Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 September 2011 10:25

አንዱን ለመካብ ሌላውን ማንኳሰስ!

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ሐምሌ 30 ቀን 2003 ዓ.ም. እዚሁ ጋዜጣ ላይ ..ፖለቲካና የደራሲ ፖለቲከኞች.. በሚል ርዕስ በደራሲ
አለማየሁ ገላጋይ የተጻፈውን ጽሁፍ ””ደራሲW ዋና መሽከርከሪያ ርዕሰ ጉዳያቸው አድርገው የተነሱበት ..የኢትዮጵያ የተገለባባጭ ደራሲ ደሀ አይደለችም... ከጥቂቶቹ ደራሲያን በስተቀር አብዛኞቹ ደራሲያን ጉልበታም የፖለቲካ ወጀብ የሚያስጎነብሳቸው መንፈሰ ድውያን ናቸው.. የሚለው ነው፡፡በተያያዘ ነጥባቸውም ..ፎርመኛ ደራሲዎች አሉን.. ያሏቸውን እነ ብርሀኑ ዘሪሁን፣ ፀጋዬ ገ/መድህንና ሌሎችንም አንስተው ባልተገባ የሀሳብ አካሄድ ወይም ውቅያኖስን በጭልፋ... በሚመስል ቁንጽል ዕይታ ሀሳባቸውን ሲያስነብቡን በዝምታ አለፍን፡፡ እሳቸው ግን ዝምታችንን ..አበጀህ.. እንደመባል ቆጥረውት ቀጥለውበታል፡፡

