Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 03 September 2011 12:33

ራስ ትያትር እስከ መስከረም 30 ይፈርሳል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ቀድሞ ከነበረበት የእህል መጋዘንነት ወደ ትያትር ቤትነት የተለወጠው ራስ ትያትር ከ32 ዓመት አገልግሎት በኋላ ሥራ ያቆመ ሲሆን በአዲስ መልክ ከመገንባቱ በፊት ማፍረሱ እስከ መስከረም 30 ይጠናቀቃል፡፡ አሮጌው ትያትር ቤት የመጨረሻ ዝግጅቱን ባለፈው እሁድ ያቀረበ ሲሆን ከዚሁ ዝግጅት ከፊሉ ለእንቁጣጣሽ በኢትዮጵያ ሬዲየና  እንደሚቀርብ ባለፈው ሳምንት መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ሐምሌ 29 1971 ዓመተ ምህረት የመንግስቱ ለማን የትርጉም ትያትር በማሳየት ሥራ እንደጀመረ የተገኘው ማስረጃ ይጠቁማል፡፡ በእሁዱ ዝግጅት የመሰናበቻ መግቢያ ንግግር ያደረገው የትያትር ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አርቲስት ኩባራቸው ደነቀ፤ አዲሱን ግንባታ አስመልክቶ ሲናገር ..በርካታ ችግሮች ያሉበት የአዲስ አበባ ካቢኔ ለራስ ትያትር ቅድሚያ መስጠቱ ያስመሠግነዋል.. በማለት 24 ሚሊየን ብር መነሻ በጀት ለአዲሱ ሕንፃ ግንባታ የመደበውን አስተዳደር አመስግኖዋል፡፡

የአስተዳደሩ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሀላፊ የሆኑትና የትያትር ቤቱ መሥራች ባልደረባ አርቲስት ሙሉ ገበየሁ በበኩላቸው ..መሥራቾቹ ትልቅ ቦታ ደርሰዋል፤ ቤቱ ግን እንዳለ ነው.. በማለት የአዲሱን ግንባታ ተገቢነት አስምረውበታል፡፡ እዚያው ተገኝቶ የነበረው ድምፃዊ ንዋይ ደበበ፤ ከእናት ከአባት ቀጥሎ ያሳደገን  ይኼ መድረክ ነው፡፡ ኪም ኤል ሱንግ ጉንጉን አበባ ያደረጉልኝ ራስ ትያትር ለውጤት ስላበቃኝ ነው፡፡..
በቅድመ ጥናት ዲዛይን አዲስ የሚሰራው ትልቁ የራስ ትያትር አዳራሽ 1200 ወንበሮች የሚኖሩት ሲሆን ዲዛይኑ ሲከለስ ቁጥሩ 1500 ሊደርስ እንደሚችል ሥራ አስኪያጁ አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ በተለይ ለአዲስ አድማስ ገልል፡፡ በኩራባቸው ገለፃ መሠረት፤ ሰባት ፎቅ የሚኖረው የወደፊቱ ራስ ትያትር 500 ሰው የሚይዝ ሌላ አዳራሽ እና ሦስት የፓናል አዳራሾች፣ የውዝዋዜና የትያትር፣ ራሳቸውን የቻሉ ዘመናዊ ክፍሎች፣ የሙዚቃና የሥዕል ጋለሪዎች እና የአስተዳደር ሕንፃ ይኖረዋል ብሏል፡፡ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አሮጌውን ቦታ እንዳፀዳ፣ በ3000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ አዲስ ግንባታ ይጀመራል፡፡ ለዚህም ካሳ እየተጠናቀቀ ነው ብሏል ሥራ  አስኪያጁ፡፡ አርቲስቶችና ሌሎች ድጋፍ ሰጪ አካላት እስከዚያ የት ይሆናሉ ብለን ለየጠቅነውም፣ ፒያሳ የሚገኘው ..እስክስታ አዳራሽ.. መድረክ ለትያትር እንዲመች ሆኖ ይዘጋጃል፣ ሌላ ቢሮ እንከራያለን ብሏል፡፡
አዲሱን የራስ ትያትር ኮምፕሌክስ እውን ለማድረግ የሐገር ውስጥ ትያትር ቤቶችን ጎብኝተናል፣ yWãcÜM የደረሱበትን ተረድተናል፣ ለአዲሱ ትውልድ ዘመናዊና የላቀ አገልግሎት እንሰጣለን ብሏል - የራስ ትያትር 14ኛ ሥራ አስኪያጅ አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ፡፡

 

Read 5300 times Last modified on Saturday, 03 September 2011 12:39