Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 08 December 2012 14:17

ሊንድሴይ ሎሃን መበጥበጧን ቀጥላለች

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

የፊልም ባለሙያዋ ሊንድሴይ ሎሃን በዓል ባህርይዋ ሳቢያ ህይወቷ ሊቃወስ እንደሚችል ተገለፀ፡፡ የፊልም ተዋናይዋ በየቀኑ ሁለት ሊትር ቮድካ በመጠጣት መረን ለቃለች ያለው ቲኤምዜድ፤ ድረገፅ ወደ አዕምሮ ህክምና ተቋም መግባት እንደሚያስፈልጋት ገልጿል፡፡ ባለፈው ሳምንት በኒውዮርክ በሚገኝ የምሽት ክለብ ሰው ደብድባለች ተብላ በቁጥጥር ስር የዋለችው ሊንድሴይ፤ በዋስ ከተፈታች ከ24 ሰዓታት በኋላ በሌላ ክለብ ውስጥ እንደእብድ ሲያደርጋት እና አላግባብ ስትበጠብጥ መታየቷ ጉድ እንዳስባለ ተዘግቧል፡፡ በምሽት ክለብ ሰው በመደብደብ ክስ ቀርቦበት በአዲሱ የፈረንጅ ዓመት መግቢያ ፍርድ ቤት የምትቀርበው ሊንድሴይ ሎሃን፤ ዳኛዋ ከማንኛውም ሊያስከስስ የሚችል ብጥበጣ እንድትቆጠብ የጣሉትን ገደብ ጥሳለች፡፡

ባለፈው አመት ስታሽከረክር በነበረችው መኪና አደጋ አድርሳ ጥፋቷን በመካዷ በፍርድ ቤት ከማናቸውም ስርዓት አልበኝነት እንድትቆጠብ ማእቀብ ተደርጎባት የነበረችው ተዋናይቷ፤ ሰሞኑን ይህን ማዕቀብ ስትጥስ በመሰንበቷ ቢያንስ ለ245 ቀናት እስር ቤት እንድትገባ ሊፈረድባት ይችላል ተብሏል፡፡ በሌላ በኩል በፍቺ የተለያዩት ወላጆቿ በሊንድሴይ ሎሃን ዙርያ ከፍተኛ እሰጥ አገባ ውስጥ መግባታቸው እየተገለፀ ነው፡፡ አባቷ ማይክል ሎሃን በአሜሪካ የ2012 “ምርጥ አባት” ተብሎ የተመረጠ ሲሆን እናትዬው ግን የቀድሞ ባሏ በልጃቸው የተወሳሰበ ህይወት እና ቀውስ አላስፈላጊ የሚዲያ ሽፋን ለማግኘት የሚስገበገብ ነው ተብሎ ተወግዟል፡፡ ማይክል ሎሃን የልጁን የእለት ተእለት ተግባራት በመከታተል እና መረጃዎችን ለሚዲያዎች በማቀበል አተኩሮ እየሰራ ሲሆን ካለችበት የአዕምሮ ቀውስ እንድትላቀቅ ልዩ የስነልቦና ህክምና ያስፈልጋታል በሚል ድምፁን እያሰማ ይገኛል፡፡ በግል ባህርያዋ አወዛጋቢነት በርካታ የፊልም ስራዎች እያመለጧት ያለችው የ26 አመታ ሊንድሴይ ሎሃን፤ ሃብቷ ከ300ሺ ዶላር እንደማይበልጥና ዘንድሮ ገቢዋ 2 ሚሊዮን ዶላር ብቻ እንደሆነ ታውቋል፡፡ አርቲስቷ በቅርብ ጊዜም በገንዘብ ችግርም ህይወቷ መቃወሱ አይቀርም እየተባለ ነው፡፡

Read 5176 times

Latest from