Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 September 2011 10:32

የፍልስጤሞች ነፃ መንግሥት ይሳካ ይሆን?

Written by 
Rate this item
(2 votes)

ከአውሮፓ­ አገራት ድጋፍ እያገኙ ነው
ጥላሁን አክሊሉ
በሚቀጥለው ሳምንት የዓለም አቀፉን ማህበረሰብና የተለያዩ ሚዲያዎችን ትኩረት የሚስብ ስብሰባ በኒውዮርክ
የተባበሩት መንግሥታት /ቤት ውስጥ ይካሄዳል፡፡ የስብሰባው ዓላማም     ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ፣ ያለ
መንግሥት የኖረችውን የፍልስጤም ነፃ መንግስት ለመመስረት የሚካሄድ ስብሰባ ነው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት አባል አገራት 192 ሲሆኑ፣ ፍልስጤማዊያን የራሳቸውን መንግስት ለመመስረት የ128 አባል አገሮች ወይም 2/3ኛ ድም ማግኘት አለባቸው፡፡

የፍልስጤሙ ፕሬዝዳንት መሀመድ አባስ፤ የተባበሩት መንግሥታት አባል አገራት ለፍልስጤማዊያን ድምፃቸውን እንዲሰጡ ከፍተኛ ቅስቀሳ እና ማግባባትእያካሄዱ ይገኛሉ፡፡ ከአንድ ወር በፊት ከኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከጆናስ ጋሃር ስትዮር ጋር በኦስሎ ባደረጉት ውይይት፤ የፍልስጤም ነፃ መንግሥት መመስረትን ኖርዌይ ሙሉ በሙሉ እንደምትደግፍ አረጋግጠውላቸዋል፡፡ መሀመድ አባስ በበኩላቸው ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሲገልፁ፤ ሕዝባቸው ከእስራኤል ጋር ለአመታት የዘለቀውን አለመግባባት መፍትሄ እንዲያገኝ እንደሚሻ እና ፍልስጤማዊያን ነፃ መንግሥት የሚቋቋምበትን ቀን በናፍቆት እየተጠባበቀ እንደሚገኝ ነግረዋቸዋል፡፡ መሀመድ አባስ አክለውም፣ ከእስራኤል ጋር ለመደራደርና የሰላም ስምምነት ለማድረግ እንደሚፈልጉ የገለፁ ሲሆን፣ ድርድሩ እስራኤል እ.ኤ.አ በ1967 ዓ.ም በሃይል የያዘቻቸውን የምስራቅ ኢየሩሳሌም ክልል ለፍልስጤማዊያን መመለስ እንዳለባት የሚያካትት ነው ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ መሀመድ አባስም ሆኑ ፍልስጤማዊያን የይገባኛል የግዛት ጥያቄያቸውን ለጊዜውም ቢሆን ተወት አድርገው በአገራቸው መንግስት በሚመሰረትበት ጉዳይ ላይ አተኩረዋል፡፡
መሀመድ አባስ የተባበሩት መንግሥታት አባል አገራት ከፍልስጤማዊያን ጐን እንዲቆሙ ቢማፀኑም፣ በተባበሩት መንግሥታት ድምን በድም የመሻር መብት ያላትና ዋነኛ ተሰሚ የሆነችው ዩናይትድ ስቴትስ፣ የፍልስጤማዊያንን ጥያቄ ውድቅ ታደርገዋለች የሚል ስጋት አለ፡፡ ፍልስጤማዊያን የራሳቸውን መንግስት መመስረታቸው ለእስራኤል ሕልውና አደጋ ነው የምትለው አሜሪካ፤ ፍልስጤማዊያን ከነፃ መንግሥት ጥያቄያቸው በፊት ከእስራኤል ጋር መደራደርና የእስራኤልን ይሁንታ ማግኘት አለባቸው የሚል አቋም አላት፡፡ በአሜሪካ አቋም በጣም የተበሳጩት መሀመድ አባስ፤ ጥያቄያችን በፀጥታው ምክር ቤት (Security council) ውድቅ ከሆነ፣ የፀጥታው ምክር ቤት የበላይ ለሆነው ለተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ (UN General Assembly) እናቀርባለን ሲሉ በእልህ ተናግረዋል፡፡
