Saturday, 17 September 2011 10:14

በመርካቶ የታየውን ክፍተትአለማየት

Written by  ብርሃኑ ሰሙ
Rate this item
(0 votes)

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በአገራችን የሚገኙት     ዕውቅ ዩኒቨርስቲዎች፣ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው አውሮፕላን ማረፊያዎች፣ አውቶቢስ መናኸሪያዎች፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድቦች፣ ቴአትርና ሲኒማ ቤቶች... በጣት የሚቆጠሩ ነበሩ፡፡ የሚበዙት ደግሞ በመንግሥት ይዞታነት ነበር የሚታወቁት፡፡ እንዲህ አይነት እጥረት የሚታይባቸውን መስኮች ለማስፋፋት በመንግሥት እየተሰሩ ካሉት ውጭ በግል ባለሀብቶች ተሰርተው ተስፋ ሰጪ ነገር እየታየ ካለባቸው የአገልግሎት ዘርፎች አንዱ የግል ሲኒማ ቤቶች ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱ ነው፡፡

ለምሳሌ በአዲስ አበባ ከተማ ከለገሀር ፒያሳ፣ ከጊዮርጊስ እስከ መርካቶ ባለው ቅያስ ብቻ ይገኙ የነበሩት የቴአትርና ሲኒማ ቤቶችን ቁጥር ከፍ ያደረጉና በተለይ ለፊልም ማሳያነት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት በቦሌ፣ በጐተራ፣ በእንቁላል ፋብሪካ... ተገንብተዋል፡፡ በቀጣይነትም ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ቁጥር እንደሚጨምር ተስፋ ሰጪ ምልክቶች ቢኖሩም ክፍተቱን ተረድተው ፈጣን ምላሽ ለመስጠት መትጋት እያለባቸው የተዘናጉ መስለው ከሚታዩ የአዲስ አበባ ከተማ ሰፈሮች አንዷ መርካቶ መሆኗ እየታየ ነው፡፡
የአፄ ኃይለሥላሴ የፖለቲካ ተቀናቃኝ ነበሩ በሚባሉት በራስ ኃይሉ ተ/ኃይማኖት መሥራችነት በ1930 ዓ.ም ሲኒማ ማሳየት የጀመረው የመርካቶ ሲኒማ ራስ ቴአትር ቤት ፈርሶ በአዲስ መልክ ሊገነባ መሆኑ ተገልጿል፡፡ አሁን የሚፈርሰው ቤት በጣሊያን ዘመን የተገነባ ነው፡፡ ጠላት እስከተባረረበት ጊዜ ድረስም ፊልም በማሳየት ቆይቷል፡፡ የራስ ቴአትር የ30 አመት ጉዞ ልዩ እትም (ከሐምሌ 1971 - ሐምሌ 2000 ዓ.ም) መጽሔት የራስ ቴአትር ታሪካዊ ሂደት ምን እንደሚመስል ሲገል፤
.....በ1930 ዓ.ም በራስ ሀይሉ ተ/ሀይማኖት ስም ተሰይሞ ሲኒማ ራስ የተሰኘው ቤት የህንፃ ግንባታው የተጠናቀቀው በ1929 መሆኑ ይታወቃል፡፡ የተለያዩ ፊልሞችን ማሳየት ጀምሮ ነበር...፡፡..
|b1933 ›.M ፋሽስቱ የኢጣሊያ መንግስት ከመላው አገር ከወጣ በኋላ ሲኒማ ቤቱ ጥቂት ሲሰራ ቢቆይም የኋላ ኋላ አገልግሎቱን በማቋረጥ፣ ከ1948 ዓ.ም ጀምሮ በግሪካዊው አስመጪና ላኪ ሚስተር ጆርጅ ሜሪ ሊያስ ባለቤትነት የቡናና የቦሎቄ ማበጠሪያ ወፍጮ ቤትም ሆኖ ሲሰራ ቆይቶ፣ በ1950 ዓ.ም ደግሞ የመዘጋት እጣ ገጥሞታል፡፡..
