Saturday, 10 September 2011 12:27

የእንግሊዝ ክለቦች በገቢናበወጪተጠናከረዋል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(5 votes)

የእንግሊዝ ክለቦች በክረምቱ የዝውውር ገበያ ከ777 ሚሊዮን ዶላር በላይ በማውጣት ከአውሮፓ ሊጎች የላቀ
ወጪ ማስመዘገባቸው  ሲታወቅ የግብይት mºnù ከባለፈው ዓመት በ33
በመቶ ማደጉን የዴሊዮቴ ጥናት አመለከተ፡፡ ከዚሁ ግብይት በክረምቱየዝውውር ገበያ የመጨረሻ ቀን ከ160
ሚሊዮን ዶላር በላይ የዝውውውር ሂሳብ ወጥቷል፡፡ አርሰናል ቼልሲ፤ ሊቨርፑል፤ ማን ሲቲና ማን ዩናይትድ የዝውውር ወጪያቸው በእያንዳንዳቸው ከ70 ሚሊዮን  ዶላር በላይ የተመዘገበ ሲሆን በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ካሉ ክለቦች የገበያ እንቅስቃሴ 66 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ እነዚሁ አምስቱ ክለቦች ወስደውታል፡፡

በአምስቱ የአውሮ ታላላቅ ሊጎች በክረምቱ የዝውውር ገበያ በድምሩ 2.64 ቢሊዮን ዶላር ወጥቷል፡፡ በሌሎች የአውሮፓ ሊጎች በዝውውር ገበያው በጣሊያን 640 ሚሊዮን ዶላር፤ በስፔን 480 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም በፈረንሳይ 264 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ሆኖ ከባለፈው ዓመት ብልጫ ያሳዩ ግዢዎች በየሊጎቹ ተፈመዋል፡፡
የዝውውር መስኮቱ በ3 ወራት ጊዜ ውስጥ የተከናወነ ቢሆንም ዋና ዋናዎቹ ዝውውሮች የተፈፀሙት በመጨረሻው ቀን ነው፡፡ በመላው ዓለም ፊፋ በሚያውቀው በዚህ የዝውውር ጊዜ በተፈፀሙ ግብይቶች ከፍተኛውን ድርሻ የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ይወስዳሉ፡፡
የእንግሊዝ ክለቦች ከፈፀሟቸው ዝውውሮች 75 በመቶ ክፍያዎች የተፈፀሙት ከሌሎች አገራት ለተዘዋወሩ ተጨዋቾች ነው፡፡ በክረምቱ የዝውውር ወቅት 5192 ዝውውሮች በዓለም ዙርያ  መካሄዳቸውና 2043 ክለቦች በግብይቱ መሳተፋቸውን የሚገልፀው የፊፋ ድረገ  መረጃ በገበያው ለአንድ ተጨዋች የወጣው ከፍተኛው ሂሳብ 67.8 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን ዝቅተኛው ደግሞ 45 ዶላር መሆኑን አመልክቷል፡፡
በዝውውር ገበያው ከተከናወኑ ግብይቶች ፋብሪጋዝ ወደ ባርሴሎና፤ አጉዌሮ ወደ ቼልሲ፤ ጃቪዬር ¬ስቴሮ ወደ ፒኤስጂ እንዲሁም ሳሙኤል ኤቶ ወደ አንዚ መዛወራቸው ትኩረት ያገኙ ሲሆን በዝውውራቸው ብዙ ተብሎላቸው በየክለባቸው ተረጋግተው የቆዩት የማን ሲቲው ካርሎስ ቴቬዝ፤ የኢንተርሚላኑ ዌስሊ ሽናይደር፤ የቶትንሃሙ ሉካ ሞድሪች፤ የሪያልማድሪዱ ሪካርዶ ካካ እና የሳንቶሱ ¬BlÖ ኔይማር ናቸው፡፡ በዝውውር ገበያው ከፍተኛውን ግዢ ሰርጂዮ አጉዌሮ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ወደ  ኢስትላንድ ያዛወረው ማን ሲቲ ያስመዘገበ ሲሆን ለአርጀንቲናዊው ዝውውር 67.8 ሚሊዮን ዶላር ወጪ አድርጓል፡፡ ከዝውውሮች ሁሉ በአስገራሚነቱ የሚወሳው የ30 ዓመቱ ካሜሮናዊ ሳሙኤል ኤቶ ኢንተር ሚላንን ለቅቆ ወደራሽያው ክለብ አዚን የተዛወረበት ሁኔታ ሲሆን ግብይቱ 39 ሚሊዮን ዶላር ተከፍሎበታል፡፡ ሲሆን የእግር ኳሱ ዓለም ውዱ ደሞዝተኛ ሆኗል፡፡ ሳሙኤል በሩስያዊ የነዳጅ ነጋዴ ባለቤትነት በተያዘው ክለቡ በሳምንት 400ሺ ዶላር የሚታሰብለት ይሆናል፡፡

 

Read 5517 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 12:30