የእስራኤልና የፍልስጤም የሰላም ስምምነት ላለፉት 60 ዓመታት አንዴ ቦግ ሌላ ጊዜ ጥፍት እያለ አካባቢው የጦርነትና የግጭት ቀጠና በመሆን የዘለቀ ሲሆን፣ ከሁለቱም ወገኖች አያሌ ዜጐች አልቀዋል፡፡ ሁለቱም ወገኖች በሃይማኖት፣ በግዛት፣ በዘር እና በርእዮተ ዓለም ልዩነት እርስ በእርስ በመጋጨትና አንዱ የሌላው ፀር በመሆን ሕዝቦቻቸውን ለእልቂት ዳርገዋል፡፡ በተለይም እስራኤል ባላት ዘመናዊ የጦር ሠራዊትና የጦር መሣሪያ የተነሳ ፈርጣማ ጡንቻዋን ለዓመታት በፍልስጤማዊያን ላይ በማሳረፍ አያሌ ዜጐችን ለሕልፈት ዳርጋለች፡፡
በሁለቱም ሕዝቦች መካከል የተቀጣጠለው እሳት ዓለም አቀፍ መልክ በመያዝም ንፈኝነትንና አሸባሪነትን አስከትሏል፡፡በሌላ በኩልም እስራኤል በመንግሥትነት ከተቋቋመችጊዜ  ጀምሮ በየዓመቱ ከአሜሪካ የአንድ ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ታገኛለች፡፡
የተባበሩት መንግስታት እ.ኤ.አ በ1947 እስራኤልን ሉዓላዊ መንግስት በማለት እውቅና ከመስጠቱ በፊት ቦታው ላይ ይኖሩ የነበሩት ፍልስጤማዊያን ነበሩ፡፡ ልክ ዛሬ ፍልስጤማዊያን አገር ሳይኖራቸውም በመላው ዓለም እንደተሰደዱት እስራኤል በመላው ዓለም ተሰደው ይኖሩ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ ከ1800 ዓ.ም ጀምሮ በአውሮፓ በስደት ይኖሩ የነበሩት አይሁዳዊያን ቦታው በታሪክ የእነርሱ መሬት እንደሆነ በመግለ፣ ወደ ጥንት መሬታቸው ለመመለስ እንቅስቃሴ ጀመሩ፡፡ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት እንደፈነዳ፣ የጀርመኑ ናዚ ፓርቲ (National Party of Germany) ከ4 ሚሊዮን በላይ አይሁዳዊያንን በዘር ጥላቻ አሰቃቂ ጭፍጨፋ አካሄደባቸው፡፡ ከጀርመን በተቃራኒ የተሰለፉት የአሜሪካ፣ የእንግሊዝ፣ የፈረንሣይና የሶቭየት ሕብረት ሃይሎች ጦርነቱን በበላይነት ካሸነፉ በኋላ አሜሪካ የእስራኤል መንግሥት የሚመሰረትበትን ሁኔታ መተለም ጀመረች፡፡ ኦቶማን ቱርኮችን በማሸነፍ ከ1917 ዓ.