Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Monday, 08 August 2011 09:29

ሊዮናርዶ ዲካርፒዮ በከፍተኛ ገቢ ይመራል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሊዮናርዶ ዲካርፒዮ ዘንድሮ ከፍተኛ ገቢ በማስመዝገብ ጆኒ ዲፕ የያዘውን የአንደኝነት ደረጃ መረከቡን ፎርብስ መጽሔት አስታወቀ፡፡በቅርቡ ..ዘ ግሬት ጋትስቢ.. የተባለ ፊልሙን ለዕይታ የሚያበቃው ዲካርፒዮ፡ በከፍተኛ ገቢ መሪነቱን የተቆጣጠረው 77 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማስመዝገብ ነው፡፡

አምና በ75 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አንደኛ የነበረው ጆኒ ዲፕ፤ ዘንድሮ 50 ሚሊዮን ዶላር አስመዝግቦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ አዳም ሳንድለር በ40 ሚሊዮን ዶላር፣ ዊል ስሚዝ በ36 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ቶም ሃንክስ  በ35 ሚሊዮን ዶላር እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ አግኝተዋል፡፡ በፎርብስ የከፍተኛ ገቢ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ባለፈው ዓመት በ50 ሚሊዮን ዶላር ገቢ 5ኛ ደረጃ ላይ የነበረው ሊዮናርዶ ዲካርፒዮ፤ ባለፈው ዓመት የሠራቸው ..ሻተር አዲስ ላንድ.. እና ..ዘ ኢንሴፕሽን.. የተሰኙ ሁለት ፊልሞች ከ1.2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማስገኘታቸው ተገልጿል፡

Read 3756 times