ርዕሰ አንቀፅ

Rate this item
(27 votes)
ከዝነኛው ኤዞፕ ተረቶች አንዱ እንዲህ ይላል፡- ከዕለታት አንድ ቀን ተኩላዎች ወደ ውሾች መንደር መጡ ይባላል፡፡ “እንደምናችሁ ውሾች?”ውሾችም፤ “እኛ ደህና ከርመናል፡፡ እናንተስ ተኩላዎች እንዴት ሰነበታችሁ?” አሉ፡፡ ተኩላዎችም፤ “እናንተ ውሾች በጣም ታሳዝኑናላችሁ” “ለምን?” “እስከዛሬ እኛና እናንተ ጠላት መሆናችን እጅግ ያሳዝናል፡፡ አለመተሳሰባችንና አለመነጋገራችን…
Rate this item
(18 votes)
አንዳንድ ተረት ካልተደጋገመ የሚሰማ የለም፡፡ ይሄንንም በድጋሚ አቅርበነዋል፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ትልቅ ዝሆን አንድ ትልቅ ገደል ውስጥ ወድቆ ይሞታል፡፡ ሌሊቱን የተራቡ ጅቦች ወደ ገደሉ አፋፍ መጥተው፣ ዞር ዞር ሲሉ ዝሆን እጅግ አዘቅት በሆነው ገደል ውስጥ ገብቶ መሞቱን አዩ፡፡ ከፊሎቹ…
Rate this item
(20 votes)
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ከዳር አገር ወደ ዋናው ከተማ የመጡ አዛውንት ለንጉሱ አቤቱታቸውን ለማቅረብ ከዙፋን ችሎቱ ዘንድ ተቀምጠው ተራቸውን ይጠብቃሉ፡፡ ባለሟሎች ስነ-ስርዓት እያስከበሩ ሁሉን በወግ በወግ ያስተናግዳሉ፡፡ አንዱ ሲጨርስ ሌላው ግባ ይባላል፡፡ በዚሁ ደንብ እኒያ የዳር-አገር መኳንንት ተራቸው ይደርስና ይቀርባሉ፡፡…
Rate this item
(13 votes)
ከዕለታት አንድ ቀን መልኩ ወደ ቁራ የሚሄድ አንድ ጥቁርና ነጭ ዥጉርጉር ወፍ በአንድ ጫካ ውስጥ ይኖር ነበረ፡፡ በእርሻ ማሳው ውስጥ የሚያማምሩ ነጫጭ እርግቦች እየተመገቡ፣ ብር ትር እያሉ ሲጫወቱ አየ፡፡ ከወፋፍርነታቸው መልካም ተመግበው እንደኖሩ ያስታውቃሉ፡፡ የገላቸውና የላባቸው ንጣት ዐይን ይስባል፡፡ ያ…
Rate this item
(22 votes)
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ሐኪም በሽተኛውን ሊጠይቅ ወደ በሽተኛው ክፍል ይሄዳል፡፡ ሐኪም፡ “እንደምናደርክ ወዳጄ?”በሽተኛ፡“ደህና ዶክተር፤ አንተስ ደህና አደርክ?”ሐኪም፤ “እኔ ደህና አድሬአለሁ፡፡ ለመሆኑ ህመምህ እንዴት ነው?”“በጣም ያልበኛል እንጂ ደህና ነኝ”ሐኪም፤ “ይሄ ጥሩ የመዳን ምልክት ነው፤ አይዞህ” አለውና ሄደ፡፡ በሶስተኛው ቀን ሐኪሙ…
Rate this item
(20 votes)
አንድ አርሶ አደር በአጥር ግቢው ውስጥ አንድ የፍሬ ዛፍ ነበረው፡፡ ሆኖም ይሄ ዛፍ ፍሬ አላፈራም፡፡ ስለዚህም አርሶ አደሩ፣“አንተ ዛፍ፤ስንት ዓመት ሙሉ ደጃፌ ቆመህ አንዲት ፍሬ እንኳን ሰጥተኸኝ አታውቅም፡፡ አሁን መቆረጫህ ሰዓት ደርሷል - ተዘጋጅ!” አለው፡፡በዛፉ ላይ በየቅርንጫፉ ውስጥ የሚኖሩና በጥላው…