ም ጀምሮ ፍልስጤሞችን ማስተዳደር የጀመረችው ታላቋ ብሪታኒያ፤ በወቅቱ በፍልስጤሞችና በአይሁዳዊያን መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለመቆጣጠር ከአቅም በላይ ስለሆነባት፣ የተባበሩት መንግሥታት አካባቢውን በበላይነት እንዲቆጣጠር አሳልፋ ሰጠች፡፡ የተባበሩት መንግሥታትም በአሜሪካ ፍላጐትና ግፊት መሰረት የፍልስጤም ግዛት የአይሁዳዊያንና የአረቦች (የፍልስጤሞች) እንዲሆን ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ ለእስራኤልም መንግስትም እውቅና ሰጠ፡፡ እስራኤል ነፃ መንግሥት መሆኗን ካወጀች በኋላ አሜሪካ፣ እንግሊዝና ፈረንሣይ ወዲያው የእስራኤልን መንግስትነት ሲቀበሉ፣ ሶቭየት ሕብረት ግን ብዙም ባታምንበትም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የኅይል አሰላለፉ ከእነ አሜሪካ ጋር መሆኑና በወቅቱ ከተፈጠረው ወዳጅነት በመነሳት የእስራኤልን ሉዓላዊ መንግሥትነት ተቀበለች፡፡ ቀስ በቀስም ሌሎች የአውሮፓ፣ የእስያና የአፍሪካ አገራት እስራኤል ነፃ ግዛት እንደሆነች ተስማሙ፡፡
ይሁን እንጂ ፍልስጤሞችና ሌሎች አረብ አገራት የተባበሩት መንግስታትን ውሳኔ አጥብቀው ተቃወሙ፡፡ አረብ አገራት እስራኤል የያዘችው ቦታ የፍልስጤሞች እንጂ የአይሁዳዊያን አይደለም በማለት ውሳኔውን አጥብቀው ኮነኑ፡፡በወቅቱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር የነበሩት ዴቪድ ቤን ጉሪዮን ሲናገሩ፣ ..ይህ ዛሬ ያገኘነው መሬት አዲስ መሬት አይደለም፤ አባቶቻችን ጥንት ይኖሩ የነበረበትን ቦታ ነው መልሰን የያዝነው.. ብለው ነበር፡፡ የእስራኤል መንግስት ከመመስረቱ በፊት በሕቡዕ የተቋቋመው የእስራኤል የስለላ ድርጅት (ሞሳድ) በስደት ይኖሩ የነበሩትን አይሁዳዊያንን፤ በመቀስቀስና በማነሳሳት የላቀ ሚና ተጫውቷል፡፡ በተለይም አይሁዳዊያን ወደ መሬታቸው ለመመለስ ብርቱ ፍላጐትና ጉጉት እንዲያድርባቸው ለማድረግ በመሐፍ ቅዱስ ላይ ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ ከአምላክ ተስፋ የተሰጣቸውን ጥቅስ ይጠቀም ነበር፡፡ ..ከአሕዛብ መካከል አወጣችኋለሁ፣ በብርቱ ክንድና በተዘረጋች እጅ፣ መአትንም በማፍሰስ ከተበተናችሁባቸውም አገሮች ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፤ ወደ አሕዛብ ምድረ-በዳ አመጣችኋለሁ.. ትንቢተ ሕዝቅኤል 20፡34፡፡ የሚገርመው ብሪታኒያ አይሁዳዊያንን ላለማስገባት ስታንገራግር፣ ሞሳድ ለብሪታኒያ የጦር መኮንኖች የመሐፍ ቅዱስ ጥቅስን በማስፈራሪያነት ተጠቅሟል፡፡ይሁንና እስራኤል ነፃ መንግሥት መሆኗን ባወጀችበት አመት ግብ፣ ዮርዳኖስ፣ ሶሪያ፣ ኢራቅ፣ ሊባኖስና ሳውዲ አረቢያ በመተባበር በእስራኤል ላይ ጦርነት አወጁ፤ ነገር ግን በጦርነቱ ድል ሳያገኙ ቀሩ፡፡ በሌላ በኩል እስራኤል ተጨማሪ ግዛቶችን አስፋፍታ ያዘች፡፡ እ.ኤ.አ በ1949 ዓ.ም ዮርዳኖስ የፍልስጤሞች መኖሪያ የሆነውን ዌስት ባንክን እንዲሁም ግብ የጋዛ ሰርጥን እንዲያስተዳድሩ አረቦች ተስማሙ፡፡
