Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 September 2011 10:17

የዘመን ሐሳበ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

የኢትዮጵያ ዘመን መቁጠሪያ መሠረቶች
ዘመን ማለት በመላው ጊዜ ውስጥ የሚገኝ፤ በልብ ውስጥ የሚያዝ ወሰነ ጊዜ፣ ቀጠሮ ጊዜ፣ ጊዜ ዕድሜ ነው፡፡ ዘመን ማለት ቁጥር ያለው ጊዜ ነው፡፡ ጊዜ የተባለው ምንት ዓለም ከተፈጠረች ጊዜ ጀምሮ እስካለችበት ጊዜ ድረስ የሚኖር ያለ ሲሆን ይህን ጊዜ ከፍሎ ወሰን፣ ድንበር፣ ቀጠሮን አድርጐ በጊዜ ውስጥ ያሉ ጊዜያትን ቁጥር እሚያደርግለት ደግሞ ዘመን ነው ብሎ፣ በምኑም ምኑም ፈጽሞ መሳይ የሌለው የኢትዮጵያ ሐሳበ ዘመን ተረድቶ - አስረድቶ፤ ጊዜውን በዘመን የመለየትና የማስለየት ሥራውን ይጀምራል፡፡

***
እንዲህ አድርገን ዘመን የተባለውን ዐውቀን በልባችን እንይዘው ዘንድ
ወንበል ፍካሬሁሰ ለዘመን
በውስተ ልብ ወሰነ ጊዜ ውእቱ
በኲሉ ጊዜ
ብሎ የሚመክረን ይህ ባሕረ ሐሳብ (ሐሳበ ዓለም) እንደተገለው የተፈታውን ዘመን በሦስቱ የጊዜ/ዘመን አቅጣጮች እንደሚከፈሉና እነርሱም ያለፈው፣ የሚመጣውና ያለው (ያሁኑ) ተብለው እንደሚጠሩ ይገልጻል፡፡
ጊዜ ዕድሜም የተባለ ይህ ዘመን በሦስት አቅጣጫ
ይወሰዳል፡-
ዘኀኀለፈ - ያለፈሙ፣
ወዘይመጽእ - የሚመጣውም
ዘኀኀሎ - ያለውም (ያሁኑ)  
ይላል፡፡
ትናንት፣ ዛሬና ነገን ያሰበ የዘመን መቁጠሪያን ሊያበጅ ነውና ወደ ኋላም፣ ወደ ፊትም፣ ያለውንም ሦስቱ የዘመን መንገስት ያደርጋል፡፡ እንዲህ አድርጐ ከኋላ ጀምሮ ሊመጣ እስካለው ድረስ የሚሸክፍበት ይህን ብልሃት የምናደንቀውና ከቶውኑ የብዙዎች የጋራ ቤት ከነበረ ተገኝቶ እንዲህ በኢትዮጵያውያን መጠበቁን፣ የሰውን ልጅም ለረጅም ጊዜ ያገለገለ ነው እንድንል የሚያስገድዱንን የሳይንሳውያንን ገለጻ እዚኸው ላይ እናመጣለን፡፡
ስለጊዜ መቆጠር ሳይንሱ ሲናገር፣ ጊዜን ዘመን ብሎ መቁጠር የመጣው በጥንቱ ዘመን የነበረው የሰው ልጅ ትናንት፣ ዛሬና ነገ ብሎ ከያዘው ግንዛቤ የመጣ ነው ይላል፡፡ (ኢንካርታ) እዚህ ላይ ሐሳቡ የጥንት መሆኑን ብቻ ሳይሆን የጥንቱ ዘመን ሰው (በዓለም አቀፍ ደረጃ) የነበረው ሰው ግንዛቤና አከፋፈል እንደነበር ይገልጻል፡፡ በዛሬ ዘመን ውስጥ እንዲህ አድርጐ የሚከፍል የጥንት አከፋፈል በዚህ መቁጠሪያ መገኘቱ ምናልባት ጥንታዊና የሰው ልጆች የጋራ ቤት ከነበረው የወረደ እንደሆነ ለማመልከት የሚያስችል ይሆናል፡፡
