Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 September 2011 12:31

ለ2012 የአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ የሞት ሽረት ይሆናል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በ2012 ኢኳቶርያል ጊኒና ጋቦን ወደ የሚያዘጋጁት የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ሲደረግ በቆየው ዓመት የፈጀ የማጣርያ ውድድር በምድብ 2 ያለችው ኢትዮጵያ በ5ኛው ዙር ወደቀች፡፡ ከወር  በሚደረጉ የመጨረሻ ዙር ግጥሚያዎች ማጣርያው ሲገባደድ በታላላቅ ቡድኖች የሞት ሽረት ትግል ይታይበታል፡፡

ከአዘጋጆቹ ጋቦንና ኢኳቶርያል ጊኒና ጊኒ ሌላ ቦትስዋና፤ ኮትዲቯር፤ ቡርኪናፋሶና ሴኔጋል ማለፋቸውን x በማጣርያው የመጨረሻ ዙር ጨዋታዎች 21 ብሄራዊ ቡድኖች ለቀሩት 10 የማለፍ እድሎች የሚተናነቁ ይሆናል፡፡ ያለፉትን ሶስት የአፍሪካ ዋንጫ ድሎችን አከታትላ ያሸነፈችው ግብ ከማጣርያው መሰናበቷ አስገራሚ ሆኗል፡፡ ታላላቆቹ ናይጄርያ፤ ደቡብ አፍሪካ፤ ካሜሮንና ቱኒዚያ በከፍተኛ ውጥረት የግብ እጣ እንዳይገጥማቸው ይጫወታሉ፡፡
y²Ê ሳምንት yኢትዮጵያ  ብሔራዊ  ቡድን ኮናክሪ ላይ   በጊኒ  1ለ0 ሲሸነፍ  በሌላ ጨዋታ በአናታናናሪቮ ማዳጋስካር በናይጄርያ 2ለ0 ተሸንፋለች፡፡ ከምድብ 2 የመጨረሻው ዙር ጨዋታ በናይጄርያና ጊኒ ትንቅንቅ ብቻ ትኩረት ቢያገኝም እዚህ አዲስ አበባ ላይ ኢትዮጵያ ከማዳጋስካር ለስንብት ይጫወታሉ፡፡
አሰልጣኝ ቶም ሴንትፌይት ወደ ቤልጅየም ለዕረፍት ተጉዘው ከተመለሱ በኋላ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር መሥራታቸውን ሲቀጠሉ ለ3 ወራት የፈረሙበት የኮንትራት ቅጥር እንዲራዘም ፍላጎት ነበራቸው፡፡ በጊኒ ከደረሰው ሽንፈት በሃላ የፌዴሬሽኑ ውሳኔ ምን እንደሚሆን የታወቀ ነገር የለም፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ  በሁለት የውጪ አገር አሰልጣኞች እላለፈው አንድ ዓመት ባደረገው የማጣርያ ተሳትፎ በቂ የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን አለማድረጉ፤ የዝግጅት ትኩረት ስላነሰውና  በሌሎች የአስተዳደር ችግሮች በመበደሉ በውጤታማነቱ ላይ ተዕኖ ፈጥሮበታል፡፡ ከወር በሃላ በመላው አህጉሪቱ የሚደረጉ የ6ኛ ዙር የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ ማጣርያ ግጥሚያዎች የታላላቅ ቡድኖችን የማለፍ ያለማለፍ ሁኔታ የሚወሰኑ ናቸው ፡፡  በምድብ 1 ማሊ መሪነቱን እንደያዘች ላይቤርያን ከሜዳ ውጪ ስትገጥም ካሸነፈች ለማለፍ ብትችልም በሌላ የምድቡ ጨዋታ ከኬፕቨርዴና ዚምባቡዌ የሚያሸንፈውም እኩል የማለፍ እድል ይኖረዋል፡፡ ምድብ 2 ላይ ጊኒ በሶስት ነጥብ ልዩነት መሪነቱን ብትይዝም በመጨረሻው የማጣርያ ግጥሚያ ከናይጄርያ ጋር በአቡጃ የሚያደርጉት ፍልሚያ አላፊውን ይወስናል፡፡ ከምድብ 3 ዛምቢያ መሪ ሆና ለማለፍ ሰፊ እድል ስትይዝ ሞዛምቢክና ሊቢያ በጥሩ ሁለተኛነት የማለፍ እድላቸውን አመቻችተው በመጨረሻ ድል የሚያነጣጥሩ ይሆናል፡፡ በምድብ 4 አራቱም ቡድኖች የማለፉን እድል በመጨረሻው ግጥሚያ የሚወስኑ ናቸው፡፡ መሪነቱን በእኩል 8 ነጥብ የተያያዙበት መካከለኛው አፍሪካና ሞሮኮ ቢሆኑም  በ3 ነጥብ ይዘው የሚከተሉት አልጄርያና ታንዛኒያ ተስፋ እንደሰነቁ  ናቸው፡፡ በምድብ አምስት ሴኔጋል ማለፏን ስታረጋግጥ በመውደቅ አጣብቂኝ ውስጥ የነበረችው ካሜሮን በ5ኛው ዙር ካሸነፈች በሃላ በጥሩ ሁለተኛነት የማለፍ እድሏን አስፍታለች፡፡ በምድብ 6 መሪነት ለማለፍ ሰፊ እድል ያላት ደቡብ አፍሪካ ናት፡፡ በምድብ 7 ሱዳንና ጋና በካርቱም በሚያደርጉት የመጨረሻ የማጣርያ ፍልሚያ አላፊነታቸውን ይወስናሉ፡፡ በምድብ 9 ኡጋንዳ ከ34 ዓመታት በሃላ ለአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ለመብቃት በመጨረሻ ጨዋታዋ ኬንያን በማስተናገድ 1 ነጥብ የሚያስፈልጋት ሲሆን አንጎላ ወደ ጊኒ ቢሳዎ ተጉዛ የምታስመዘግበው ስኬት በተፎካካሪነት  ያደርጋታል፡፡

 

Read 3265 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 12:33