Administrator

Administrator

Monday, 18 August 2025 17:10

"ፉካ"

የደራሲ ዘቢብ መልኬ "ፉካ" የተሰኘ  አዲስ መጽሐፍ የፊታችን ረቡዕ ነሐሴ 14 2017 ዓ.ም አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት አዳራሽ ውስጥ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይመረቃል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ማሻሻያን ተከትሎ፣ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎችን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስጠንቅቋል።
ሚኒስቴሩ እንዳለው፣ የመስከረም 2018 የደመወዝ ጭማሪው የሠራተኞችን ኑሮ ለማሻሻል ያለመ አዎንታዊ እርምጃ ነው። ነገር ግን፣ አንዳንድ ነጋዴዎች ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመው ዋጋ በማናርና ሰው ሰራሽ የምርት እጥረት በመፍጠር ተስተውለዋል።
በመሆኑም ሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ፣ የዋጋ ጭማሪ፣ ምርት መደበቅና አላግባብ ማከማቸት የሚፈጽሙ ነጋዴዎች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
በተጨማሪም የንግድ መዋቅሩ ከፀጥታና ከፍትህ አካላት ጋር በመተባበር የገበያ ማረጋጋት ሥራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥልና በአጥፊዎች ላይም እርምጃ እንዲወሰድ መመሪያ አስተላልፏል።
ፍልስጤማዊቷ የቁንጅና ንግሥት ናዲን አዩብ ሀገሯ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳታፊ በምትሆንበት የወይዘሪት ዩኒቭርስ (Miss Univers) የቁንጅና ውድድር እንደምትሳተፍ ተሰምቷል።
የ27 ዓመቷ ወጣት ናዲን አዩብ ሀገሯን ወክላ ታይላንድ በሚደረገው የዓለም ወይዛዝርት ውድደር ላይ ተሳታፊ እንደምትሆን የፍልስጤም ባለሥልጣናት ናቸው የተናገሩት።
ሥነ-ጽሑፍ እና ሥነ-ልቦናን ያጠናችው ናዲን አዩብ፤ በ2022 የወይዘሪት ፍልስጤምን የቁንጅና ዘውድ መድፋቷ ይታወቃል።
በፍልስጤማዊያን ዘንድ ተስፋ የተጣለባት ናዲን፤ በኅዳር ወር 2025 በታይላንድ ፓክ ከሬት ከተማ ከዓለም ዙሪያ ከተወጣጡ ቆነጃጅት ጋር እንደምትወዳደር ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያ በዓለማቀፍ ለጋስነት በ22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች
በ2024 የዓለም አቀፍ ልግስና ሪፖርት መሠረት፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ለጋስነት 22ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ፣ የአፍሪካ አህጉር ደግሞ በዓለም ቀዳሚዋ ለጋስ አህጉር ሆና ተመዝግባለች።
የቻሪቲስ ኤድ ፋውንዴሽን (CAF) ባወጣው ሪፖርት፤ ኢትዮጵያውያን በ2024 ዓ.ም. በአማካይ 1.51 በመቶ ገቢያቸውን ለበጎ አድራጎት፣ ለቀጥታ እርዳታና ለሃይማኖታዊ ልግስና ማዋላቸውን ጠቁሟል።
ሪፖርቱ አፍሪካውያን ከሌሎች አህጉራት ጋር ሲነጻጸር በከፍተኛ ሁኔታ ከገቢያቸው የበለጠውን ክፍል ለልግስና እንደሚያውሉ ገልጿል።
አፍሪካውያን ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በአማካይ 1.54 በመቶ ገቢያቸውን የለገሱ ሲሆን፣ ይህም በአውሮፓ ከተመዘገበው የልግስና መጠን አማካይ 0.64 በመቶ በእጥፍ ይበልጣል።
ጥናቱ እንደሚያመለክተው፣ የአንድ ሀገር ሀብት እየጨመረ ሲሄድ የልግስና ደረጃው የመቀነስ አዝማሚያ ያሳያል። ከፍተኛ ገቢ ያላቸው አገሮች በአማካይ ከገቢያቸው 0.7 በመቶ ብቻ ሲለግሱ፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ አፍሪካውያን አገሮች ግን ከፍተኛ የልግስና መጠን አስመዝግበዋል ብሏል።
(CapitalNews)
• በአስተዳደሩ ስር የሚገኙ መ/ቤቶች በጀታቸውን
በቁጠባ እንዲጠቀሙ ተነግሯቸዋል