ያን ዓይነት አከፋፈል ጊዜን ለመቁጠር ወዳስቻለ እርምጃ እንዳደረሰ በመላ የተጠቆሙትን ሦስቱን ክፍሎች /አቅጣጫዎች/ በትክክል ጊዜውን ለማወቅና ለመግለጽ ሊኖሩ የሚገቡ እንደሆኑ ደግሞ፣ ስለጊዜ ከነበረው ሳይንሳዊ ግንዛቤ ለየት ያለ እሳቤ ላይ በተደረሰበት 20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ውስጥ ስቴፈን ሆኪንግ ጊዜውን እንዲሁ ከፍሎ፣ በሥዕልም ጭምር አቅርቦ ገለጻውን ሲያደርግበት እናገኛለን፡፡ (የጊዜ አጭር ታሪክ ተብሎ በአማርኛ ሊጠራ የሚችለውን መጽሐፍ ይመለከቷል፡፡)
ሐሳበ ዘመኑ ጊዜን መነሻ፣ መድረሻ ያለው ወይም ዘላለማዊ ያለመሆኑን፣ እንዲሁም ፍጽምና የሌለው ..አንጻራዊ.. መሆኑን ከመነሻው ዘመን የተባለውን ጊዜውን ..ወሰነ ጊዜ.. ብሎ ከገለው የምንረዳው ነው፡፡
ሦስቱን ክፍሎችንም ከላይ እንደቀረበው በሳይንሳውያኑ ዘንድም እንደ አዲስ የተያዘ መሆኑን አየን፡፡ እዚህ ላይ ይህን ሐሳበ ዘመን እንዲህ ለማየት የሚያስችል አቋም ቢኖር ኖሮ፣ በሳይንሳዊው የጊዜ አገላለጥ ላይ ስመ ጥር የሆኑት ቁንጮ ሳይንቲስቶች (እነ አልበርት አንስታይንና ስቴፈን ሆውኪንግ) የጠቆሙትን ነጥቦች በመያዝ ረገድም ቀዳሚዎች እንዳልነበሩም ይኸው የሐሳበ ዘመኑ አገላለጽና አከፋፈል ያሳውቀናል፡፡ ሌላው እስከዚህ ባየነው የዘመን መቁጠሪያ አያያዝ፣ በዓለም ላይ አሉ ከሚባሉት ልዩ መሆን ብቻ ሳይሆን እንዴት ባለ ጥንቃቄ ጊዜ የተባለውን ምንነት፣ ዘመኑንም ጭምር እንደተረዳውም ሳይቀር እናይለታለን፡፡
***
ዘመንን አስቀድሞ በሦስቱ መንገዶች እንዲታሰቡ ካደረገ በኋላ፣ እንደገና በያንዳንዱ አቅጣጫ የሚወሰደውን ዘመን በ5 ክፍሎች ይከፍላቸዋል፡፡ እነዚህ አምስት መሠረታዊ የዘመን ክፍሎች፡- ዓመት፣ ወር (ኅ)፣ ዕለት፣ ሰዓትና ኬክሮስ በማለት ከትልቁ ጀምሮ እስከመጨረሻው ትንሹ የጊዜ ክፋይ፣ የዘመን ርዝማኔ ድረስ ከፍሎ ያቀርባል፡፡
ይህ መሠረታዊ አከፋፈሉ ነው 5ቱ የመቁጠሪያው መሠረታውያን አሐዳዊ መጠኖችን ያስገኘለት፡፡ የሐሳበ ዘመኑ መሠረታውያን አሐዶችም (Fundamental Units) እነዚሁ 5ቱ ክፍሎች ናቸው፡፡
እዚሁ ላይ ልናያቸው የምንችላቸውን ነጥቦች በመንቀስ፣ በነዚህም መቁጠሪያው ፈጽሞ የተለየ፣ ራሱን የቻለ እና ምንኛ ጥንቃቄን ይዞ እንደተዋቀረ፣ ለነዚህም የየራሳቸውን መዋያ (function) ሰጥቶ ወደ መቁጠር ማስቆጠሩ እንደሚገባ ልናስተውል ይገባል፡፡
