Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Sunday, 24 July 2011 07:39

..ፌስቡክ.. ወላጆች ልጆቻቸውን የሚቆጣጠሩበት መድረክ ሆኗል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ብዙ ወላጆች የልጆቻቸውን ነገረ ስራ ለማየትና ለመቆጣጠር እንደ ..ፌስቡክ.. ያሉ የማህበራዊ ግንኙነት ማቀላጠፊያ ድረ-ገጾችን እንደሚጠቀሙ በቅርቡ የተደረገ ጥናት አመለከተ፡፡ በየትኛውም የዓለማችን ክፍል ከሚገኝ ሰው ጋር በኢንተርኔት በቀጥታ ጓደኝነት መመስረትና መወያየት በሚቻልበት በዚህ የዲጅታል ዘመን የልጆች ማህበራዊ ትስስር በመኖሪያ ቤት አካባቢ እና በትምህርት ቤት ውስጥ ብቻ የማይወሰን ሲሆን አብዛኛዎቹ አፍላ ወጣቶች የማህበራዊ ግንኙነት በሚደረግባቸው የኢንተርኔት መድረኮች ውስጥ እጅግ በጣም በርካታ ጓደኞች እንዳሏቸው ይነገራል፡፡

እናም ወላጆች ልጆቻቸው በኢንተርኔት የማህበራዊ ግንኙነት ማቀላጠፊያ መድረኮች ላይ ሲወጡ ያላቸው ትክክለኛ ሰብዕና (ባህሪ) ምን ይመስላል የሚለውን ለመመልከት ፌስቡክን እንደ አንድ አማራጭ ወስደው መጠቀም ጀምረዋል፡፡   
ጥናቱ እንደ¸ÃmlKtW ሃምሳ አምስት በመቶ የሚሆኑት ወላጆች የልጆቻቸውን ሁኔታ በድብቅ በኢንተርኔት የሚከታተሉ ሲሆን አምስት በመቶ የሚሆኑት ደግሞ አጠቃቀሙን ቢያውቁበት ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይሉ ገልፀዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በአውስትራሊያ ውስጥ ከሃያ እናቶችና አባቶች መካከል አንደኛቸው ማንነታቸው በማይታወቅ መልኩ ወይም እንዳይታወቅባቸው በልጆቻቸው ጓደኞች በኩል አድርገው ልጆቻቸው በፌስቡክ የሚላላኳቸውን ነገሮች እንደሚከታተሉ እንደሚያጣሩ በጠቀሰው በዚሁ ጥናት መሰረት፤ ልጆቻቸው የሚጻጻፏቸውን ነገሮች ማየት የሚችሉበትን ገጽ (አምድ) ከፍተው የሚመለከቱ ሲሆን 29 በመቶ ያህሉ ደግሞ ልጆቻቸው የሚልኳቸውን ምስሎች ይመለከታሉ፡፡ በ..ቡልጋርድ ኢንተርኔት ሴኪውሪቲ.. (Bullguard Internet Security) የተደረገው ጥናት እንዳመለከተው ልጆቻቸው በኢንተርኔት የሚያደርጓቸውን ነገሮች ለምን እንደሚከታተሉ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ ሩብ (25%) ያህሉ ወላጆች የልጆቻቸውን ሁኔታ ለመከታተል እና ለመቆጣጠር ያላቸው ብቸኛ አማራጭ ወይም መንገድ ኢንተርኔት እንደሆነ የገለ ሲሆን ስድስት በመቶው ደግሞ ከልጆቻቸው ጋር ተጣጥመው ማውራት የሚችሉበትን ሁኔታ ለመገንዘብ ስለሚረዳቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ስድስት በመቶ የሚሆኑት ወላጆች በበኩላቸው፤ የልጆቻቸውን አጠቃላይ ሁኔታ ለመቆጣጠር ካላቸው ከፍተኛ ስሜት የመነጨ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡  በአስራዎቹ አጋማሽ ላይ የሚገኙ አፍላ ወጣቶች በሚጠቀሙባቸው እንደ ..ፌስቡክ..፣ ..ማይስፔስ..፣ እና ..ትዊተር.. ባሉ የማህበራዊ ግንኙነት ማቀላጠፊያ ድረ-ገጾች ላይ ወላጆች የሚያደርጓቸውን ክትትሎች ማቆም እንዳለባቸው እና መድረኮቹ ከቁጥጥር ነፃ መሆን አለባቸው የሚል እምነት እንዳላቸው የጠቆመው የዜናው ምንጭ፤ እንደውም ከ 7,700 በላይ አባላት ያሉት አንድ የወጣቶች ቡድን ወላጆች በፌስቡክ እንዳይሰልሉ ..እባካችሁ ስለ እግዚሃር ስትሉ በተቻላችሁ መጠን ወላጆች ፌስቡክን እንዲቀላቀሉ አትፍቀዱላቸው.. የሚል  መልዕክት ለተጠቃሚ ወጣቶች በኢንተርኔት እንዳሰራጩ ታውቋል፡፡

 

Read 4697 times Last modified on Sunday, 24 July 2011 07:43