Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 15 December 2012 15:40

ሐረር ሬዲዮ ተዘጋ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በ1957 ዓ.ም በማቀባበያ ጣቢያነት ተቋቁሞ ላለፉት 48 ዓመታት ለምስራቅ ኢትዮጵያና ለአካባቢው ሀገሮች አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ሐረር ሬዲዮ ተዘጋ፡፡ ካለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ የጣቢያው ስርጭት እንደተቋረጠ ታውቋል፡፡ በአሁኑ የኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቭዢን ድርጅት (ኢሬቴድ) በያኔው የኢትዮጵያ ሬዲዮ በማቀባበያ ጣቢያነት የተቋቋመው ሐረር ሬዲዮ፤

በ1965 ዓ.ም ስቱዲዮ በመገንባት የኦሮሚኛ ስርጭት የጀመረ ሲሆን በ1971 የሶማሊኛ፣ በ1985 ደግሞ የሐረሪ ቋንቋዎች ሥርጭት ጀምሮ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ አገልግሎቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ መምጣቱን የጠቆሙት አድማጮች፤ ጣቢያው ተደማጭ ዝግጅቶች ቢኖሩትም ኢሬቴዲ በቂ ድጋፍ ባለማድረጉ ለሕዝብ ጆሮ መድረስ እያቃተው ነው ሲሉ ባለፈው ሐምሌ በስፍራው ለነበረ የአዲስ አድማስ ዘጋቢ ነግረውት ነበር፡፡

Read 4434 times