Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 20 August 2011 11:18

የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች አጀማመር ተቃውሷል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በአውሮፓ የእግር ኳስ ታላላቅ ሊጎች የ2011-12 የውድድር ዘመን አጀማመር ያማረ አልሆነም በእንግሊዝ በህዝባዊ አመጽ፣ በጣሊያንና በስፔን በተጨዋቾች ማህበራት የስራ ማቆም አድማዎች የየሊጐቹን አጀማመር አቃውሰዋል፡፡ 20ኛ ዓመቱን የያዘው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ባለፈው ሳምንት ሲጀመር በመላው አገሪቱ ተቀጣጥሎ የነበረው ህዝባዊ አመ እንዳያውከው ተሰግቶ ነበር፡፡ በእንግሊዝ ባለፈው ሰሞን በተቀሰቀሰው ዓመ መካሄድ የነበረባቸው ሶስት የካርሊንግ ካፕ ግጥሚያዎች ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፏል፡፡

በፕሪሚዬር ሊጉ በለንደን ከተማ ቶትንሃም ከኤቨርተን የሚያደርጉት ግጥሚያም ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ ሃላፊዎች በተለይ በለንደን ከተማ ከሚገኙ ክለቦችና ከእንግሊዝ ሜትሮፖሊቲየን ፖሊስ ጋር ባደረጉት ምክክር የሊጉ ጨዋታዎች በወጣላቸው ፕሮግራም እንዲካሄዱ ተወስኖ የውድድር ዘመኑ ተጀምሯል፡፡ በመላው አገሪቱ ተከስቶ የነበረው ህዝባዊ አመጽ ግን የጨዋታዎችን ፕሮግራም አዛብቷል፡፡ ይህም በቀጣይ ሳምንታት የውድድር ዘመኑን ሊያውክ እንደሚችል ተገምቷል፡፡  በዘንድሮው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሉግ 3 ክለቦች ቼልሲ፣ አስቶንቪላና ፉልሃም በአዳዲስ አሰልጣኞች በመመራት የውድድር ዘመኑን ጀምረዋል፡፡ ኪዊፒአር፣ ኖርዊች ሲቲና ስዊንቪያ ሲቲ ከታችኛው ዲቪዚዮን ሊጉን የተቀላቀሉ ክለቦች ናቸው፡፡
የስፔኑ ፕሪሚዬር ሊጋ በተጨዋቾች ደሞዝ አለመከፈል አድማ ይደረጋል ተብሎ የውድድር ዘመኑ የመጀመሪያ ሁለት ሳምንት ጨዋታዎች ሊስተጓጐሉ እንደሚችሉ ተሰግቷል፡፡ የስፓኒሽ ላሊጋና የሰኮንዴ ዲቪዠን ተጨዋቾች የስራ ማቆም አድማ እንመታለን የሚል አቋም የያዙት ከሳምንት በፊት ነበር፡፡ ከ100 በላይ ተጨዋቾች በማድሪድ ሆቴል ተሰብስበው ባሳለፉት ውሳኔ የሪያል ማድሪድ አምበል ኤከር ካስያስና የባርሴሎናው ካርሎስ ፒዮልም ድጋፍ አድርገዋል፡፡ የተጨዋቾች ማህበሩ በያዘው አቋም ደሞዝ ያልተከፈላቸው ተጨዋቾች በአስቸኳይ ፈንድ ክፍያቸውን ማግኘት አለባቸው ፌዴሬሽኑ ደግሞ ውዝፍ የደሞዝ ክፍያ እስከ 2015 እ.አ.