በመጀመሪያ በዓለም ላይ ከ40 በላይ ናቸው ከሚባሉት ውስጥ በዛሬ ጊዜ እነዚህን 5 የዘመን መቁጠሪያ መሠረታዊያን አሐዶች ያደረገ አንድም ሌላ ካሌንደር አለመገኘቱን እንያዝ፡፡ ብዙዎች ባለሦስት መሠረታዊ አሐዶች ሆነው ይገኛሉ፡፡ ሰዓትንና ኬክሮስን የትኛውም የታወቀ ካሌንደር መሠረታዊ አሐዶች አላደረጋቸውም፡፡ ዓመት፣ ወርና ዕለት ብቻ በቂያቸው እንደሆኑ አደርገው በእነሱ ሲቆጥሩ፣ ለመግለጽ ያህል ከዕለት ያነሰውን የጊዜ ክፍል በሰዓት እየሰፈሩ ይናገሩታል፡፡ ይህንን በጠቅላላ ካሌንደሮች ላይ የቀረበ ጽሑፍ፣ ..ሰዓት የካሌንደር መሠረታዊ አሐድ ባይሆንም ሲጠቀሙበት ይገኛል፣.. በማለት በቀጥታ ሲገልው ይገኛል፡፡ እንደዚህ ያለው ጽሑፍ የኢትዮጵያውን ዐውቆት በነበር፣ ..ከኢትዮጵያው በቀር፣.. ብሎ መጨመር በቻለ ነበር፡፡
እንዲህ ለማለት የሚያበቃውን መነሻ ሐሳብ ወይም ግንዛቤ ለመያዝ የሚቻለው ደግሞ ለሦስቱ፣ ማለትም ለዓመት፣ ወርና ዕለት በየካሌንደሩ የተሰጣቸው ከምድርና ከሰማይ ላይ ብርሃናት ጋር የተያያዘ፣ የነዚህ የተፈጥሮ ሥርዓት የሚያስገኛቸው የጊዜ ወይም የዘመን መጠን እያደረጉ ሲገልቸው መገኘታቸው ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ፣ ሰዓትን እንዲሁ ተገልጾ ባለመገኘቱ፣ ምንነቱን ወስነው ስላላገኙዋቸው ከምን ጋር ተገናኝቶ እንደሚገለጽ የማይታወቅ መሆኑን በመጠቆም፣ ..መሠረታዊ አሐድ.. እንዳልሆነላቸው ተገልጾ ይገኛል፡፡ ሰዓትን ብቻ እንዲህ መግለጻቸውም ሰዓት የተባለ አሐድ bየመቁጠሪያውM ሆነ በሌላው ጊዜን በመቁጠር የሚያገለግል በመሆኑ ነው፡፡
ኬክሮስ የተባለውን ግን ማንም የማይጠቀምበት፣ የቀረ አሐድ ስለሆነ ከጥያቄም አላስገቡትም፡፡ በኢትዮጵያው ግን ሁለቱም የየራሳቸው የሆነ መዋያ ተደርጐላቸው በቁጥር ትምህርቱ ይገለጻሉ፡፡
እዚሁ ላይ መጤን የሚገባው አንድ ዋነኛ ነጥብ፣ እነዚህ አሐዶች የሚባሉት ከፀሐይ ወይ ከጨረቃ አሊያም ከሁለቱም እና ከመሬት ሥርዓተ ዓውድ ጋር እያያዙ የመፍታቱ ነገር ነው፡፡ ዓመት ምድር በፀሐይቱ ዙሪያ ዞራ የምትፈጽምበት ጊዜ፣ ወር ጨረቃይቱ ተመልሳ የምትታይበት፣ ዕለትም ምድሪቱ በራሷ ዛቢያ አንዴ የምትሾርበት ጊዜ ተብለው ከተያዙ፣ ‘ሰዓትS ምን ይባል? úMNTS?’