በነሐሴ 7 ቀን 2003 ዓ.ም. የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዕትም ላይ ደግሞ ከታሪክ ሊቃውንት ይልቅ ..የተረት አባቶች.. እያሉ ቀድሞ የነበሩትን የታሪክ ፀሐፊዎች ስም ይዘረዝሩልናል፡፡ እኔ በዛሬው ጽሁፌ ለማንሳት የምሞክረው ..የተረት አባቶች.. ብለው ከፈረጇቸው ፀሐፊያን ውስጥ አንዱ የሆኑትን ተክለፃዲቅ መኩሪያን ነው፡፡
እንደሚታወቀው የታሪክ አጻጻፍ ስልት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የሚሄድ ነው፡፡ በጥንት ጊዜም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታሪክን መዝግቦ ማስቀመጥ (Documentation) ባለመኖሩ የነበረውን የታሪክ እውነታ ማግኘት ይቻል የነበረው በቃል ከሚተላለፈው ነበር፡፡ ይህም አፈ-ታሪክ የምንለው ነው፡፡ በፊት የነበሩት ሽማግሌዎች መጻፍ ባለመቻላቸው ምክንያት የነበረውን እውነታ በቃል ከትውልድ ወደ ትውልድ ያስተላለፉት ነበር፡፡ የነበረውን ነገር ጽፈውት ቢሆን ምንጭ ይሆን ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ባህል በመሠረቱ አፈአዊ እንጂ ጽሁፋዊ አልነበረም፡፡ ፈረንጆቹም የሚበልጡን ሁሉንም ነገር ትንሽ ትልቅ ሳይሉ በጽሁፍ ያሰፍሩት ስለነበረ ነው፡፡
ተክለጻዲቅ መኩሪያ የታሪክ መጻህፍትን ለመጻፍ የተነሱት በግላቸው ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ማወቅ ይወዱ ስለነበር፣ የተፃፉት የታሪክ መፃሕፍት በውጭ አገር ሰዎች በየራሳቸው ቋንቋ በመሆኑና መጽሐፉንም የሀገራችን ህዝብ ሊያነበው ባለመቻሉ፣ በሀገራችን ኢትዮጵያ የታሪክ ጽሁፍ ያነሰ በመሆኑ ነበር፡፡ በ1934 ት/ቤቶች ሲከፈቱ ተክለጻዲቅ የትምህርት ሚኒስትር መዝገብ ቤት ሹም ሆነው ይሰሩ ነበር፡፡ የትምህርት ሚኒስትሩ ኃላፊ በአንድ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያን ታሪክ የሚያስተምሩት መምህራን ፈረንጆች መሆናቸው እና የሚያስተምሩትም የራሳቸውን ቋንቋ በመጠቀም ሲሆን፤ ከራሳቸው ምንጭ በመነሳትና ራሳቸው እንደተረዱት አድርገውም እንደሚቀርቡ፣ በመጨረሻ ኢትዮጵያን የሚያክል ሀገር የራሷን ታሪክ የሚጽፍላት የራሷ የሆነ ሰው አለመኖሩን ሲናገሩ በመስማት በመቆጨትና የራሳቸውን ድርሻ ለማበርከትም ነበር፡፡
ተክለጻዲቅ ..ከአ ቴዎድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ.. በሚለው መጻህፋቸው መግቢያ ላይም እንዲህ BlêL:- .....የኢትዮጵያን ታሪክ ከመሠረቱ ጀምሮ ለመመርመርና ለማወቅ ለመጻፍም የሚያስብ ሰው...
ሀ. ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ከኢትዮጵያና ከውጭ ሀገር ደራሲዎች የተጻፉትን መጻህፍት በሙሉ በቤቱ ማኖርና ቋንቋቸውንም ማወቅ፤
ለ. በግዕዝና በውጭ አገር ቋንቋ የተጻፉትን እያስተያየ፣ ልዩነታቸውንና የሚፋለሱበትን ማወቅ፤
ሐ. ያነበበውን ሁሉ በዝርዝር ወይም አርዕስት አርዕስቱን ባሳብ መያዝ፤
መ. ታሪክ የተደረገበትን ስፍራ እየዞሩ ባይን ማየት፤
ሠ. ለጽህፈት አእምሮን የተደራጀ አድርጎ መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ዘመናዊዎቹ የታሪክ ሊቃውንት (Modern Historians) የጥንቶቹን የታሪክ ሐፊያን የሚነቅፏቸው በዘመናዊ የአጻጻፍ ስልት አልተጻፈም በማለት ነው፡፡ ነገር ግን ተክለጻዲቅ በጻፉበት ዘመን ዘመናዊው የአጻጻፍ ስልት አልነበረም፡፡
እኛ የምናውቀው የቀደመ ታሪካችንም ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው በነዚህ በቀደሙት የታሪክ ፀሐፊያን ነው እንጂ ሌላ ምንጭ አልነበረም፡፡ አፈታሪክንም ሙሉ በሙሉ ተረት ነው ለማለት አያስደፍርም፡፡ ነገር ግን በቅብብሎሽ ምክንያት የሚጨመርና የሚቀነስ ሊኖረው ቢችልም መሠረት ሳይዝ ግን አይነሳም፡፡ ለምሳሌ ቅኔ አንድ ሰው የሚቀኘውና የሚያቀርበው በቃሉ ነው፡፡ ካቀረበው በኋላ እንኳን ጽፎ የማስቀመጥ ባህል አልነበረም፡፡ እንዲሁም በጽሁፍ ማስፈርም ክልክል ነበር፡፡ ስለዚህ ቅኔውን የሚማሩት በትክክል እና ቃል በቃል ፈሩን ሳይለቅ ሲሆን፤ ለተከታዮቻቸውም የሚያስተላልፉት እንደዛው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ከዘመን ወደ ዘመን ..የእከሌ ቅኔ.. እየተባለ ለሚመጣው ትውልድ ሲተላለፍ ቆይቷል፡፡  
ተክለጻዲቅ በዘመናቸው የኢትዮጵያን ታሪክ ከመነሻ እስከ መድረሻ አከታትለውና አቀጣጥለው እስከ ዘመናችን ድረስ አቅርበውልናል፡፡
..ከአፄ ቴዎድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ..