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኝ የትኛውም መስሪያ ቤት ለስብሰባ፣ ለግምገማና ለስልጠና የሆቴል አዳራሾች መከራየት የሚከለክል ትዕዛዝ የፋይናንስ ቢሮ ማስተላለፉ ተገለጸ፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን፤ አስገዳጅ ካልሆነ በቀር ሁሉም የከተማ አስተዳደር ቢሮዎችና ከፍለ ከተሞች ለሆቴል ኪራይ መክፈል እንደማይችሉ ለሸገር ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ ፋይናንስ ቢሮ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው፤ በ2018 በጀት ዓመት ሁሉም ክፍለ ከተሞች ስራቸውን ለመገምገምም ሆነ ለስልጠና ከበጀታቸው ላይ ለሆቴሎች ኪራይ መክፈል አይችሉም፡፡
መስሪያ ቤቶቹ ልዩ ልዩ ስብሰባዎችን፣ ስልጠና እና ግምገማዎችን ለማድረግ በየክፍለ ከተሞቻቸው የሚገኙ የመንግስት የመሰብሰቢያ አዳራሾችንና ካፍቴሪያዎችን እንዲጠቀሙ ደብዳቤው ያዛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2018 በጀት ዓመት እቅድ መከወኛ 350.1 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙን ያስታወሰው ቢሮው፤ 70 በመቶ የሚሆነው ለካፒታል በጀት የተደለደለ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ መስሪያ ቤቶች የተመደበላቸውን በጀት በቁጠባ እንዲጠቀሙም አሳስቧል፡፡
(ሸገር ኤፍኤም)
ዋልያ መፅሕፍት የተለያየ ይዘት ያላቸውን በጥሩ የህትመትና የወረቀት ጥራት ፣ የሀሳብ ጥልቀት የሞላቸውን መፅሐፍት ለማቅረብ እየታተረ ይገኛል።
የሚሳም ተራራ፣ ማእበል ጠሪ ወፍ ፣ ዝይን ፣ቆንጆዎቹ ፣ ግርባብ ፣ ሲጥል፣ በታችም በምድር እና ሌሎች የተወዳጅ ደራስያን ተወዳጅ መፅሐፍትን ሲያቀርብላችሁ በደስታ ነው ።
እኒህን መፅሐፍት በየትኛውም የመፅሕፍት መደብር ጎራ ብትሉ ተዘርግተው እናንተን ይጠብቋችኋል።
ዋልያ መፅሀፍት
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
• ጎረቤቶቿ በሙሉ የእረብ ሊግ አባል ናቸው
ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ አባል ብትሆን መድረኩን ተጠቅመው ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅምና ህልውና በተቃራኒ የሚሰሩ አካላትን ለመሞገትና ሴራዎችንም ለማክሸፍ ይጠቅማታል ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል፡፡
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሚመለከት ለኢፕድ በሰጡት ማብራሪያ፤ ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ አባል ብትሆን ያለንን መልከአምድራዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት በማጠናከር ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል፤ ብለዋል።
ግብጽ በተደጋጋሚ የታላቁ ህዳሴ ግድብን በተሳሳተ መንገድ ለአረብ ሊግ አባላት በማቅረብ የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲያዝ ስታደርግ የቆየችውም ኢትዮጵያ አባል ሀገር ባለመሆኗ መሆኑን ጠቅሰው፣ አባል ብትሆን በወቅቱ ትክክለኛ መረጃ ለመስጠት እንደሚያስችላትም ጠቁመዋል።
ጎረቤት ሀገራት በሙሉ ሱዳን፣ ሱማሊና ጅቡቲ የአረብ ሊግ አባል መሆናቸውንና ኤርትራም ታዛቢ መሆኗንም አምባሳደር ዲና ገልጸዋል።
የአረብ ሊግ አባል ሀገራት ከፍተኛ ሀብትም እንዳላቸው ገልጸው፤ ከነሱ ጋር ንግድን ለማጠናከርና በአጠቃላይ በመድረኩ ስለኢትዮጵያ በጎ ድምጽ እንዲኖር ለማድረግ እንደሚቻል አመላክተዋል።
ኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄዋ እንዲሳካ አባል ሀገራትን ማሳመንና የብሪክስ አባል ለመሆን የተደረገውን ጥረት በዚህም መድገም እንደሚገባ አምባሳደሩ መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
ዋልያ መፅሕፍት የተለያየ ይዘት ያላቸውን በጥሩ የህትመትና የወረቀት ጥራት ፣ የሀሳብ ጥልቀት የሞላቸውን መፅሐፍት ለማቅረብ እየታተረ ይገኛል።
የሚሳም ተራራ፣ ማእበል ጠሪ ወፍ ፣ ዝይን ፣ቆንጆዎቹ ፣ ግርባብ ፣ ሲጥል፣ በታችም በምድር እና ሌሎች የተወዳጅ ደራስያን ተወዳጅ መፅሐፍትን ሲያቀርብላችሁ በደስታ ነው ።
እኒህን መፅሐፍት በየትኛውም የመፅሕፍት መደብር ጎራ ብትሉ ተዘርግተው እናንተን ይጠብቋችኋል።
ዋልያ መፅሀፍት
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
May be an image of 1 person and text
 