እንዲህ ብለው ከብርሃናትና ከምድሪቱ ሥርዓት ጋር አዛምደው ሲፈቱ፣ እነዚያ የተፈጥሮ ሥርዓቶች እነዚህን ዓመት፣ ወርና ዕለትን እንዳስገኙዋቸው ወይም እንደወለዷቸው መግለጻቸውን ልብ ይሏል፡፡ እነዚያ ተፈጥሯዊ ሥርዓቶች ባይኖሩ ዓመት - በሉ - ወር፣ ወይም ዕለት አንዳቸውም የማይኖሩ አድርገው እንዲያስቧቸው ግድ የሚል አገላለጽ ነው የሰጧቸው፡፡ በሳይንሱ በኩል ሰዎች ሁሉ ይህን እውነት ብለው እንዲይዙ መደረጉንም እናውቃለን፡፡
የኢትዮጵያው ግን ያሉትን ዘመናት/የዘመን ክፍሎች ወይም አሐዶች/ወይም በዝርዝር ከዓመት እስከ ኬክሮስ ያሉትን ከየትኛውም ሌላ ተፈጥሮአዊ ሥርዓት ጋር እንዲህ በጥብቁ አቆራኝቶ ሲገልጻቸው አይገኝም፡፡ አንዴ ዘመን ማለት ወሰነ ጊዜ፤ የቀጠሮ ጊዜ ማለት ነው፡፡ ብሎ የፈታው ነው እዚህ ላይም የሚያዘው፡፡ እንዲህ በማድረጉ ከብርሃናቱ ጋር ያለቅጥ የጠበቀ፣ ፍምነት ያለውን የሚያስሳፍር፣ የማይቻልና የማይሆን ስህተት ውስጥ ገብቶ ከመጠበብ፣ ዐሥሩን ልኬት ሲቀያይር ከመገኘት፤ ጊዜ የሚባለውን ምንት ራሱን የቻለ ምንት ከመሆን ይልቅ የሌሎች ተፈጥሯዊ ሥርዓት ውጤት ከማድረግ አትርፎታል፡፡ እርግጥ ነው ..ጊዜን የሥራው መቁጠሪያ አደረገው፤.. ተብሏል፡፡ ይህ ማለት ግን የብርሃናቱ ሥርዓት ተለይተው የዘመን ወላጆች ሆኑ ማለት አይደለም፤ ብርሃናቱ ሳይኖሩም ጊዜና ዘመን ነበረ፡፡
ይህን ከዚህም በኋላ ራሱን ችሎ መነሳት በሚገባው ብርሃናቱን በምናነሳበት ክፍል እናነሳዋለን፡፡ ነገር ግን በዚህም ረገድ ይህ ሐሳበ ዘመን የተለየ እንደሆነ ይዘን እንጓዝ፡፡ ጥንቃቄውንና ብልህነቱንም ጭምር፡፡
***
ዕለትን፣ ሰዓትንና ኬክሮስን ከነመዋያቸው የሚገልው መጽሐፍ ደግሞ ይህ ነው፡፡
ኬክሮስ ..የማይከፈል.. ዘመን ሲሆን፣ ሰዓት ደግሞ ..የሚከፈል.. ዘመን ይባላል፡፡ በኬክሮስ ማንኛውም የጊዜ መጠን ይሰፈራል - ይቆጠራል፡፡ አንድ ሥራ የፈጀው የጊዜ መጠን (ሌት ይሁን ቀን ሳይለይ፣ ሳይከፈል) በኬክሮስ ይነገራል - እንደ ሐሳበ ዘመኑ ቢሆን፡፡
