Administrator
አንጋፋው ሠዓሊ ጥበበ ተርፋ አረፉ !
ጥበበ ተርፋ ማመጫ፤ በሐረር ከተማ በ1941 ዓ.ም ተወለዱ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሐረር መድኃኒዓለም ት/ቤት እንዳጠናቀቁ ወደ አዲስ አበባ ሥነ ጥበብ ት/ቤት (በአሁኑ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ አለ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት) በመግባት ተመርቀዋል።
በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሥነጥበብ ልምምድ ውስጥ ተዋጽዖአቸው ከፍ ያለ ሥፍራ የሚሰጠው ነበረ:: የሥዕል ሥራቸውን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ለዕይታ ያበቁ ሲሆን፣ በሙያው ስምና ዝና ያፈሩ አንጋፋ ሙያተኛ ነበሩ::
አቶ ጥበበ ተርፋ የሥራቸው አቅጣጫ ተወልደው ባደጉበት ሐረር ላይ በማተኮር የትላንቱንና የዛሬውን ገጿን በቀለማት እንቅስቃሴ ይገልጹ ነበረ። አቶ ታዬ ታደሰ ባዘጋጁት የሠዓልያን ታሪክ ውስጥ ጥበበ "የተለያዩ ቴክኒኮችን የሚጠቀሙ ሲሆኑ፤ የሚያደንቁት ግን ኤክስፕሬሽኒዝምን ነው" በማለት መጻፋቸው ይታወሳል::
ሠዓሊ ጥበበ ተርፋ ማመጫ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ህይወታቸው ማለፉን ሰምተናል:: ለመላው ቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለአለ_የሥነጥበብ_ት/ቤት ማህበረሰብ፣ ለሙያ ጓዶቻቸውና አድናቂዎቻቸው መጽናናት እንዲሆንላቸው እንመኛለን።
ቀብራቸው ነገ ረቡዕ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም. በየካ ሚካኤል ቤተክርስትያን ከቀኑ 8:30 የሚፈጸም ይሆናል። ነፍስ ይማር።
(አገኘሁ_አዳነ_ድልነሣሁ)
በ45ኛው ዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የሁለተኛነት ደረጃ በመያዝ ጨርሳለች፡፡
በሰርቢያ ቤልግሬድ በተካሄደው የ45ኛው ዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአምስት ምድቦች ማለትም 8ኪ.ሜ. ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ፣ 6 ኪ.ሜ. ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ፣ 4x2 ኪ.ሜ የድብልቅ ሪሌ ሴት/ወንድ ፣ የ10 ኪ.ሜ. የአዋቂ ሴቶች እና አዋቂ ወንዶች በተካተቱበት ውድድር ከ51 አገራት የመጡ 485 የሚሆኑ አትሌቶች ተፎካክረውበታል። በዚህም ውድድር ኢትዮጵያ በ14 ሴት እና በ14 ወንድ በ28 አትሌቶች የተወከለች ሲሆን በ ሁለት ወርቅ ፣በስድስት ብር እና በሁለት ነሃስ በአጠቃላይ በ10 ሜዳሊያ ከአለም የሁለተኛነት ደረጃ በመያዝ ውድድሩርን ጨርሳለች ፡፡
ግሪን ዌቭ አሊያንስ ከኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ጋር በትብብር ለመሥራት ስምምነት ፈጸመ
ግሪን ዌቭ አሊያንስ ከኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ጋር በአረንጓዴ ልማት ዙሪያ ለመሥራት የሚያስችለውን ስምምነት በዛሬው ዕለት ረፋዱ ላይ ፈጸመ፡፡
ስምምነቱን የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ም/ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያና የግሪን ዌቭ አሊያንስ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ረድኤት ያዘው በባለሥልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ተፈራርመዋል፡፡
የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ በፊርማ ሥነስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በጠ/ሚኒስትሩ ሃሳብ አመንጪነት የተጀመረውን አረንጓዴ ልማት ለማስቀጠል መንግሥታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት አጋርነት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፤ በዚህ ረገድ የዛሬው ስምምነት ፋይዳው የላቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ባለሥልጣን መ/ቤቱ ከመጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የአየር፣ የውሀ፣ የአፈርና የድምጽ ብክለትን ለመቀነስ የሚያስችል የ6 ወራት ዘመቻ መጀመሩን የገለጹት ወ/ሮ ፍሬነሽ፤ በአጋርነት መሥራት ዘመቻውን ውጤታማ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
የግሪን ዌቭ አሊያንስ መሥራችና የቦርድ ሰብሳቢ አርቲስት ሚኪያስ ነጋሳ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር፤ የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የሚያከናውናቸው ሥራዎች ሰፊ ከመሆናቸው አንጻር መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት አጋርነት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዛሬ የተከናወነው ስምምነት የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴውን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚረዳ ነው ብለዋል፡፡
የዓባይ ግድብ ግንባታ መታሰቢያ ቴምብር ይፋ ሆነ
የደራሲ አበራ ለማ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
የደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ "የዓለማችን ምስጢራት" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ከሰሞኑ ለአንባቢያን ቀርቧል።
ይህ አዲስ መጽሐፍ የፊታችን መጋቢት 28 2016 ዓ.ም በወመዘክር አዳራሽም ይመረቃል ተብሏል።
"ግጥም ሲጥም" የኪነጥበብ መሰናዶ ነገ ይካሄዳል!