..ከአፄ ልብነ ድንግል እስከ አፄ ቴዎድሮስ..
..ከአፄ ይኩኖአምላክ እስከ አፄ ልብነ ድንግል..
..ከአክሱም እስከ ዛግዌ..
..ሜርዎዬ (ኑብያ)..
እያንዳንዳቸው ከ300 ገጽ በላይ ያላቸውን እንዲሁም
..አህመድ ግራኝ..
..ቴዎድሮስና የኢትዮጵያ ታሪክ..
..ሚኒልክና የኢትዮጵያ ታሪክ.. የሚባሉትን መጻህፍት የጻፉ ሲሆን፤ የስነ ጽሁፍ መነሻ የሚባሉትንም ግጥሞች ለኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1951 ዓ.ም. ያስተዋወቁ ናቸው፡፡ ቀጥሎም ለጻፉት ምንጫቸው የሆኑትም uMR””ተክለጻዲቅ ለስራቸው ምን ያህል ጥንቁቅና ኃላፊነት የሚሰማቸው ፀሐፊ መሆናቸውን እንደማስረጃ የሚያሳየን፣ ..ከአፄ ቴዎድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃ/ስላሴ.. በሚለው መጻህፋቸው መግቢያ ላይ እንዳሉት፤ መጽሐፉ ከመታተሙ በፊት ከፕሮፌሰር ታምራት አማኑኤል፣ ከአቶ አርአያስላሴ እና ከመሳሰሉት ምክር እንደወሰዱና እንዳስገመገሙ ስናይ ተራ ተረት ፀሐፊ አለመሆናቸውን XNrÄlN””ሌላW ..ከአፄ ይኩኖ አምላክ እስከ አፄ ልብነ ድንግል.. የሚለውን መጽሐፍ የጻፉት በ1934 ዓ.ም. ሲሆን፤ የታተመው በ1936 ዓ.ም. ነበር፡፡ ምክንያቱም ጃንሆይ በጊዜው ከነበረው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር መገናዘብ አለበት በማለት ኮሚቴ አቋቁመው ለ2 ዓመታት እስከሚታተም ድረስ የማጣራት እና የማመሳከር ስራ በኮሚቴው አማካኝነት ሲሰራ ስለነበረ ነው፡፡ተክለጻዲቅ  በአንዱ ጽሁፋቸው መግቢያ ላይ የጻፉትም፤ ይሄ እኔ ያቀረብኩት የታሪክ መጽሐፍ የተሟላ አይደለም፡፡ መቅረብም ባለበት ሁኔታ ቀርቧል አልልም፡፡ ምክንያቱም እኔ በተነሳሁበት ጊዜ እንደዚህ የተሰራ የቀደመ ነገር አልነበረጥም፡፡ ቢኖር ኖሮ እኔ ደግሞ አሁን ከዛ ላቅ ያለ ነገር አቀርብ ነበር፡፡ አሁንም ይሄ መጽሐፍ ለሚቀጥሉት ፀሐፊያን እንደመነሻ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳትም የቀረውን ለመመርመርና ለማወቅ የሚረዳ ነው ብለዋል፡፡እንግዲህ በዚያ በጨለማ ዘመን እና የሰለጠነ የአጻጻፍ ስልት ባልነበረበት ወቅት ያላቸውን አቅም በመጠቀም፣ የኢትዮጵያን ታሪክ ለመጭው  ትውልድ ለማስተላለፍ መሞከራቸውና ለአገራቸው መቆርቆራቸው ሊያስመሰግናቸው እንጂ ሊያንኳስሳቸው ባልተገባ ነበር፡፡yqdÑT የታሪክ ፀሐፊያን ስለሰሩት ስራ ጥያቄ ማንሳትና ድክመቱንም መመርመር የሚቻል ነው፡፡ ነገር ግን አበርክተው ስላለፉት ነገር ዋጋውን መስጠትም መዘንጋት አያሻም፡፡ከመምህሩ ደቀ መዝሙሩ ሆነ አንጂ አለማየሁ የሚያደንቋቸው የታሪክ ሊቃውንት ራሳቸው ስለኢትዮጵያ ታሪክ የተዋወቁትና፣ ወደዚያም እንዲያዘነብሉ ካደረጓቸው WS_ የመጀመሪያውን ደረጃ የሚይዙት ተክለጻዲቅ መኩሪያ ÂcW””አለማየሁ የሚያደንቋቸው የታሪክ ሊቃውንት ለኢትዮጵያ ህዝብ በቋንቋው ጽፈው ያበረከቱት ምንስ ነገር አለ? ካለ ቢጠቅሱልን? ምናልባት ባህሩ ዘውዴ በእንግሊዝኛ የጻፉትን መጽሐፍ በአማርኛ ተርጉመው ማቅረባቸው እሰይ ከማሰኘቱ በቀር፡፡ በመጀመሪያ እኮ ስለኢትዮጵያ ታሪክ ማወቅ ያለበት የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ ፈረንጆቹ አይደሉም፡፡ ለመሆኑ ከተክለጻዲቅ መኩሪያ ሌላ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያውቀውና ሊያነበው የሚችል መጽሐፍ የጻፈ ሌላ ሰው ነበርን?አንዱን ለማድነቅ አንዱን ማንኳሰስም ጎበዝ አያሰኝም፡፡ አለማየሁ የሚያደንቋቸው የታሪክ ምሁራን እንኳን ተክለጻዲቅ መኩሪያን የአለማየሁን የሚያክል ድፍረት የተሞላበት ትችት ለመናገር የሚደፍሩ አይመስለኝም፡፡  የሚያደንቁትን ለመካብ ሲባል እኮ ያላደነቁትን ከስሩ በመጋዝ ገዝግዞ መጣል አያስፈልግም፡፡ እነዚህን ..የተረት አባቶች.. የሚሏቸውን በመተቸት ለማውረድ ከመሞከር እንደው በራስ ስራ መፎካከር የሚሻል አይመስልዎትም?
ምንም ስለታሪክ ለማወቅ ሳይመረምሩ እና ካለምንም የታሪክ ዕውቀት በመነሳት የሚያደንቋቸው የታሪክ ሊቃውንት ያሉትን በመጥቀስ ለማስተጋባት መሞከር የገደል ማሚቱ አያሰኝም? ይሄን ሁሉ የሰራን ሰው በሁለት ሀረግ በመመስረት ምንም እንዳልሰራ በማድረግ ..ተረት ተረት.. ነው ማለትዎ ኢ-ፍትሃዊና ትልቅ ድፍረት ይመስለኛል፡፡በመጨረሻም የአለማየሁ ጽሁፍም አንድ ደራሲ በጨዋታ መሀል የነገሩኝን አስታወሰኝ ..ክፉ መናገርና ቂጣ መጋገር አያቅትም.. የሚለውን፡፡

 

Read 6457 times Last modified on Saturday, 17 September 2011 10:26