'ከዚህ እዚያ ድረስ ለመሄድ ይህን ያህል ሰዓት Yf©ል#' ሳይሆን፣ እንዲህ ያለው ያልተለየ የጊዜ መጠን በኬክሮስ ነው የሚገለው፡፡ ምክንያቱም፣ ሰዓት ..የሚከፈል.. የሌት ወይም ..የቀን.. የሚባል የአንድ የታወቀ ጊዜ መቁጠሪያ መለያ እንጂ እንዲህ የማንኛውም ጊዜ ርዝመት መቁጠሪያ ሁኖ አልተሠራምና ነው - እንደ ቁጥር ትምህርቱ ቢሆን ኖሮ፡፡
ዕለት ሌሊቱንና መዓልቱን የሚሰበስባቸው፣ ..ዮም-ዛሬ.. የሚባል ጊዜ ነው፡፡ ሰዓት የተባለውም የዚህ ዕለት የተባለ ክፍለ ዘመን 1-24ኛ ጊዜ ነው፡፡ ዕለትን በ24 እኩል የሆነ ጊዜ መጠን ሲከፍሉት፣ አንዲቷ ክፍል ብቻ ሰዓት ትባላለች፡፡
ዕለት ሌሊቱንና መዓልቱን የሚሰበሰብ ነው ተብሏል፡፡ ይባል እንጂ ሌሊቱን ከመዓልቱ፣ መዓልቱን ከሌሊቱ አንድ አድርጐ፣ ከ1 እስከ 24ኛ ሰዓት የሚቆጥሩበት አቆጣጠር በዚሁ በኢትዮጵያው ሐሳበ ዓለም ፈጽሞ - በጭራሽ የተከለከለ ነው፡፡
..ብርሃንን ከጨለማ፤ ታቦትን ከጣዖት.. ምን አንድ አደረገው? - የጽልመቱ ጊዜያት እስከ 12ኛ ሰዓተ ሌሊት ድረስ ይቆጠራሉ፡፡ የመዓልቱም ጊዜ እስከ 12ኛ ሰዓት መዓልት ይቆጠራል፡፡ የግድ እያንዳንዱ እስከ 12 መቆጠር እንዳለበት የሐሳበ ዘመኑ ትምህርት ይገልጽና ምክንያቱን እንዲህ ሲል ይናገራል፡-
የፀሐዩ መግቦት (ጊዜ) ከጨረቃው በምን ያህል እንደሚበልጥ፣ ወይም እንደሚያንስ፣ አሊያም እኩል የሚሆኑበትን ዕለት ያሳውቅ ዘንድ፡፡ ይኼም የሚሆነው k4tÜ ወቅቶች መፈራረቅ የተነሳ ነው፡፡ (አቡሻክር፤ በአቅራቢው ቃል የቀረበ””) የአንድ ዕለት የሌሊት ጊዜ እና የመዓልት ጊዜ ከሌላው ጋር ሁሌ እኩል እንደማይሆን፣ የሐሳበ ዘመኑ መሠረቶች ወይም ሕግጋትን ከገለ መጻሕፍት ሁሉ የሚቀድመው ሄኖክ 1122-1287 ዓመተ ዓለም፤ 4379-40 ቅ.ል.ክ የነበረ) ከዛሬ 6ሺ ዓመት አስቀድሞ የገለው ነው፡፡ እሱም ገና ያን ጊዜ የዚህ የሌትና መዓልቱ መበላለጥ ወይም እኩል መሆን ከ4ቱ ወቅቶች መፈራረቅ የተነሳ እንደሆነ የገለው ነው፡፡ይህም በዚህ ሐሳበ ዘመን እንዲህ ታውቆና ተገልጾ፣ ለሺዎች ዘመናት ሲኖር የቆየው ሳይንስም ባለፉት ጥቂት መቶ ዓመት ዕድሜው ውስጥ ይህንኑ አረጋግጦ እያስረዳው ይገኛል፡፡
ይህን የወቅት መፈራረቂያ ጊዜም የሚያስለዩ ናቸውና ሌሊቱና መዓልቱ ለየብቻ መለየትና መቆጠር አለባቸው፡፡