"ግጥም ሲጥም "ለሁሉም ክፍት የሆነ የኪነጥበብ መድረክ ተመልሷል። በዚህም ሳምንትም የቦታ ለወጥ አድርጎ ነገ ረቡዕ መጋቢት 25 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ገርጂ በሚገኘው ደስክ አዲስ ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።
"እንዲህ ያለም የለ"መጽሐፍ ረቡዕ ይመረቃል
"እንዲህ ያለም የለ"መጽሐፍ ረቡዕ ይመረቃል
የገጣሚ ሀብታሙ ሀደራ "እንዲህ ያለም የለ" የተሰኘ የግጥም ስብስብ መጽሐፍ የፊታችን ረቡዕ መጋቢት 25 2016 ዓ.ም ከ10:30 ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ ይመረቃል።
”የኢትዮጵያ ሙዚቃ ቀን” በእስራኤል ሊካሄድ ነው
- • ጎሳዬ ተስፋዬ፣ ሳሚ ዳንና ጃኪ ጎሲ ይሳተፉበታል
ታዋቂ የኢትዮጵያ ድምፃዊያን የሚሳተፉበት “የኢትዮጵያ ሙዚቃ ቀን” በእስራኤል ቴላቪቭ እንደሚካሄድ አፍሮ ስታይል ኢንተርቴይመንት አስታወቀ፡፡
የእስራኤል የነፃነት ቀንን ምክንያት በማድረግ፣ ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ፣ም የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቀን በቴላቪቭ የሚካሄድ ሲሆን፤ አፍሮ ስታይል ኢንተርቴይመንት ባዘጋጀው በዚህ ኮንሰርት ላይ ጎሳዬ ተስፋዬ፤ ሳሚ ዳንና ጃኪ ጎሲ እንደሚጫወቱ ተገልጿል። ታዋቂ የጃማይካ ዳንስሆል አርቲስትም በኮንሰርቱ ላይ እንደሚሳተፍ ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቀንን ለማክበር የተሰናዳው መርሐግብር ከሚያዚያ 29 እስከ ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን፤ በተለያዩ የሙዚቃ ዝግጅቶችና በእስራኤል ከተሞች በሚካሄዱ ጉብኝቶች የሚታጀብ ይሆናል ተብሏል።
ከሚያዚያ 29 እስከ ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ.ም በእየሩሳሌም ከተማ ጉብኝቶች የተዘጋጁ ሲሆን፤ ግንቦት 5 በሃንገር 09 አዳራሽ ቴላቪቭ ላይ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ቀን ልዩ ኮንሰርት እንደሚካሄድ ተጠቁሟል፡፡ በተመሳሳይ ቀን የቴላቪቭ ከተማን ለማስጎብኘትም ታቅዷል። ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም በሚር ያቆብ አዘጋጅነት በቴላቪቭ ሐንገር 09 አዳራሽ፣ የሬጌ ሙዚቃ ዝግጅትና ዳንስ እንደሚቀርብም ታውቋል።
"ልጄስ"ተከታታይ ድራማ በቅርቡ ይጀምራል!
"ዕንቁ ሴት፣ ንቁ ሴት፣ ዝግጁ ሴት"
"ዕንቁ ሴት፣ ንቁ ሴት፣ ዝግጁ ሴት"
"ዕንቁ ሴት፣ ንቁ ሴት፣ ዝግጁ ሴት"የተሰኘ ቅዳሜ መጋቢት 21 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ሰንጋተራ በሚገኙ ፐርፐር ብላክ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
በዕለቱም ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ፣ አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ ፣ ሲሰተር ዘቢደር ዘውዴ ጭምሮ የተለያዩ እንግዶች ሀሳቦቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።