Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 September 2011 09:58

የቢዮንሴ እርግዝና የወርቃማ ዘመኗ መጨረሻ ተባለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሰሞኑን 30ኛ ዓመት የልደት በዓሏን ያከበረችው የቢዮንሴ እርግዝና ይፋ ከሆነ በኋላ ከቢላደን ግድያ ወሬ የላቀ ትኩረት ማግኘቱን የተለያዩ ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ በሙዚቃ፤ በአልባሳት፤ በሽቶና በቮድካ መጠጥ ንግዶች በከፍተኛ ገቢ እየተተኮሰች ያለችው ቢዮንሴ፤ የ5 ወራት ንስ መያዟ በይፋ ከታወቀ በኋላ አንዳንድ ዘገባዎች የፖፕ ንግስቷ ወርቃማ ዘመን የመጨረሻ ምእራፍ ሲሉ g””ቢዮንሴ ማርገዟን ይፋ ያደረገችው ከ2 ሳምንት በፊት በተደረገው የኤምቲቪ የሙዚቃ ቪድዮ አዋርድ ላይ ነበር፡፡

በትዊተር ድረገ ጉዳዩን በተመለከተ በሰኮንድ 8860 መልእክቶች በዓለም ዙርያ መሰራጨታቸው በቢንላደን ግድያ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ሰብሮታል፡፡ ቢዮንሴ እድሜዬ 30 ሲሞላ ልጅ እወልዳለሁ ብላ በተደጋጋሚ መናገሯን የምስራቹን በገለፀችበት ወቅት ያሳወቀች ሲሆን የመጀመርያ ልጇን ያረገዘችው ከ3 ዓመታት በፊት በምስጢር ጋብቻ ከፈፀመችው ከ41 ዓመቱ ራፐር ጄይዚ መሆኑ እጅግ አስደስቷታል፡፡ ጄይ ዚ ዘንድሮ ለቢዮንሴ ያለውን ፍቅር ለመግለ በ27 ሚሊዮን ዶላር በትሮፒካል ደሴት መሬት ገዝቶላታል ያለው ዴይሊ ሜል፤ ራፐሩ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ገቢው በቢሊዮን ዶላር የሚሰላ ሊሆን እንደሚችል ገልፆ ከዚህ ጋር በተያያዘም አዲሱ ልጇቸውን ..የቢሊዮን ዶላር ህፃን.. አስብሎታል ሲል ዘግቧል፡፡ በአሜሪካ የመዝናኛ ኢንዱስትሪ በዓመታዊ ገቢያቸው ከፍተኛነት የመጀመርያውን ደረጃ የያዙት ቢዮንሴና ጄይዚ ዘንድሮ በድምሩ 72 ሚሊዮን ዶላር አግኝተዋል፡፡

 

Read 3419 times Last modified on Saturday, 17 September 2011 10:00