የግጥም ጥግ
ጥበብአትፅናኝሞትን አንመልሰው፣ እናውቃለን አይሸሽስንት ጥፍራም ኀዘን፣ አይተናል መሰለሽ፤ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማይቀር አምነንስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማይቀር አምነሽ፤ዳሩ ታውቂዋለሽ፡፡አቀጣጡ ክፋት፤አመጣጡ ምፃት፤ግን ከሄደው ሁሉ፣ ከተመላለሰውምን ይባላል ይኼ፤ ’ባንቺ የደረሰው?!ምን ይባላል ይኼ? አንቺስ ምን ልትባይ?እኩይ ነው እታለም፣ ሽንገላ እንደ ሥራይ፡፡በእድፋም ጥፍሩ፤ ቧጦሽ ጥፍራም ኀዘንመፅናናት…
Read 2374 times
Published in
የግጥም ጥግ
“ሰው ነህ የሚል ማተም” አዳም አባታችን አንደተፈጠረ ገነት ነውየኖረውገነት ለመኖሩ ምክንያት የሆነውከፍጥረታት ሁሉእጅግ “የከበረ” ሰው ስለሆነ ነው።እየሱስ በሞቱፍቅሩን የገለፀውኤጄቶ ላውራልህፋኖ ሆይ ልንገርህቄሮዬ ሆይ ስማኝሰዎች ለተባልነው ለኔና ላንተ ነው።የእስልምናም ትምሀርት ተግባራቱሲታይ ከነአበቃቀሉሰውን ያስቀድማል ከፍጥረታት ሁሉስለዚህ አዳምጠኝበየትም የሰፈርክ የትም የምትገኝአንተ ባለ መውዜር…
Read 2147 times
Published in
የግጥም ጥግ
የድል በርተፅፎ ባይታይምአቅጣጫ ሚጠቁም ጉልህ ማሳሰቢያለጀግና መውጪያው ነው የፈሪዎች መግቢያ***የላጤ ሐገርከአቅመ አዳም ልንገባ ደጁ ተሰልፈንሃያ አመት ከሞላን ሃያ አመት አለፈን***ለፓርቲዎቻችንከአምስት አመት እንቅልፍ ድንገት ስትነሱህዝቡ ቀድሞ ነቅቷል እንዳትቀሰቅሱ***ታራሚየኔና ያንቺ ነገር ግራ ነው ለዳኛአብረን መቆም ሳንችል አብረን የምንተኛ***ጊዜ የሰጠውጊዜን ጊዜ ሲወልድ ቀን…
Read 1929 times
Published in
የግጥም ጥግ
እኔ ተጎድቼ ነ.መትዝ ይልሻል ውዴ ሆዴ፣አንቺ የልቤ ሁዳዴ!ፆም እንያዝ ተባብለንእንዳቅማችን ተሟሙተንአንድ ሆቴል “በልተን ጠጥተን”“ቦዩን አልጋ አለ ወይ?” ብለንትዝ ይልሻል ምን እንዳለን?“ይቀልዳሉ እንዴ ጋሼ?እንኳን አልጋው ይቅርናጨለማው ተይዟልኮ!” አለን፡፡ዕውነትም ዙሪያውን ብናይ፤ጨለማው በመኪና ሞልቶመኪናው በጥንዶች ትንፋሽ፣ የፍቅር ምጥ ሳግአግቶዕውር ጨለማ በዕውር ሰው፣ ፆም…
Read 2436 times
Published in
የግጥም ጥግ
ሞልትዋል ብላቴናደመረ ብርሃኑ(በአዲስ አድማስ 15ኛ ዓመት የግጥምውድድር 2ኛ የወጣው ግጥም)ነበር ፍጹም ጨቅላ በጥቁር አፈር ላይ በጥቁርተፀንሶጥቁር የወለደው ጥቁር ስጋ አልብሶ፣ነበር ብላቴናከጥቁር ገላ ውስጥ ነጭ ወተት ግቶአጥንቱ የጸና የቆመ በርትቶ፣ ነበር ደቀ መዝሙርጥቁር ብላቴናበነጭ ጠመኔ በጥቁር ሰሌዳሀ ሲሉት ሃ ብሎ A…
Read 2160 times
Published in
የግጥም ጥግ
ፍለጋደስታን ስፈልግ ነውደስታዬ የራቀኝፍቅርን ስሻ ነውፍቅር የጠፋብኝሰላምን ሳስስ ነውሰላሜን ያጣሁትፍላጐቴን ስገድልሁሉን አገኘሁት፡፡(2011፤ዳዊት ፀጋዬ)_________ ሀይል“ክፉና መልካምከልዑል አፍ ይወጣል”ተብሎ ተጽፏልእናምበዚህች አጽናፍ ዓለምሁለት ሀይል የለምብቸኛው ሀይልእግዚአብሔር ነው እርሱሰይጣን የሚሆነውምእግዚአብሔር ራሱ፡፡(2011፤ዳዊት ፀጋዬ)
Read 2053 times
Published in
የግጥም ጥግ