Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 20 August 2011 11:16

ኢትዮጵያ በዓለም የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ስልጣን አገኘች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የ31 ዓመቷ ኢትዮጵያ ሃብተማርያም ሰሞኑን የሞታውን ሙዚቃ አሳታሚ ም/ፕሬዚዳንትና የዩኒቨርሳል ሙዚቃ አሳታሚ ከፍተኛ የኃላፊነት ሹመቶችን አገኘች፡፡ ኢትዮጵያ በእነዚህ ሹመቶች በዓለም የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ከፍተኛውን ስልጣን ከያዙት ባለሙያዎች ተርታ መግባቷን ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡ ዩኒቨርሳል ሚዩዚክ ግሩፕ በዓለም የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ከሚጠቀሱ 4 ታላላቅ ኩባንያዎች አንዱ ሲሆን የኩባንያው ከፍተኛ ባለስልጣን የሆነችው ኢትዮጵያ በጊዜያችን ከሚገኙ ምርጥ የሙዚቃ ስራ አስኪያጆች ግንባር ቀደሟ ናት ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ ሃብተማርያም፤ በአዲሱ ሃላፊነቷ ምርጥ የግጥም ደራሲዎች፣ አርቲስቶችና፣ ፕሮዲዩሰሮችን የለማፈላለግ ሥራ ይጠብቃታል፡፡ በዩኒቨርሳል ሚዩውዚክ ግሩፕ በተሰጣት የሹመት ከእነሜሪ ጄ ብላይጅ፣ ማርያ ኬሪ፣ ኤሚነም፣ 50 ሴንት፣ ዲኤምኤክሰ አር ኬሊና ከሌሎች ታላላቅ ሙዚቀኞች ጋር እንደምትሰራ ይጠበቃል፡፡ ሞታውን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የዴፍ ጃም አሳታሚ ስራዎችን በማሻሻጥና በማከፋፈል ስራ ላይ ተሰማርቷል፡፡ ስቲቪ ዎንደርና ቤቢ ፌስ ሥራቸው በሞታውን ከሚታተምላቸው አርቲስቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ በኒውዮርክና ሎስአንጀለስ የምትሰራው ኢትዮጵያ ሃብተማርያም፤ ለዩኒቨርሳል እና ለአይስላንድ ዴፍ ጃም ኩባንያ ሊቀመንበርም በረዳት ታገለግላለች፡፡
በ17 ዓመቷ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን እንደጨረች ላፌስ ሪከርድስ በተባለ የሙዚቃ አሳታሚ መስራት የጀመረችው፤ ኢትዮጵያ በ2001 እ.ኤ.አ ላይ በሎስአንጀለስ በሚገኝ ኤድመንድ የሙዚቃ አሳታሚ የሠራች ሲሆን ከ2003 እ.ኤ.አ ጀምሮ ዩኒቨርሳል ሚዩዚክ ግሩፕን ተቀላቅላለች፡፡ በዩኒቨርሳል የሙዚቃ አሳታሚ መስራት ከጀመረች በኋላ ጀስቲን ቢበር፣ ክሪስ ብራውንና ሲያራን የመሳሰሉ ኮከቦችን ወደ ሙዚቃ ገበያው አምጥታለች፡፡

Read 3770 times