እንደገና በየዕለቱ የዕለቱና የመዓልቱ ጊዜ ተደምሮ፣ 24 ሰዓት እንደሆነ መገለና መያዙ ..የጐደለውን ሞልቶ፤ የተረፈውን ትቶ.. ተብሎ በሚገለጽ የአቆጣጠር ዘዴ ሙሉ ሙሉ ሰዓት የሆነውን በመቁጠር እንጂ፣ ሽርፍራፊ ደቂቃን ጊዜያት መኖራቸው ተስቶ አይደለም፡፡ እነዚህ ሽርፍራፊዎች ተደማምረው ሙሉ ሰዓት፣ ከዚያ ሙሉ መዓልትና ሙሉ ሌሊት የሆኑ ጊዜ እሚቆጠሩ ሆነው፣ ለጊዜው YgdÍlù””
እነዚህ ተራፊ ጊዜያት ናቸው ..ጳጉሜን.. የሚባሉት፡፡ በያንዳንዱ ዕለት ምን ያህል ..ተራፊ.. ወይም ጳጉሜን ጊዜ እንዳለ ማወቅ የሚቻለውም፣ ይልቁንም ያለ ተራፊ ጊዜ ከመዓልቱ ይሁን ከሌሊቱ ሊለይ የሚችለው እያንዳንዱን እንዲህ ለየብቻ እስከ 12 ድረስ መድበው የቆጠሯቸው እንደሆነ ነው፡፡
ሌሊቱና መዓልቱ እኩል 12 ሰዓት በሚሆኑበት ጊዜ ሊታወቅ የሚችል ትርፍ ጊዜ፣ ወይም የአንድ ዕለት የጳጉሜን ጊዜ መጠንም በዚህ የዘመን መቁጠሪያ የታወቀ፣ የተሰፈረ፣ የተቆጠረም ነው፡፡|ፀሐይÂ ጨረቃ እኩል 12 - 12 ሰዓታት በመገቡበት ዕለት ፀሐይ 1 ከኬሮስ ከ52 ካልዒት k36 ሣልሲት ትርፍ ጊዜ ¬b‰lC””´ይህ በማንኛው ረገድ ከ12 ሰዓት በላይ ሆኖ እንደተገኘ ለመገንዘብ የተቻለው እንዲያ ሰዓታተ መዓልትና ሌሊት በ12 - 12 ተወስነው በመቆጠራቸው ነው፡፡
(እዚህ ላይ በየዕለቱ የሚተርፈውን የጳጉሜን ጊዜ በኬክሮስ እና የርሱ ደቂቃን በሆኑት ካልዒትና ሣልስት የተባሉ መስፈሪያ መቁጠሪያዎች መቀመጡን ልብ ይሏል፡፡ ከመዓልቱም ከሌሊቱም ያልሆነ፣ ..ያልተከፈለ.. የአንድ ጊዜ ርዝመት (Indefinite length of time) በመሆኑ ነው በኬክሮስ መቆጠሩ፡፡ እንደ ሐሳበ ዘመኑ ቢሆን፣ እንደዚህ ያሉት በጭራሽ በሰዓት አይቆጠሩም አይለዩም፡፡ ሰዓት ወይ የሌሊቱን አሊያም የመዓልቱ 12ቱ ጊዜዎችን ብቻ በቁጥር ለይቶ መቁጠሪያ ነው ተብሎ የተደነገገ ነውና፡፡ በሌሊትና በመዓልት የተከፈሉትን የእያንዳንዱን 12ት ሰዓታትን 1፣2፣3፣. . . እያሉ እስከ 12 ድረስ የቁጥር መለያ እየሰጡ ለመለየት ብቻ የተሠራ ነው - እንደ ሐሳበ ዘመን፡፡
