Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 September 2011 12:23

ሉሲም ሆኑ ባናያና ለኦሎምፒክ 90 ደቂቃ ቀራቸው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በአዲስ አበባ ስታድዬም በሚደርገው
የመልስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካ ይገጠማሉ”” ለሉሲ
በ4 ንፁህ ጎል ማሸነፍ ፤ ለባናያና አቻድልና በ2 ንህ ጎል መሸነፍ የለንደን
ኦሎምፒክ ትኬት የሚቆረጥባቸው እድሎችይሆናሉ ፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ከሳምንት በፊት ስዌቶ በሚገኘው ኦርናልዶ ስታዲየም ተገናኝተው ባናያናዎች  3ለ0 በመርታታቸው የማለፍ እድላቸውን ቢያሰፉም፤ በሜዳቸው የሚጫወቱት ሉሲዎች ተመጣጣኝ ዕጣ ይዘዋል፡፡

የደቡብ አፍሪካው አሰልጣኝ ጆሴፍ ማክሆሃ ኢትዮጵያን በሜዳችን 3ለ0 ማሸነፍ  ስንችል ግብ ስላልተቆጠረብን የማለፍ እድላችንን አስፍቶታል ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ላይ 3 ግቦችን በማስቆጠር ሃትሪክ የሰራችው የባናያና አጥቂ ኖኪ ማቱሊ በመልስ ጨዋታውም ያለንን የማለፍ እድል  ስትል በልበሙልነት ተናግራለች፡፡ ደቡብ አፍሪካን በሴቶች እግር ኳስ በለንደን ኦሎምፒክ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በመወከል ታሪክ የመስራቱ እድል እንደሚያጓጓቸውም ገልፃለች፡፡ ፡፡ ኢትዮጵያውያኖቹ ፈታኝ ግጥሚያ ቢያደርጉም በተከላካይ መስመር ያለባቸው ድክመት bmºqM አሸንፈናቸዋል ያለችው ኖኪ በመልሱ ጨዋታ ማሸነፍን ብቻ እንደምትፈልግ ተናግራለች፡፡ ከ2 ዓመት በፊት የአፍሪካ ሴቶች እግር ኳስ ኮከብ ተጨዋች ሆና በካፍ የተሸለመች ነች፡፡ ቢፕ ቢፕ በሚል ቅል ስሟ የምትታወቀው ኖኪ ማቶሊ ዘንድሮ የደቡብ አፍሪካ ምርጥ የሴት ስፖርተኛ ተብላ የተሸለመች ስትሆን ለባናያና በ61 ጨዋታዎች 51 ጎሎችን አስመዝግባለች፡፡  በቀጣይ የውድድር ዘመናት ደግሞ በአሜሪካ ወይም በራሽያ በፕሮፌሽናልነት የመስራት ፍላጎት አላት ፡፡
የደቡብ አፍሪካ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በጀርመን ተካሂዶ በነበረው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከጫፍ ደርሰው ነበር፡፡ በኢኳቶርያል ጊኒ ተሸንፈው ወደቁ፡፡ የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃናት ይህ ሽንፈት ኢኳቶርያል ጊኒ ባሰለፈችው ቡድን በርካታ ዜግነት የቀየሩ ተጨዋቾችን በማሰለፍ መገኘቱን ተችተዋል፡፡ ባናያናዎች ወደ ለንደን ኦሎምፒክ ሉሲዎችን በመጣል ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ያልቻሉበትን አጋጣሚ እንደሚያካክሱ tºBÌL””
ባናያናዎች ወደ ኦሎምፒክ ከተሻገሩ ታዋቂው የአገሪቱ የነዳጅ አምራች ኩባንያ በስፖንሰርሺፕ እንደሚደግፋቸው አሳውቋል፡፡ ዋናው የደቡብ አፍሪካ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን እዚህ አዲስ አበባ ላይ ሲጫወት በሞዛምቢክ ደግሞ ሁለተኛው ቡድን በኦልአፍሪካን ጌምስ የጋና አቻውን ይገጥማል፡፡ የ58 ዓመቱ የባናያናዎች አሰልጣኝ ደቡብ አፍሪካ በመልስ ጨዋታው በኢትዮጵያ የምታደርገውን ፍልሚያ በማሰብ እንቅልፍ ማጣታቸውን ኪክኦፍ ለተባለ መሄት ሲገልፁ በጨዋታ ስትራቴጂያቸው በተከላካይ መስመር ytºÂkr አሰላለፍ ይዘው እንደሚገቡ ገልፀዋል፡፡ የደቡብ አፍሪካ ጋዜጦች የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በማጥቃት አጨዋወቱ በተለይ በሜዳው  ቢገልፁም የባናያናዎች የተከላካይ መስመር ብቃቱ የሚያስተማምን በመሆኑ አያሳጋም ብለዋል፡፡

 

Read 3323 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 12:25