አ. ተጠናቅቆ እንደሚፈም ገልል፡፡ የተጨዋቾች ማህበሩ ባለፈው የውድድር ዘመን በላሊጋውና በሴኮንዴ ዲቪዠን ለሚገኙ ከ200 በላይ ተጨዋቾች 50 ሚሊዮን ዩሮ አለመከፈሉን በማስታወቅ አድማው እንደማይቀር እያሳሰበ ቆይቷል፡፡ የስፔን ክለቦች በተጨዋቾች ዝውውርና የደሞዝ ክፍያ ከገቢያቸው የላቀ ወጪ በማድረግ ይታወቃሉ፡፡ በላሊጋና በሴኮንዴ ዲቪዠን ያሉ 42 ክለቦች በ5.7 ቢሊዮን ዶላር እዳ የተዘፈቁ ናቸው፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን ብቻ የላሊጋ የደሞዝ ክፍያ በ133 ሚሊዮን ዩሮ ጨምሯል፡፡ የስፔኑ ፕሪሚዬር ሊጋ በ2011-12 የውድድር ዘመን ለታሪኩ ለ81ኛ ጊዜ የሚደረግ ነው፡፡ የውድድር ዘመኑን የተቀላቀሉ አዲስ ክለቦች ሪያል ቤቲስ፣ ራዩ ቫልኬ ኖና ግራናዳ ናቸው፡፡ በአዲሱ የላሊጋ የውድድር ዘመን 7 ክለቦች በአዳዲስ አሰልጣኞቻቸው የሚቀርቡ ሲሆን ከእነሱም መካከል አትሌቲኮ ማድሪድ፣ ሪያል ሶሲዬዳድና ሲቪያ ይጠቅሳሉ፡፡
ከሳምንት በኋላ የሚጀመረውና በታሪክ ለ80ኛ ጊዜ የሚካሄደው የጣሊያን ሴሪኤ አጀማመርም መቃወሱ አይቀርም፡፡ የጣልያን እግር ኳስ ተጨዋቾች ከክለቦቻቸው ከሴሪኤ የበላይ ኃላፊዎች ጋር በቅጥር ኮንትራት ዙሪያ በፈጠሩት አለመግባባት አድማ ሊመታበት እንደሚችል ከሳምንት በፊት ተነግሯል፡፡ ይሄው ውዝግብ በሳምንቱ አጋማሽ ላይ የተካረረ ደረጃ ደርሷል፡፡ የካቢኔ ሚኒስትሮች ብልሹ ብለው የወረፏቸውን ተጨዋቾች ከገቢያቸው ሶሊዳሪቲ ቀረጥ መክፈል እንደሚገባቸውና እጥፍም ቢደረግባቸው ተገቢ ብለው በመናገራቸው ነው፡፡ የጣሊያን መንግስት በቅርቡ ይፋ ባደረገው ህግ በሴሪኤ የሚጫወቱ ተጨዋቾች ከዓመታዊ ገቢያቸው 50 ሚሊዮን ዩሮ በሶሊዳሪቲ መልክ እንዲከፍሉ ተደንግጓል፡፡ ተጨዋቾች ይህ እዳ የክለቦች መሆን አለበት የሚል ሙግት በመያዝ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ቢሆንም የጣልያን መንግሥት የተጨዋቾች ድርሻ መሆኑን እየገለ ነው፡፡ በአዲሱ የ2011-12 የውድድር ዘመን ከዝቅተኛ ዲቪዚዮን በማደግ ተሳታፊ የሚሆኑት አትላንታ፣ ሲዬና እና ኖቫራ ሲሆኑ 11 ክለቦች የውድድር ዘመኑን በአዳዲስ አሰልጣኞቻቸው እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል፡፡       
ከተጀመረ 2 ሳምንት ያለፈው የጀርመኑ ቦንደስ ሊጋ ከሌሎች የአውሮፓ ታላቅ ሊጎች አንፃር ሰላማዊ የውድድር ዘመን ተለፍቶበታል፡፡ በታሪኩ ለ49ኛ ጊዜ የሚደረገው ቦንደስሊጋ ውስጥ ዘንድሮ የተቀላቀሉት ሄርታ በርሊን፤ ኦግስበርግና ሞንቼ ግላድባክ ሲሆኑ ባየር ሙኒክና ባየር ሌቨር ኩዘንን ጨምሮ 5 ክለቦች በአዳዲስ አሰልጣኞቻቸው የውድድር ጀምረዋል፡፡

 

Read 4748 times Last modified on Saturday, 20 August 2011 11:21