Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Sunday, 24 July 2011 07:43

በቅርቡ ሞባይል ስልክ የሌለው ሰው አይኖርም

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በዓለማችን የተንቀሳቃሽ ስልክ ስርጭት በ2016 እ.ኤ.አ መቶ በመቶ እንደሚደርስና የሞባይል ስልክ አገልግሎት ማግኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችል ተገለ፡፡ ..ሰንዴይ ሞርኒንግ ሄራልድ.. ጋዜጣ ያወጣው ዘገባ እንደ የተንቀሳቃሽ ስልክ ስርጭት ሽፋን ከአምስት አመት በኋላ በዓለም አቀፍ ደረጃ መቶ በመቶ የሚሆን ሲሆይ ይሄም ማለት እያንዳንዱ ሰውም የሞባይል ተጠቃሚ ይሆናል እንደማለት ነው፡፡

ዘገባው አክሎ እንደጠቆመው ከተጠቃሚው ግማሽ ያህሉ የኢንተርኔት አገልግሎት በሚሰጡ ዘመናዊ ሞባይሎች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡  
የሞባይል ስልክ ሽፋን ወይም ተደራሽነቱ በ2016 /እ.ኤ.አ/ ምናልባትም ከዚያ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ በመላው ዓለም ሙሉ በመሉ ይሆናል ያሉት የኤሪክሰን ኩባንያ የተንቀሳቃሽ ስልክ መስመር ዝርጋታ ክፍል ዋና ሃላፊ አልፍ ኤዋልድሰን፤ ጨምረው እንደተናገሩት በጣም ፈጣን የሆኑ ሞባይሎችን ፍላጐት ለማርካት ኩባንያቸው በሰከንድ አንድ ጊጋ ባይት ይዘት ያለውን መረጃ የማስተላለፍ አቅም ያላቸውን ተንቀሳቃሽ ስልኮች አምርቶ ማቅረብ ይጀምራል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በአሁኑ ሰአት በአውስትራሊያ ያለው የሞባይል መስመር (በአገልግሎት ላይ የዋሉት ..ሲም.. ካርዶች) ብዛት በመቶኛ ሲሰላ 115 ፐርሰንት ነው፡፡ ማለትም 22.6 ሚሊዬን ህዝብ ባላት አውስራትሊያ ውስጥ 26 ሚሊዬን የሞባይል መስመሮች አሉ፡፡

 

Read 4250 times Last modified on Sunday, 24 July 2011 07:46