Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 20 August 2011 11:24

ቀነኒሳ ክብሩን ሊያስጠብቅ ነው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ10ሺ ሜትር በዓለም ሻምፒዮና በመሳተፍ የያዘውን ክብር ለማስጠበቅ እንደወሰነ ታወቀ፡፡
ከሳምንት b|§ በኮርያዋ ከተማ ዳጉ በሚጀመረው በ13ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከአጭር ርቀት እስከ ማራቶን በሚካሄዱ ውድድሮች የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የነበረውን የበላይነት ለማስጠበቅ ከኬንያ፣ ኤርትራ፣ ኡጋንዳ፣ ከአሜሪካና ከእንግሊዝ አትሌቶች ከባድ ትንቅንቅ ውስጥ ይገባል፡፡

አትሌት ቀነኒሳ በዓለም ሻምፒዮናው ላይ በ10ሺ ሜትር ክብሩን ለማስጠበቅ በመወሰን እንደሚሰለፍ ሰሞኑን የገለፁት ማናጀሩ ጆስ ሄርማንስ ናቸው፡፡ የ29 ዓመቱ ቀነኒሳ ከ2010 መግቢያ አንስቶ በእግሩ ላይ በደረሰበት ጉዳትና በተለያዩ ምክንያቶች ከዓለም አቀፍ ውድደሮች ርቆ ቆይቷል፡፡ ቀነኒሳ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው በሚኖረው ተሳትፎ በ10ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳልያውን መውሰድ ከቻለ በሩጫ ዘመኑ 5ኛው የዓለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳልያ ሆኖ ስለሚመዘገብ በርቀቱ ከፍተኛውን ስኬት ያገኘ አትሌት ሆኖ በክብረወሰን ይሰፍራል፡፡ ላለፉት 8 ዓመታት በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድደሮች በ5ሺና በ10ሺ ትልቁን ውጤት ያስመዘገበው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ10ሺ ሜትር በዓለም አቀፍ ውድድር ላይ ተሸንፎ አያውቅም፡፡
ቀነኒሳ ሁለት የኦሎምፒክ እንዲሁም አራት የዓለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳልያዎችን በ10ሺ ሜትር ያስመዘገበ ሲሆን የርቀቱን ሪከርድ እንደያዘ ነው፡፡

 

Read 4882 times Last modified on Saturday, 20 August 2011 11:34