Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 September 2011 09:40

ዛጐል ቤተመፃህፍት የልጆች ሥነ ሁፋዊ ዝግጅት ጀመረ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ፈረንሳይ ለጋስዮን በተለምዶ ብረት ድልድይ በሚባለው አካባቢ የሚገኘው ዛጐል ቤተመፃህፍት አዲስ ወርሃዊ የልጆች ሥነ ሁፋዊ ዝግጅት ጀመረ፡፡ የድርጅቱ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት ሥነ ሁፋዊ ዝግጅቱ በሌሎች ዘርፍ የሚገኙ ባለሙያዎች ለልጆች በሚሆን መልኩ በየወሩ ልምድ የሚያካፍሉበት ሲሆን ልጆች ዘወትር እሁድ በቤተ መፃህፍቱ በነፃ ያነባሉ፡፡

የነገው  ዝግጅት በተመሳሳይ ስፍራ ከጧቱ 3፡30 ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን የክብር እንግዳዋም በ12 ዓመቷ የግጥም መሐፍ ለንባብ ያበቃችው ታዳጊ ማህሌት አፈወርቅ እንደሆነች ማወቅ ተችሏል፡፡
የልጆች ግጥሞች እና ትርዒቶች በሚያቀርቡበት ዝግጅት አርቲስት አንዱዓለም አባተ አዝናኝ ትረካ፣ ደራሲ ውዳላት ገዳሙ ብድሯን ያልከፈለች ወፍ ከተሰኘ መሐፏ ትረካ እንዲሁም ኢንጂነር ነፃነት ጆቴ yኢንጂነርnT ልምዷን ኢንጂነር ለመሆን ለሚፈልጉ ልጆች ገለፃ ያቀርባሉ፡፡

 

Read 3412 times Last modified on Saturday, 17 September 2011 09:42