Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 13 August 2011 11:19

..ያንቺው ሌባ.. ፊልም ሰኞ ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በግሪን ማውንት ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበውና ሰፊ ፊልም ፕሮዳክሽን የሰራው ..ያንቺው ሌባ.. ፊልም ሰኞ ማምሻውን በሐርመኒ ሆቴል ይመረቃል፡፡ ኤሪክ ጀንሰን እና ለምለም መኮንን በፕሮድዩሰርነት ያሠሩት ፊልም ደራሲና አዘጋጅ በላይ ጌታነህ ነው፡፡ በፊልሙ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ፣ ሰይፈ አርአያ፣ ሳሃር አብዱልከሪም፣ ሰሎሞን ገብሬና ሌሎችም ተውነውበታል፡፡ የ108 ደቂቃ ርዝመት ያለው ፊልሙ በአምስት ወራት እንደተጠናቀቀ ማወቅ ተችሏል፡፡ ..ያንቺው ሌባ.. ከሰኞው ምርቃት ለላ ነገ በአዲስ አበባና በክልሎች ይመረቃል፡፡

..መለስ እና ግብ.. መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ
የአረና ትግራይ ለዓላዊነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አሥራት አብርሃም ..መለስ እና ግብ.. የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ አበቁ፡፡ ቀደም ሲል ..ከአገር በስተጀርባ.. በሚል ርእስ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው መጽሐፍ ለገበያ አብቅተው የነበሩት ደራሲው 110 ገጽ ባለው አዲሱ መጽሐፋቸው ..የቦንድ ወግ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የኢህአዴግ የዕድሜ ማራዘሚያ መድሀኒቶች.. የሚሉ በአጠቃላይ አሥራ ሁለት መጣጥፎችን አካተዋል፡፡ መጽሐፉም በ30 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡

Read 5197 times