Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Sunday, 31 July 2011 14:02

ፈረሱ ምን ሆኖ ነው እየሳቀ የሚያለቅሰው?

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የኢቲቪ ጋዜጠኛ - ፈረሱ ለምን እንደሳቀ ምንም የሚያጠያይቅ ነገር አይደለም፡፡ ድልን በድል ላይ እየተቀዳጀ በሚዲያ ካፑን ለመውሰድ ወደ ፍፃሜው ጨዋታ ስላለፈ ነው፡፡ እነ ፍቅር ይልቃል እነ ሰኢድን የያዘ ቡድን በጋዜጠኝነት ብቻ ሳይሆን በእግር ኳሱም አሸናፊ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

ተፈጥሮ ከተሞክሮ ጋር የዋንጫ  ጨዋታ ቢያደርግ ተፈጥሮ ማሸነፉ ቅንጣት እንደኢቲቪ ዋንም ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር በሚያደርገው የዛሬው ጨዋታ ኢቲቪ ማሸነፉ አለማጠራጠሩ ፈረሱን...በደስታ አፍነከነከው፤ አሳቀው፡፡
ፈረሱ ያለቀሰው፤ አምስት ሰአት ላይ አበበ ቢቂላ እስቴዲየም ገብቶ የዋንጫውን ጨዋታ መመልከት ከጀመረ ከሃያ ደቂቃ በኋላ ነበር፡፡ ሁለተኛው ጐል ካልታሰበ አዲስ አድማስ ሰማይ ላይ እንደ ጮራ ተፈንጥቆ ግብ ውስጥ ሲንፀባረቅ፡፡ ፈረሱ አለቀሰ፤ እንዴት እሸነፋለሁ ብሎ፡፡ እያለቀሰ፤ መሸነፉ ካልቀረ ያሸነፈውን ቡድን ቢደግፍ እንደሚሻለው አመነ፤... ብርቱካን አይነቱን ማሊያ ለብሶ እንባ ቢያንቀውም ማጨብጨቡን ጀመረ፡፡
የአዲስ አድማስ ደንበኛ - ዋናው ፍላጐቱ ጋዜጣው በእየቅዳሜው ገዝቶ ማንበብም ቢሆንም፤ ፈረሱ አዲስ አድማስ በስፖርት በኩል እያደረገ ያለውን ተሳትፎ ሰሞኑን ሰምቶ ደስ አለው፡፡ ሳቀ፡፡ የበለጠ ያስቀው የነበረው ደግሞ የሚወደው ጋዜጣ የሀገር አቀፍ የስርጭት ሽፋን ዋንጫ ተዘጋጅቶ ተወዳዳሪ ቢሆን ነበር፡፡ ለማንኛውም በእስፖርቱ በኩል የመጣው መነቃቃት ሌሎች መነቃቃቶችን መፈጠሩ አይቀርም ብሎ ሲስቅ ከረመ፡፡
ፈረሱ ያለቀሰው እስፖርቱ የመቀራረቢያ ሳይሆን የመናናቂያ አጋጣሚ መፍጠሩን ሰምቶ ነው፡፡ በሀሳብ እና አቋም ይጠላለፉ የነበሩ ሚዲያዎች ማሊያ ለብሰው ሜዳ ሲገቡ በአካል እና በአፍ የሚጠላለፉ ባላንጣ ሆነው ቁጭ ማለታቸው ሲነገረው ፈረሱ አለቀሰ፡፡ መፎካከር ለመፈቃቀር አልያ ለመቀራረብ ካልሆነ እንደ ድሮው ተራርቆ ባለመቀራረብ መከባበር መሻሉን ተገንዝቦ ፈረሱ አለቀሰ፡፡ ዋንጫውን ማን እንደወሰደ ለማወቅ የነበረውን ጉጉት አጥቶ የጋዜጣ ደንበኝነቱን ብቻ እንደ ጥንቱ አጠናከረ፡፡

Read 3693 times

Latest from