 
 
 
Monday, 18 August 2025 16:21

ቡሄ - ነገ!!

ቡሄ - ነገ!!
የቡሄ በዓል መከበር የጀመረው ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን በደብረ ታቦር ተራራ ከመገለጡ ጋር ተያይዞ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ከዚህ ክስተት ጀምሮ ሙልሙል መስጠት፣ ችቦ ማብራትና ጅራፍ ማጮኽ የበዓሉ ትውፊታዊ መገለጫዎች ሆነው ዛሬን ደርሰዋል፡፡
ቡሄና የሙልሙል ስጦታ
በቡሄ በዓል አከባበር ትውፊቱ መሰረት፤ ብርሃን በደብረ ታቦር ተራራ በተገለጠ ጊዜ በአካባቢው የነበሩ እረኞች የመሸ ስላልመሰላቸው ወደ ቤታቸው አልተመለሱም ነበር፡፡ በዚህ የተጨነቁ ወላጆችም ልጆቻቸው/እረኞች የሚበሉትን ቂጣ/ዳቦ በመያዝ ወዳሉበት ቦታ ይሄዳሉ፡፡ በቦታውም ዳቦውን ለልጆቻቸው ይሰጣሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ቡሄ፤ ልጆች በየቤቱ እየዞሩ እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ ዳቦ/ሙልሙል የመስጠት ባህል ሆኖ መቀጠል ችሏል፡፡
ቡሄና ችቦ ማብራት
በቡሄ በዓል ችቦ የሚበራው በደብረ ታቦር ተራራ ብርሃን መገለጡን በማስመልከት ነው፡፡ ብርሃን የማብራት ትውፊቱ ከክረምትና የጨለማ ዘመን ወደ ብርሃንነት፣ ከጭጋግ ወደ ፀሐይና ብሩህነት የምንሸጋገርበት ወቅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፡፡
ቡሄና ጅራፍ ማጮህ
የቡሄ ሌላው ገጽታ የጅራፍ ግርፊያው ነው፡፡ ከበዓሉ ቀን በፊት ጅራፍ በማዘጋጀትና ወደ ተራራማ አካባቢዎች በማምራት ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ትውፊታዊ ትርጓሜ አለው፡፡ የመጀመሪው የኢየሱስ ክርስቶስን በጅራፍ መገረፍ የሚያመሰጥር ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጅራፉ ሲጮኽ የሚያሰማው ድምጽ የባህርይ አባቱ አብ የሰጠው ምስክርነት እንደነጎድጓድ መሰማቱን ያስረዳል፡፡
ቡሄ በአማራ ክልል
ቡሄ በአማራ ክልል እንደየአካባቢው ሁኔታ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር በዓል ቢሆንም፣ ከላይ የጠቀስናቸውን ዳቦ፣ ችቦ እና ጅራፍ ማጮኽ ዋና መገለጫዎቹ ናቸው፡፡ ቡሄ ለየት ብሎ ከሚከበርባቸው አካባቢዎች ውስጥ ደብረ ታቦር ከተማ ቀዳሚ ብትሆንም በሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደርና ጎጃም ውስጥ በሚገኙ ሁሉም አካባቢዎችም የቡሄ በዓል በድምቀት ይከበራል፡፡
(Visit Amhara)
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
የመንግስት ሠራተኛው ያለውን የኑሮ ውድነት ተቋቁሞ ለመላው የንግዱ ማህበረሰብ ተገቢውን አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡
የንግዱ ማህበረሰብ መንግስት ለሚወስዳቸው የሪፎርም እርምጃዎች አጋዥ እየሆነ መጥተዋል።
ይሄው ተግባር አሁንም ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። ይሁንና እንዳንድ የንግዱ ህብረተሰብ አካላት ከእዚህ ቀደም በተለምዶ የደመወዝ ጭማሪ ተደረገ በሚል በሸቀጦች ዋጋ ላይ እንደሚጨምሩ ይታወቃል፡፡
 
በሰሞኑ በሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ አስታኮ እና ለኑሮ ውድነቱ መቋቋሚያ ተብሎ በተደረገው የደመወዝ ማሻሻያ ዜና በመስማት ህገወጥና ምንም ምክንያት በሌለው መንገድ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉት ላይ መንግስት ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ ይሆናል፡፡
ህገወጥ የዋጋ ጭማሪ አድርገው በሚገኙት ላይ ደግሞ መንግሥት አስተማሪ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን በቅድሚያ ያሳውቃል፡፡
በመጨረሻም ሕዝባችንን በንጽሕናና በትጋት በማገልገል፤ ከሚገባንና ከሚጠበቅብን በላይ በመሥራት፤ ሙስናና ብልሹ አሠራርን በመታገል፤ ከዕቅዶቻችን በላይ በማከናወን፤ የኢትዮጵያን ብልጽግና እንደምናረጋግጥ መንግሥት ጽኑ እምነት አለው፡፡
 
የብልጽግና ጉዟችን በቀጠለ መጠን፣ በየምዕራፉ ሁላችንም የብልጽግናን ትሩፋት መቋደሳችን አይቀሬ ነው፡፡
ለዚያ ደግሞ ሁላችንም ወገባችንን አጥብቀንና ታጥቀን መትጋት አለብን፡፡ ይህ ሲሳካ ነጻነታችንን በደማቸው እንዳጎናጸፉን ቀደምት አባቶቻችን እና እናቶቻችን ሁሉ፣ እኛም ሀገራቸውን ለማበልጸግ ዋጋ የከፈሉ ትውልዶች ተብለን ታሪክ ሲዘክረን ይኖራል።