ሥራዎች እንደሚገኙበት አመልክቷል፡፡

በክልሉ ከ450 ሺ በላይ ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ይፈልጋል ፀደይ ባንክ በአማራ ክልል የተከሰተውን የረሃብ አደጋ ለመመከት፣ የ50 ሚ. ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፤ የገንዘብ ድጋፉን
የፀደይ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ መኮንን የለውምወሰን፤ ለአማራ መልሶ ማቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ፣ ባለፈው ቅዳሜ በባንኩ ዋና መ/ቤት በተከናወነ ሥነሥርዓት ላይ አስረክበዋል።
አቶ መኮንን ድጋፉን አስመልክተው እንደገለጹት፤ ባንኩ በአማራ ክልል የሰዎችብ ሞት ጭምር ያስከተለውን የድርቅና የረሃብ ችግር ለመቅረፍ የሚደረገውን ጥረት አቅም በፈቀደ መጠን ለማገዝ በማሰብ የገንዘብ ድጋፉ እንዲሰጥ ወስኗል።
የአመልድ ዳይሬክተር ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ በበኩላቸው፤ ፀደይ ባንክ በራሱ ተነሳሽነት ለተጎዱ ወገኖች ያደረገውን ድጋፍ በድርጅታቸውና በተረጅው ወገን ስም አመስግነዋል። በተገኘው ድጋፍ
አስቸኳይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች፣ ዕርዳታውን እንደሚያደርሱም ቃል ገብተዋል።
 አክለውም ዳይሬክተሩ፣ እንደ ፀደይ ባንክ ሁሉ፣ ሌሎች የዘርፉ ተዋንያንና ተቋማት
ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ያደርጉ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።
ዶ/ር አለማየሁ አያይዘውም፣ በአማራ ክልል በተለይ ከግንቦት ወር ወዲህ ከዝናብ መጥፋት ጋር ተያይዞ በተለይ በዋግኸምራና ሰሜን ጎንደር ዞኖች የሰዎችና የእንስሳት ሞት ያጋጠመበት አስከፊ ሁኔታ መከሰቱን ጠቅሰዋል።
ረሃቡ በሰዎች ላይ የጤና ችግር ከማስከተሉም በተጨማሪ 16 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸውን፣ ከፍተኛ የእንስሳት እልቂት ማጋጠሙን ተናግረዋል። በክልሉ በአሁኑ ወቅት ከ450 ሺ በላይ ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እንደሚፈልግም ጠቁመዋል፡፡

ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ ከኤሴቅ ዲኮርና ኢቨንት ኦርጋናይዘር ጋር ባለፈው አርብ አራት ኪሎ በሚገኘው ወወክማ አዳራሽ ፣ባዘጋጀው የሥራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የስፖርት ፌደሬሽኖች በተገኙበት፣ የጋራ ውይይትና ምክክር ተካሄደ፡፡ በዚህ ዝግጅት በ298 ት/ ቤቶች በ149
የት/ ቤት አዳራሾች የስፖርት ስልጠናዎች እንደሚጀመር የተገለጸ ሲሆን፤ ይህንንም ስራ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ አሰልጣኞችን በመመደብ፣ ስልጠናው በመስጠት፣ ውድድሮችን በማዘጋጀት እንዲሁም ኤሴቅ ዲኮር እና ኢቨንት ኦርጋናይዘር በትምህርት ቤት ያሉ አዳራሾችን ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ በማዘጋጀት በጋራ እንደሚያከናውኑት ተጠቁሟል፡፡


የውይይቱና ምክክሩ ዋነኛ አላማ ፣ ሁሉም የቴኳንዶ፣ የማርሻል አርት ባለሙያዎች በጋራ ሆነው እየተመካከሩ በመስራት ይህን የስፖርት ዘርፍ ለማጠናከርና ከፍተኛ ተሰጥቶት ማህበረሰቡ ዘንድ ተወዳጅ እንዲሆን ማስቻል ነው። ኤሴቅ ዲኮር እና ኢቨንት ኦርጋናይዘር “ ትምህርት ለትውልድ“ በሚል መርህ፣ ከሃምሌ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወጣቶችን ከተለያዩ ሱሶችና ከአልባሌ ቦታ ለመጠበቅ አቅዶ በመነሳት፣ ከት/ሚር ስምምነት በመፈጸም ወደ ስራ የገባ መንግስታዊ ያልሆነ የግል ድርጅት ነው ተብሏል።በመዲናዋ በሚገኙ 298 ት/ ቤቶች
የስፖርት ስልጠናዎች ሊጀመር ነው ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ ከኤሴቅ ዲኮርና ኢቨንት ኦርጋናይዘር ጋር በዛሬው ዕለት አራት ኪሎ በሚገኘው ወወክማ አዳራሽ ፣ባዘጋጀው የሥራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የስፖርት ፌደሬሽኖች በተገኙበት፣ የጋራ ውይይትና ምክክር ተካሄደ፡፡ በዚህ ዝግጅት በ298 ት/ ቤቶች በ149 የት/ ቤት አዳራሾች የስፖርት ስልጠናዎች እንደሚጀመር የተገለጸ ሲሆን ይህንንም ስራ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ አሰልጣኞችን በመመደብ፣ ስልጠናው በመስጠት፣ ውድድሮችን በማዘጋጀት እንዲሁም ኤሴቅ ዲኮር እና ኢቨንት ጋናይዘር በትምህርት ቤት ያሉ አዳራሾችን ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ በማዘጋጀት በጋራ እንደሚያከናውኑት ተጠቁሟል፡፡ የውይይቱና ምክክሩ ዋነኛ አላማ ፣ ሁሉም የቴኳንዶ፣ የማርሻል አርት ባለሙያዎች በጋራ ሆነው እየተመካከሩ በመስራት ይህን የስፖርት ዘርፍ ለማጠናከርና ከፍተኛ ተሰጥቶት በማህበረሰቡ ዘንድ ተወዳጅ እንዲሆን ማስቻል ነው። ኤሴቅ ዲኮር እና ኢቨንት ኦርጋናይዘር “ ትምህርት ለትውልድ“ በሚል መርህ፣ ከሃምሌ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወጣቶችን ከተለያዩ ሱሶችና ከአልባሌ ቦታ ለመጠበቅ አቅዶ በመነሳት፣ ከት/ሚር ስምምነት በመፈጸም ወደ ስራ የገባ መንግስታዊ ያልሆነ የግል ድርጅት ነው
ተብሏል።