እ.ኤ.አ በ1967 ዓ.ም አረቦች እንደገና በመደራጀት በእስራኤል ላይ ጦርነት ከፈቱ፡፡ እስራኤል በጦርነቱ ሁሉንም አረብ አገራት ድል ከማድረጓም በላይ፣ የጐላን ተራራን ከሶሪያ፣ የጋዛ ሰርጥንና የሲና በረሃን ከግብ እንዲሁም ምስራቅ ኢየሩሳሌምንና ዌስት ባንክን ከዮርዳኖስ ጠቅልላ ወሰደች፡፡ እስራኤል ግዛታቸውን ከያዘች በኋላ አረቦች ሉዓላዊ አገር መሆኗን አምነው እስካልተቀበሉ ድረስ እንደማትመልስ ተናገረች፡፡ እ.ኤ.አ በ1973 ዓ.ም አረቦች እንደገና በመተባበር ለአራተኛ ጊዜ በእስራኤል ላይ ጦርነት ከፈቱ፡፡አሁንም ግን በጦርነቱ ተሸነፉ፡፡ የአረቦች አቋምና ምላሽ ያስቆጣት እስራኤል 700,000 የሚጠጉ ፍልስጤማዊያንን ከዌስት ባንክ በማስወጣት ከአውሮፓ የመጡ አይሁዳዊያን ስደተኞችን አሰፈረችበት፡፡ የሰፈራ እንቅስቃሴዋን አሁንም ድረስ መቀጠሏም ይታወቃል፡፡
እ.ኤ.አ በ1970ዎቹ ፍልስጤሞችን ነፃ ለማውጣት የፍልስጤም ነፃ አውጪ ድርጅት (PLO) በያሲር አረፋት አማካኝነት ተቋቋመ፡፡ “PLO” በእስራኤል ላይ የሽምቅ ውጊያ በማድረግ፣ የእስራኤል አውሮፕላን ላይ ቦንብ በማጥመድ እና በከተሞች ቦንብ በማፈንዳት ይታወቅ ጀመር፡፡ በተለይም እ.ኤ.አ በ1972 በሙኒክ ኦሎምፒክ ላይ ለመሳተፍ ወደ ሙኒክ የሚያመሩትን የእስራኤል ስፖርተኞችን ብላክ ሴፕተምበር (Black September) የተባለው y”PLO” ድጋፍ ያለው አሸባሪ ቡድን አግቶ ከገደላቸው በኋላ ‘PLO’ በአሸባሪነት ተፈረጀ፡፡
እ.ኤ.አ በ1980 “Intifada” የተባለው የፍልስጤም የአመ ቡድን በእስራኤል ላይ ጥቃት ማድረስ ጀመረ፡፡ ወጣቶቹ ፍልስጤማዊያን በእስራኤል ወታደሮች ላይ ድንጋይ ወይም ቦንብ መወርወር እንዲሁም ሰላማዊ እንቅስቃሴãCN ማወክና አልፎ አልፎ ራሳቸውን መስዋዕት በሚያደርግ አመ ውስጥ ይሳተፉ ነበር፡፡
የወጣቶች እንቅስቃሴ (Intifada) በጣም ያማረራቸው ሰላማዊ እስራኤል \ እስራኤል በሃይል ከያዘችው የፍልስጤም መሬቶች ለቃ እንድትወጣና ሰላም እንዲሰፍን ሲጠይቁ፣ ሌሎች አክራሪ አይሁዳዊያን ደግሞ መሬታችንን አሳልፈን አንሰጥም የሚል አቋም ያንፀባርቁ ነበር፡፡ አገሪቷን ለረጅም ጊዜ የሚመራው የቀኝ ክንፍ (Right wing) ፓርቲ አባላት አክራሪዎች በመሆናቸው ለፍልስጤም ወጣቶች አመ በተደጋጋሚ ተገቢ ያሉትን ቅጣት ሰጥተዋል፡፡እ.ኤ.አ በ1979 በግብና በእስራኤል መካከል የሰላም ድርድር ሲካሄድ፣ እስራኤል በሃይል የያዘችውን የሲና በረሃን ለግብ መልሳለች፡፡ በተለይ የቀድሞዋ ሶቭየት ሕብረት ከፈራረሰች በኋላ በርካታ አረብ አገራት ከሶቭየት የሚያገኙት ድጋፍ በመቋረጡ፣ የአረብ አገራት በእስራኤል ላይ ያላቸው አቋም እየተለሳለሰ መጣ፡፡ እ.ኤ.አ በ1994 ዓ.ም እስራኤልና ዮርዳኖስ የሰላም ስምምነት አደረጉ፡፡ ይሁን እንጂ በኢራን የሚደገፈው እንደ ሂዝቦላ እና በሶሪያ የሚደገፈው ሃማስ የመሳሰሉ እስላማዊ ኃይሎች በከተማ ውስጥ ከሚፈጠር አመ አንስቶ እስከ የሚሳየል ጥቃት በእስራኤል ላይ ፈመዋል፡፡X.x¤.x b1993 ›.M b«Q§Y ¸nþSt½R ይሳቅ ራቢን እና በያሲር አረፋት መካከል የተካሄደው ስምምነት ታሪካዊ የሚል ውዳሴ ያገኘ ሲሆን፣ ሁለቱም በጋራ የሰላም የኖቤል ተሸላሚ መሆናቸው ይታወሳል፡፡ ይሳቅ ራቢን ከኖቤል ሽልማቱ በኋላ ሲናገሩ፤ ..