Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 20 August 2011 11:08

የአጭር ፊልም አሸናፊዎች ይሸለማሉ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

.ደርቢ.. 3ድ ፊልም ነገ ይመረቃል
ብሉ ናይል ፊልም እና ቴሌቪዢን አካዳሚ፣ ከስዊዘርላንድ ኤምባሲ እና ከጀርመን የባህል ተቋም (ጎተ) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የአጭር ፊልም ውድድር የተጠናቀቀ ሲሆን አሸናፊዎች በመጪው ረቡዕ በጎተ በሚከናወነው ሥነ ሥርዓት የገንዘብ ሽልማት ያገኛሉ፡፡ የአካዳሚው ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ኃይሌ በተለይ ለአዲስ አድማስ እንደገለት፤ ለአሸናፊዎቹ ከ3 እስከ 10ሺ ብር የገንዘብ ሽልማት ይደረጋል፡፡

በዚሁ መሠረት የ5 ደቂቃ ፊልም ፋንታ በሚል ርእስ የሠራው ድርብድል አሰፋ 10ሺ ብር፣ ስደት የሚል ፊልም የሰራው ኤፍሬም አለሙ 6ሺ ብር እና “The Triumph of Mind Over Matter” የሚል ፊልም የሠራው ሙሉጌታ ገብረኪዳን 3ሺ ብር እንደሚቀበሉ ይጠበቃል፡፡ይህ በዚህ እንዳለ ዮናስ ጌታቸው ፕሮዲዩስ ያደረገውና አንዱዓለም ጌታቸው ጽፎ ያዘጋጀው ..ደርቢ.. b3D ቴክኖሎጂ የተዘጋጀ የአማርኛ ፊልም ነገ ይመረቃል፡፡ ፊልሙ በዋነኛነት bኤGzþbþ>N ማእከል ትልቁ አዳራሽ እንዲሁም በሌሎች 30 ከተሞች ይመረቃል፡፡ በ90 ደቂቃ የቤተሰብ ኮሜዲ ፊልሙ ላይ እነ ዘሪሁን አስማማው፣ መኮንን ላዕከ፣ ለምለም በየነ፣ መሠረት ሕይወት፣ ኤልያስ ተስፋዬና ሌሎችም ተውነዋል፡፡
ቫንዳም ወደ ትወና ተመለሰ
ቤልጀማዊው ተዋናይ፣ የፊልም ዳይሬክተርና የማርሻል አርት አርቲስት ጂን ክላውድ ቫንዳም ወደ ትወና መመለሱን ቢቢሲ በዘገባው አስታወቀ፡፡ የ50 ዓመቱ ቫንዳም አዲስ የሚሰራው ፊልም ..ዩፎ.. የሚል ርዕስ እንደያዘ ያመለከተው ዘገባው፤ ጡረታ በወጣ የውትድርና አማካሪ ገድል ላይ ያተኮረ ሳይንሳዊ ልቦለድ ፊልም እንደሆነ ታውቋል፡፡
ቫንዳም በመሪ ተዋናይነት የሚሳተፍበትን ይህን ፊልም የሚሰሩት የእንግሊዝ ባለሙያዎች መሆናቸውን የገለፀው ቢቢሲ፤ ለፊልም ስራው የታጨው  ከሚስቱ ጋር በኢሜል በተደረገ ግንኙነት መሆኑን ጠቅሶ በ2012 ዓ.ም ለዕይታ እንደሚበቃ ጠቁሟል፡፡ የፊልም ቀረፃው በእንግሊዟ ከተማ ደርቢ ሰሞኑን ተጀምሯል፡፡ በሌላ በኩል በቀጣይ ወር በቡልጋርያ ቀረፃው በሚጀመረ
ው.. ፊልም ላይ ቫንዳም ከጆንትራ ቮልታ፤ ከቻክኖሪስ፤ ከብሩስ ዊልስና ከሲልቨስተር ስታሎን ጋር እንደሚሰራ ታውቋል፡፡
የ50 ዓመቱ ቫንዳም፤ የብራሰልሱ ºåNc¾ በሚል ቅል ስሙ የሚታወቅ ሲሆን ..ብለድ ስፖርት.. ..ዩኒቨርሳል ሶልጀር..ና በዓለም ዙርያ 100 ሚሊዮን ዶላር ባስገኘው ..ታይም ኮፕ.. የተሰኙ ፊልሞቹ አድናቆትን አትርፏል፡፡

Read 6868 times