ርዕሰ አንቀፅ

Rate this item
(8 votes)
ከዕለታት አንድ ቀን ሁለት ወንድማማች ዝንጀሮዎች በአንዲት ዝንጀሮ ወዳጃቸው ይጣላሉ፡፡ አንደኛው ለሁለተኛው፤ “እንግዲህ እዚች ሚስቴ ዝንጀሮዬ ጋ ድርሽ እንዳትል” ይለዋል፡፡ ሁለተኛው፤ “አይ ወዳጄ እኔ ልልህ ያሰብኩትን ነው አንተ አሁን ያልከው፡፡ የሀሳብ መመሳሰል ያስገርማል፡፡ ዞሮ ዞሮ እዚች ሚስቴ ጋ ድርሽ ካልክ…
Rate this item
(10 votes)
ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት የውሃ ኤሊ የመውለጃዋ ጊዜ ደርሶ ኖሮ ከውሃው ወጥታ ወደ ባህሩ ዳርቻ ትሄዳለች፡፡ይቺ ኤሊ ቀስ እያለች በረጅሙ የአሸዋ መንገዷ ስታዘግም ሁለት ጓደኛሞች ያዩዋታል፡፡ አንደኛው ፤ “ይቺ ዔሊ ወዴት ነው የምትሄደው?” ይላል፡፡ ሁለተኛው፤ “የመውለጃ ጊዜዋ ደርሶ ይሆናል” አንደኛው፤…
Rate this item
(13 votes)
አንድ ንጉሥ የመሞቻቸው ሰዓት ሲደርስ ሁለት ወንዶች ልጆቻቸውንና አንዲት ሴት ልጃቸውን ጠርተው፤ “ልጆቼ፤ እንግዲህ ዕድሜዬ እየገፋ፣ ጉልበቴ እየላመ፣ አቅሜም እየደከመ የመጣበት ሰዓት ነውና ከመንግሥቴ የት የቱን መውረስ እንደምትመርጡ ሀሳብ እንድትሰጡኝ እፈልጋለሁ” አሉ፡፡ ታላቅ ወንድም ምንም ሀሳብ ሳይሰጥ ዝም አለ፡፡ ሁለተኛው…
Rate this item
(14 votes)
ከእለታት አንድ ቀን አንዲት ቀበጥ ልጅ ከእናቷና ከሴት አያቷ ጋር አብራ ትኖር ነበር፡፡ ከቀበጥነቷም በላይ የሥራ ዳተኝነቷ አስቸጋሪ ነበር፡፡እናትና አያት ይወያያሉ፡-አያት - እንደው የዚችን ልጅ ነገር ምን ብናደርግ ይሻላል?እናት - እረ እኔም ከዛሬ ነገ እጠይቅሻለሁ እያልኩ ስፈራ ስቸርኮ ነው የቆየሁት፡፡…
Rate this item
(5 votes)
ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት እጅግ በጣም ክፉ ሚስት የነበረችው ገበሬ ነበረ፣ ይባላል፡፡ ይህች ሚስቱ ማታ ከእርሻ ተመልሶ፣ ሞተር ቀንበሩን ሰቅሎ ገና እፎይ ሳይል እንዲህ ትለዋለች - “መጣህ፤ በል ምግቡን አሙቀው”“እሺ የእኔ እመቤት” ብሎ ፍቅሩን ጭምር ገልፆላት፣ወጡን ምድጃ ላይ ይጥዳል፡፡ “በል…
Rate this item
(6 votes)
በድሮ ጊዜ አንድ አንቱ የተባሉ አገረ ገዢ በየክፍለ ሀገሩ እየተዘዋወሩ ህዝቡን እየሰበሰቡ ያነጋግሩ ነበር ይባላል፡፡ አብረዋቸው አዋጅ ገላጮች ነበሩ፡፡ አዋጅ ገላጮቹ በታወጁ አዋጆች ላይ ጥያቄ ቢነሳ የሚያብራሩ የሚገልጡ ናቸው፡፡ ህዝብ ከተሰባሰበ በኋላ፣ ባለሟሉ ይነሳና “የአገራችን ህዝብ ሆይ! አገረ ገዢው እዚህ…