Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Sunday, 31 July 2011 14:48

..ካፒቴን አሜሪካ.. በገቢ ይመራል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ባለፈው ሳምንት ለዕይታ የበቃው ..ካፒቴን አሜሪካ፣ ዘ ፈርስት አቬንጀር.. የተባለው ፊልም የሳምንቱን ከፍተኛ ገቢ በማስመዝገብ ቦክስ ኦፊስን እየመራ እንደሆነ ታወቀ፡፡ በካርቱን ኮሚክ መጽሐፍ ..ካፒቴን አሜሪካ.. ላይ ተመስርቶ የተሠራውን ፊልም፤ ጆ ጆንሰን ዲያሬክት ሲያደርገው ክሪስ ኢልንሰና ቶሚሊ ጆንስ በመሪ ተዋናይነት ተሳትፈውበታል፡፡

የፊልሙ ታሪክ አንድ አሜሪካዊ ወታደር ባልታወቀ አጋጣሚ ጀግና ከሆነ በኋላ በአሜሪካ የጦርነት ዘመቻዎች ማግስት ያሉ እውነታዎችን ለመታገል የሚፈፀመውን ገድል ይተርካል፡፡ በ140 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተሠራው ፊልሙ ለዕይታ በበቃበት የመጀመሪያ ሳምንቱ በዓለም ዙሪያ ያስገኘው ገቢ 76 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ታውቋል፡፡

Read 5560 times