Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 September 2011 09:44

ሕፃናትን በነፃ የሚያስተምር ሙአለ ሕፃናት ተከፈተ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ የወጣበትና ደረጃውን የጠበቀ የተባለለት ሙአለ ሕፃናት በምዕራብ ሸዋ ጊንጪ ከተማ ተከፈተ፡፡ “World Together Ethiopia” በተባለ የደቡብ ኮርያ በጐ አድራጊ ድርጅት በሁለት ሚሊየን አንድ መቶ ዘጠና ብር ወጪ የተቋቋመው ሙአለ ሕፃናት በአንድ ጊዜ ዘጠና ሕፃናት ተቀብሎ ያስተናግዳል፡፡

የኮርያ ዘማች ኢትዮጵያውያን ጀግኖችን በመዘከር የተቋቋመውና ..ሎቲ ድሪም ሴንተር.. በመባል የሚታወቀው ትምህርት ቤት ከትናንት ወዲያ ተከፍቶ ሥራ ጀምሯል፡፡ የማዕከሉ የሙዚቃ አስተባባሪ ወይዘሪት ማእዶት ጌታሁን ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት በነፃ የሚያስተምረው ትምህርት ቤት ለወላጆች ልጅ አስተዳደግ ላይ የሥነ አእምሮ ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን ለሕፃናቱ የትምህርት ቤት ልብስ፣ ጫማና የትምህርት መሣርያ በተመሳሳይ መልኩ እንደሚያቀርብና ለቁርስ ማዘጋጃ በወር ለአንድ ሕፃን ሃያ ብር ብቻ ያስከፍላሉ፡፡ በ180 የግንባታ ቀናት የተጠናቀቀው ሙአለ ሕፃናት ሲመረቅ ልጆች የመዝሙር ድግስ ያቀረቡ ሲሆን በ2004 ዓመተ ምህረት ለመማር የተመዘገቡ ሕፃናት በተወካዮቻቸው ..እዚህ አጥንቼ ትልቅ ሰው ለመሆንና መምህሬን ለማክበር፣ ሥርዓት ለመጠበቅ ቃል እገባለሁ.. ብለዋል፡፡ በሌላም በኩል አዲስ አበባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ13ኛ ጊዜ በቀንና ማታ መርሐግብሮች ያሰለጠናቸውን 265 የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች ዛሬ ጧት 2፡30 በአዲስ አበባ የስብሰባ ማዕከል ያስመርቃል፡፡ ተመራቂዎቹ በአውቶሞቲቭ ኤንጅን ሰርቪስ ሜካኒክስ፣ ኮንክሪት ዎርክ፣ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂና በሌሎችም ዘርፎች የተማሩ ናቸው፡፡

 

Read 4680 times Last modified on Saturday, 17 September 2011 09:47