ደቂቃን አሐዶችን ወደፊት ስንመለከት ኬክሮስና የደቂቃኑን ምን ያህል እንደሆኑ፣ ይህን ያንድ ዕለት የጳጉሜን ጊዜም እንዴት ሆኖ ተንከባልሎ የጳጉሜን ዕለታትን እንደሚያልገኝ ካልዒት፣ ሣልስት. . . የተባሉትን ደቂቃን ጊዜያት ምን ያህል እንደሆኑ ሲገለ ስለምንረዳ አሁን ሰዓታተ መዓልትና ሰዓተ ሌሊት ለየብቻ k ድረስ የመቆጠራቸውን ነገር ማጤን የጀመርነውን ይዘን XNq_ል””ሌሊት እና መዓልት ለየብቻ ይለዩ ዘንድ ሥርዓቱ በተገለበት ላይ፣ በተለይ የጽልመቱን ጊዜ፣ |ቀጠሮን ያደርጉበታልና ሌሊት ብለው «„T´ የሚል አብነት አለ፡፡እዚህ ላይ እንዲያ በስም ተለይቶ ሌሊት መባሉ ብቻ ከተናፃሪው መዓልት የተለየ የዕለት ክፍለ ጊዜ መሆኑን ለብቻ በሰዓታተ ሌሊት በሚቆጠር ክፍለ ዘመን መለየት እንዳለበት፣ በዚያ ..ቀጠሮን ይይዙበታልና.. ብሎ ለይቶ ይናገረዋል፡፡ ..ጊዜ ቀጠሮ.. ማለት ..ወሰነ ጊዜ.. እንደሆነ ደግሞ አስቀድሞ ስለ ዘመን አገላለጥ (ፍቺ) በቀረበበት የተጠቆመ ነው፡፡ ወሰነ ጊዜ ማለትም ዘመን ማለት እንደሆነም አውቀናልና ያን ጊዜም በሰዓታት ይለዩት ዘንድ ተሠራ፡፡ በእርግጥም ሌቱን የቀጠሮ ጊዜ ወይም ..ቀጠሮ ያደርጉበታልና´ መባሉን፤ ይኽ ሐሳበ ዘመን ከወጣበትና ከተሠራበት ቤተ ሃይማኖት በጉልህ የታወቁ የልደት፣ የጥምቀትና የትንሳኤ ሥራዎች የተፈሙት በሌሊት እንደሆነ ከመገለም በላይ፣ ዳግመኛ የሚመጣበትም በየትኛይቱ ሌሊት እንደሆነ ባይታወቅም ከሌሊቶች ባንዱ እንደሆነ ከመጻሕፍቱም ጠቅሰው የሚተነትኑት ሆኖ ይገኛል፡፡ዳግመኛ ከሥነ ፍጥረት ጀምሮ ሌትና መዓልቱ እንዲያ፡- ቀዳማይ ሰዓተ ሌሊት፣ ቀዳማይ ሰዓተ መዓልት፣ ሁለተኛው ሌሊት ሰዓተ መዓልት. . . እየተባለ እስከ 12ኛ ሰዓተ ሌሊትና እስከ 12ኛ ሰዓተ መዓልት እየተቆጠረ ሲገለጽ ይገኛል፡፡ ከዚህ በኋላ ስለ ሠለስቱ ብርሃናት ወይም ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት የመፈጠር ምክንያት ሲገለጽ፡- ..ትልቁ ብርሃን በመዓልት፣ ትንሹ (ጨረቃ) በሌሊት ይሰለጥኑ ዘንድ፣.. ተብሎ ተለይቶ የተገለው ቃልም ግድ የሚለው ነው፡፡ስለሆነም ያንድ ዕለት ሌሊት እና መዓልት ለየብቻ እስከ 12ኛ ተቁ ድረስ በሚቆጠሩ ሰዓታት ሌሊትና ሰዓታት መዓልት ተለይተው የሚቆጠሩ መሆኑ ይህ በኢትዮጵያ የሚታወቀው ሐሳበ ዘመን ያስተምራል፡፡