በእኛና በፍልስጤሞች መካከል ሰላም ለመፍጠር ስንል በሃይል የያዝነውን መሬት አሳልፈን እንሰጣለን.. በማለት ገልፀዋል፡፡ ይሁን እንጂ ይሳቅ ራቢን መሬትን ለፍልስጤማዊያን አሳልፈው ለመስጠት መስማማታቸው በርካታ አክራሪ አይሁዳዊያንን ያስቆጣ ሲሆን፣ በተለይም የይሳቅ ራቢን ድርጊት ያበሳጨው ወጣት ተማሪ ደረታቸው ላይ በጥይት መትቶ gD§*cêL””የፍልስጤሞች ነፃ መንግሥት ሊታወቅ የቀናት እድሜ በቀሩት በዚህን ወቅት በአውሮፓ ፀረ-ዮናዊነት አቋሞች እየተስፋፉ ይገኛሉ፡፡ እስራኤል በሃይል የያዘችው ቦታ የፍልስጤሞች ነው የሚሉ ድምፆች ከወደ አውሮፓ በስፋት መስተጋባት ጀምረዋል፡፡ “The Middle East” የተሰኘው መሔት “Sanctions Threats against Israel Ground” በሚል ርእስ ሰሞኑን እንዳስነበበው፤ በአውሮፓ የእስራኤል ምርቶችን ላለመግዛት (Boy cott እቀባ እየተካሄደ ነው ብሏል፡፡ በግንቦት ወር ላይ University of London Union (ULU) የተባለ የተማሪዎች ማህበር ለፍልስጤሞች ድጋፍ በመስጠት በእስራኤል ምርቶች ላይ እቀባ እንዲካሄድ ቅስቀሳ መጀመሩ ይታወሳል፡፡ y‘ULU’ አባላት 120 ሺህ የሚደርሱ ሲሆን፣ በአውሮፓ ትልቁ የተማሪዎች ማህበር ነው፡፡ ይህ ማህበር በርክሌ የተባለው ትልቁ የእንግሊዝ ባንክ የደቡብ አፍሪካውን አፓርታይድ ይደግፍ በነበረበት ወቅት በባንኩ ላይ ቦይኮት በማድረግ ባንኩን ለኪሳራ ዳርጐታል፡፡ በተመሳሳይም አሁን ባለው የእስራኤል ቀኝ ክንፍ መንግስት ላይ ጠንካራ ተቃውሞ አስነስቷል፡፡ የእስራኤል መንግስት በበኩሉ፤ በአውሮፓ ውስጥ የተፈጠረውን ጫና ለመቆጣጠርና ለማርገብ በኬኒሴት (የእስራኤል ፓርላማ) በኩል ተደጋጋሚ ውሳኔዎችን እያስተላለፈ ይገኛል፡፡ሻፒራ የተባለ በአውሮፓ የሚኖር ፍልስጤማዊ የፖለቲካ አቀንቃኝ (Political Activist) ሲናገር፤ ..የእስራኤል መንግስት ዘረኛ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ እስራኤል በፍልስጤሞች ላይ በወሰደችው እርምጃ የአፀፋ መፍትሄው በአውሮፓ ያሉ ምርቶቿን ከመግዛት ወይም ከመጠቀም መታቀብ ነው ብሏል፡፡እንግዲያው በቀጣዩ ሳምንት በሚካሄደው ስብሰባ እስካሁን ከተባበሩት መንግሥታት አባል አገራት ውስጥ ከ100 በላይ የሚሆኑ ለፍልስጤሞች ድም እንደሚሰጡ አንዳንድ አለም አቀፍ ሚዲያዎች ይፋ ያደረጉ ቢሆንም፣ የአሜሪካ አቋም እስካሁን በግል ባለመታወቁ የፍልስጤሞች ጉጉት ባዶ ሕልም ሆኖ እንዳይቀር ያሰጋል፡፡

 

Read 5636 times Last modified on Saturday, 17 September 2011 10:34