Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

ጥበብ

Saturday, 08 September 2012 10:48

ሞት የገደለው ማንን ነው?

Written by
Rate this item
(0 votes)
ጨረቃና ከዋክብትን፤ ሰማይና ምድርን፣ ሰውንና እንስሳውንም የማላይበት ጊዜ ይመጣል፡፡ የሚነፍሰውን ንፁህ አየርና የሚያማልል መስክ፤ ከአበባ ወደ አበባ የሚፈነጥዙትንም ቢራቢሮዎች ዳግመኛ አይቼ የማልደነቅበት ጊዜም ይመጣል፡፡ በዝንቦች የቀናት እድሜ ፌሽታ የምቀናበትም ወቅት… ያ ጊዜ ከሩቅ እንደሚሰማ አስፈሪ የዝናም ኮቴ ሲጮህ አይሰማኝም… ልጅ…
Rate this item
(4 votes)
የአማርኛን ስነ ጽሁፍ ካሳደጉት ታላላቅ ኢትዮጵያዊያን መካከል ባለቅኔው ዮፍታሄ ንጉሴ ይጠቀሳሉ፡፡ ዮፍታሄ ንጉሴ የተወለዱት በጎጃም ክፍለ ሀገር በደብረ ኤልያስ በ1885 ዓ.ም ሲሆን በደብረ ኤልያስ ደብር የጥንቱን የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ትምህርት በሚገባ ተምረዋል፡፡ ዮፍታሄ በልጅነታቸው የዜማ ትምህርት ያስተማሯቸው መሪጌታ አደላ ንጉሴ ሲሆኑ…
Saturday, 01 September 2012 11:47

የእናት ሞት!

Written by
Rate this item
(5 votes)
እናቴን እወዳታለሁ፡፡ ማን እናቱን የማይወድ አለ እንዳትሉኝና እንዳንጣላ፡፡ ስለሷ ሳስብ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ምቾት ይሰማኝ ነበር፤ ደስታ እና በራስ መተማመን፡፡ እሷን ሊቆጣና ሊሳደብ ይነሳ በነበረ ጊዜ ሁሉ ከአባቴ ጋር ተጣልቼያለሁ፡፡ ይህ ማለት ግን እሱን ለመቋቋም የሚያስችል አካላዊ ብቃት ነበረኝ…
Saturday, 01 September 2012 11:45

ንጉሥም እንደ ሰው!

Written by
Rate this item
(1 Vote)
ያው ሰው - ኖሮ ኖሮ ኑሮን ዞሮ - ዞሮ ደፈና ሕይወቱን ወይ ኢምንት ጉልበቱን በጊዜ እየኖረ - ጊዜውን ጠብቆ - በጊዜ እየሞተ ስንቱ በሞት ሰፈር - በዛ በረከተ ሞት ላይሞት ሰው ሞተ አፈረ - ባከነ - ባዘተ - ቃተተ፡፡
Saturday, 01 September 2012 11:41

ጀግና መቃብር የለውም

Written by
Rate this item
(0 votes)
አገር ከዳር ዳር ሲያለቅስ - ባንድ ቃል እንደመከረ ሃዘኑም እንደ ልማቱ - ህዝብን አስተባበረ፤ እንደ ድንገት ደራሽ ጐርፍ - ደግሞም እንደ ሃይል መራሽ እንዲህ ያል’ የመሪ ፍቅር - በታሪክ አልታየም ጭራሽ ህልም መሰል እውነታ - በቁሜ አየሁኝ ሣልተኛ
Saturday, 01 September 2012 11:38

ትዝታ ድክመቴ ነህ

Written by
Rate this item
(3 votes)
አንዳንድ ፀሎቶች አሉ፡፡ የሚደማሙ፣ ለራሳቸው ነፍስ ዘርተው ራሳቸውን የሚገሉ፣ ለጥ ያለ ሜዳ ላይ እንደልብ መራወጥና መድረስ እየቻሉ የተራራው ግዝፈት ላይ መሆናቸውን የሚወጥሩ፡፡ ፀሎቶቹ በሙሉ የሚፀልዩት ባልደረሱ እየተባሉ ነው፡፡ መመኘትን እየቀረፁ ዝም ብለው ስድነትን የሚኖሩ፡፡ የሚቀርቡ ሆነው ተፈጥረው የሚርቁ፡፡ የትም ሳይሄዱ…