ይህም ማለት ከ1-24 ድረስ (እንደ ዩቲሲ) መቁጠር፣ ወይም ..አንቲ ሜሪድያን.. እና ..ፕሪ ሜሪዲያን.. ወይም ..ኤኤሞ.. እና ..ፒኤም.. በሚባሉት ሁሉ በዚህ ሐሳበ ዘመን ፈጽሞ የማይቻሉ ሆነው ይገኛል፡፡kተፈጥሯዊW ክስተት አንጻርም ሲታይ ይህ የሐሳበ ዘመኑ ሥርዓት ምን ያህል ልክ እንደሆነ ብቻ ሳይሆን፣ ከትናንሾቹ ክፍለ ዘመን (የጊዜ ክፍል) ጀምሮ የጊዜ ቆጠራው ጉዳይ ልዩ ጥንቃቄና ትኩረት እንደተሰጠው ጭምር የምናይበት ነው፡፡ሰዓት የተባለው አሐድም የመዓልት እና የሌሊት የተባሉ 12 እኩል የሆኑ የብርሃን ጊዜን እና እንዲሁ እኩል የሆኑ 12 የሌሊት ጊዜያትን በቅደም ተከተል 1፣2፣3... በሚሉ መለያ ቁጥሮች እንዲለዩ ብቻ የተሠራ ሆኖ ይገኛል፡፡ (አቴኖጎባር በተባለ ድረ ገጽ ‘The only intelligent calendar’ ተብሎ መገኘቱ እንዲህ ያለውን ጥንቃቄውን ሁሉ የሚያነሳ ነው፡፡)ይህ ደንብ በእጅና በሌሎች ሰዓቶች በ12 ቢሶል ብቻ ተከፍለው ከድሮ ጀምሮ መሠራት ከጀመሩበት ጋር ሲታሰብ፣ ቀድሞ በሌሎችም ዘንድ ይኼው ሥርዓት የነበረበት ጊዜ እንደነበረ አያመለክተንስ ይሆን?በጣም የሚያስገርም ጥቆማ፣ በተለይም ፒ.ኤም እና ኤ.ኤም የሚባለውን አቆጣጠር አስመልክቶ፣ ከጥቂት ዓመታት በፊት በኢሲኤ አዳራሽ በተዘጋጀ አንድ ዓውደ ጥናት ላይ ..በዚያ መቁጠር ጊዜውን በጥንቃቄ የማስለየት ችግር መፍጠሩ ብቻ ሳይሆን መሠረታዊ የሆነ የሃይማኖት ኑፋቄነት እንዳለበትም.. ጭምር ተገልጾም ነበር፡፡ሰዓት እንዲያ በሌትና በመዓልት የተከፈለ የያንዳንዱን 12 እኩል ጊዜያት በቁጥር ስያሜ ለይቶ መጥሪያ፣ መቁጠሪያ የሆነ፣ የታወቀ (definite) ዘመን መቁጠሪያ እንደሆነው፤ ሌላውን ደግሞ ዛሬ ብዙም ሲያገለግል የማይገኘው አምስተኛውና ከመሠረታውያኑ አሐዶች የመጨረሻው ትንሹ ክፍለ ዘመን የሆነው ..ኬክሮስ.. የተባለው አሐድ ሆኖ ሊያገለግል ተመድቧል፡፡ ከርሱ ያነሱትን ደግሞ መሠረታዊያን ያልሆኑ ክፍልፋይ አሐዶች፣ ደቂቃን የተባለ እስከ 10-3 ማይክሮሰኮንድ ድረስ የደቀቁ ጊዜያትን የቆጠሩባቸው አሐዶችም አሉ፡፡ለዛሬ ግን በዚሁ ይብቃን፡፡ መልካም አዲስ ዓመት!!

 

Read 5226 times Last modified on Saturday, 17 September 2011 10:21