Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 06 August 2011 15:50

ፈረሱ ምን ሆኖ ነው እየሳቀ የሚያለቅሰው?

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሟች፡- እ-ፎ-ይ ተገላልኩ ብሎ ነው የሳቀው ፈረሱ፡፡ የሞት ሎተሪ ወጣለት፤ የሞት ዲቪ. . . ፈነዘጠ፡፡ ከእንግዲህ የኑሮ ውድነት. . . ስቃይ. . . ጦም ማደር ብሎ ነገር እሱንእይመለከተውም፡፡ ፡፡ ፡፡ ከራሚ ይጭነቀው፡፡ ሞት የቀረ መስሎት ተስፋ ቆርጦ ነበር፤ . . .ለካ ይዘገያል እንጃ አይቀርም. . . ከሞት ኤምባሲ ቪዛ ተመታለት፡፡ . . . በሞተ ሀገር ላይ ከመኖር ተገላገለ፤ ሳቀ፡፡

ያለቀሰው ከመንግሥት የመጣ መርዶ ሰምቶ ነው፡፡ . . .አዲሱን የግብር ማስተካከያ ሳትከፍል መሞት አትችልም ብሎ ከለከለው መንግሥት፡፡ ምን ይዋጠው ፈረሱን? ..የሬሳ ሳጥን እና የቀብር ጣጣውን ቀባሪ ይጭነቀው ማለትም አይቻልም.. ተባለ፡፡ የኖርክበትን እና ልትኖር የተመኘህበትን ዓመታት በአዲሱ የግብር ማስተካከያ መሠረት ቀድመህ ካልከፈልክ መሞት አትችልም ብለው መገላገያውን በር ዘጉበት፡፡ ፈረሱን ሞቱ እንደ ሽንቱ ወጥሮታል፡፡ የግብር ገንዘብ መክፈል አይቻልም፡፡ ጥሪቱን በሙሉ አሟጧል፡፡ ለመክፈል በህይወት መኖር መቻል ያስፈልጋል፡፡ . . . የምሞተው መኖር ስላልቻልኩ አይደለም ወይ? ብሎ ቢጠይቅም መልስ የሚሰጠው አጣ. . .፡፡ ሞቱ ወጥሮት እንባውን ለቀቀው፡፡
ኢንተርፕርነር፡- ፈረሱ የሳቀው መንግሥት ያወጣውን ማስታወቂያ አይቶ ነው፡፡ ..ለተቀላጠፈ የግብር አሰባሰብ ግብአት እና ማስፋፊያ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ሀሳቦችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል.. ይላል ማስታወቂያW፡፡ ፈረሱ የተማረበትን ሞያ የሚመለከት ስለሆነ ተደስቶ ሳቀ፡፡ የተማረው ጠማማ ሀሳቦችን በገፍ ማምረት ነው፡፡ በጠማማ ሀሳብ ሥራ ፈጣሪነትን፡፡ . . .ብዙ የግብር መሰብሰቢያ አዲስ መንገዶች ተከሰቱለት፡፡ . . .ለምሳሌ ሰውን በኪሎው መጠን ግብር እንዲከፍል ማድረግ እና በትኬት በሚሠሩ ሚዛኖች ሀገሩን ማጥለቅለቅ. . . ወይም በየሰዉ እግር ላይ መቁጠሪያ በማሰር በእርምጃ ልክ ካርድ የሚሞላበት ሰዓት ነገር ከቻይና ማስመረት. . . የመቶ ብር የእርምጃ ካርድ. . . (ያለዎት የእርምጃ ካርድ አነስተኛ ነው. . . ወዘተ የሚል). . . ወይም የፈገግታ ካርድ (ጉንጭ ላይ የሚገጠም)፣ ወይም የወሬ ካርድ ማሽን ላንቃ ላይ የሚለጠፍ፣ ወይም የሰላምታ ካርድ እጅ እና አንገት ላይ የሚጠለቅ. . . ወይም የወሲብ ካርድ. . . ማለቂያ የለውም. . . ፈረሱ ሳቀ ጨረታውን እንደሚያሸንፍ እርግጠኛ ሆኖ፡፡
ፈረሱ ያለሰው መንግሥት የፈጠራቸውን የግብር መሰብሰቢያ ተጨማሪ ሐሳቦች ተቀብሎ ካደቀለት በኋላ የሀሳብ ግብርም መጀመሩን ሲያረዳው ነው፡፡ ከፈጠራቸው ልማታዊ ሀሳቦች ላይ በአዲሱ የግብር ማስተካከያ ተመን አስር እጥፍ ቀረጥ ሲነሳላቸው ለሱ ምንም አልቀረውም፡፡ ከእዳ በስተቀር፡፡ . . .በነጻነት ማልቀስ ጀመረ፡፡ . . .ግን ለእንባም ግብር እንደሚከፈል ሲታወሰው ወደ ውስጥም ለማልቀስ ፈራ. . .፡፡ ጭጭ-ዋጥ!

 

Read 3645 times Last modified on Saturday, 06 August 2011 15:51