በዬል ዩኒቨርስቲ በፖለቲካል ሳይንስ የተመረቀችው መክሊት፤ በ2008 ..ኢይት ሶንግስ.. ከዚያም በ2010 ..ኦን ኤ ዴይ ላይክ ዚስ.. የተባሉ ሁለት አልበሟቿን በፖርቶ ፍራንኪ ሬከርድስ አሳታሚነት ለገበያ አቅርባ በመላው አሜሪካ ከፍተኛ ተደማጭነት ማግኘቷን ዘገባው አትቷል፡፡ ..አርባ ምንጭ ኮሌክቲቭ.. በሚል በባህር ማዶ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶችን በማስተባበር የሚሰራ ተቋም የመሠረተችው መክሊት ሀደሮ፤ ዘመናዊና ባህላዊ ሙዚቃን አጣምሮ በመሥራት በመላው ዓለም የኢትዮጵያ ዘፈኖች ገበያ የሚያገኙበትን ሁኔታ እያመቻቸች መሆኑ ታውቋል፡፡