..በ1952 ዓ.ም አርመናዊ ዜግነት ያላቸው ሰው የሲኒማውን ስራ ሲያስቀጥሉት ቆይተው በ1955 ዓ.ም ደግሞ የመዘጋት እጣው ተደገመ፡፡ ድፍን ሦስት ዓመታት ደግሞ ለቢሊያርድ ማጫወቻነት፣ ለመጋዘንነት፣ ለሌላም አገልግሎት ሲውል ቆይቶ በ1958 ዓ.ም በሮበርት ጄሪያን (አርመናዊ) እጅ ገብቶ ..እስከ 1968 ዓ.ም የሲኒማ ቤትነቱን ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡..
|b1968 ›.ም የከተማ ትርፍ ቦታና ቤቶችን ለመንግስት ባደረገው አዋጅ ሲኒማ ቤቱ በባህልና ስፖርት ጉዳይ ሚኒስቴር ስር ሆነ፡፡ በወቅቱ ቴአትርና ሙዚቃ እንዲታይበትና የሀገሪቱም የኪነ ጥበብ እድገት ከፍ እንዲል እንደ አንድ ርምጃ በመቆጠሩ፤ የምንጊዜውም የራስ ቴአትር ራስ በሆኑት ተስፋዬ ለማ በባህል ሙዚቃ የሰለጠነ ቡድን፣ በቴአትር ዘርፍ ደግሞ በአምባሳደር ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ስልጠናውን ባጠናቀቀው ቡድን ራስ ቴአትር በ1971 ዓ.ም የቴአትር ሥራ በቴአትር ቤቱ ጀመረ፡፡..
ባለፉት 73 ዓመታት ከሲኒማና ቴአትር ጋር በተያያዘ ሦስት የተለያዩ ታሪኮች የነበሩት የመርካቶ ሲኒማ ራስ አዳራሽ፤ ለአገሪቱ ጥበብና ጥበበኞች ማደግ የራሱን አስተዋኦ ቢያበረክትም የቴአትር ቤቱ አዳራሽ ለአርቲስቶቹም ሆነ ለተገልጋዩ ምቹ ሳይሆን ሰባት አስርት ዓመታት አስቆጥሯል፡፡
የሲኒማ ራስ አርቲስቶች የገጠማቸውን ችግር ለመቅረፍ እንዲያስችል አሁን እስክስታ አዳራሽ በመባል የሚጠራውና ፒያሳ ሲኒማ ኢምፓየር አጠገብ ይገኝ የነበረው ስቴሪዮ ክለብ በ1974 ዓ.ም ተሰጥቷቸዋል፡፡ በ1956 ዓ.ም የተቋቋመው ሲኒማ አዲስ ከተማም በሲኒማ ራስ ስር እንዲተዳደር ተደርጓል፡፡ መርካቶ ውስጥ ሁለተኛው ሲኒማ ቤት ሆኖ በመቋቋሙ ይታወቅ የነበረው ሲኒማ አዲስ ከተማ ለፊልምም ሆነ ለቴአትር ምቹ ባለመሆኑ ለባለሀብቶች በኪራይ ተሰጥቶ፣ የፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ማሳያ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ለጥበብ ሥራና ለአርቲስቶቹ ብቻ ሳይሆን ለተመልካቹም ምቹ ያልነበረው ራስ ቴአትር ቤትን በአዲስና ዘመናዊ መልኩ ለመገንባት የታሰበው እውን ሊሆን የስንብት ፕሮግራም በነሐሴ ወር 2003 ዓ.ም ተከናውኗል፡፡ አዲሱ ሕንፃ ተገንብቶ እስኪያልቅም የቴአትር ቤቱ ባለሙያዎች ሥራዎቻቸውን ፒያሳ በሚገኘው እስክስታ አዳራሽ ማቅረባቸውን እንደሚቀጥሉ xúWqêL””yራስ ቴአትር ዘመናዊ ሕንፃ በተያዘለት ጊዜ ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ መርካቶ ውስጥ ከሚታዩ ክፍተቶች አንዱ የሲኒማ ቤት አለመኖር ነው፡፡ የሲኒማ ማሳያ አዳራሾች ባልነበሩባቸው ቦሌ መድሐኒዓለም፣ ጐተራ፣ ቦሌ ሚሌኒየም አዳራሽ፣ እንቁላል ፋብሪካ፣ ካዛንቺስ... አካባቢዎች አለም፣ ኤድናሞል፣ እምቢልታ፣ ዮፍታሄ... ሲኒማ ቤቶች ተከፍተው በቀጣይነት መስራት መቻላቸው እየታየ መርካቶን በመሰለ ታላቅ የንግድ ቦታ፣ ሲኒማ ራስ ለእድሳት ከመዘጋቱ በፊት በግሉ ዘርፍ የተከፈተ ወይም የተቋቋመ ሲኒማ ቤት አለመኖሩ ምነው ጃል አያስብልም?

 

Read 3003 times Last modified on Saturday, 17 September 2011 10:17